👉 እውቀት የሚጀምርበት ነገር :-
* ኸጢቡ አልበግዳዲ እንደህ ይላል:- እውቀት ፈላጊ የሆነ አካል ካፍ ያለውንና ላቅ ያለውን የአላህን ቁርአንን በመሸምደድ ሊጀምር ይገባዋል።ምክንያቱም ቁርአን በመቅደምም ይሁን ሊያስቀድሙት የሚገባው የእውቀቶች ሁሉ የመጀመሪያውና በላጩ ስለሆነ ነው።ከዛም ከቁርአን ቀጥሉ ሊማሩት የሚገባው የነብዩ ﷺ ሀድስና አካሄዳቸው(ሲራ) ነው።ለሰው ልጂ የነብዩንﷺ ሀድስንና አካሄዳቸውን መማር ግድ ይለዋል ምክንያቱም የሸሪዓ መሰረትና ዋናው ስለሆነ።
ከፍ ያለው አላህ እንድህ ይላል:-
وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ( الحشر :7)
መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡
ከፍ ያለው አላህ እንድህ ይላል:-
مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ (النساء :80)
መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡
ከፍ ያለው አላህ እንድህ ይላል:-
وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ (النجم :3)
ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡
https://t.me/menhajuselefhttps://t.me/menhajuselefhttps://t.me/menhajuselef