በእኛ አምሳል የመጣ ጂበራል ነው።
=====================
(ደረጄ በላይነህ)
አንዳንዴ ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ እንዳይሆን የዚህ ዐይነቱን ድንቅ መለየት ያሻል። መጽሐፉን ሳይታተም አይቸዋለሁ፤ሌላኛው በእኛ ልክ፣በእኛ አምሳል የመጣ ጂበራል ነው። መጽሐፉ ዝም ብሎ የሚሸመጠጥ አይደለም፤እንደቡና እሸት የሚለቀም ነው። ደግሞ ደጋግሞ ማንበብ፣ማሰላሰል ይፈልጋል፤እውነት ለመናገር ወጣት የጻፈው ሳይሆን ምራቁን የዋጠ፣የማስተዋሎች እርከኖችን ያለፈ ሰው ድርሰት ይመስላል።
ኪናዊ ለዛውን ስናይ በየአንጓው የየራሱ ጣዕምና ለዛ አለው። የተንዠረገገ ፍሬም ጎምርቶ ፣ያጓጓል። መጽሐፉን ሳነብብ የተሠማኝ ስሜት ደግሞ፣ታላቁ ኀያሲና ገጣሚ ጆን ድራይደን እንዳለው የየዘመኑ ጂኒየስ ዐይነት ሆኖ ነው። እያንዳንዱ ዘመን የየራሱ ከሳቴ አለውና በርግጥም በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ የተለየ ቅርጽ፣ጥልቀትና ውበት ያለው ነው። እንደዚህ በሌላ በር ማንኳኳት ደስ ይላል፤መጋረጃው ሌላ ቀለም ሲኖረው ድባብ ይቀይራል።
እንደ ግጥም ባለዜማ፣እንደ ዝርው ዝርግ ነው፤ብዙ ተሸክሟል፤ብዙ ዐይኖችም አሉት፤ የባለሞያ እንጀራ ይመስል ሺህ ቦታ ያያል።
▬▬▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!
◎ የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!
- https://t.me/Open_reading1