TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
ቀደምት ኢትዮጲያውያን

19 Jan 2022, 18:33

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

በዓለ ጥምቀት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።



በዓለ ጥምቀት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚከበሩት በዓላት አንዱና ዋናው የጥምቀት በዓል ነው። የጥምቀት በዓል ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ትሕትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ተጉዞ በአገልጋዩ በቅዱስ የሐንስ እጅ የተጠመቀበትን ዕለት የምናስብበት ከጌታችን ዓበይት በዓላት አንዱ ገናና በዓል ነው፡፡

በአፍ መነገሩ፣ በልብ መታሰቡ፣ ምስጋናውም ሁሉ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕለቱን ተፀንሶ ዕለቱን ተወልዶ ማድግና የወደደውን ሁሉ ማድረግ ሲቻለው ፍጹም አምላክ ብቻ ያይደለ ፍጹም ሰውም በመሆኑ ዘመን የማይቆጠርለት እርሱ ከብቻዋ ከሐጢአት በቀር በሰው ሥርዓትና ጠባይዕ ቀስ በቀስ በማደጉ 30 ዓመት ሲሆነው ሊጠመቅ ወደርዳኖስ ወንዝ ሔደ ትብሎ ዘመን ተነገረለት፡፡ ዮርዳኖስ እንደደረሰ ጌታችን ተለይቶ የሚታወቅበት ምልክት ሳይኖረው ቅዱስ ዮሐንስ በመገልጥ አወቀው። ይህንንም ራሱ ሲመሰክር «እኔም አላውቀውም ነበር፥ ዳሩ ግን በውኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ፦ መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየው፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው አለኝ» (ዮሐ. ፩፥፴፫) ይላል። ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀት በውሃ ያጠምቅ እንደነበረና ልጅነት የሚገኝበት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ምሉዑ የድኅነት ምሥጢር የሚገኘውና የሚታወቀው ግን ከእርሱ በኋላ ከሚመጣው ከክርስቶስ የተነሣ እንደሆነ መስክሯል።

ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ባመሰገነበት በአንቀጸ–ብርሃን ድርሰቱ የአብን ነገር የነገረን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ የውልድንም ነገር አጎልቶና አስፍቶ የነገረን አብ እንደሆነ ሲያስረዳ «ልጅህ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንተ ብቻ አባቱ እንደሆንክ እርሱም ብቻ ልጅህ እንደሆነ አስተማረን።በሰማይ እናት በምድርም አባት የለውም ብለን እናምናለን። መምጣቱን ካአባቱና ከእውነት መንፈስ ከጰራቅሊጦስ በቀር የሚያውቅ ሳይኖር ከሰማይ ወረደ ብለን እናምናለን» ሲል ተናግሯል። ይህም የጥምቀት መንሠረቱ ነው። አባቱን አብን ሕይወቱን መንፈስ ቅዱስንና እሱን ወልድን ማወቅ እና ማመን ከሌለ በውሃና በመንፈስ ቅዱስ አንዲቱን ጥምቀት መጠመቅና ልጅነትን ማገኘት አይቻልም።

ቅዱስ ዮሐንስ በመንፈስ ቅዱስ ተልኮ «እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸ ከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል» (ማቴ.፫፥፲፩)። እያለ የላቀ ጥቅም የምታሰጠው ጥምቀት ከእርሱ የትገኝ የጌታችንን መምጣት በጉጉት እየጠበቀ፣ ትንቢት እየተናገረ፣ የተጠራለትንና የተመረጠለትን ሥራውን እያከናወነ ሕዝቡን እያዘጋጀ ሳለ አስቀድሞ የተናገረለት ክርስቶስ በሥፍራው ተገኝቶ የጽድቅ ሥራውን ተመለከተከለት ወደደለት። አጥምቀኝ ብሎ ሲጠይቀው እውነተኛ ሥራውን እንደወደደለትና እንዳጸደቀለት ያጠይቃል።

ዛሬ እያንዳንዳችን ወደምንገኝምበት ዮርዳኖስ ጌታችን ቢመጣና ቢጎበኘን በቅዱስ ዮሐንስ ምትክ የተሾመለትን ሥራ፣ የተጠራለትን አገልግሎት በተሰጠው ጸጋ እያከናወነ የሚያገኘው ነቢይ፣ ሐዋርያ፣ ጳጳስ፣ ካህን፣ ዲያቆን፣ ዘማሪና ምእመን ያገኝ ይሆን? እውነቱን እንናገር ካልን እንዲያ ሲያደርግ የሚገኝ በጎ አገልጋይ በጭንቅ ካልሆነ በቀላሉ በሩቅ ካልሆነ በቅርቡ ማግኘት ከባድ ነው

41 0 0
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Наш блог Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot