Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እስክንድር ነጋ፣ ቅልስልሱ እባብ
~~~~~~~~~~~~
እስክንድር ነጋ ሲበዛ ተንኮለኛ የሆነ ቅልስልስ እባብ እንደሆነ በሚገባ አውቃለሁ። ግን በዚህ ደረጃ ቅርሻቱን ባደባባይ የሚተፋ ደነዝ እንደሆነ አስቤው አላውቅም። የሞጣውን የመስጂዶችና የሙስሊሞች ንብረት ቃጠሎ ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር ግንኙነት ባለው የተደራጀ የአሸባሪ ቡድን የተፈፀመ ሊሆን ይችላል እያለ ነው። ስለዚህ መስጂዱንና ንብረቱን ያቃጠለው እራሱ ሙስሊሙ ነው ማለት ነው።
እስክንድር በቅርቡ በአውሮፓ እና አሜሪካ በሄደበትም ይህንን ቡድን በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ለማድረግ ሲሰራ እንደነበር ተናግሯል። ማንን እየከሰሰ ተንኮል ሲሸርብ እንደነበር አያችሁ አይደል? ሙስሊሙ ላይ ስንት አይነት ቁማር እንደሚጫወቱ ተመልከቱ እንግዲህ። የመንግስት አካላት፣ የቤተ ክህነት ሰዎች፣ ማህበረ ቅዱሳን እና አደገኛ ቦዘኔዎች ተቀናጅተው ማቃጠላቸው አልበቃ ብሎ በቁስላችን በህመማችን ላይ ሌላ ዙር ጥቃት ከፍተውብናል።
ያገር ውስጡ አልበቃ ብሎ በምእራብ ሃገራት እየተሽሎከለኩ የሚያሴሩብን ሌላ ረጅም ሴራ እንዳለ እየነገሩን ነው። በነገራችን ላይ በነ መለስ ጊዜም የተፈፀመብንም ይሄው ነው። በ1997ቱ ምርጫ "ኢህአዴግ ለሙስሊሞች በሚሰራው ‘ፌቨር’ የተነሳ በ20 አመት ጊዜ ኢስላም በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው። አክራሪ እስልምና እና አሸባሪነት በከፍተኛ ፍጥነት እግሩን እየተከለ ነው" እያሉ ምእራባውያን ዘንድ መንግስትን ከከሰሱ በኋላ ነው ኢህአዴግ የምእራባውያኑን ድጋፍ ለማግኘት ሲል በሙስሊሙ ላይ ከወትሮው የተለየ ቀጥተኛ ዘመቻ የከፈተው።
ዛሬም እነ እስክንድር እያደረጉት ያለው ይህንኑ ነው። የመንግስት አብዛኛው አካሄድ ወደነሱ ያዘነበለ ከመሆኑም ጋር ሙስሊሙ ላይ እየደረሰ ያለው መከራ እነሱ በሚፈልጉት መጠን ስላልሆነ ሰፊና የተቀናጀ ስራ እየሰሩ እንደሆነ ፍንጭ እየሰጡን ነው። እውነት ለመናገር እኛ ከነሱ ቅንነት አንጠብቅም። ለኢስላምና ለሙስሊሞች አንዱ ከሌላው ያላቸው ርቀት እምብዛም ነው። በዚህ ረገድ "የአንድነት ሃይሉ" ከፅንፈኛ ብሄርተኛው አይለይም። በሁለት እግሩ ተደላድሎ እስኪቆም ድረስ እንጂ በሙስሊሞች ጉዳይ ላይ በመንግስትና በተቃዋሚ መካከል ያለው ርቀትም ብዙ አይደለም። ስለዚህ የኛ ጉዳይ የኛ ብቻ ነው። የረጅምና የአጭር ጊዜ እቅዶችን ነድፈን መንቀሳቀስ ያለብን እኛው ነን። የኛን ስራ ሌላ አካል እንዲፈፅምልን መጠበቅ የዋህነት ነው። ሁሉም በየፊናው ሊንቀሳቀስ ይገባል። ደግሞም እንችላለን ኢንሻአላህ። ዲናችንን ከነዚህ እባቦች ለመከላከል እንዲሁም ሕዝባችንን ከነዚህ ተኩላዎች ለማትረፍ ወገናችንን በዲኑም በዱንያውም ለማንቃት መታገል ያስፈልጋል።