➻ስለ ዲናችን ጠንቅቀን እንወቅ!!
በምንችለው ሁሉ እንተግብር!!
、、、、、
የተለያየ አጀንዳ በተነሳ ቁጥር መደናበር፣ መወዛገብና መጨቃጨቅ በዋነኝነት የእውቀት እጥረት ችግር ነው። ታዲያ ችግሩ ይህ ሆኖ ሳለ ለችግሩ ትክክለኛውን መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በዱኒያዊ ጉዳዮች ተጠምደው ይህን ትልቁን ድርሻ ሲዘነጉት ይስተዋላል።
አብዛኛው ሰው በየ አቅጣጫው ጭንቀቱ ውጣ ውረዱ ለዱኒያዊ ጥቅም ነው። ዱኒያዊ ጥቅምም ቢሆን እንዴት ማግኘት እንዳለበት ሸሪዓዊ እውቀት ያስፈልገዋል። አላህ እውቀትን እንዲጨምርለት ከመለመን ይልቅ፣ ስለ ዲኑ ግንዛቤ እንዲሰጠው ከመለመን ይልቅ ዱኒያን እንዲጨምርለት በመለመን ለዱኒያ መጨነቅ የብዙዎች መለያ ነው። ለዱኒያ ሳይጨናነቁ አላህ ዱኒያውንም እንዲያስተካክል ዱዓ ማድረጉ የሚወገዝ ባይሆንም ዲን እንደ ትርፍ ነገር ተቆጥሯል።
የእውቀትን ትሩፋትና ወሳኝነት የሚገልፁ ብዙ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎች አሉ። አላህ ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እውቀትን ጨምርልኝ በል ሲል ይናገራል:-
فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ ۗ وَلَا تَعْجَلْ بِالْقُرْآنِ مِن قَبْلِ أَن يُقْضَىٰ إِلَيْكَ وَحْيُهُ ۖ وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا
«እውነተኛው ንጉስ አላህም (ከሓዲዎች ከሚሉት) ላቀ!፡፡ ወደ አንተ መወረዱም ከመፈፀሙ በፊት በማንበብ አትቸኩል፡፡ “ጌታዬ ሆይ! እውቀትንም ጨምርልኝ” በል፡፡» ጧሀ 114
ይህ አንቀፅ የእውቀትን ትልቀነት ያስገነዝበናል። ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እውቀትን እንጂ ሌላ ነገር "ጨምርልኝ በል" ብሎ አላዘዛቸውም።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር:-
اللَّهُمَّ انْفَعْنِي بِمَا عَلَّمْتَنِي، وَعَلِّمْنِي مَا يَنْفَعُنِي، وَزِدْنِي عِلْمًا
“አላህ ሆይ! ባሳወቅከኝ ነገር ጥቀመኝ፣ የሚጠቅመኝን ነገርም አሳውቀኝ፣ እውቀትንም ጨምርልኝ” ትርሚዚይ 3599 ላይ ኢብኑ ማጀህ 251 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ በሶሂህ ኢብኑ ማጀህ ሶሂህ ብለውታል።
የተለያዩ የሺርክና የክህደት ቡድኖች እስልምናን ለማጥቃት በአንድነት ተነስተው ይንቀሳቀሳሉ፣ የቢድዐ/የጥመት አንጃዎች ሁላቸውም ባሉበት መንገድ አንድ ባይሆኑ እንኳን የሱናውን ሰው በመታገል ግን በተዘዋዋሪም ሆነ በግልፅ አንድ ናቸው። ታዲያ በእንዲህ ያለ ሁኔታ ላይ ከሁሉ ነገር በላይ እውቀት መታጠቅ ግዴታ ነው። ሁሉም በያለበት በሚችለው አቅም ሁሉ ለእውቀት ከምን ጊዜውም በላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጥና ራሱንም ሆነ ቤተሰቡን በእውቀት ሊያደራጅ ይገባል።
እውቀት ሲባል ያወቁትን ማሳወቅንም ይመለከታል። አንዳንድ ሰዎች ተምረው አውቀውት በጊዜው ገብተዋቸው ያለፉት ኪታብ መልሶ ሲጠፋቸው ይስተዋላል፣ ይህ ትልቅ ጥፋት ነው። ለዚህ መፍትሄው መሻይኾች እንደሚሉት ያወቁትን በማስተማር መበርታት ነው ይላሉ። ያወቁትን ማሳወቅ በራሱ እውቀት እንዲጨምር ከሚረዱ ነገሮች አንዱ ነው።
እውቀት ያለውና የሌለው ፈፅሞ እንደማይገናኝ ይታወቃል!፣ አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ አለ:-
قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ
«እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?፣ በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው፡፡» አዝ-ዙመር 9
አዋቂና መሃይም ፈፅሞ እኩኩል አይሆኑም!። በሚያሳዝን ሁኔታ አንድ ሰው ይህን ተጨባጭ እያወቀ ሲታመም ለሰውነቱ በትክክል እውቀት ያለውን የጤና ባለ ሞያ ሲፈልግ ለአኼራ ለዱኒያው የህይወቱ ዋስትና ለሆነው ዲን ጊዜ ግን ያለ እውቀት ራሱ ሲያቦካ ይስተዋላል። ይህ ደግሞ ከባድ ዋጋ የሚያስከፍለው ጉዳይ ነውና ትክክለኛ እውቀት ያላቸው ሰዎች ዘንድ እውቀት ሊቀስም ይገባል!፣ እውቀት በሌለን ነገር ደግሞ ዝምታ ይስፋን!።
እውቀት የሚገኝበት መንገድ ከምን ጊዜውም በላይ ሰፊ ነው፣ ዒልም የሚሰጥባቸውን ቦታዎች ጎራ ብሎ መቃኘትና መደበኛ ሆኖ በደረጃ የሚመጥንን ቂርኣት መከታተል ነው!። ይህ ከከበደ የተለያዩ መሻይኾች በድምፅ አቅርተው ያለፏቸው በየ ደረጃው የተለያዩ ትምህርቶች አሉ፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተጎልቶ ጊዜ ከማቃጠል የመሻይኾችን ት/ቶች አውርዶ በስርኣት መማር ይቻላል።
እውቀት ደረጃው የላቀ ነው!፣ ለዚያም ነው ትግስት የሚፈልገው። አላህ እውቀት ኖሯቸው በእውቀታቸውም ተግባሪ የሆኑ ሰዎችን ከሌሎች የላቀ ደረጃ እንዳላቸው ሲገልፅ እንዲህ ብሏል:-
يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
«አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፡፡ አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡» አል ሙጃደለህ 11
አላህ በአማኞች ውስጥ ያሉ አዋቂዎችን በሰበሰቡት እውቀትና ተግባር ምክንያት ደረጃቸውን ከፍ ያደርጋል ማለቱ ነው።
በሌላ አንቀፅም አዋቂዎች ፈሪሀ አላህ እንደሆኑም ሲገልፅ እንዲህ ብሏል:-
إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ
«አላህን ከባሮቹ ውስጥ (ተገቢውን መፍራት) የሚፈሩት አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡» ፋጢር 28
ከፍጡሮቼ የሀያልነቴን፣ የአሸናፊነቴንና የስልጣኔን ደረጃ የሚያውቅ ነው የሚፈራኝ ማለቱ ነው። ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አሉ:- “እውቀት ማለት ሀዲስን በብዛት መሸምደድ አይደለም፣ ነገር ግን እውቀት ማለት አላህን በመፍራት ብዛት ነው!።”
ሀሰኑል በስሪ (ረሂመሁላህ) “አዋቂ ማለት አላህን በምስጢር የፈራ ነው!” ይላሉ።
እውቀት አላህን ከመፍራትና ከተግባር ጋር ካልሆነ ከአይሁድ ያመሳስላል። ያለ እውቀት በመሃይምነት አላህን ማምለክም ከክርስቲያኖች ያመሳስላል። በመሆኑም እንወቅ! ባወቅነው ለመተግበር የአቅማችን እንጣር!። ከመሃይመነት ጭለማ በመውጣት የተለያዩ የጥመት ቡድኖችን ለይተን አውቀን እንጠንቀቅ እናስጠንቅቅ!።
◦◦🖋ኢብን ሽፋ: ጁማዱል ኡላ 21/1442 ዓ. ሂ
Join ➴➘➘➷
◦➧ http://t.me/Menhaje_Aselefiy