/ተጎንጓኝ ስንኞች/
እስቲ ዛሬያችንን እውነትን መደርደሪያ እንድትሆነን እና የልብ የልባችንን እንድንወያይባት እንፍቀድ፤እንጠያየቅ፤እንመካከር ! ማን በገጻችን ላይ የእለታትን ምስል እያሳረፈ ነው ? ምን በየትኛው ቀን አትርፈናል ? ዛሬን ለማን በስጦታ መልክ ሰጠን ? ከአላማችን የሚያደርስ ከምን ምን አተረፍን ? እነሆ እንደመግቢያ እንዲ ካልን፣መሀሉ አይነገርም ብለን ወደ ሌላኛው ጠርዝ እንዝመት...
1. የጠፉት፣በጎች
ለአንዷ በግ ብሎ ~ ከሰማይ ወረደ
አንዷን በግ ሊታደግ ~ እንደበግ ታረደ
አንዷን በግ አድኖ ~ ወደ አባቱ ሄደ
° ° °
የምፅአት ቀን ደርሶ ~ መለከት ሲነፋ
ዘጠና ዘጠኙ ~ የገቡበት ጠፋ
° ° °
የገቡበት ጠፍቶ ~ ዘጠና ዘጠኙ
ታስሰው ታስሰው ~ ከሲኦል ተገኙ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
2. ይሁዳ
እኚያ ጓደኞችህ ጴጥሮስ ወይ ዮሀንስ
ናትናኤል ፊሊጶስ
ቀራጩ ማቲዎስ
ሌሎቹም በሙሉ
ጌታ ሆይ እኔ እሆን? እኔ እሆን? ሲሉ
አይደለም ሲባሉ
የእነሱ እናቶች በደስታ ሲዘሉ
ምናለች እናትህ አንተን ሲጠቁምህ
ከደሙ ላይ ነክሮ ምልክት ሲያደርግህ
ዐይኗ ምን አነባ ልቧ ምን ታዘበ
ከናንተ አንደኛው ዲያቢሎስ ነው ሲልህ እግር እያጠበ
ከየት ነው ትዕግስቷ
የእናትህ አንጀቷ
የመቻል ፅናቷ
ምናለች ? ይሁዳ ምናለች እናትህ? አንተን ሲጠቁምህ?
ምልክት ሲያደርግህ
እንደ ማሪያም አለቀሰች?
ለኔ ስትል ብላ ወድቃ ተማፀነች?
ወይንስ ለልጇ ያንተ እናት ጨካኝ ነች?
ምናለች እናትህ ታማኝ ነው ስትል ይሁዳ ያለችህ
የሰው ልጅ ይሰቅሉታል
ሰቅለው ይገድሉታል
ቢገድሉት ይነሳል
ግና ላሰቀለው
ግና ላስገደለው
ወዮለት ለዛ ሰው
ብሎ ሲናገርህ
ምናለች እናትህ አንተን ሲጠቁምህ
ከደሙ ላይ ነክሮ ምልክት ሲያደርግህ
እናትህ መለሰች
እንዲህ ተናገረች?
እውነት ነው ጌታ ሆይ ባይወለድ በተሻለው
ግና እንድወልደው እናቱ እንድሰኝ ማሕፀኔን ብትፈታው
በአርኣያ በአምሳልህ ሰው አርገህ ብትሰራው
የወለድኩስ እኔ የፈጠረው ማነው
ብላለት መለሰች
ወይንስ ምን አለች
ምን አለች እናትህ?
አንተን ሲጠቁምህ
ምልክት ሲያረግህ!!
ኤፍሬም ስዩም
አግኙን
@zeki23Etete
@aduyes
@test17
መርጣችሁ ለምርጦቻችሁ ለማጋራት
👇👇👇
@mekereze
@mekereze
@mekereze
ፈጣሪ በምህረት ዐይኑ ምድራችንን ይመልከትልን ።
አሜን !!!
እስቲ ዛሬያችንን እውነትን መደርደሪያ እንድትሆነን እና የልብ የልባችንን እንድንወያይባት እንፍቀድ፤እንጠያየቅ፤እንመካከር ! ማን በገጻችን ላይ የእለታትን ምስል እያሳረፈ ነው ? ምን በየትኛው ቀን አትርፈናል ? ዛሬን ለማን በስጦታ መልክ ሰጠን ? ከአላማችን የሚያደርስ ከምን ምን አተረፍን ? እነሆ እንደመግቢያ እንዲ ካልን፣መሀሉ አይነገርም ብለን ወደ ሌላኛው ጠርዝ እንዝመት...
1. የጠፉት፣በጎች
ለአንዷ በግ ብሎ ~ ከሰማይ ወረደ
አንዷን በግ ሊታደግ ~ እንደበግ ታረደ
አንዷን በግ አድኖ ~ ወደ አባቱ ሄደ
° ° °
የምፅአት ቀን ደርሶ ~ መለከት ሲነፋ
ዘጠና ዘጠኙ ~ የገቡበት ጠፋ
° ° °
የገቡበት ጠፍቶ ~ ዘጠና ዘጠኙ
ታስሰው ታስሰው ~ ከሲኦል ተገኙ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
2. ይሁዳ
እኚያ ጓደኞችህ ጴጥሮስ ወይ ዮሀንስ
ናትናኤል ፊሊጶስ
ቀራጩ ማቲዎስ
ሌሎቹም በሙሉ
ጌታ ሆይ እኔ እሆን? እኔ እሆን? ሲሉ
አይደለም ሲባሉ
የእነሱ እናቶች በደስታ ሲዘሉ
ምናለች እናትህ አንተን ሲጠቁምህ
ከደሙ ላይ ነክሮ ምልክት ሲያደርግህ
ዐይኗ ምን አነባ ልቧ ምን ታዘበ
ከናንተ አንደኛው ዲያቢሎስ ነው ሲልህ እግር እያጠበ
ከየት ነው ትዕግስቷ
የእናትህ አንጀቷ
የመቻል ፅናቷ
ምናለች ? ይሁዳ ምናለች እናትህ? አንተን ሲጠቁምህ?
ምልክት ሲያደርግህ
እንደ ማሪያም አለቀሰች?
ለኔ ስትል ብላ ወድቃ ተማፀነች?
ወይንስ ለልጇ ያንተ እናት ጨካኝ ነች?
ምናለች እናትህ ታማኝ ነው ስትል ይሁዳ ያለችህ
የሰው ልጅ ይሰቅሉታል
ሰቅለው ይገድሉታል
ቢገድሉት ይነሳል
ግና ላሰቀለው
ግና ላስገደለው
ወዮለት ለዛ ሰው
ብሎ ሲናገርህ
ምናለች እናትህ አንተን ሲጠቁምህ
ከደሙ ላይ ነክሮ ምልክት ሲያደርግህ
እናትህ መለሰች
እንዲህ ተናገረች?
እውነት ነው ጌታ ሆይ ባይወለድ በተሻለው
ግና እንድወልደው እናቱ እንድሰኝ ማሕፀኔን ብትፈታው
በአርኣያ በአምሳልህ ሰው አርገህ ብትሰራው
የወለድኩስ እኔ የፈጠረው ማነው
ብላለት መለሰች
ወይንስ ምን አለች
ምን አለች እናትህ?
አንተን ሲጠቁምህ
ምልክት ሲያረግህ!!
ኤፍሬም ስዩም
አግኙን
@zeki23Etete
@aduyes
@test17
መርጣችሁ ለምርጦቻችሁ ለማጋራት
👇👇👇
@mekereze
@mekereze
@mekereze
ፈጣሪ በምህረት ዐይኑ ምድራችንን ይመልከትልን ።
አሜን !!!