👆
''ፓርቲዎች በአዋጁ ዙሪያ አለመስማማታቸው እንቅፋት ሆኖብኛል'':- ምርጫ ቦርድ
************************************
ቀጣዩን ምርጫ ለማስኬድ እየተዘጋጀ ቢሆንም ፓርቲዎች በአዋጁ ዙሪያ አለመስማማታቸው እንቅፋት እንደሆነበት ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ዙሪያ የጠራው ውይይት ያለስምምነት መጠናቀቁን በተመለከተ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ሰብሳቢዋ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ፓርቲዎቹ ሐሳብ ሰጥተውበት በፓርላማ የጸደቀ አዋጅ ቢሆንም ለተፈጻሚነቱ ወደፊት ከመምጣት ይልቅ በየጊዜው አዲስ ሐሳብ በማንሳታቸው መቸገራቸውን ገልጸዋል፡፡ አዋጁን ተከትሎ የወጡ 39 መመሪያዎችን በተመለከተ ከፓርቲዎቹ ጋር ውይይት ቢደረግም አሁንም የጊዜ ገደብ በሌለው መልኩ ፓርቲዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ማንሳታቸውን አመልክተዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከፓርላማው ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉም የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ጠቁመዋል፡፡ የ2012ን ሀገራዊ ምርጫን ለማካሄድ ቦርዱ በጥሩ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝም መናገራቸውን የዘገበው አብመድ ነው፡፡
@kushmedia