ግዕዝ ሙላት /Geez Mulat\ ግጥሞቹ


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


አነ ግጥም_
አነ ቃል _
አነ ግዕዝ _
አነ ጥበብ

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




ከምኔው መጡ ከምኔው ሄዱ.....?


በምን መርዝ ልርሳሽ
ምኑን ስር ልጠጣው፣

የሰጠሺኚ ፍቅር
በልጦ እየሻረው፣

____
2011 ዓ/ም

@geez_mulat


____

አንዳንድ ሰላም አለ ዝምታን ሚፈራ፣

ራሱን ደብቆ በጩኸት ሚሰራ፣

___
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat


____

አንዳንድ ከንፈር አለ ፥
ማር የሚመስል፣
ለስላሳ እሚመስል፣

የሂዎት እሬትን ፥
ደብቆ ሚያበስል ፣
ደብቆ ሚቆስል፣


___
ግዕዝ ሙላት

@geez_mulat


____


አንዳንድ ከንፈር አለ ማር የሚመስል፣

የሂዎት እሬትን ደብቆ ሚያበስል ፣


___
@geez_mulat


አጉብጠን ጋላቢ፣
ከሂዎት ቀንጫቢ፣
ከብርድ ላይ ላቢ፣
ከደርቅ ጡት ጠቢ፣
ሆንን ለጦቢያይቱ
ገዳይና አሳቢ፣
እስከመቼ እንሁን ደረቅ ዘር ደራቢ፣

_
የሆነች ሀገር ትናፍቀኛለች

__
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat ^^


አንዳንድ ሰማይ አለ ፣
አንዳንድ ዝርግ አለ፣
ደመናን አምኖ ፀሀይን የጣለ፣

_


ማደሪያሽን ባላውቅ በዋልሽበት ሄድኩኚ፣
አላርፍ ብትይ አይድል የተንከራተትኩኚ ፣
ፀንቶ ለማፍቀሩ እኔ መች አነስኩኚ፣
____

ግዕዝ ሙላት

@geez_mulat
photo..:Geez


መልካም የፈረሶች ቀን 😏

____
ቀለሙን ብጠይቅ ፈረሱን፣
እሱ ምን አውቆት መልሱን፣
በህገ ተፈጥሮ በአምላክ መኖሩን ፣

እጂማ ዘሩን ፣
እጂማ አይነቱን፣
ሰው ካልሰዬመው ስሙን፤
የት አውቆት ቀለሙን፣

ሆኖም ደርሶ ባይዋጋም፣
ሰውን ይመስል
ፈረስ ሰው አይበላም፣

----
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat

መልካም የፈረሶች ቀን !!


Watch "ምን ይሻላል ?? #ግጥም (ገጣሚ ግዕዝ ሙላት )@comedianeshetu @geez_mulat #ኦርቶዶክስ #ኦርቶዶክስ #ዘለሰኛ" on YouTube
https://youtu.be/h42r1HTG9wc


ሲመሽ
____

ሚደምነው ለኔ ፥ ሚጨልመው ለአንቺ፣
ሚያነቅፈኚ እኔ፥ የምትደሚው አንቺ፣

ገና ሳላውቅ መንጋት
ገና ሳላውቅ ማለም፣
ሲነጋ እንዲታወቅ
ይመሽ ጀመረ ይበልጥ እንድደመም፣

በድንግዝግዝ ሰማይ፥ መማሩን ለሚችል፣
መሽቶበት ለሚውል፥
ወገግ ሲል ማዬት ፥ምን ያህልስ ደስ ይል፣

___
ግዕዝ ሙላት

@geez_mulat


አሁን ደሞ
ነጋ
አሁን ደሞ
መሼ
በሚል ሀሳብ ተወጥሬ ፣
እንዴት ተስፍ ይታዬኚ በምሬት ታጥሬ ፣

ተመስገን ለዛሬ
___

ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat


አያ ሙሌ
____

አያ ሙሌን መስዬ
ቅርፅ ጥን ስሰራ፣
ሙሉጌታን ይመስል
ከሀሳቦች ጋራ ፣
ሁኜ ባላጋራ፥
ከራሴ ስዳራ ፣
ማንም ሳይረዳው
ከዘመኔ በሯል የፊደሌ ቁራ፣

እፅፍለው እኔ፣ ብዕርን አምኜ፣
ከዘመን ቀድሞ፥ የፃፍኩት ስንኜ፣
ይረዱትስ ይሆን ከትናንቱ ሁኜ
ትውልድ ይዘክረው ፥እኔ ሞት ላይ ሆኜ፣

እንጃ እሆን_ ይሆን አያሙሌ፣
ለማትነሳ ጥበብ
በስጋ መረገጥ ይሆናል እድሌ ፣

እያልኩኚ በውኔ፣
ስንኚ እቀርፃለው
ፊቱን ሳዬው በአይኔ ፣
____

መታሰቢያነቱ:_

ለባለቅኔው :ሙልጌታ ተስፍዬ (አያ ሙሌ)
( ሳይነሳ ለወደቀው )

---
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat


አሁን ደሞ የyoutube ቻናላችን ጋር እንግባና subscribe እናድርግ


https://youtu.be/qoCM-Xdp6so


ታላግጪአለሽ አንቺ
____--


መውደቅ እስኪደርስ ጭቃ እስኪነካሽ፣
ንፁህ ያልሽው ወንዙ አስቆ እስኪበላሽ፣

ላለቀሰ ሁሉ ሳቅሽን ስትገልጭ፣
በሀዘን ኮፈን ደመና ቀድሞ እጂ
ሰማዬ ነበር በአንቺ የሚቋጭ፣

በምትሰሚው ሁሉ እየሄድሽ ብትከፍቺ፣
ብቻ ቀን ጠብቂ
በሀዘንሽ ሰአት
ሀዘናት በሙሉ ያለግጣሉ በአንቺ፣

_
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat




የyoutube ቻናሌን ግቡና እዬት እስኪ መልካም ነገር አታጡበትም !!



___




ስትቀርቢኚ ጋኔሌ ይነሳል😁
___-

ደግ አረግሽ ደግ አረኩ
ስቴጂ ከአይኔ፣
ከማልቀስ በፊት
ጥርሴ አልታየም እጂ
ስቄለው እኔ፣

እውነቱን ልንገርሽ ለሳቄ ምሳሌ፣
ትቶኛል ለቆኛል...
አንቺ ከሄድሽ ኋላ የሚያስጮህ ጋኔሌ😁፣
ለካ

መቅረብሽ እርኩሰት የጋኔል አለሌ፣
መራቅሽም ሆኖ.. ተገኜ የመዳን ፀበሌ ፣

ሸሸሺኚ
ሸሸውሽ፣
ሸኜሺኚ
ሸኜውሽ፣

እዚህ ላይ ደግ አረኩ፣
ያላረግሺው እኔ ብቻ አረኩ፥
እኔ አንቺን አይደለው
ስትክጂኚ ግን ታመንኩ፣
____

ግዕዝ ሙላት
👇👇👇👇👇
@geez_mulat

Показано 20 последних публикаций.

228

подписчиков
Статистика канала