አንድ ሰው ወንጀል ፈፅሟል ሚባለው ምን ምን ሲሟላ ነው?
**
ይህን ጉዳይ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 23 ይመለከተዋል። በዚህ አንቀፅ መሰረትም አንድ ወንጀል ተፈፅሟል ለማለት ከታች የተዘረዘሩት ሶስት ነገሮችን ሊያሟላ ይገባል። እነዚህም፣
1) ወንጀሉን የሚያቋቀቁመዉ ህጋዊ ፍሬ ነገር ሊኖር ይገባል no law, no crime
ይህም ማለት አንድ ድርጊት ወንጀል ነው ለማለት የግድ በህግ ወንጀል ነው ተብሎ ሊደነገግ ይገባል:: ስለዚህ ድርጊቱ ምንም እንኳን የተወገዘ ቢሆንም በ ህግ እስካልተደነገገ ድረስ ፈፃሚው በወንጀል ጥፋተኛ አይባልም።
2) ወንጀሉን የሚያቋቀቁመዉ ግዙፋዊ ፍሬ ነገር ሊኖር ይገባል
በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ ሰው በህግ የተከለከለው ነገር ካላደረገ ወይም የታዘዘውን ነገር ከማድረግ ካልተቆጠበ በቀር ጥፋተኛ አይባልም።
3 አንድ ሰው ምንም እንኳን በ ህግ የተከለከለውን ነገር ቢፈፀምም ያንን ድርጊት ለመፈፀም አስቦ ካልሆነ ወይም ህጉ በግልፅ በቸልተኝነት ያስቀጣሉ ብሎ ባስቀመጣቸው ወንጀሎች በቸልተኝነት ካልፈፀመው በቀር ጥፋተኛ አይባልም።