Репост из: Muhammed Mekonn
➡️ የዓሹራእ ፆም
«»«»«»«»«»
☑️ ሙእሚን መልካም ስራ ቀብር እስከሚገባ ድረስ አይጠግብም
አላህ ለባሮቹ የተለያዩ ወደርሱ የሚያቀርባቸውና ምንዳቸውን ከፍ የሚያደርግላቸው መልካም ስራ የሚሰሩበትን እድል ሰጥቶአቸዋል ከእነዚህ እድሎች አንዱ የዓሹራእ ፆም ነው።
↪️ የሙሃረም ወር አስረኛው ቀን ማለት ነው ይህ ቀን አላህ ነብዩላሂ ሙሳንና ተከታዮቻቸውን ከፊርዓውንና ሰራዊቱ ነጃ ያወጣበትና አማኞች በከሀዲያን ላይ ድል የሰጠበት ቀን ነው።
➲ የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - መዲና ሲገቡ እዛ የነበሩ አይሁዶች ሲፆሙ አገኙዋቸው ምክንያቱን ሲጠይቁዋቸው አላህ ለሙሳ በፊርዐውን ላይ ድል የሰጠበት ቀን ነው አሉዋቸው እሳቸውም ለሙሳ ከናንተ እኔ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው እሳቸውም ፆመው ተከታዮቻቸውን እንዲፆሙ አዘዙ ሶሃባዎቹ ይህ ቀን አይሁዶች ያከብሩታል ሲሏቸው አላህ ካቆየኝ የሚቀጥለው አመት ዘጠነኛውን ቀን እፆማለሁ አሉ የአላህ ቀደር ሆነና ሳይደርሱ ወደ አኼራ ሄዱ።
♻️ በመሆኑም የኢስላም ሊቃውንቶች የዓሹራን ፆም በተመለከተ፦
❶ኛ ዘጠነኛና አስረኛውን ቀን መፆም
❷ኛ አስረኛውና አስራ አንደኛውን ቀን መፆም
❸ኛ አስረኛውን ቀን ብቻውን መፆም
❹ኛ ዘጠነኛ አስረኛና አስራ አንደኛውን ቀን መፆም!!! በሚል አስቀምጠውታል።
✅ የሚያስገኘው ቱሩፋትን በተመለከተ
የአላህ መልእክተኛ "ያለፈውን ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አድርጋለሁ ብሐዋል" ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ሰዎች ዘጠነኛው ቀን ያመለጠው ሰው አስረኛውን ቀን መፆም እንጂ አስራ አንደኛውን ቀን መፆም አይቻልም ምክንያቱም እሳቸው ያሉት አላህ ካቆየኝ ዘጠነኛውን ቀን እፆማለሁ እንጂ አስራ አንደኛውን አላሉም የሚል ነው። ከላይ እንዳየነው የተፈለገበት አይሁዶቹን መኻለፍ እንጂ ቁጥሩ አይደለም ዋናው አስረኛው ቀን ነው ከዛ ውጪ ያለው ለራሱ ሳይሆን ለሌላ ጉዳይ ነው የተፈለገው ያ ጉዳይ ከፊትም ከኀላም ባሉት ቀናት ከተገኘ የተፈለገው ነገር ተገኘ ማለት ነው።
➧ ይህም ሙኻለፋው ነው። ይህን አልቀበልም የሚል ልክ የአላህ መልእክተኛ በተኛ ውሃ ላይ አትሽኑ ባሉበት ሀዲስ ላይ አንድ ሰው ሌላ ቦታ በእቃ ሸንቶ አምጥቶ ቢደፋበት ችግር የለውም ምክንያቱም አትሽኑበት ነው እንጂ ያሉት ሌላ ቦታ ሸንታችሁ አምጥታችሁ አትድፉበት አላሉም እደሚሉት ነው!!!
አላህ ከተጠቃሚዎች ያድርገን
http://t.me/bahruteka