||በአገራችን ብዙ ሀብታሞች አሉ፤ ብዙ ባለ ጸጎች ግን የሉንም! /ዶክተር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ - ችቦ/
ሀብታሞች ከባለጸጎች የሚለዩት ገንዘብ የሚያገኙት የሌሎችን በመቀማትና እንዲያም ሲል በማደህየት ሲሆን ባለጸጎች ግን ሀብትን በድካማቸው ይፈጥሩታል፡፡ ታላቁ የአሜሪካ የመኪና አምራች ኩባንያ ባለቤት ሚስተር ፎርድ ሥራውን የጀመረው አካፋና ዶማ በማምረት ነበር፡፡ ባለጸጎች ለሌሎች ይተርፋሉ እንጅ አይቀሙም፡፡ ሀገራችን ባሳለፈቻቸው ሠላሳና አርባ ዓመታት የኢኮኖሚ ዕድገት ጭላንጭል ቢታይባትም በሞራልና በሕግ ባለመመራቱ ብዙ ባለ ሀብቶችን እንጅ ብዙ ባለ ጸጐችን አልታደለችም።
እነዚህ ድካምን ሳያዩ፣ ልፋትን ሳይቀምሱ ገንዘብ ያግበሰበሱ ባለ ሀብቶች የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ከማናጋታቸው በላይ በወጣቱ ሥነ ልቡና ላይ የፈጠሩት ጠባሳ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ከትንሽ ወደ ትልቅ፣ ከጠባብ ወደ ሰፊ፣ ከውድቀት ወደ ስኬት፣ ከኮረኮንች መንገድ ወደ ደልዳላ ጉዞ፣ ከመሳሳት ወደ መታረም በመጨረሻም ከማጣት ወደ ማግኘት ከአካልና ከአዕምሮ ብስለት ጋር እንደሚታደግ ለወጣቶች ያስተማራቸው አርዓያ የሚሆናቸው አልነበረም። ትናንት ምንም ያልነበረው ድንገት ዛሬ በርካታ ሚሊዮን ብሮች፣ ብዙ ህንጻዎች፣ ተሽከርካሪዎች፤ ድርጅቶች እንዳሉት ይሠማሉ። በቃ የሀብት መንገድ አጭርና አቋራጭ ብቻ እንደሆነ፣ በድካም በጊዜ ሂደት መበልፀግ ሞኝነት እስኪመስላቸው ድረስ ስነ ልቡናቸውን አጣመምናቸው፡፡
በጥቅሉ ከባለጸጎች ስኬት ጀርባ ብዙ የፈሰሰ ወዝ፣ የተንጠባጠበ ላብ፣ የተኮማተረ ጅማት፣ የታጠፈ አንጀት፣ የተላጠ ትከሻ አለ፡፡ ከሀብታሞች ታሪክ ጀርባ ግን ቅሚያ፣ ውንብድና እና ማጭበርበር ይኖራል፡፡ ሀብት ከፈጠረው የቀላ ደረት፣ የወዛ ፊት ጀርባ የቆሸሸ ኅሊና ሊኖር ይችላል።
@Open_reading1