"አንባቢ" ሲባል ቀርጸን ያቆምነው የሆነ ምስል አለ። የማይስቅ፣ የማይጫወት፣ ኮስታራ፤ በየንግግሩ አፍታ “እገሌ እንትን የሚለው መጽሐፉ ላይ እንትን አለ” እያለ በጥቅስ የሚያታክተን፤ ከእጁ መጽሐፍ የማይጠፋ ዓይነት ነገር። እንደዚህ ዓይነቱ ሰው ለእኔ የ“woody allen”ን ገለጻ ከወሰድን ለ“PseudoIntellectual”ነት የቀረበ ነው። ለምንድነው የእኛ ሐገር ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ተቋም ሆነው ሳለ አዳዲስ ግኝቶች በመፍጠር ላይ የማናገኛቸው? ለምንድነው እንደበቀቀን እገሌ የተባለ ፈረንጅ ያወራውን መሸምደድ ዕውቀት የመሰለን? …ማንበብ ለእኔ ማንበብን ብቻ የሚወክል ሐሳብ አይደለም። አንብበህ ምን አመጣህ? ምን አዲስ ነገር አሰብህ? በምን መልኩስ ለወጠህ የሚለውንም ያጠይቃል። ሥነ ልቡና ሲባል Freudን ፤ ፊዚክስ ሲባል Einsteinን እያልን ስንት ዘመን ልንዘልቅ ነው? እነዚህ ሰዎች የሠሩት ሥራ ለእኛ የሚሰጠውን ጥቅም ማሳነሴ ሳይሆን (ኧረ ምን ቆርጦኝ!) እኛ ምን ሠራን? የሚለውንም ደፈር ብለን አብረን እንድናየው ነው።
.
ማንበብ አሳቢ ካላደረገ፤ አንባቢ የተባለው ሰውም የመፍትሔ ሐሳብ ጠቋሚ ካልሆነ ወይም በንባብ የቀሰመውን ልምድ ጠርቆ ውበት አልያም ዕውቀት የሚሆን ነገር "እንካችሁ!" ካላለን ምን ይፈይዳል? አንባቢ የመሆን መገለጫ በተዓብዮ የዕውቀት ምሬት ተሞልቶ "አይ ይሄ ማኅበረሰብ!" እያሉ መብሰክሰክ አይደለም። በምትሰድበው ሕዝብ ውስጥ የልጅ ልጅህን የሚገራ ስንትና ስንት ግለሰብ አለ? …እና "ማንበብ" ትንሽ አንብቦ በቅጡ ማሰብም ሊሆን ይችላል። ምን ይመስልሃል? ለምን "ተምረናል አውቀናል፣ በቅተናል!" ከምንል ከእኛ አያቶቻችን የተሻለ የሕይወት መረዳት ኖራቸው? ብለን አንጠይቅም?! መቼስ ነው “አቦ ይቺ ፀሐይ!” ብዬ ሳማርር “አክብራት! ቀድማህ የተፈጠረችው እሷ ናት!” እንዳሉኝ ሽማግሌ የምበስለው? የምን ጊዜም ኦቶባዮግራፊ የምንላቸው መጻሕፍቶች በደምብ የተኖሩ የግለሰብ ሕይወት ትርክቶች ናቸው። በሩቅ አላዋቂ እያልክ የምታናንቀው ሰው ሕይወት በመጽሐፍ መልክ ቢጻፍ ያንተ ክላሲክ ኦቶባዮግራፊ ሥራ ሆኖ ሊቀመጥ ይችላል። በማንበብ ብትበልጠው በመኖር ደግሞ የሚበልጥህ አለ። ረጋ በል!
.
4. ማንበብ ላይጠቅምህ ይችላል። አለማንበብም ሊጎዳህ ይችላል።
.
አብዛኛውን ጊዜ ደራሲያን የሚጽፉትን የማይኖሩ ናቸው። ስለተስፋ ጽፎ በጻፈው ጽሑፍ የተጽናና ማነው? ስለለጋስነት ጽፎ እጁ የሚሰስት ደራሲ ሊኖር ይችላል። አንዳንዴ እንዲህ ዓይነት የዋህነት አያለሁ። "እገልዬ!" የሚያስብል ፍቅር፣ "የት አባቱ!" የሚያስብል ጥላቻ ምናልባት የንባብ ባሕላችን ባለመዳበሩ ወይም የምናገኛቸው መጻሕፍት ውስን ስለሆኑ የገጠመን ይመስለኛል። አድናቆትና ትችታችን መሠረቱ የተምታታ ነው። ሥራውንና ሠራተኛውን ፤ ደራሲውንና ድርሰቱን ለይተን አልያዝንም። ለይተን አልተውንም። ግን በዚህ ሁሉ መሐል " ፍጹም አውቃለሁ!" ባዮች ነን። "እኔ የማውቀው አለማወቄን ነው" የምትለዋ የአርስቶትል አባባል ብትለመድም ተራ ንግግር አለመሆኗ እያደር የገባኝ በየቀኑ ለአዳዲስ መጻሕፍትና ለአዳዲስ ደራሲያን ራሴን ክፍት እያደረግሁ በመጣሁ ቁጥር ነው። ማንበብ ውስጡ እየገባን በሄድን ቁጥር ሰፊ ባሕር ውስጥ እንደመጥለቅ ነው። ያልዳሰሰን ውኃ ገና በዚያ አለ። ያልነካን መገለጥ ገና በዚህ አለ። ያልኖርነው በረከት ገና ወዲያ አለ። እንወቅ። እናንብብ። ነገር ግን የማያነበውን ሰው ጥሰነው እንደሄድንና፤ እንደእኛ ማሰብ እንማይችል አድርገን የምንቆጥር ከሆነ ግን ሁሉንም ወዲያ ጥለን ወይ ቁርሀን፤ ወይ መጽሐፍ ቅዱስ እንግለጥ። ያልተቆረጠ ግብዝነት ውስጣችን አለ ወገን። እና እንደእኔ እይታ ማንበብ ሙሉ ሰው አያደርግም። አለማንበብ ግን ሊያጎድል ይችላል። አንብቤያለሁ የመኮፈሻ መሣሪያ መሆን የለበትም። ያነበበ ሰው ትሁት ነው። ያነበበ ሰው ዝቅ ብሎ ለመማር አይጨንቀውም። ያነበበ ሰው ለመናቅም ለመከበርም ግድ አይሰጠውም። ያነበበ ሰው በፍቃድ ባሪያ እንደሆነ ንጉሥ ነው። እና የንባብ ባሕል በዘመቻ ሰው ላይ የምትጭነው ነገር ሳይሆን፤ ትውልድ ላይ መሠረት ባለው መልኩ የሚቀረጽ የኑሮ ስልትና እቅድ ነው።
እንደመውጫ(ባልተያያዘ ዜና)
.
4. ስብሐትና faulkner
Faulkner አንዴ ተጠየቀ “አንዳንድ ሰዎች ሁለቴም ሦስቴም አንብበውት ጽሑፍህን አይረዱትም። ምን ቢያደርጉ ትመክራለህ?” ሲመልስ ምን አለ? “ለአራተኛ ጊዜ እንዲያነቡት።”
ስብሐት አንዴ ተጠየቀ። “አንዳንድ ሰዎች ደጋግመን አንብበንም ስብሐት የሚጽፈው ነገር አይገባንም ይላሉ። ምን ቢያደርጉ ትመክራለህ?” ስብሐት ሲመልስ ምን አለ? “ለምን አትተወውም?! ምን አታገለህ?!”
-
እንዲህ የተንዘላዘለ ፅሑፍማ ያለመፈክር አይዘጋም።
.
እናንብብ! እናስነብብ! የሚያነብ ትውልድ እንፍጠር!
This weeks recommendation;- saul bellow - “seize the day”
ሄኖክ በቀለ ✍