አንድ ወጣት አንዲት ቆንጆ ልጅ ይወድና ፍቅሩን ለመግለፅ በጣም ይፈራል፡፡ ጓደኞቹ እንዲነግራት ቢያበረታቱት ደፍሮ መጠየቅ አልቻለም፡፡ በቃ እሷን እያሰበ በትምህርቱ እየደከመ ሳቅ ጨዋታ እያስጠላው ሰውነቱ እየቀነሰ መጣ፡፡
ጭንቀታም መሆን እጅግ ያሳሰባቸው ጓደኞቹ በስንት መከራ አግባብተው እንዲነግራት ያደርጉታል፡፡ እናም ሲፈራ ሲቸር በጣም እንደሚወዳት ይነግራታል፡፡
እሷም ቀብራራ ነገር ነበረችና እንዲህ አለችው 'ውይ በጣም ይቅርታ እንኳን የፍቅር ጥያቄህን ልቀበል ይቅርና በአለም ላይ ማንን ትጠያለሽ ብባል አንተን ነው የምለው እና ይሄን ጥያቄ ደግመህ እንዳታነሳብኝ ' አለችው፡፡
ልጁም ምንም እንዳልተፈጠረ ተረጋግቶና ፈገግ ብሎ ወደ ጓደኞቹ ይመለሳል፡፡ ጓደኞቹም ፈገግታውን ሲያዪ ልጅቷ የፍቅር ጥያቄውን እንደተቀበለችው አምነው በደስታ ተቀበሉት አንደኛው ጓደኛው 'እሺ አለችህ አይደል? በጣም ደስ ይላል' ሲለው ወጣቱ ልጅ 'አረ በፍፁም !እንደውም በዓለም ላይ እንደኔ የምትጠላው ሰው እንደሌለ ነው የነገረችኝ' አላቸው፡፡
ጓደኞቹ ግራ ተጋብተው 'ታድያ እንዴት አላዘንክም እንዴት አልተከፋህም?' አሉት እሱም ረጋ ብሎ እንዲህ ሲል ,መለሰላቸው ''ለምን እከፋለው ለምንስ አዝናለሁ? እኔኮ ያጣሁት በአለም ላይ ከምንም በላይ የምትጠላኝን ልጅ ነው፡፡ እሷ ግን ያጣችው በአለም ላይ ከምንም በላይ የሚወዳት ሰው ነው ስለዚህ እኔ ሳልሆን ማዘንም መከፋትም ያለባት እሷ ናት'' አላቸው፡፡
ይሄ ታሪክ የኛም ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ የምንወደው ሰው ጥላቻውን ሲያሳየን ወይም ሲርቀን እንከፋለን እናዝናለን እናለቅሳለን ግን ይሄን ማድረግ ያለበት ያ ትቶን የሄደ ሰው እንጂ እኛው ልንሆን አይገባም፡፡
Join ፦ @family345
From @mdfunny