Репост из: ማርከን ዜማ Marken Zema ✟ 🇪🇹
የቀኑ መልዕክት
መሪህ ልክ ነው!
የትኛውንም ርቀት ሂድ የሄድከውም መንገድ አስደሳች ይሁን እንዲሁም መንገዱ አሰልቺ አስጨናቂም ይሁን የሄድክበት ርቀት ሚለካው በአንተ የአካሄድ ጥበብ ሳይሆን የእግዚአብሔር ርህራሄ መጠን ነው።
እስራኤላውያን በሙሴ በኩል ከእግዚአብሔር ከመጣ ትእዛዝ የግብፃውያንን ብር ወርቅ ከሰበሰብ በኋላ ሁሉም ተሰብስበው ከግብፅ በመልአኩ ምሪት ቀይ ባህር ጋር ደረሱ ከኋላ ደግሞ ምርጥ ሚባሉ የግብፅ ሰረገሎች ተከተሏቸው። በእንደዚህ አይነት በማይመስል ሁኔታ ውስጥ የግብፅን ወርቅ የበዘበዙት እስራኤላውያን የባህሩን ግርማ አይተው ፈርተው እንኳን እንዳይመለሱ ግብፅን በመበዝበዛቸው ብቻ የመመለስ ሞራል እንኳን አልነበራቸውም ግን የመራቸው በዚያም ሁኔታ ውስጥ ልክ ነበር። ከዛም ድንቅ መልእክት ሙሴ ለህዝብ እንዲህ ሲል ነገራቸው “እግዚአብሔር (ያህዌ) ስለ እናንተ ይዋጋል፤ እናንተ ያለባችሁ መታገሥ ብቻ ነው።” ዘጸአት 14፥14 ሚመራህ ተዋጊ ነው........በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔር ስርአትን ሊያስተምርህ ምንም ወደ ማይኖርበት ወደ ምድረበዳ ይመራሀል። ብዙ ጊዜ ለልቤ ምነግራት "ምድረበዳ የእግዚአብሄርን የሀሳብ ማሳያ ናት" እያልኩ ነው ካስታወሳችሁ ሆሴዕ 2:14-15
“ስለዚህ እነሆ፤ አባብላታለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም እወስዳታለሁ፤ በፍቅር ቃል አነጋግራታለሁ።በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤ የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ። በዚያም ከግብፅ እንደ ወጣችበት ቀን፣ እንደ ልጅነቷም ጊዜ ትዘምራለች።" አንዳንድ ምድረበዳዎች እግዚአብሔር ሚያወራባቸው ናቸው።የጣልናቸውን ነገሮች ማንሻ ናቸው። እናም እግዚአብሄር ምድረበዳ ወደሚመስል ሚወስዳችሁ የልብን ሊያወራችሁ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ትንሽ ነገሮች ሲሳኩልን እና ስንለወጥ በእግዚአብሔር ፊት ልባችን እንዳያብጥ ማስተንፈሻ ቀስት ናት እስራኤላውያን ነገር ሞልቶላቸው ከእግዜር ለመራቅ ሲሞክሩ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ሁሌ ሚናገራቸው ቃል አለ "በበረታች ክንድ ከግብፅ ያወጣኋቹ" እያለ የትላንታቸውን ጭንቅ እያስታወሰ የዛሬ ሙላት እንዳያጠፈቸው ያደርጋቸዋል። ስለዚህ መሪያችሁን ተከተሉት እርሱ ልክ ነው!
መልካም አዳር!
@Gift29
@Markengeta