📌 ወደ ካምፓስ ስንሔድ ምን ምን ነገሮችን ይዘን መሔድ አለብን❓
👉 ከበሶ እስከ ዳቦቆሎ
👉 ከለውዝ ቅቤ እስከ ማርማራታ
👉 ከሻንጣ እስከ ፒኪኒ
ቢኒያም ከፋለ(ዞግ) አስፈላጊ የሚባሉ ሸመታዎችን እንደሚከተለው አቅርቦላችሗል።
ሰላም ውዶቼ እንደምን አላችሁ ❓
📚 እስቲ ዛሬ ተማሪዎች ወደ ካንፓስ ሲገቡ መያዝ ያለባቸው ነገሮች እንመልከት ፦
📌 በምግብ ዘርፍ ፦
📚 እናትህ በር አንኳኩታ ከእንቅልፍ ቀስቅሳ ልጄ ቁርስ ደርሷል ብላ መጥራት ወፍ በቃ ቀርቷል ። አሁን ጠዋት 1:30 ተነስተህ ለሻይ እና ዳቦ መሰለፍ አለብህ በቀን 3 ካልተሰለፍክ ዶርም ድረስ በሰሃን አይቀርብልህም መቼስ ደሞም እንደማሚ WOW የሚያስብል ግሪስ እንዳይመስል.... ናላ የሚያዞር ፈውስ ነው ሚቀርብልህ... ኮብል ከምስር ጋር ፥ ሽሮ ያለ ዘይት ፤ ስጋ ወጥ ያለ ስጋ ለመብላት ነው ተሰልፈህ የምትውለው ። አስበው በዛ ላይ ችከላ አለ ይሞረሙረሃል ከዛ እናትህ ትናፍቅሃለች ታዲያ በበሶ ካልሆነ በምንም አታገኛትም ። በሶ ሆድ ብቻ መሙላት አይደለም ናፍቆት ማረሳሻም ነች ። ብትወድም ባትወድም በሶ ያዝ ፤ ኩኪስ ፤ ዳቦቆሎ ፤ የመሳሰሉ በባህላቹ ያሉ ደረቅ የስንቅ ምግቦች በደንብ ያዙ ታመሰግነኛለህ ።
💡 በሶ
💬 በሶ ብትወድም ባትወድም ጥቂትም ቢሆን ያዝ መበጥበጡ ራሱ LIFE አለው ፤ ለአንድ ሴሚስተር ከ2-5 ኪሎ በቂ ነው ብዬ አስባለሁ ፍሬሽ ስትሆኑ ግን የካፌ ምግብ ስለማይስማማቹ እስከ 6 አርጋቹሁ ያዙ ። በሶ ስትይዙ ከቻላቹሁ በማሸጊያ ፌስታል አሽጋችሁ ብትይዙ ለመያዝም ያመቻቹሃል ለሙዱም አሪፍ ነው ።
💡 ኩኩሲ ፡
📚እኔ ኩኩሲ በጣም ነው የምወደው ስለዚህ በኩንታል ልይዝ አስቢያለሁ እና በሶ ለማትወዱ አሪፍ መፍትኤ ነው ከ2-3 ኪሎ ለሴሚስተር ብትይዙ በጣም አሪፍ ነው ። ኩኩሲ ነፍስ የሆነ ነገር ነው ኩኩሲ በበሶ አስባቹሁታል ። ግን እመኑኝ ካልቆጠባቹሁ የዶርም ጀመኣ 3 ቀን አያቆያትም እና ስንቅ መሆኑን አስባቹሁ ቢያንስ ሁለት ወር ማስቀመጥ ይኖርባቹሃል ። አገኘው ብላቹሁ ጨርግዳቹ ጨርግዳቹ በሳምንት ጨርሳቹሁ ጨላ ሲነጥፍ በኃላ ጉድ እንዳትሆኑ እንደውም ገንዘብ እስኪጠር ኩኩሷን አትንኳት ከነካቹሁም በቁጠባ ።
💡 ዳቦቆሎ ፦
💬 ይቺም በጣም አሪፍ ነገር ናት እስከ 2 ኪሎ ብትይዙ አትጎዱም ። ስትተክዙ ማታከዣ ስትቸክሉ ማቻከያ ትሆናለች ። ዳቦ ቆሎም መቆጠብ አለበት እና ለቁጠባ አሪፉ መንገድ ማሸግ ነው ። 2 ኪሎው ዳቦቆሎ 3 እሽግ ፌስታል ቢወጣው አንድ እሽግ በወር የሚል ዕቅድ ይዛቹሁ መቆጠብ ትችላላቹሁ ።
💡 የለውዝ ቅቤ ፤ ማር ፤ ማርማራታ ፤ የመሳሰሉ የሚቀቡ ምግቦችም ፦
💬 ማር ካልሆነ አብዛኞቹ በከተማ ስለምታገኙ እዛው የዳቦ ዋጋ አጣርታችሁ የማይጎዳ ከሆነ ሸመትመት ማረግ ትችላላችሁ ነገር ግን የማር ሀገር የምትኖሩ ከሆነ በደንብ ያዙ ትፈወሳላችሁ እመኑኝ በተረፈ በቃ (ማር ሀገራቹሁ ምርጥዬ ከሆነ ይዛቹሁ ኑ ሌሎቹን ከመጣቹሁ ወዲህ በተመደባችሁበት መግዛት ትችላላቹሁ) ደሞ አንዳንድ ግቢ ፍራፍሬ በጣም ርካሽ ነው በተለይ ወደ ደቡብ ታዲያ ደቡቦች ለምግብ እንዳታስቡ ያረጋቹሃል ። ያው የጠገበ ስለትምህርቱ ስለማያስብ አትጎዱ እንጂ ሰርክ ሀሳባቹሁ ፈውስ መሆን የለበትም ተመርቋቹሁ ስራ ስትይዙ ታማርጣለቹሁ ለግዜው ያገኛቹሁትን ጠርጋቹሁ በደንብ ቸክላቹሁ በአሪፍ ግሬድ መመረቅ አስቡ ። ደሞ ክረምት ነው በቆሎም አለ ትግጣላችሁ .....
💬 ምግብ እንደሙዳችሁ የሚመቻችሁን እና በየሀገራችሁ ለስንቅ የሚዘጋጁ ነገሮችን ያዙ ( ግቢ መግባት የሚችሉትን ) ሽንብራም ፤ በሶም ፤ ማርም ብቻ ይሆናል ያላችሁትን እና የሚሞዳችሁን ፈውስ ያዙ ።
📌 በቁሳቁስ ዘርፍ ፦
💡 ሻንጣ ፦
📚 ብዙዎች ቀለል ብለው መግባት ይሞዳቸዋል ፥ አንዳንዶች ደሞ እንደ ሰርግ ካልታጀብን ይላሉ ብዙዎቻችሁ መረዳት ያለባችሁ ነገር ግቢ ስትገቡ የምትገቡ እናንተ እንደሞዳችሁ እና እንደአቅማችሁ ፥ እንደ አስተሳሰባችሁ እና ፍላጎቶቻችሁ እንጂ ስለ ሰዎች አትጨናነቁ እነሱ የራሳችሁ ቢዝነስ ይወርኩ ። እናንተ በራሳችሁ የሚሞዳችሁን እና የሚያስፈልጋችሁ ነገር አድርጉ ።
💬 ጀለስ 4 ግብዳ ሻንጣ ተሸክሞ ግቢ ስለሚቆሰው እኔም የሚል ፎክክር ትታችሁ ምንድነው ሚያስፈልገኝ ❓አቅሜ የቱ ያክል ነው ❓በሉ ቤተሰብ አታስቸግሩ ከሌሎች እኩል ለመሆን በሚል የFamily ኑሮ አታናጉ ። እናም እንደሙዳቹሁ ተራመዱ ።
📚 ሻንጣ (እንደኔ) አንድ በጀርባ የሚነገት Bag ብትገዙ ( ከሌላችሁ ካላችሁ ግልግል ) እና ሌላ ትንሽዬ (የምትጎተተዋ) ብርድልብስ እና የመሳሰሉ ትልልቅ ነገሮች የምትይዙበት ሻንጣ ቢኖራችሁ አሪፍ ነው ።
💬 ለበዓል እና ለዕረፍት ወደ ቤተሰብ ስትመጡ ለቀናት የሚሆን ልብሳችሁን በጀርባ ሚነገተው Bag ትይዛላችሁ የተቀሩትን ደሞ በቀረችው ቦርሳ ግቢ ታስቀምጣላችሁ ( ሙሉ ዕቃ በየግዜው ስለማታንኳትቱ ማለት ነው) ነገር ግን እንደ ግቢው ርቀት ፥ እንደ እናንተ የሸመታ ብዛት ፥ እንደ ያዛችሁተ ዕቃ ነው የሚወሰነው ስለዚህ በፍላጎታችሁ መሰረት ብትይዙ መልካም ነው ።
🎗በተረፈ እንደኔ ከቻላችሁ ለክላስ የምትሆን አነስ ያለች 250 -300 ብር የምትገዛውን Bag እዛው ግቢ ብትገዙ አሪፍ ነው ( በፊት ካላችሁም ስትመጡ ዕቃ ነገር ያዙባት እና በዛው ትማሩባታላችሁ ። )
📌 የልብስ ሸመታ ፦
📚 ይሄም የሚወሰነው እንደደረሳችሁ ግቢ የአየር ንብረት እና የእናንተ ሙድ ነው ፤ መቼስ ሰመራ ደርሶህ መርጦ ሳትይዝ አትሄድም ፤ መቼስ ደብረብርሃን ደርሶህ ከጋቢ ማይተናነስ ጃኬት መያዝ አትረሳም ፤ ብቻ እንደግቢው እና ሙዳችሁ እና አቅማችሁ ይወሰናል ፤ ፋሽን ተከታይ ናችሁ ❓ዘናጭ ናችሁ❓ ደሃ ናችሁ
❓ቀለል ያለ አለባበስ ይመቻቹሃል ወይስ ቂቅ ካካለችሁ ይጨንቃቹሃል ብቻ ሙዳችሁ ምንድነው ብላችሁ " እንደ ሙዴ " ብሎ መቀወጥ ነው ። ምን ያክል ልብስ ልያዝ ምናምን ለምትሉ (በግሌ)
💡 ለወንዶች ፦
📚 3-5 ሱሪ እና 1ቱታ ፤ 1 ቁንጣ ፤ 2-3 ቲሸርት ፤ 2-3 ሸሚዝ ፤ 1-2 ጃኬት ፤ 6-8 ካልሲ ፤ 3-5 ፓንት ፤ 2-3 ሽፍን ጫማ + 1 ነጠላ ጫማ ፤ 1-2 ቀበቶ ፤ የረሳሁት ነገር ካለ እጨምራለሁ ።
💡ለሴቶች ፦
📚 ሴቶች ግቢ ሲገቡ በጣም ግብዳ ሻንጣ ሲሸክፉ ሁሌ እመለከታለሁ ብዙ ግዜ በምንድነው የሚሞሉት ብዬ ጠይቄ መልሱ አላገኘሁም ። ለማንኛውም ሴቶችዬ የእናንተ አለባበስ ወዲ በሉት ወዲ ለማለት ትንሽ ይከብዳል ። ብቻ ከታይት እስከ ጉርድ እንዳሻችሁ እና እንደፍላጎቶቻችሁ ሸምቱ (ሂጃብ እና ነጠላውም እንዳይረሳ እህትአለም) እንደምክር Body ነገር በከትከት አርጋችሁ ያዙ እኔ ነኝ ያልኳቹሁ ታተርፋላችሁ ።በተረፈ በንፅህና ስለማትታሙ ካልሲ እና ፓንት በርከት አርጎ የመያዝ ግዴታ የለባችሁ (ጭብጨባ ለሴቶች )
@ze_campus_tips@ze_campus_tips@ze_campus_tips