የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ከ9_ወራት_በኋላ_ተማርዎችን ከዛሬ ጀምሮ ተቀብሎ የመማር ማስተማር ስራዉን የሚጀምር ይሆናል፡፡
30/03/2013 ዓ.ም
************************
ዓለም አቀፍ ክስተት የሆነው የኮሮና ቫይረስ በጤና፣ በኢኮኖሚና በሰው ልጆች የአኗኗር ዘይቤ ላይ ካሳደረው አሉታዊ ተጽዕኖ ባለፈ በስራ ገበያና በትምህርት ዘርፉ ላይ ያደረሰው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡
መጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ቫይረሱ ወደ ሀገራችን እንደገባ መረጋገጡን ተከትሎ ስርጭቱን ለመግታት፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ መንግስት የትምህርትና ሥልጠና ተቋማትን መዝጋትን ጨምሮ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡
በዚህም ምክንያት በኮሌጃችን የገጽ ለገጽ ትምህርትና ሥልጠና እንዲሁም የሙያ ብቃት ምዘና ላለፉት በርካታ ወራት ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ይህን ተከትሎም ተማርዎቻችን ከቤታቸው ሆነው የተለያዩ የትምህርትና ሥልጠና ሰነዶች እንዲደርሳቸው ለማድረግ የተለያዩ አማራጮችን ሲጠቀም ቆይተናል፡፡
ጤና ሚኒስቴር ባቀረበዉ ምክረ ሃሳብ መነሻ፡ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት በቂ ዝግጅት አድርገዉ ተገቢ ጥንቃቄዎች በመዉሰድ፡ ክልከላዎችንና ግዴታዎችን በማክበር እንዲከፈቱ ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት፡ ኮሌጁን መልሶ ለመክፈት የነበረውን የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ በማጠናቀቅ፡ የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን በክልል ጤና ቢሮ በማስገምገም ብቁና በቂ ዝግጅት ማድረጉ ከተረጋገጠ በኋላ ተመራቂ ተማሪዎችን ብቻ እንዲንቀበል አቅጣጫ ተላልፏል፡፡
በዚህ መሰረት የኮሌጃችን አካዳሚክ ኮሚሽን በቀን 25/03/2013 ዓ.ም በወሰነዉ ዉሳነ፡
1ኛ. በ2010 ዓ.ም የት/ት የተመዘገቡትን:
i). Comprehensive nursing
ii). HIT
iii). Medical laboratory technician
iv). Pharmacy
V). Midwifery
Vi). Urban and rural health extension እንዲሁም
2ኛ. በ2011 ዓ.ም የት/ት ዘመን የተመዘገቡትን:
Vii). Upgrading health extension
Viii). Emergency medical technician ተማርዎችን ከዛሬ ማለትም ከቀን 30/03/2013 ዓ.ም ጀምሮ ተቀብሎ የመማር ማስተማር ስራዉን የሚጀምር ይሆናል፡፡
አጠቃላይ የመማር ማስተማር ሥራ በተማርዎችና በመምህራን መካከል በእጅ የሚቀባበል የወረቀት አሰራርን ያስወገደ ወይም የቀነሰ እንዲሆን ተማርዎቻችን የwifi አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በቂ ዝግጅት ተደርገዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡ ዉድ ተማርዎቻችን ወደ ኮሌጃችን ቅጥር ግቢ ስትመጡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ አለባችሁ፡፡
ዛሬም ቢሆን አካላዊ እርቀታችንን በመጠበቅ፤ እጃችንን በተደጋጋሚ በውሃና ሳሙና በመታጠብ፤ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ በማድረግ እራሳችንን እና የምንወዳቸውን ቤተሰቦቻችንን ከኮሮና በሽታ እንታደግ፡፡