Legal info🚮 (የሕግ-መረጃ )⚖️


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ይህ channel በማንኛው ህግ በተለቀቁ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የተፈጠረ ነው።
እባክዎን በቡድኑ ውስጥ ቢያንስ 50 አባላትን ይጨምሩ እና ማንኛውንም የኢትዮጵያ ህግ ተዛማጅ ጥያቄዎችን ይጠይቁን ። ግን ያነሰ ጊዜ እና ጉልበት የሚጠይቁ ጥያቄዎችን መጠየቅ ከፈለጉ ፣ እንደ ቁሳቁስ ፣ በማንኛውም ጊዜ መጠየቅ ይችላሉ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Http://t.me/lawabelethio

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አጣሪ ጉባዔው በ55 የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ ሰጠ።
አርብ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ጉባዔ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ተገቢው ምርመራ እና ማጣራት ተደርጎባቸው ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች መካከል 55 በሚሆኑት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ ሰጥቷል።

በዕለቱ ጉባዔው ከተወያዬባቸው 55 አቤቱታዎች መካከል በቁጥር 49 የሚሆኑት ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም ሲል እንዲዘጉ ወስኗል።
በሌላ በኩል 3 የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ ደግሞ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎባቸው ለውሳኔ እንዲቀርቡ ጉባዔው አቅጣጫ አስቀምጧል።
በተጨማሪም በሦስት የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታ ላይ ደግሞ ተጠሪዎች ምላሽ እንዲሰጡ ጉባዔው ትዕዛዝ ሰጥቷል።


የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ
👇👇👇👇👇👇👇👇http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio


የተጨማሪ_እሴት_ታክስ_አዋጅ_ቁ_1141_2016_ማውጫ_እና_ትርጓሜ.pdf
1.1Мб
Share የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁ. 1141 - 2016 ማውጫ እና ትርጓሜ.pdf
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇Telegram channel here
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio


አድስ አዋጅ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
ታማሚዎች በሐኪም እርዳታ እንዲሞቱ የሚደነግገው ህግ ፀደቀ።
በኢትዮጵያ የወንድ የዘር ፈሳሽ፣ የሰውነት አካል መለገስ እና በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት እና አስተዳድር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። አዋጁ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጀምረው የማያውቁ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የጤና አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የሚያደርግ ነው። ለአብነትም መዳን በማይችል እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሀኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደው፣ የሰውነት አካልን ያለ ክፍያ መለገስ፣ የወንድ የዘር ፍሬ እንዲለገስ እና ሌሎችም አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን ይፈቅዳል። ምክር ቤቱ ላለፉት ወራት የተለያዩ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

አዋጅ ቁጥር 1362/17 ሆኖ ከታተመበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።


አድሱ የነዳጅ ሕግ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የነዳጅ ግብይት ስርዓትን ለመቆጣጠር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው አዲስ አዋጅ በግብይት ሂደት ውስጥ የሚታዩ ህገ ወጥነቶችን ለመቀነስ ያግዛል ተብሎ ታስቧል፡፡
ሀገሪቱን ከፍተኛ የውጭ መንዛሪ ከሚጠይቁ ከውጭ ከሚገቡ ሸቀጦች መካከል አንዱ የሆነው ነዳጅ የዋጋው መጨመር እና መቀነስ በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ጉልህ እንደሆነ ይነገራል፡፡
መንግስት በድጎማ የሚያቀርበውን የነዳጅ ምርት በሂደት ሙሉ ለሙሉ ድጎማውን በማንሳት በሚመጣበት ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ አቅዶ ተከታታይ የዋጋ ማሻሻያዎችን በተለያየ ጊዜ እያደረገ ይገኛል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ በግብይት ሰንሰለቱ ውስጥ የሚታዩ ህገወጥነቶችን ይቀርፋል ያለውን አዲስ አዋጅ በምክርቤት አጽድቋል፡፡
አዋጁ በዘረዘራቸው የህግ መተላለፎች መሰረት በገንዘብ እና በእስራት የሚያስቀጡ ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡
በአዋጁ መሠረት ከመሸጫ ዋጋ በላይ በመሸጥ የሚፈጸም የመጀመሪያ ጥፋት ከ350 ሺህ - 500 ሺህ ብር ያስቀጣል።
ድርጊቱ በተደጋጋሚ ከተፈጸመ ደግሞ የገንዘብ መቀጮው ላይ ከ3 እስከ 5 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት እንደሚኖር ከአዋጁ ያገኝነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በአዋጁ መሠረት የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ ያከማቸ፣ ሊሸጥ ከሚገባው ሰው፣ ቦታ እና የግብይት ሥርዓት ውጪ ሲሸጥ የተገኘ" ማንኛውም ሰው፤ ከ3 - 5 ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከ350 ሺህ - 500 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል። 
የነዳጅ ምርቶችን ሆን ብሎ ከባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል ለግብይት ማቅረብ ከ5-7 ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከ350 - 500 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ አዋጁ ላይ ተመላክቷል፡፡
በአዋጁ መሠረት የነዳጅ ውጤቶች ከተፈቀደለት የማጓጓዣ መስመር ውጪ ማጓጓዝ፣ ከተፈቀደለት ማራገፊያ ስፍራ ውጪ ማራገፍ ወይም ወደ ጎረቤት ሀገር በኮንትሮባንድ ማጓጓዝ፤ ከ5 ዓመት - 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት እና ከ400 ሺህ እስከ 700 ሺህ ብር ያስቀጣል።
ከሚመለከተው አካል በጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኝ የነዳጅ ውጤቶችን የነዳጅ ማደያ በሌለባቸው አካባቢዎች መሸጥ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከ300 - 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ጥፋት ነው።
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣንን ወይም የሚመለከተውን አካል የቁጥጥር ሂደት መቃወም እና ማሰናከል ከአምስት ዓመት በማይበልጥ እስራት እና ከ200 እስከ 500 ሺህ ብር ያስቀጣል፡፡
በሌላ በኩል የነዳጅ መቅጃ መሳሪያዎች የልኬት ሜትር ማስተካከያ ተደርጎበት በፕሎምፕ የታሰረውን መቁረጥ ወይም ልኬቱን ማዛባትም በተመሳሳይ ከ350 እስከ 500 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ አዋጁ ደንግጓል።
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio


በወንጀልና በሙስና የተፈራ ንብረት የማስመለስ አዋጅ ጸደቀ
**
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው14ኛ መደበኛ ስብሰባው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል። አዋጁ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈራን ንብረት ማስመለስ የሚያስችሉና የሕግ-ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዕጸገነት መንግስቱ በረቂቅ አዋጁ የተደረጉ ማስተካከያዎችና የተጨመሩ አንቀጾችን አስመልክተው ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል። ቋሚ ኮሚቴው በአዋጁ ላይ በአስረጅ፣ በህዝብና የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ግብዓት እንደሰበሰበ ገልጸዋል። የንብረት ማስመለስ አዋጅ የመንግስትና የህዝብ ንብረትን ለማስመለስ የነበረውን የሕግ ክፍተት የሚሞላ እንደሆነ አስረድተዋል። አዋጁ ዜጎች በላባቸውና በወዛቸው ንብረት እንዲያፈሩ የሚያበረታታ፣ በወንጀል ንብረት የሚያፈሩትን ተጠያቂ የሚያደርግ፣ የአገርን ዕድገት የሚያሳልጥ እንደሆነ አስተያየት የሰጡ የምክር ቤት አባላት አንስተዋል። ግለሰቦች በወንጀልና በሙስና ያፈሩትን ንብረት የሚያስመልስ በመሆኑ በተፈጻሚነቱ ላይ ጥንቃቄ ማድረግና አስፈጻሚ አካላትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ እና የዜጎችን ንብረት የማፍራት መብት እንዳይጋፋ መታየት አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል። የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዕጸገነት መንግስቱ በአዋጁ ሃብት የማፍራትና የማውረስ ሕገ-መንግስታዊ መብትን የሚቃረን ድንጋጌ አለመካተቱንም አብራርተዋል። የጸረ-ሙስና ትግል እንዲጠናከር የሚያደርግ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘና የተመዘበረ የአገር ሃብትን ለማስመለስ የሚያስችልና ሕገ-ወጥነትን የሚያስቆም አዋጅ እንደሆነም ጨምረዋል። ምክር ቤቱ በአዋጁ አስፈላጊነትና ወቅታዊነት ላይ ዝርዝር ውይይት በማድረግ በ ሶሰት ተቃውሞ እና በአራት ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።Parliament approves asset recovery bill with retroactive seizures up to ten years
DRAFT
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio


አድስ ዜና 👇👇👇👇👇👇👇👇
በህገወጥ የነዳጅ ግብይት የታየዘ ግለሰብ ነዳጁ ተወርሶ በእስራት እና በገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ የሚያደርገው አዋጅ ጸደቀ‼️
***

ምክር ቤቱ  6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባዔ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ  እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባዔው፤ የነዳጅ ውጤቶችን  ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርት በመመርመር አጽድቋል፡፡

በዚህም  ነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ለመደንገግ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ በሁለት ተቃውሞ   በአንድ ድምጽ ተአቅቦ ጸድቋል፡፡
አዋጁ ከያዘቸው ጉዳዮች መካከል፤

መንግሥት ከሚያወጣው የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ተመን ውጪ በተደጋጋሚ የመገበያየት ወንጀል እንዲሁም የነዳጅ ምርቶችን ከባዕድ ነገሮች ጋር መቀላቀል  ከ3 ዓመት እስከ 5 አመት ጽኑ እስራት እንዲሁም  ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺ  ብር ቅጣት ይጥላል፡፡

የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ያከማቸ፣  በዚህም   ሊሸጥ ከሚገባው ሰው ቦታና የግብይት ስርዓት ውጭ ሲሸጥ የተገኘ ወይም አደጋ ያስከትላሉ በተባሉ መያዣዎች ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ የተያዘው የነዳጅ ውጤት ተወርሶ ከ3 ዓመት በማይበልጥ እስርና ከብር 350 ሺህ እስከ 500  ሺህ ብር   የሚደርስ ቅጣት ይፈጸምበታል የሚሉ ነጥቦች ይገኙበታል፡፡


ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፍትሕ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት በክልሉ ሥር በሚገኙ ወረዳዎች ዳኛ ወይም ዐቃቤ-ሕግ ሆኖ ለመሥራት ለሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ያወጣው ማስታወቂያ

ብዛት፡- 300
የመመዝገቢያ ጊዜ፡- ከታኅሳስ 30 እስከ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም
http://t.me/lawabelethio




መቼም ቢሆን እራስህን መሆን ልመድ:: የራስህን ባህሪ የራስህን አለባበስ የራስህ የሆነ ችሎታ አድርግ : አንተ በአንተ ላይ ሚያምርብህ ካንተ ጋር ሚሄድ ነገር እያለ ጉደኛህ ስላደረገ የሆነ ሰው ላይ ስላየህ አታድርግ
~ሰው ፀጉሩን አሳደገና አንተም አታሳድግ
~ሱሪ ዝቅ አድርገው ሲሄዱ አይተህ ሚያምር መስሎህ አንተም ዝቅ አታድርግ ይልቅ በስነሥርአት ልበስ
~የቅርብህ ሰው የሄደበት ቦታ እንሂድ ስላለህ ብቻ አትነዳ እራስህን ሆነህ የራስህን መንገድ ተከተል
~እስከ መቼ ሌላ ሰውን እየሆንክ ትኖራለህ ወደዚ ምድር የመጣህው የራስህን ሥራ ሰርተህ ልታልፍ ነው እንጂ ጊዜህን በማይሆን ነገር የሰውን ሃሳብ እየተከተልክ እንድትጨርስ አደለም
ምትወደውን ሥራ የምታምንበትን አድርግ

እህቴ ሆይ
አንቺም ሰውን ብቻ አትከተይ
#ጉአደኛሽ ልደት አከበረች ብለሽ አታክብሪ ልምድሽ ያልሆነ ነገር ሰው አደረገ ብለሽ አታድርጊ አንቺ አንቺው ነሽ
#ሴቶች ልብሳቸውን ከፍ አርገው ለበሱ ሰውነታቸው ታየ ብለሽ አንቺም እንዳታረጊ ሴት ልጅ ሚያምርባት ሰውነቷን  ስትሸፍን ነው
#አንቺ መማር ምትፈልጊው ነገር እያለ ጉአደኛሽ ይቅር ሌላ እንማር ስላለች አላስቀይማትም ብለሽ እሷን አትከተይ በራስሽ ወስኚ ቢቻል ምክር ተቀበይ እንጂ ሁሌ የሌላ ሰውን መንገድ እየደወገምሽ አትኑሪ
~ባለሽ ነገር ተሰጦሽ በሆነ ነገር ስሪበት

ሁሌም እራሳችሁን በመሆን ኑሩ ሕይወት ጣዕም ያላት እራስን በመሆን ውስጥ ነው::

        
                 የ NESS ብዕር

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio
http://t.me/lawabelethio


የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ እና በሰው የመነገድ ወንጀሎችን በተፋጠነ ሁኔታ እልባት እንዲያገኙ የሚያግዝ መምሪያ(ማኑዋል) ላይ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሄደ
***
የጀስቲ
ስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በህጻናት ጉልበት ብዝበዛ እና በሰው የመነገድ ወንጀሎች በተፋጠነ ሥርዓት እልባት መስጫ ረቂቅ የአሰራር መምሪያ ላይ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት፣ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እንዲሁም የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በቀን 26/04/2017 ዓ.ም የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

መምሪያው በህጻናት ጉልበት ብዝበዛ እና በሰው የመነገድ ወንጀል ተጎጂ ለሆኑ ህጻናት ፈጣን፣ ፍትሃዊ እና ተደራሽ በሆነ ሥርዓት ፍትህ የሚያገኙበትን የጉዳዮች አስተዳደር እና የዳኝነት ስልቶች በመዘርጋት እና በማጠናከር የጉዳዮችን አላስፈላጊ መዘግየት ለመቀነስ እና ህጻናትን ለሚመለከቱ የወንጀል ጉዳዮች ልዩ ትኩረት በመስጠት የህጻናትን እድሜ፣ ጾታ፣ ለአደጋ ተጋላጭነት እና ልዩ ፍላጎት ያማከለ አሰራርን በፍርድ ቤቶች ለመዘርጋት አላማ በማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ ለሊሴ ደሳለኝ የሰብዓዊ መብታቸው የተጣሰባቸው እና ጉዳት የደረሰባቸው ህጻናት ለደረሰባቸው ጉዳት የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት ያላቸው ቢሆንም አሁን በስራ ላይ ያለው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ህግ ለሁሉም ወንጀሎች በአንድ አይነት መንገድ መልስ የሚሰጥ እንጂ በህጻናት ጉልበት ብዝበዛ እና በሰው የመነገድ ወንጀልን በተመለከተ በልዩ ሁኔታ የሚያይበት ሥርዓት ባለመዘርጋቱ ከግዜ ወደ ግዜ እየተበራከተ ከመጣው ጉልበት ብዝበዛ እና በሰው መነገድ ወንጀል ጉዳት የደረሰባቸው ህጻናት ላይ ፈጣን፣ ፍትሃዊ እና ተደራሽ በሆነ ሥርዓት ፍትህ ከማስገኘት መብት አንጻር ከፍተኛ ተግዳሮት እየገጠመ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

አክለውም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት እና የህጻናቱን መብት ለማረጋገጥ ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ታምኖበት ረቂቅ የአሰራር መመሪያ ለፍርድ ቤቶች መዘጋጀቱና ግብዓት መሰብሰቡ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ረቂቅ መምሪያውን በማዘጋጀት የተሳተፉት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ክብርት ዳኛ ሩታ ገ/ጻዲቅ እና ጠበቃ ጌድዮን ሲሳይ ሲሆኑ መምሪያውን ለማዘጋጀት የተደረጉ ሂደቶች፣ የተዳሰሱ ሀገር አቀፍና አለምአቀፍ ህጎች፣ የተደረጉ ምልከታዎች እንዲሁም መምሪያው ያካተታቸውን ድንጋጌዎች አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል::

ረቂቅ መምሪያው ላይ ገለጻ እና ሰፊ ውይይት ተደርጎ በርካታ ግብዓቶች የተገኙ ሲሆን ግብዓቶቹን በማካተትና በማዳበር መምሪያዉ  በቅርብ ግዜ ጸድቆ ስራ ላይ ይዉላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት
http://t.me/lawabelethio


ፍቺ
• የሁለት ተጋቢዎችን የትዳር ግንኙት በሕግ መሠረት ማቋረጥ
ጋብቻ ከሚፈርስባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው የፍቺ ውሣኔ ሲሰጥ መሆኑ የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 75/ሐ/ ያመለክታል፡፡ ጋብቻ አንድ እንደሆነ ሁሉ ጋብቻው በፍቺ ሊፈርስ የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ሁለት የጋብቻ ስርአቶች መከናወናቸውም ሁለት ጊዜ የፍቺ ውሣኔ እንዲሰጥ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ተጋቢዎቹ ግንኙታቸውን ማቋረጥ ከፈለጉ ጋብቻው በሁለት አይነት ስርአት ስለተፈፀመ ግንኙቱን ለማቋረጥ እያንዳንዱን ጋብቻ አስመልክቶ የፍቺ ውሣኔ ሊሰጥ የሚገባው አይሆንም፡፡ የሕጉም አላማ ይህ አይደለም፡፡
አንድ ወንድ እና ሴት ኢትዮጵያ ውስጥ ከተጋቡ በኋላ በድጋሚ በውጭ አገር ጋብቻ መስርተው በዛው አገር በፍርድ ቤት ፍቺ ከፈጸሙ በግራ ቀኙ መሐከል የነበረው ጋብቻ አንድ ብቻ በመሆኑ በውጭ አገር የተሰጠው የፍቺ ውሣኔ ይህን በመካከላቸው የነበረውን አንድ ጋብቻ እንዳፈረሰ ተደርጎ ሊቆጠር ይገባል፡፡ ግራ ቀኙ ውጭ አገር ከሄዱ በኋላ ሌላ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት መፈፀማቸው ሁለት ትይዩ /Parallel/ ትዳር ውስጥ ነበሩ ሊያሰኛቸው አይችልም፡፡ በመሆኑም በመካከላቸው የነበረው የጋብቻ ግንኙነት አንድ የመሆኑን ያሕል የሚፈርሰውም በአንድ የፍቺ ውሣኔ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 40781 ቅጽ 8
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio


የሕግ ጉደይ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://t.me/lawabelethio
ውል ማፍረስ
• በህጉ የተቀመጡት የውል አመሰራረት መስፈርቶችን ያለሟላና ግድፈት ያለበት በመሆኑ የተነሳ የውሉ ወይም በውሉ የተቋቋሙትን ግዴታዎች መቅረት
ውል ማፍረስና ውል መሠረዝ በውል የተቋቋሙት ግዴታዎች ከሚቀሩባቸው መንገዶች ውስጥ የሚካተቱ ቢሆንም ምክንያታቸውና ውጤታቸው የተለያዩ ነው፡፡ የውል ማፍረስ ከውል አመሠራረት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን ውሉ ከአመሰራረቱ በህጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ባለማሟላቱ ግድፈት ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል የውል መሰረዝ ጉዳይ ከውል አመሰራረት ችግር የሚነሳ ሳይሆን ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታውን ካለመወጣት የሚመነጭ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 32299 ቅጽ 8


☞  የእድሜ ልክህን እውቀት ለመገብየት  የግድ የእድሜህ ፍፃሜ ላይ መድረስ አይጠበቅብህም ነገር ግን በእድሜም ሆነ በልምድ ከሚበልጡህ ቀስመህ ህይወትህን ማስዋብ ጥበብ ነው

☞  ምክር ብትሰማ በነፃ ትማራለህ አሻፈረኝ ካልክ ዋጋ ከፍለህ ትማራለህ

☞ ሁሉን ካላየሁ አላምንም አትበል  ከተጎዱ መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ

☞  ቆንጆ ትዳር እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ  ምክንያቱም የምትኖረው ከፀባይዋ ጋር እንጂ ከመልኳ ጋር አይደለም

☞ ለሰዎች  አንተ የሚጠበቅብህን አድርግ እንጂ ምላሻቸውን አትጠባበቅ

☞  ትችትን አትፍራ ፤ ስህተትህን ግን አጥራው እውነትን ተናግረህ ተገፋ እውነትን በመናገር የሀሰት ወዳጅህን ታጣዋለህ የእውነት ወዳጅህን ታተርፋለህ።

☞  ለህሊናህ ተገዢ ሁን፤  የገባህን አድርግ፤ ያመንክበትን ተናገር

☞ በቦታህ መምህር ያለ ቦታህ ተማሪ ሁን፤ ቃሎችህ ቁጥብ ይሁኑ፤  በአደባባይ እጅህን እንደሰንደቅ አላማ አውለብልበህ አስተያየት አትስጥ ምክንያቱም ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም።

☞  ሁሉን ላውራ አትበል ዝም ያሉት ይታዘቡሃል እውቀትህ በአላዋቂዎች ላይ ካንቀባረረህ ለውድቀት ቅርብ ነህ አስተውል

☞ ብልህ ሰው ከሽማግሌው ምክር ሲማር ሞኙ በሽምግልናው ይማራል
https://t.me/lawabelethio
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇))))))👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇)))))https://t.me/lawabelethio






የመ/ቁ.16648
                                         ታህሣስ 20 ቀን 1998 ዓ.ም.
        
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
           2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
           3. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
           4. ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ
           5. ወ/ሮ ሆሳዕና ነጋሽ
አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን
መልስ ሰጭዎች፡- እነ አቶ አንለይ ያየህ /27 ሰዎች/

ስለ ስራ ክርክር- የይርጋ ጊዜና የዕዳ ጥያቄ ቅድሚያ- የመብት ጥያቄ ስለሚቀርብበት የጊዜ አቆጣጠር - የይርጋ ጊዜ መቋረጥ - የይርጋ መብትን ስለመተው - ኃላፊነት የተሰጠው ባለስልጣን ስላለው ስልጣን - የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 162፣ 163፣ 164፣ 165፣ 166 (በጉዳዩ የተሰጠው የህግ ትርጉም የአዋጅ ቁ.42/85ን በመሻር በወጣው አዋጅ ቁ.377/96 ድንጋጌዎችም ተፈፃሚነት አለው)

መ/ሰጭዎች በጌዶ፣ነቀምት እና ጊምቢ ባከናወነው የትራንስሚሽን መስመር መዘርጋት ስራ ለተሳተፉት ሌሎች ሰራተኞች አመልካች መጋቢት 15 ቀን 1992 ዓ.ም የሰጠው የሁለት ዕርከን ጭማሪ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ነሐሴ 15 ቀን 1993 ዓ.ም ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ባቀረቡት ክስ ክሱ በይርጋ ሊታገድ ይገባዋል በማለት አመልካች ያቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቦርድ ውድቅ በማድረግ በፍሬ ነገሩ ውሳኔ በመስጠቱና ውሳኔውም በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመጽናቱ የቀረበ አቤቱታ፡፡

ውሳኔ፡- የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳዩ ወሳኝ ቦርድ የሰጠውና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያጸናው ውሳኔ ተሽሯል፡፡
1. በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 162 /3/ መሰረት የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓትና የሌሎች ክፍያዎች ጥያቄ ሊጠየቅ ይገባው ነበር ከሚሰኝበት ጊዜ ጀምሮ የስራ ውሉ ተቋርጦ ቢሆን እንኳን ይህን ከግምት ሳያስገባ እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
2. የሰራተኛው ወይም የአሰሪው ጥያቄ በተተኪዎቻቸው ወይም በወራሾቻቸው በሚቀርብበት ጊዜ በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 162/3/ እና 162/3/ በተደረጉ የይርጋ ድንጋጌዎች ይመራል፡፡
3. የሰራተኛው ወይም የአሰሪው ተተኪዎች ወይም ወራሾች የሰራተኛውን ወይም የአሰሪውን ሳይሆን የራሳቸውን መብት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡት ጥያቄ በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 162/3/ እና 162/4/ በተደነገጉት ሳይሆን በአንቀጽ 162/1/ በተደነገገው የይርጋ ድንጋጌ ይመራል፡፡
4. በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 164/1/ መሰረት የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚቋረጠው ክሱ በአዋጅ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን በተሰጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ወይም በፍርድ ቤቶች በተቋቋሙ የስራ ክርክር ችሎቶች የቀረበ እንደሆነ ነው፡፡
5. ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ባልተሰጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ወይም በስራ ክርክር ችሎት የቀረበ ክስ በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 164/1/ መሰረት የይርጋ ጊዜን መቆጠር አያቋርጥም፡፡
6. በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 164/2/ መሰረት የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚቋረጠው አቤቱታው የቀረበው ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀረበ እንደሆን ብቻ ነው፡፡
7. ለአሰሪ የቀረበ አቤቱታ በአዋጅ ቁ.42/85 (377/96) አንቀጽ 164(2) መሰረት የይርጋ ጊዜ መቆጠርን አያቋርጥም፡፡
8. በአዋጅ ቁ.42/85 (377/96) አንቀጽ 166(1) ከፍትሐ-ብሄር ህግ ቁጥር 1793 ጋር ተገናዝቦ መታየት አለበት፡፡
9. ሰራተኛ ወይም አሰሪ በአዋጅ ቁ.42/85 (377/96) አንቀጽ 166(1) ለመጠቀም በድንጋጌው የተመለከቱት ሁኔታዎች መከሰታቸውን እና ክሱ በይርጋ የሚታገድበት ከመድረሱ በፊት ያልቀረበው በድንጋጌው ከተመለከቱት ሁኔዎች ቢያንስ በአንዱ መከሰት ምክንያት መሆኑን በማስረጃ ማረጋገጥ አለበት፡፡


ለፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል
*****
የፍትህ ሚኒስቴር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለተቋሙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ስልጠና በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሀና አርአያስላሴ እንዳሉት እንደሀገር የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ከነዚህ ስራዎች አንዱ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምን ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትሯ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያገለግል ወጥ ፣አስተማማኝና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ስርኣት ለመዘርጋት ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አውስተዋል፡፡

የዲጂታል ስርኣት በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት መሆኑን ክብርት ሚኒስትሯ አንስተው ከፍትሕ አንፃር ወንጀልን ለመከላከል፣ወንጀል ከተፈፀመ በኃላ አጥፊዎችን ለመለየት ፣ሀሰተኛ ምስክርነትን ለመከላከል እና ሀቀኛ ምስክሮችን ለመለየት፣ በተደጋጋሚ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ለመለየት እንዲሁም የማረምና ማነፅ ተግባራትን ለማከናወን ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ፅህፈት ቤት ፍትሕ ሚኒስቴርን በቴክኖሎጂ የመደገፍ ስራን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀው፤የዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ዋና ዳይሬክተርና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዮዳሔ ዘ-ሚካኤል በበኩላቸው ዲጂታል ብሔራዊ መታወቂያ በፍትሕ ተቋማት መካከል ያለውን የመረጃ ልውውጥ ቀላል፣ቀልጣፋና ታዓማኒ ያደርገዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የስልጠና መድረኩ በዛሬ ውሎው ከቤት እስከ መስሪያ ቤት፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ውጥኖች እና ወቅታዊ ውጤቶች፣የብሄራዊ መታወቂያ የፖሊስ እና ስትራቴጂ መሰረት፣ የኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 ላይ ያተኮረ ነበር፡፡👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ.
Telegram
https://t.me/lawabelethio


የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ሰጠ፡፡
፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሰረት ጉባኤው በእለቱ በቀረቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ተወያይቶ
1. አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ላይ የቀረበባቸው የዲሲፕሊን ክስ የክስ ምክንያት ያለው በመሆኑ መልስ እንዲሰጡበት፤
2. ሁለት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች የቀረበበት የዲሲፕሊን ክስ ተጨማሪ ማጣሪያ ተደርጎበት  በድጋሚ ለጉባኤ እንዲቀርብ፤
3. በሰባት የተለያዩ መዝገቦች የክስ ሂደታቸው ሲታይ የነበሩ ስምንት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛች የቀረበባቸው የዲሲፕሊን ክስ አቤቱታዎች ዳኞቹን የማያስጠይቁ  በመሆኑ ውድቅ እንዲደረጉ፤
4. በሌላ በኩል ጉባኤው የአርባ ሰባት የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ሬጅስትራሮች  ሹመት መርምሮ አጽድቋል፡፡
የሬጅስትራሮቹ ሹመት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን የሰው ሃይል እጥረት ለማቃላልና ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት  አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio



Показано 19 последних публикаций.