Репост из: ༒⋆ ·٠•●Åđmïŋ●•٠· ⋆ ༒
༒ Dn Wegen ༒
+ የወይን ጠጅ ጠግበዋል +
‹በዓለ ሃምሳ› እስራኤል ከግብፅ የፋሲካን በግ አርደው ከወጡ ከሃምሳ ቀን በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ በሲና ተራራ በድንጋይ ሰሌዳ ላይ የተጻፈ ሕግን የሠጠበት ዕለት ነው፡፡ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶ ከግብፅ ሳይሆን ከሲኦል ባርነት ፣ ከፈርዖን ሳይሆን ከዲያቢሎስ አገዛዝ ነፃ የወጣን እኛ ክርስቲያኖችም የጌታችንን ትንሣኤና የሐዲስ ኪዳኑን ፋሲካ ባከበርን በሃምሳኛው ቀን ልክ እንደ አይሁድ ልማድ በዓለ ሃምሳን እናከብራለን፡፡ ለዚህ ምክንያታችን ግን ከፋሲካ ነፃነት በኋላ በሃምሳኛው ቀን ለሙሴ በጽላት ላይ የተጻፈ ሕግን የሠጠው አምላክ በሐዋርያት ልብ ውስጥ በቅዱስ መንፈሱ አዲስቱን የወንጌል ሕግ የቀረጸበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡
በዚህች ዕለት መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ሐዋርያት እንደ ደብረ ሲናው ነቢይ ሙሴ በፈጣሪ ‹በአንተ ካለው መንፈስ ወስጄ በእነርሱ ላይ አደርገዋለሁ› ተብሎ የተነገራቸውና ከእነርሱ ተወስዶ የሚሠጥባቸው አልነበሩም:: (ዘኁ 11:17) ሐዋርያት የተሠጣቸው መንፈስ ለሌላው ሲሠጡ እንደ ሻማ ብርሃን ለሌላው ቢለኮስ የማያልቅና እየጨመረ የሚሔድ ከሙሴ የሚልጥ ጸጋ ያላቸው ናቸውና ቤተ ክርስቲያን በዓለ ሃምሳ የተሠኘውን የደብረ ሲና በዓል ወርሳ በድምቀት ታከብረዋለች፡፡
ለነገሩ የሚገርመው ለሐዋርያት የተሠጣቸው ለሙሴ ከተሠጠው ባይበልጥ ነበር፡፡ ሙሴ እኮ የተከራከረው ከፈርዖን ጋር ነበር ፣ ሐዋርያት ግን ከዲያቢሎስ ጋር ነው፡፡ እግዚአብሔርም ይህንን ውጊያቸውን አይቶም ነው እንደሙሴ ለኮልታፋ አንደበታችሁ አሮንን ልኬላችኋለሁ በማለት ፈንታ መንፈስ ቅዱስ አንደበት አድርጎ የሠጣቸው (መንፈስ ቅዱስ አሮን ይኩነኒ አፈ አለ ደራሲው!) እነርሱ የተሠጣቸው ኮልታፋን አንደበት የሚያቃና ብቻ ሳይሆን ሰባ ሁለት አዳዲስ ቋንቋዎችን እንደ ተወለዱበት ያህል የሚያናግር መንፈስ ነበር፡፡ ስለዚህ በዓለ ሃምሳ ከኦሪት ይልቅ ለሐዲስ የሚስማማ በዓል ነው፡፡
★ በሌላ ቋንቋ ይናገሩ ጀመር ★
እግዚአብሔር ዛሬ በሰናዖር ሜዳ የበተነውን የዓለም ቋንቋ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰበሰበው፡፡ በቋንቋና በዘር የማትገደብ የሁሉ ቤት ትሁን ዘንድ የጠራትና ቤዛ የሆናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደተወለደች አፏን ፈትታ በዓለም ቋንቋዎች ሁሉ መራቀቅ ጀመረች፡፡ አዲሶቹ ጳጳሳትና ካህናትዋ በቋንቋው ሁሉ እየተናገሩ ሁሉ ‹የገሊላ ሰዎች አይደሉም እንዴ እንዴት የተወለድንበትን ቋንቋ ይናገራሉ?› እያለ የሚያደንቃቸው ሆኑ፡፡
በእርግጥም ቤተ ክርስቲያንና ካህናት በአንድ ቋንቋ አጥር መታጠር ፣ በአንድ አካባቢ ሰው ብቻ መደመጥ አያምርባቸውም፡፡ ለዓለም የሚያበራ የወንጌል ብርሃን ይዘው ለተወለዱበት ቀዬ ብቻ ቢያበሩ ወይም ቢጨነቁ ምኑን ካህናት ሆኑ? አብርሃም የብዙኃን አባት ለመሆን የወገኖቹን ሀገር እንደተወ የብዙኃን አባት የሚሆን ካህንም ወገኑን ትቶ ካልወጣ አብራም (የጥቂቶች አባት) እንጂ አብርሃም (የብዙኃን አባት) መሆን አይችልም፡፡
ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አገልጋዮችዋን ከቋንቋ እስራት ፈትታ ነጻ አወጣቻቸው፡፡ የገሊላውን ዓሣ አጥማጅ ጴጥሮስን በግሪክ ቋንቋ እያናገረች ፣ ሌዋዊውን ማቴዎስ በአረቢኛ እያራቀቀች ያለ ልምምድ ዓለምን የምትማርከዋ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ተወለደች፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከቋንቋና ከነገድ ከጎሣ እስራት የተፈታችበት ይህ ዕለት ‹የቤተ ክርስቲያን ልደት› ተብሎ ከተጠራ ቤተ ክርስቲያን መልሳ ዘር ቆጠራ ውስጥ የገባችበት ዘመን ምን ተብሎ ሊጠራ ይሆን?
★ ክርስቶስን በበዓለ ሃምሳ ስናስበው ★
በእርግጥ በዓለ ሃምሳ ጌታችን ካረገ ከዐሥር ቀናት በኋላ የተፈጸመ በመሆኑ በዚህ ዕለት በቃሉ መሠረት መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያቱ የላከበት ቀን ነው፡፡ ይሁንና ከሐዋርያቱ የማይለየውን ጌታ በዚህች ዕለት ሲያርግ አንጋጥጠው ፈዝዘው ካዩት ሐዋርያት ጋር ዋሊያ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ እየናፈቅን ለአፍታ እናስታወሰው፡፡
ጌታችን በዛሬው ዕለት የሦስት ዓመት ተማሪዎቹን እንደየአቅማቸው የሃያ ፣ የሠላሳ ፣ የሃምሳ ፣ የሰባ ቋንቋ ተናጋሪዎች አደረጋቸው፡፡ ከዓሣ አጥማጅነት የጠራቸውን ፣ ከተናቁበት የሰበሰባቸውን የገሊላ የገጠር ሰዎች ከአይሁድ አልፎ በዓለም የታወቁ ወደር የማይገኝላቸው የቋንቋ ሊቃውንት አደረጋቸው፡፡ እርሱ ሲገልጥ ልምምድ አያስፈልግምና በእግዚአብሔር የተማሩት ምስኪኖች የዓለምን ጠቢባን የሚያሳፍሩ ምሁራን ሆኑ፡፡ አጋንንት በተገዙላቸው ጊዜ "ጌታ ሆይ አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ብለው ሊነግሩት የሮጡት ደቀ መዛሙርቱ ጌታ ቀድሞ ባያርግ ኖሮ ዛሬ ወደ እርሱ እየሮጡ "ጌታ ሆይ በመንፈስህ ቋንቋ ሁሉ ተገለጠልን" ብለው በደስታ በነገሩት ነበር።
እዚህ ላይ የጌታን ፍቅሩ እንናገር ወይንስ ትሕትናውን? ከትሕትናው ከጀመርን ለሐዋርያቱ እስከ ሰባ ቋንቋ ገልጦ ያራቀቃቸው ጌታ ለሠላሳ ሦስት ዓመታት በምድር ሲመላለስ በአንድ ቋንቋ ብቻ መናገሩ ምንኛ ይደንቃል? ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ለፍጥረት ቋንቋን የሠጠ ፣ በሰናዖር ሜዳ ቋንቋን የበተነ እርሱ የዕብራይስጥን ፊደል ሊማር ከመምህር እግር ሥር ተቀመጠ›› ብሎ ያደነቀውን ጌታ ስለ ትሕትናው እናድንቀው፡፡ እርሱ ሁሉን ቋንቋ የሚያውቅ የሚሰማ ሆኖ ሳለ በአንድ ቋንቋ ብቻ መወሰኑ እንዴት ያለ ትሕትና ነው፡፡ እኛ አጥርተን የማናወራው እንኳንም ቢሆን የምናውቀው ሌላ ቋንቋ ያለ እንደሆን በየዐረፍተ ነገሩ እያስገባን እውቀት በዝቶ እንዳስጨነቀው ስንሆን ሁሉን አዋቂው ጌታ ግን በትሕትና አንድን ቋንቋ ብቻ ተናገረ፡፡
ምስኪኖቹን የገሊላ ሰዎች ሐዋርያትን በብዙ በማያውቁት ቃል እየተናገረ አላስጨነቃቸውም፡፡ ‹የምነግራችሁ ብዙ ነገር አለኝ አሁን ግን ልትሸከሙት አትችሉም ፤ መንፈስ ቅዱስን እልክላችኋለሁ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል› ብሎ አቆይቶ በዛሬው ዕለት ግን ቋንቋን ከእውቀትና ከድፍረት ጋር ሠጣቸው፡፡ ‹‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ያደርጋል ከዚያም የሚበልጥ ያደርጋል›› ብሎ ያስተማረ ጌታ በእርሱ ለሚያምኑ ደቀመዛሙርቱ እርሱ ያላስተማረበትን ብዙ ቋንቋ እንዲናገሩ አደረጋቸው፡፡ (ዮሐ. 14፡12)
ፍጡራን መምህራን ደቀመዛሙርቶቻቸውን ራሳቸውን አስመስለው ያደርሱ ይሆናል እንጂ ከራሳቸው በላይ አላደረጉም፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ብቻ ለተማሪው ‹በእኔ ላይ ያደረ መንፈስ እጥፍ ድርብ ይሁንብህ› ብሎ በፍጡር አቅሙ መጎናጸፊያውን ወደ ሰማይ ሲወሰድ ላየው ኤልሳዕ ሰጥቶት ነበር፡፡ ፈጣሬ ልሳናት ክርስቶስ ግን አንጋጠው ሲያርግ ላዩት ሐዋርያት በእርሱ ሕያው ሆኖ የሚኖር መንፈስ ቅዱስን በላከላቸው ጊዜ እርሱ መናገር ሲቻለው በትሕትና ያልተናገረውን ብዙ ቋንቋ እንዲናገሩ አደረጋቸው፡፡
ይቀጥላል..........