❤️"የደሀ ልጅ ፍቅር"❤️
ክፍል 2
በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ,
ክረምት አልቆ መስከረም ሲጠባ አዲስ ተስፋ አዲስ አመት
ተጀመረ የማትሪክም ውጤት መጣ .በሚገርም ሁኔታ በከፍተኛ
ደረጃ ነበር ያለፍኩት .ደስ የሚል ዜና እናቴ ይሄንን ስትስማ
የሚሰማትን ደስታ ሳስብ በጣም ተደሰትኩ .,ሜላትም አልፋለች
በከፈተኛ ውጤት ባይሆንም ጥሩ ሰርታለች ሁለታችንም ተደሰትን
ኦ አምላኬ ነገን አንተ ታውቃለህ አልኩ በልቤ!!
ሜላቴ እናቴጋ መሄድ አለብኝ አልኳት አብረን እንሂድ አለችኝ እሽ
ብያት እናቴ ጋ ሄድን እናቴ ገና ከውጪ ስታየኝ ፊቴ በደስታ
መሞላቱን ስታይ እልልታዋን አቀለጠችው ተንበርክካ ጌታ ሆይ
አንተ ታውቃለህ አለች!!የደስታ እንባ በጉንጮቻ ላይ ኮለል ብለው
ወረዱ እኔም ተንበርክኬ እናቴን አቀፍኳት በደስታ ተላቀስን ,"እናቴ
ገና አኮራሻለው"አልኳት በጆሮዋ የደስታ እንባ እየተናነቀኝ,.
ሜላት ፍዝዝ ብላ የሚሆነውን ሁሉ ታያለች እሷም ግን በቁሟ
እንባዋ ይወርድ ነበር ,እኔና እናቴ ተቃቅፈን ተነሳን እናቴ በቃ
ቤተክርስትያን ተሳልሜ ልምጣ ገብርኤል ስለቴን ሰምቷል ብላ
ነጠላዋን አንጠልጥላ ከቤት ተመስገን ተመስገን!!እያለች ሄደች
,ናቲ ,"አይገርምህም እኔም እንዳንተ ጅግና ነው የምሆነው"ብሎ
መጥቶ ተጠመጠመብኝ .,ጎበዝ እንደዚህ አስብ እሽ ብዬው
መጣሁ እዚሁ ሁን ብዬው ሜላትን ልሽኝ ወጣሁ,.
ሜላት የሆነ ነገር ውስጧን እየከነከነው ነው ግን ምን እንደሆን
አላውቅም.ወደ ኪሷ ገብታ 20 ብር አውጥታ እንካ አለችኝ ምን
ላድርገው አልኳት ካፌ ገብተን ትንሽ እናውራ አለችኝ እሽ
አልኳትና ብሩን ወደ ኪሴ ከተትኩት.,
ካፌ ገብተን ሻይ አዘዝን ታውቃለህ ፍቅሬ የናንተ ቤተሰብ በጣም
ያስቀናል አለችኝ መሬት መሬት እያየች .እኔ አሁን እቤት ስገባ
ማለፍና መውደቄን እንኳን አልጠየቅም እንኳን ይሄን ያክል ፍቅር
ላይ ይቅርና አሰቀንታችሁኛል አለችኝ እንዳቀረቀረች,.እኛ ቤት
ንፁህ ፍቅር እንዳለ አውቃለው የሷን ስትነግረኝ ግን ግራ
ገባኝ.,ብቻ በፍረሀት ለምን?አልኳት .እ!አለች,.እኛ ቤት ማንም
ስለምይንም አይጨነቅም ትማራለህ ካልተሳካልህ የፈረደበት
የአባቴ ካንፖኒ አለ እዛ ትገባለህ በቃ ይሄ ነው አለችኝ በንዴት,.
አሁን ደግሜ ሌላ ጥያቄ ለመጠየቅ አልደፈርኩም ዝም አልኩ
ለማንኛውም እንሂድ አለችኝ እሽ ብያት የሰጠችኝን ብር ከኪሴ
አውጥቼ ከፍዬ ከካፌው ወጣ እሷን ታክሲ አስይዜ ቻው ተባብለን
ተለያየን,.
ወደ ቤት እየተመለስኩ ብዙ ነገሮችን አሰብኩ ለምን ቤተስብ
ፍቅር የለውም ,ለነገሩ ገንዘብ ስላላቸው ባይማሩስ ሜላትም
ዝም ብላ ነው የምትደክመው ምናለ እኔ የነሱ ቤተሰብ በሆንኩ.,!
አይ ተመስገን እንኳንም አልሆንኩ የእናቴ ፍቅር ከገንዘብ በላይ
ነው ::እያልኩ ወደ ቤቴ ገባሁ .,እቤት ስደርስ እናቴ ብና አቀራርባ
ሻማ ገዝታ ጠበቀችኝ ደስ አለኝ ,"እናቴ እወድሻለው"ብዬ
ግንባሯን ስሜ ተቀመጥኩኝ.,
እናቴ ደስ ስላላት ደስ ብሎኛል,በቃ እናቴ ከዛም ከዛም ብላ
ያጠራቀመቻትን ብር ሰብስባ ዬኒፎርም ልታሰፋልኝ ስታስብ ሜላት
ዬኒፎርሙን ቀድማ አሰፍታ አመጣችልኝ በጣም ሰነገጥኩ እኔ
ከዚህ በላይ እንድትረጂኝ አልፈልግም አልኳት,ሜላት ግን በቃ
እሽ ብላ ዬኒፎርሙን ሰጥታኝ ከቤት ቻው ብላ ሄደች.እናቴ
ደነገጠች እኔም ተከትዬ ሳልሸኛት ፈዝዤ ቀረሁ..........
✍✍✍ይቀጥላል✍✍✍.....
ከወደዱት ሼር እና ላይክ👍 ያድርጉ
:*:*:*:*:*🌺:*:*🌹:*:🌺*:*:*:*:*:*:
••●◉Join us share
@Yfiker_Sawe ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
...📩
@Hena_251