ethio Nure( ኑሬ ረጋሳ)


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


የተለያዩ ጠቃሚ ቁም ነገሮች ያገኙበታል

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




◆የወልቂጤዉ አንጋፋዉ ተስፋ ቤተ መጽሐፍት◆

ለወልቂጤ ህዝብና በዙሪያዋ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች
ለበርካታ አመታት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

መጽሀፍት ቤቱ ህዳር 1989 አመተ ምህረት በወጣት ደራሲ
እንዳለጌታ ከበደ አማካኝነት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

መፃሕፍት ዝም ብለው ጠንካራ ልባድ እና የውስጥ ገፆች ብቻ ያላቸው አይደሉም።

ውስጣቸው ሰው አለ ፤ ሕዝብ አለ ፤ ታሪክ አለ ፤ የሰው ልጅ ውጣ ውረድ አለ ፤ አለምን የገዙ ፣ በአስተሳሰብ ሊቅነታቸው አርአያነታቸውን የምንከተላቸው ፈላስፎች ፣ተመራማሪዎች ፣ የህይወት መንገድ እያመቻቹልን እነሆ በዚህ ተጓዙ ፣ያኛው ብዙ አሜኬላና እንቅፋት አለው እያሉ የዚህችን ዓለም ምስጢራት ይገላልፁልናል በትንሽ ኪዬስ በምትመስል ሱቅ ለከተማዉ ህዝብና በዙሪያዋ ለሚገኙ ማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት የጀመረዉ ቤተ መጽሀፍቱ ሲጀምር 84 በሚጠጉ መጽሀፍት ስራ በመጀመርና በቀን በአንድ መጽሀፍት 25 ሳንቲም በማከራየት ስራ ጀመረ።

መጽሐፍት ለሰው ልጅ በተሰጠው መንበር ላይ ቁጭ ብለን ሰውየመሆናችንን ፣ ሰው የመባላችንን ልዩ ገፀ-በረከት የሚያጎናፅፉን ሀብቶቻችን ናቸው በወልቂጤ ከተማ ምንም አይነት ቤተ መጽሀፍት ወይም መጽሀፍ
መሸጫ መደብር ባልነበረበት ወቅት ይህ ቤተ መጽሀፍት የብዙዎች ባለዉለታ ነች።

ከዶክተር እስከ ኢንጅነር ?፣ ከደራሲ እስከ ሀያሲ ከተዋናይ እስከ ሰአሊ ያፈራ አንጋፋ ቤተ መጽሀፍት ነዉ።
ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ስለ ቤተ መጽሀፍቱ ጠይቄዉ እንዲህ
ብሎኛል ቤተ መጽሀፍቱ በ1989 አመተ ምህረት 84 የተለያዩ
መጽሀፍት በትንሽዬ ኪዬስ ዉስጥ በማስገባት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ይህ ቤተ መጽሀፍት ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ለመስጠት በተከፈተበት ቀን አንድ መጽሀፍ ብቻ ቀን ሙሉ የተከራየ መሆኑንና ከተከራዩም ጋር ለትዝታ የሚሆናቸዉን ፎቶ ግራፍ እንደተነሱም ነግሮኛል።

በልቂጤ ከተማ ምንም አይነት ላይብረሪና መጽሀፍት መደብር ባልነበረበት ወቅት ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት የጀመረዉ መጽሐፍት ቤቱ በቀን ወይም ለ24 ሰአት አንድ መጽሀፍ 25 ሳንቲም ሲከራይ እንደነበረና መጽሀፍ የመከራየት አቅም የሌላቸዉ ተማሪዎች ይሁን አንባቢዎች በነጻ እንዲያነቡ ይመቻችላቸዉ ነበር።

በዛን ወቅት በጠባቧ ቤተ መጻሐፍት ዉስጥ ሙሁራኖች ተሰባስበዉ በየጊዜዉ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዎች ላይ ዉይይት ይደረግበት እንደነበረና ብዙዎች ቁጭ ብለዉ ያነቡባት ነበር።

ተስፋ ቤተ መጽሐፍት ከራዘስላሴ እስከ የቀድሞዉ ጎሮ ወይም የአሁኑ አበሩስ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪዎችን የማበረታታት እና በደረጃ ለወጡ ተማሪዎች የመጽሐፍ ሸልማት ያበረክት እንደነበረ ይታወቃል።

የብዙዎች ባለዉለታ የሆነዉን ቤተ መጽሐፍት ፣ ለደራሲ መንግስቱ በስር ፣ ለደራሲ ፋሪስ አስፋ ፣ለደራሲ ሀይከል ሙባረክ ፣ለደራሲ ንጋቱ ወልዴ እንዲሁም ለራሱ ለደራሲ እንዳለጌታ ከበደ እና ለበርካታ ደራሲዎች እዚህ ደረጃ የመድረስ መነሻም ነዉ።

በቤተ መጽሐፍቱ ስም በየጊዜዉ ወልቂጤ ከተማ በጎሮ በአሁኑ ያበሩስ ትምህርት ቤት ላይ የስነ ጹሁፍ እና ድራማ ዉድድር በማዘጋጀት በአማተርና ታዋቂ በሆኑ የጥበብ ሰዎች ጥሩ ጥሩ ስራዎች ይቀርቡ እንደነበረም የቤተ መጽሐፍቱ መስራች እንዳለጌታ አስታዉሷል።

በከተማዉ በትምህርታቸዉ ከፍተኛ ዉጤት አምጥተዉ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመግባት ዉጤት ለመጣላቸዉ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላቹሁ ፕሮግራም ይዘጋጅ እንደነበረም አዉስቷል።

ተስፋ ቤተ መጽሐፍት ከቀድሞ ጎሮ ወይም የአሁኑ አበሩስ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እስከ እራዘስላሴ እና ሰላምበር ተማሪዎች ድረስ በዚህ ቤተ መጽሀፍት ለትምህርታቸዉ አጋዦ የሚሆናቸዉ መጽሐፍ ተዉሰዉ የሚያነቡት ተማሪዎች ቁጥራቸዉ
ቀላል የሚባል አልነበረም።

ተማሪዎች የክረምትን ወቅት ተጠቅመዉ የተለያዩ ልበወለድ
መጽሐፍቶች በመከራየት የእረፍት ጊዜያቸዉን በንባብ ያሳልፋሉ።

ብዙዎችም በደረጃ እንዲወጡ ቤተ መጽሐፍቱም የማይተካ ሚና እየተወጣ እንደሆነም ይታወቃል።

ዛሬ ላይ መጽሐፍት ቤቱ በጥሩ ሁኔታ ተደራጅቶ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ መጽሐፍት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

በታዋቂዉ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ የተጀመረዉ አንጋፋዉ ቤተ መጽሐፍት ለተማሪዎች ፣ለመንግስት ሰራተኞች እና ለሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች አሁንም ድረስ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የዚህን ቤተ መጽሐፍት ተገልጋይ የነበሩ አብዛኛዎች ትልልቅ ቦታ በመድረስ እና እራሳቸዉ ችለዉ በትላልቅ የስራ ሀላፊነት ተሰማርተዉ እየሰሩ እንደሆነም ይታወቃል።

መፃሐፍት ውስጥ ዋዛ እና ለዛ አለ። በዋዛና በለዛ ቋንቋ ተቀነባብሮ የሕይወትን አቅጣጫ እንድንፈትሽ ፣ እንድናውቅ ፣ እንድንመራመር ፣ እንድንጠይቅ፣ እንድንመልስ ፣ እንድናብራራ ያደርጉናል።

መፃሕፍት ሲከፋን የሚያፅናኑን፣ ስንሳሳት የሚያርሙን፣ ትዕቢትን፣ ጉራን፣ ጀብደኝነትን ከውስጣችን አስወግደው የመልካምነትን ስብዕና የሚገነቡልን የሊቃውንቶች ስጦታ ናቸው።

ይህ አንጋፋ ቤተ መጽሐፍት የብዙዎች ባለዉለታ ነዉ።
ብዙዎችን በጥሩ ስነ ምግባር እንዲቀረጹ ፣ ብዙዎች የእዉቀት ባለቤት እንዲሆኑ መሰረት የጣለ እንዲሁም ለከተማዉ ህዝብ ለዉጥ ትልቅ አሻራ እያስቀመጠ ይገኛል።

◆ኑሬ ረጋሳ◈




◈የምበላዉ እንኳን የለኝም ልጆችም ያለቅሱብኛል!

ወይዘሮ አለም ተማም

የአልጋ ቁራኛ ከሆኑ 6 አመታቸዉ ነዉ።

ቀደም ሲል ሳይታመሙ በፊት ሰዉ ቤት በመሄድ ልብስ በማጠብ እና ያገኙትን ስራ በመስራት ልጆቻቸዉን ያስተምሩ ነበር።

ሰዉነቴ ሁሉ አባብጧል ፣ አንዱ እግሬ እያጠረ ነዉ።

የሶስት ልጆች እናት የሆኑት አለም ተመም በየሰአቱ ይርበኛል፣ የምበላዉ የለኝም ጎረቤቶቼ የሚያመጡልኝ ምግብ ነዉ የምመገበዉ።

አጣጥ ሆስፒታል ለረጅም ጊዜ ተኝቼ ታክሜ ነበር ከሆስፒታሉ ሪፈር ለጥቁር አንበሳ ተጻፈልኝ አቅም የለኝም ብያቸዉ ወደ ቤቴ ገብቼ ከተኛሁ 6 አመት ሆኖኛል።

ወይዘሮ አለም ተማም በወልቂጤ ከተማ አልፋ መናፈሻ ሆቴል አካባቢ የሚገኙ ሲሆን የስጋ ደዌና የነርቭ በሽታ ታማሚ ናቸዉ።

የአጥንት ቲቢ ፣ የስኳር በሽታም ጭምር ታማሚም
ናቸዉ።

የስኳር መድሀኒት ኢንሱሊን መርፌ እንኳን የምትወጋኝ ትንሻ ልጄ ነች።

በሰዉ ቤት ነዉ የምኖረዉ የቤት ኪራይ እንኳን አንዳንድ ሰዉ ነዉ የሚከፍልልኝ ማንም የሚረዳኝ እንኳን የለኝም እዚህ የተኛሁበት ፍራሽ ላይ አልንቀሳቀስም በአንድ ጎኔ ነዉ የምተኛዉ በአንዱ ጎኔ ከተኛሁበት ረጅም ጊዜ ነዉ፣ ልጆች ናቸዉ ቁጭ የሚያደርጉኝ።

ህክምናም እፈልጋለሁ የምበላዉም አጥቻለሁኝ አሁንም አሁንም ይርበኛል እና የኢትዮጵያ ህዝብ የሚችለዉን ይደግፈኝ በማለት ይማጸናሉ።

ኢትዮጽያዊ አዛኝና ለጋሽ ህዝብ ነዉና ለእዚችህ እናታችን ያለንን እንደግፋት።

ያለዉን ያካፈለ በፈጣሪ ዘንድ ትልቅ ቦታ አለዉና ሁላችንም ተረባርበን እንርዳት እላለሁ።

መርዳት ለምትፈልጉ

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000366098627

ስልክ ቁጥር

0920823594 ሚፍታ


( ኑሬ ረጋሳ)




እጅ ጡረተኛ በሚሆኑበት ዘመን እርሳቸው ልጆቻቸውን ለመርዳትና ቤታቸውን ለመደጎም የሚያደርጉት ጥረትና መውተርተር በእውነቱ አግራሞትን እየፈጠረብኝ ነው ይላሉ።

ዕድሜና እርጅና ሳይበግራቸው የሰው እጅ አላይም ብለው ወልቂጤ ከተማን እያካለሉ መፋቂያ እያዞሩ ይሸጣሉ። ታዲያ እኚህ አባት አርበኛ አይደሉምን ሲሉ አግራሞታቸውን በጥያቄ ያስቀምጣሉ።

‹‹የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲኖር ህይወቱን ለማቆየት ሲል በተለያዩ የሥራ አማራጮች ውስጥ ተሰማርቶ ሲንቀሳቀስ ይስተዋላል። በዚህም የዕለት ገቢውን በማግኘት ህይወት ከመምራቱ ባለፈ ትዳር ይዞ ልጆች ወልዶ አሳድጎ፣ አስተምሮ በእርጅናው ወቅት ለቁም ነገር ያደረሳቸው ልጆች ሲጦሩት እና ሲንከባከቡት ታያለህ። ከእኚህ አዛውንት ጋር ያለው ልምድ ደግሞ የተለየ›› ነው።

የዝግጅት ክፍላችንም መሰል ሰዎች የሥራ ውዳድነትና የሀገር ፍቅር ስሜታቸው የላቀ ስለመሆኑ ይረዳል። በአጋጣሚውም ጎዳና ላይ በልመና የተሰማሩ ሰዎችም ሆኑ ሥራ የሚያማርጡ ወጣቶች ከእኚህ አባት አንዳች ነገር እንደሚማሩ ተስፋ ያደርጋል።


መፋቂያ በመሸጥ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩት የ80 ዓመት አዛውንት

አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ሕይወት በየፈርጁ የራሷ ቀለም፣ የራሷን ጣዕምና የራሷን መዓዛ ይዛ ትጠብቃለች። አሊያም ደግሞ ሕይወትን እንደአመጣጧ ተቀብለን የራሳችን መዓዛ እንጨምርባታለን። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሕይወት በተደላደለ መስመር ላይ ሆና የሰው ልጆችን ፍጥረት ትቀበላለች። ሌሎች ደግሞ መደላድል ፈጥረው ያጣጥሟታል።

የሆነው ሆኖ ሕይወት እኛን ትመስላለች። እኛም ሕይወትን እንመስላለን። የሰጠናትን የምትሰጠን፤ የነፈግናትን የምትነሳን ናት ሕይወት። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሕይወት በአሸናፊዎች እና ተሸናፊዎች መካከል ሆና ልክ እንደ ክብ ቀለበት ሽክርክሪት እየሰራች ከፍም ዝቅም ሳትል፤ ሳትሞላም ሳትጎድልም እንዲያው በድርበቡ እዚያው በዛው አለሁ እንዳለሁ፤ እንዳለሁ አለሁ ትላለች።

ወዳጄ ሕይወትን፤ ማሳመርም፣ ማማረርም በእጅህ ናት። በዛሬው ‹‹እንዲህም ይኖራል›› የተለያዩ የተክል ዓይነቶችን እየፈለጉና ረጅም ሰዓታትን በእግራቸው ተጉዘው የጥርስ መፋቂያ በማበጀት ለዓመታት ሲሸጡ የነበሩትንና በአሁኑ ወቅትም በዚሁ መንገድ ኑሯቸውን እየመሩ የሚገኙትን የ80 ዓመት አዛውንት ሕይወት እናስቃኛችኋለን።

ውልደት

በጉራጌ ዞን በአበሽ ወረዳ በገራባ ቀበሌ አንገዶ መንደር ተወልደው ያደጉ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው ብቸኛ ልጅ ናቸው። በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመን አዲስ አበባ ላይ ሊስትሮ ጠርገው ነው ሦስት ጉልቻ የመሰረቱት። እኚህ አባት በወልቂጤ ከተማ በአራቱም ማዕዘናት እየተንቀሳቀሱ ከተለያዩ እፅዋት አሳምረው የሰሩትን የጥርስ መፋቂያ አዙረው የሚሸጡ አባት ባርህኒ ዘብሬ ይባላሉ።

ወላጅ አባታቸው በጣሊያን ጊዜ ከሞቱ በኋላ ያቆዩላቸው የእርሻ መሬት በሰው ተወስዶባቸው እርሳቸው የበይ ተመልካች እንዲሆኑ ተፈረደባቸው። ታዲያ ብቸኛ በመሆናቸውና አይዞህ የሚል ወንድም ወይም እህት አጠገባቸው ባለመኖሩ የአባታቸውን ርስት ተከራክረው አሊያም ደግሞ ህጋዊ አካሄድን ተከትለው መርታት አልቻሉም። በዚህ ሁኔታ ኑሮን መምራት አልተቻላቸውም።

ሌሎች የሥራ አማራጮችንና የገቢ ማፈላለጊያ መንገዶች ላይ ማማተር ጀመሩ። ወጣት እያሉም አዲስ አበባ በመሄድ ጫማ በማሳመር ሥራ (ሊስትሮ) በመሥራት ህይወታቸውን መምራት ጀመሩ። በሂደትም ትዳር ይዘው መኖር ጀመሩ።

ዳሩ ግን አዲስ አበባ ከትመው መቅረት አልሆነላቸውም። የትውልድ መንደራቸው ናፈቃቸው። ከዚያም ወደ ጉራጌ መመለስ ፈለጉ። ልባቸው ያለውን አደረጉ። ከአዲስ አበባ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው በመመለስ መሬት ገዝተው ቤት ሰርተው ኑሯቸውን ‹‹ሀ›› ብለው መምራት ጀመሩ።

የመፋቂያ ሽያጭ አጀማመር

እኚህ አባት ከእናት አባታቸው ያገኙት ቤት ንብረት የለም። የተደላደለ ኑሮ ላይ ባለመድረሳቸው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ገንዘብ ለማግኘት የሚቻላ ቸውን ሁሉ ይሞክራሉ። የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) አገሪቱን እንደተቆጣጠረ አካባቢ ዋቤ ላይ ለዓመት በዓል የሚሆናቸው እንጨት ቆርጠው ለማጠራቀም በተንቀሳቀሱበት ወቅት በጫካው ውስጥ ለመፋቂያ የሚሆን እንጨት በብዛት መኖሩን አስተዋሉ።

ይህንን አጋጣሚም ወደ ቢዝነስ መቀየር እንዳለባቸው አሰቡ። ከዚያም የጥርስ መፋቂያውን ቆርጠው እና አስተካክለው በወልቂጤ ከተማ እያዞሩ መሸጥ ጀመሩ። ታዲያ ይህ ሥራ በድንገት ይጀመር እንጂ የመፋቂያው ሥራ አሁንም ድረስ ኑሯቸውን እየመሩበት፣ እየደጎሙበት መለያቸው እየሆነ መጣ።

በ80 ዓመት 8 ሰዓት የእግር ጉዞ

መፋቂያውን ለመቁረጥ ዋቤ ድረስ በእግራቸው አራት ሰዓት ለመሄድ እንዲሁም ሲመለሱ አራት ሰአት ያህል ይጓዛሉ። ይህም ብቻ አይደለም እኚህ እርጅና ያልበገራቸው አባት ከሚኖሩበትና ከወልቂጤ ከተማ ወጣ ብላ ከምትገኘው ገራባ ቀበሌ በየቀኑ ወደ ወልቂጤ ከተማ እየተመላለሱ ይሰራሉ። ታዲያ ለድካምና እርጅና እጅ ለመስጠት ከቶውንም አልፈቀዱም።

አዛውንቱ መፋቂያ በመሸጥ ራሳቸውን ብቻ መደጎም ሳይሆን በረከቱ ለልጃቸውም ተርፏል። በወልቂጤ ከተማ ላይ መፋቂያ አዙረው ሸጠው ባገኙት ገንዘብ ለመጀመሪያ ልጃቸው 60 ቆርቆሮ ቤት ሰርተው ሰጥተዋል። በዚህም ለትውልድ ትልቅ አርዓያ ስለመሆናቸው በርካቶች ይመሰክሩላቸዋል።

ለአሁኑ ወጣት ደግሞ ከምንም በላይ የመልካምነት እና የልፋት ዋጋን በሚገባ የተረዱና የሚያስረዱ ትልቅ ተምሳሌት ይሏቸዋል የአገሬው ሰው። ወልቂጤ ከተማ እየተዟዟሩ መፋቂያ በመሸጥ ኑሯቸውን መምራት መደበኛ የህይወት አካላቸው አድርገውታል። ሌላው ቀርቶ የመሬት ግብር የሚከፍሉት እንኳን ይህንን መፋቂያ ሸጠው ነው።

አሁን አሁን በሀገራችን ላይ የመስራት አቅም ያላቸው ውጣቶች ለልመና ውደ ጎዳና ሲወጡና ሲለምኑ ይታያል። እኚህ አባት ግን ለልመና ሳይሆን ለስራ፣ ቁጭ ብለው መጦር ሳይሆን ለፍቶ ማግኘትን መርጠው ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላሉ። ማታ ማታ የኩራዝ ጭስ ተቋቁመው ቀን ቆርጠው ያመጡትን የመፋቂያ እንጨት ያስተካክላሉ። እኚህ የ80 ዓመት አዛውንት ለበርካታ ዓመታት መፋቂያ እየሸጡ ቤተሰብ እያስተዳደሩ ይገኛሉ። ለአሁን ወጣት የሥራ ፈጠራን የይቻላልን መንገድ አስተማሪ ሆነዋል።

እምቢኝ ለጡረታ!

እኚህ አንጋፋና እርጅና ያልበገራቸው አባት ለጡረታ እጅ አልሰጥም በማለት ተንቀሳቅሰው የዕለት ተዕለት ገቢያቸውን ይሰራሉ። አሁንም ድረስ ቤተሰቦቻቸውን ጭምር በዚሁ የሥራ መስክ ላይ አሰማርተው ራሳቸውን እና በዙሪያቸው ያሉትን ቤተሰባቸውን በመርዳት ላይ ይገኛሉ። ቁር፣ ግለት፣ ዝናብና ውርጭ ሳይገድባቸውና ሁሉንም ነገር ተቋቁመው ኑሮን ለማሸነፍ ረጅም መንገድ ተጉዘዋል።

የመፋቂያ እንጨት ካለበት ፈልገው ሰብረው ለወልቂጤ ከተማ እየተሽከረከሩ ይሸጣሉ። እኚህ አንድ መፋቂያ በአንድ ብር እየሸጡ የሚተዳደሩት አባባ ባርህኒ ዘብሬ ሁሌም ልባም፣ ሁሌም እጅ የማይሰጡ፣ ሁሌም የማይረቱ ሆነው ዛሬም ደፋ ቀና ብለው ከሕይወት ጋር ትግል ገጥመዋል። በአጭሩ መፋቂያ አዟሪው በዚህ ዕድሜም መጦርን አልፈልግም ሰርቼ ማግኘት ነው የሚል ህልም አንግበው ከሥራ ጋር ተዋህደዋል።

አሁን ያለው ወጣት

አሁን አሁን በሀገሪቱ ወጣቱ ትውልድ የቤተሰብ እጅ ጠባቂነት የሚታይበት ሲሆን ዝቅ ብለው እራሳቸውን አሳንሰው የመስራቱ ባህል አልተለመደም። ረጅም መንገድ ተጉዘው ያመጡትን እኚህ ጀግና አባትን ጫት ቤት ቁጭ ብለው እየቃሙ ለሚውሉ ለአሁን ትውልዶች፣ ከረንቦላ ቤት ለሚውሉት ውጣቶች ትምህርት የሚሆኑ ናቸው። እኚህ አባት ትምህርት ሳይማሩ በጉልበታቸው ለፍተውና ደክመው ገንዘብ ማግኘትን መርጠው ከሊስትሮ እስከ መፋቂያ አዙሮ መሸጥ ሥራ ላይ በመሰማራት የራሳቸውና የቤተሰቦቻቸውን ህይወት መስመር አስይዘዋል።

አባት ባርህኒ ዘብሬ በወጣትነት ጊዜያቸው አዲስ አበባ ላይ በኃይለስላሴ መንግስት ዘመን ሊስትሮ በመጥረግ ገንዘብ ቆጥበው ለወግ ለማዕረግ በቅተው የሁለት ውንድ ልጆችና የሦስት ሴት ልጆች ወላጅ አባት ሆነዋል። ታዲያ እኝህ አባት ልጆቻቸውን በሂደት የህይወት መስመር እንዲይዙ የራሳቸውን ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡

ሰዎች ምን ይላሉ?

አቶ ኑሬ ረጋሣ የጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን ባለሙያ ሲሆኑ፤ ከእኚህ አዛውንት መፋቂያ ገዝተው ጥርሳቸውን ፋቅ! ፋቅ! አድርገዋል። ከዚያም አለፍ ብለው የእኚህን አዛውንት ልፋትና የማያልቅ ትዕግስት በአንክሮ ተከታትለው በጥንካሬያቸው ተደምመዋል። ሁሉ ነገራቸውን ተመልክተው ወቸ ጉድ! ብለው እጃቸው ከአፋቸው ጭነው ተገርመዋል።

በርካቶችም በእኚህ ሰው ሥራ እየተደመሙ እንደሆነ ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል። በተለይም በዚህ የእርጅና ዘመን በርካቶች በልጅ


የባህላዊ ሸንጎ አርበኛ የዌደማም ዘርፉ የህይወት ታሪክ
የዌደማም ዘርፉ ወልዴ አንሳ በ1941 አመተ ምህረት በጉራጌ ዞን በቸሃ ወረዳ በቀድሞ ስሙ
በዳቁና ቀበሌ በአሁኑ የጣናቃ ቀበሌ ልዩ ስሙ የቢጣረ በሚባለዉ መንደር ከእናታቸዉ ከወይዘሮ ቡላቁት ሸዋንግዛ እና ከአባታቸዉ ወልዴ አንሳ ተወለዱ።እድሜያቸዉን ለትምህርት ሲደርስ በእምድብር ከተማ በሚገኘዉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቀለም ትምህርታቸዉን ጀመሩ።
በእምድርብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ከተከታተሉ በኋላ ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ብዙዎችን ባፈራዉ አንጋፋዉ የእምድብር ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በ1960 አመተ ምህረት ትምህርታቸዉን አጠናቀዋል።

በ1960 አመተ ምህረት ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላም ወደ ኬንያ በመሄድ በሞያሌ ከተማ ለ6 ተከታታይ አመታት የገጠር ት/ት ቤቶች ማስፋፋት ፕሮጀክት ተቀጥረው በኃላፊነት አገልግለዋል።
አባታችን የዌደማም የሚለዉን መጠሪያ የንግስና ስማቸው ሲሆን ወላጅ አባታቸው በ1966 አመተ ምህረት ጥቅምት 30 ሲያርፋ እሳቸውን ተክተው እንዲያገለግሉ በአባታቸው ቦታ የዌደማም የሚለውን የንግስና ስምና ማዕረግ ከእነ ሙሉ ኃላፊነት ተሰጣቸዉ።የዌደማም ዘርፉ ወልዴ ከ1991 ጀምሮ እስከ ህልፈተ ህይወታቸዉ ድረስ የጆካ ባህላዊ ሽምግልና ሰብሳቢ ነበሩ።
ለብዙዎቹ ተምሳሌት የሆኑት አባታችን የዌደማም የባህላዊ ዳኝነት አስተዳደር ቦታ በ1966 አመተ ምህረት በመረከብ የደም አጨራረስ ጉዳይን በማየት ፣ የተጣላን በማስታረቅ ፣ የድንበር ግጭት በመፍታት፣በነብስ ማጥፋት ጉዳይ፣ በቤት ቃጠሎ እና መሰል ችግሮች እንዲቀረፉ ለበርካታ አመታት የባህላዊ ዳኝነት ሰብሳቢ በመሆን አገልግለዋል።
በአካባቢ ሰላም ፣ፀጥታና በልማት ተግባራት ላይ የሰላም መደፍረስ በሚያጋጥምበት ጊዜ ከሌሎች ሽማግሌዎች ጋር በመሆን፣ የተጣሉትን፣ በማስታረቅ በመሸምገል ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸው አበርክቷለ፡፡
በቅንነት እና በለጋሽነት የሚታወቁት አባታችን የድሀ ልጆችን በማስተማር ወላድ እናት እንድትጠገን በማድረግ የምስኪኖችን እንባ በማበስ እንዲሁም በመስቀልና በአረፋ በአልም ምስኪኑን በማልበስ አርደው በማካፈል እና ያላቸዉን በመስጠት የሚታወቁና ብዙዎች የሚመሰክሩላቸው ትልቅ አባት ነበሩ።
ገንዘባቸውን ጊዜያቸውን ጉልበታቸውን ለህዝብ አገልግሎት በመስጠት እና ታሪክ የማይረሳው ስራ በመስራት የምናውቃቸው የሀገር ባለ ውለታ የዌደማም በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች የከተሙት የቤተ ጉራጌ ተወላጆችን በማስተባበር በመንገድ ግንባታ ፣ በጤና ተቋም ግንባታ፣ በንፁህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ግንባታ፣በመብራት ዝርጋታ፣ በትምህርት ቤቶች ግንባታና መሰል የልማት ስራዎች በማስተባበር ለትውልድ እና ለማህበረሰቡ ታሪክ ሰርተው አልፈዋል።
ከወላጅ አባታቸው የባህላዊ አስተዳደር ስርዓት ከተረከቡ በኋላ የተጣላን በማስታረቅ ፣ የተበላሸውን በማስተካከል፣ ፍትህ ያጣዉን ፍትህ እንዲያገኝ በማድረግ ፣ በዳይ እንዲቀጣና ከጥፋቱ እንዲታረም የማድረግ ስራ የሰሩ አንጋፋ አባት ነበሩ።
በጆካ ቂጫ ስርዓት እንዲሁም ጉራጌ ዛሬ ያገኘውን ተስፋና ለውጥ እንዲኖር አሻራቸውን ያሳረፋና ሀገር ስትለማ፣ ሀገር ስትቸገር ፣ ሀገር ቸነፈር ሲደርስባት ግንባር ቀደም በመሆን የማስተባበር ስራ በመስራት ይታወቃሉ።
ከዚህም ባሻገር አባታችን የዌደማም ዘርፉ ወልዴ የዞኑ ህዝብ ልማት፣ ሰላምና ፍትህ እንዲረጋገጥ ካበረከቱት በሻገር የቀድሞ የማህበረሰቡ ጀግኖች እውቅና እንዲያገኙና ሌላ ጀግና እንዲፈጠር በመስራትም ይታወቃሉ ለዚህ ማሳያ በወልቂጤ ከተማ በጉብርየ ክፍለ ከተማ ላይ የሚገነባው የበርካታ ልማት አርበኛ የነበሩ የጀነራል ወልደ ስላሴ በረካ መታሰቢያ ሀውልት ግንባታ የማስተባበርና በኃላፊነት የማሰራት ስራ እስከ ህይወት ፍፃሜያቸው ድረስ ሲያስተባብሩ የነበሩ ናቸው።
የጆካ ባህላዊ ሸንጎ ለበርካታ አመታት እየመሩ የነበሩና ከዚህም ባሻገር በዞኑ 5ቱ የባህላዊ ዳኝነት ስርዓትን ለማጠናከር አንድ የብሄረሰቡ ባህላዊ ሸንጎ እንዲመሰረት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ታላቅ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሲሆንየዚህም ሸንጎ ወይም ምክር ቤት በሊቀመንበርነት እንዲመሩ ተመርጠው ሲመሩ የነበሩት አባታችን የዌደማም ዘርፉ ለሀገር የማይነጥፍ ስራ ሰርተዉ አልፈዋል።
ምዕራብና ምስራቅ ያለው ቤተ -ጉራጌን የበለጠ ለማጠናከርና አንድ ለማድረግ የፈቸት ፕሮግራም በማዘጋጀት በዚህም የፈቸት ፕሮግራሙ ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዉ አገልግለዋል።
እሩቅ አሳቢ እሩቅ አላሚ እና ትልቅ ተስፋ የነበራቸው የቤተ ጉራጌ ዋርካ ጉራጌ ለዘመናት ሲጠይቀው የነበረውን በክልል የመደራጀት ህገ መንግስታዊ መብቱን ፍትሀዊ በሆነ አግባብ መብቱን እና ህግን ባልተፃረረና ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በክልል የመደራጀት ጥያቄ መንገድ ሳይዘጋ የሰው ህይወት ሳይጠፋና ንብረት ሳይወድም በባህላዊ መንገድና በኖረበት ባህል መሰረት በመጠየቅ ግንባር ቀደም ተዋናይ እና ውጤትም ይጠብቁ የነበሩ አንጋፋና የልማት አርበኛ አባት ናቸዉ ።
በዞኑም ሰላም እንዲሰፍን ብሄር ከብሔር ግጭት እንዳይኖር የሀይማኖት ክፍፍል እንዳይፈጠር እንዲሁም ህዝብና መንግስት እንዲቀራረብ በማድረግ የተፈጠሩ ፀብም ይሁን ችግር በድርድር መፍ ታት እንዲቻል የአንበሳውን ድርሻ የወሰዱ ጀግናና ታላቅ አባት ነበሩ። በህይወት ዘመናቸው ለሀገር ትልቅ መሰረት የጣሉ ታላቅ የጉራጌ ምሰሶ የዌደማም ዘርፋ ወልዴ አንሳ ከባህላዊ ሸንጎ በተጨማሪ በርካታ የልማት ስራዎችን በመስራት ይታወቃሉ።
የጉራጌ የባህል ሀብትና ቋት የዌደማም በህይወት ዘመናቸዉ የሰሩትን የልማት ፣ የባህል ፣የጉራግኛ ቋንቋ እንዲለማ እና ቋንቋዉ እንዳይሞት ሲሰሩት የነበረዉን በጎ ስራ አሁን ያለዉ ትዉልድ ማስቀጠል ይኖርበታል።አንጋፋው የጉራጌ ባለ ውለታ የዌደማም ዘርፍ ወልዴ ባለትዳርና የ13 ሴት ልጆች እና የ2 ወንድ ልጆች እንዲሁም 13 የልጅ ልጆችም አላቸዉ።
የዌደማም ዘርፉ ወልዴ አንሳ ለብዙ የሀገር ሽማግሌዎች አርአያ የሚባል ስራዎች ሰርተዉ ያለፋ የጉራጌ ህዝብ ዋርካ በተወለዱ በ72 አመታቸው ድንገት ታህሳስ 21/04/2013 አመተ ምህረት ሳይታሰብ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
የቀብር ስነ ስርዓታቸው ቅዳሜ በቀን 24/4 /2013 አመተ ምህረት ከቀኑ በ 7 : 00 ሰዓት መላው ቤተሰባቸው፣ ወዳጆቻቸው፣ አድናቂዎቻቸው፣ የመንግስት ተወካዮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት በጆካ ቅዱስ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል።

ለመላዉ ኢትዮጵያውያን፣ ለመላው የዞኑ ህዝብ ፣ለቤተሰቦቻቸዉ፣ለዘመድ አዝማዶቻቸዉ፣እንዲሁም ለአድናቂዎቻቸዉ መጽናናትን እንመኛለን።

◈◆ ነብሳቸዉን በአጸደ ገነት ያኑርልን!!!◈

ታህሳስ 24/04/2013 ዓ.ም
ጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ የጆከ ቀበሌ




◆ይህ ታዳጊ ዛሬ ጉንችሬ ሆስፒታል ተኞቶ ድረሱልኝ ይላል!!

ታዳጊ አቤል ምትኩ አድኑኝ እያለ በፈጣሪ ስም ይማጸናል።

የይድረሱልኝ ጥሪዉን ያሰማል የ16 አመት ታዳጊዉ።

በእግሬ መቆም እንደናፈቀኝ ቀረዉና የኢትዮጵያ ህዝብ ይድረስልኝ ጉንችሬ ሆስፒታል ተኝቻለሁ።

ለምትረዱኝ (በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000355293867)

በጉራጌ ዞን እነሞርና ኤነር ወረዳ ካናስ ቀበሌ የተወለደዉ ታዳጊዉ ከወገቡ በታች ያለዉን ሰዉነት ማንቀሳቀስ አልቻለም።

በጉብሬ ሪፈራል ሆስፒታል 5 ወር ተኝቶ ታክሞ ምንም አይነት ለወጥ ሳያመጣ ሲቀር መልሶ አሁን ያለበት ወደ ጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመምጣት ከ5 ወር በላይ ያህል ጊዜ ተኝቶ ህክምናዉን እየተከታተለ ይገኛል።

ዛሬ መቆምን የናፈቀዉ አቤል የ16 አመቱ ታዳጊ አቤል ምትኩ የ5ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን የአልጋ ቁራኛ ከሆነ አመት አልፎታል።

ታዳጊ አቤል ምትኩ በእግሬ መሄድ ናፈቀኝ ይላል እንባ እየተናነቀዉ።

አባቴ ያለዉን ገንዘብና ንብረት እኔን ለማሳከም ሲል ጨርሷል ፣ አሁን ምንም ገንዘብ በእጃችን የለም ፣ የሚረዳን እንፈልጋለን።

እኔም ሀገር ዉስጥ ያሉት ትልልቅ ሆስፒታሎች ሄጄ እንድታከምና እንድድን የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ እሻለሁ ይላል።

ማንም ማስቸግረዉ ዘመድ አዝማድ እንኳን የለኝምና የኢትዮጵያ ህዝብ ድረሱልኝ በማለት ይማጸናል።

በጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቁስሉ በየጊዜዉ እየታጠበለት የሚገኘዉ ይህ ሮጦ ያልጨረሰ ፣ ወልዶ ያልሳመዉ ታዳጊ ሁላችንም አለንልህ ልንለዉ ይገባል።

አስታማሚዉ ወላጅ አባቱ ምትኩ ታደም እንደሚሉት ታፋዉና መቀመጫዉ አካባቢ ሰፊ ቁስል ነዉ ያለበት ብለዉ በሆስፒታሉ ቁስሉ እየታጠቡት ነዉ ያለዉ።

ሌላ ቦታ ወስጄ የማሳክምበት የገንዘብ አቅም አጥቻለሁ ፣ ያለኝን ሁሉ ገንዘብና ንብረት አሲዤ ጨርሻለሁ ይላሉ።

በሆስፒታሉ የሚገኙ ዶክተሮች እና ወረዳዉ እየረዳኝ ነዉ አሁን ያለሁት ብለዋል።

ልጄ በሀገር ዉስጥ አሉ በሚባሉ ሆስፒታሎች ታክሞ ይድንል ዘንድ ድጋፍ እንድታደርጉልኝ ስል በፈጣሪ ስም
እማጸናለሁ ብለዋል።

አቤልን መርዳት ለምትፈልጉ ሁሉ

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000355293867 አቶ ምትኩ ታደም

ወይም

በንብ ባንክ 201 SAV 31 96 ምትኩ ታደም

ድጋፍ ማድረግ ትችላላቹሁ።

ስልክ

09 42 56 23 35

የወላጅ አባት ምትኩ ታደም ኬራጎ

ሰዉ ስትሆን የሰዎችን ችግር ትረዳለህና ለዚህ ታዳጊ እንድረስለት እላለሁ።

◈◆ኑሬ ረጋሳ◈◆




እጄን ለልመና አልዘረጋም
(ማየት የተሳናቸው አርሶአደር ደሊል ሻፊ)

ማየት የተሳናቸው አርሶአደር ደሊል ሻፊ በጉመር ወረዳ ቡርዳና ደንበር ቀበሌ የሚገኙ ሞዴል አርሶአደር ናቸው፡፡

አካል ጉዳተኞች የይቻላልን አመለካከት በመላበስ ከቅርብ አመታት ወዲህ በተለያዩ የስራ አማራጮች በመሰማራት ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እየቀረፉ ነው፡፡

ታዲያ ይህ ሞዴል አርሶአደር ደሊል አካል ጉዳተኝነትን ሳይበግራቸው በመስኖ ልማት ስራ በመሰማራት ለበርካታ አርሶአደሮች አርያነት ያለው ተግባር እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ሁለቱም አይኖቼ አይታዩኝም ብዬ እቤት ውስጥ አልቀመጥም-- ማንኛውም ሰው አንድ እጁ ከተያዘ ወይም አንድ አይኑ ከተያዘ አካል ጉዳተኛ ነኝ ብሎ እራሱን ማዋረድ የለበትም ስራ ፈጣሪ በመሆን እራሱን መቻል ይኖርበታል ይላሉ፡፡

ሰው ወደ ስራ ይሄዳል እንጂ ስራ ወደ ሰው አይመጣም ያሉት
አርሶአደሩ እራስህን ለማሸነፍ ወደ ስራ አሳምነህ ከገባህ ውጤታማ መሆን ትችላለህ በማለት ለረጅም አመታት በግብርና ስራ ተሰማርተው እየሰሩ እንደሆነም ገልጸውልናል፡፡

ትልቁ ነገር ረሀብ ከሀገር የሚጠፋው በበጋ ወራት በመስኖ ልማት ስራ በስፋት ሲሰራበት ነው ብለው በራሳቸው ጉልበት በርካታ የውሀ ጉድጓዶች በመቆፈር ባቄላ ፣ ድንች፣ካሮት፣ጎመንና የመሳሰሉት በማምረት በወረዳው አሉ ከሚባሉ ሞዴል አርሶአደር በግንባር ቀደም ይታወቃሉ፡፤
ማየት የተሳናቸው አርሶአደር ደሊል ሻፊ የ6 ልጆች አባት ሲሆኑ አስተምረው በግብርና ስራቸው በሚያገኙት ገንዘብ በመደገፍ ወደ ንግድ ስራ ገብተው የራሳቸውን የገቢ አቅም በማሳደግ ህይወታቸው እየመሩ እንደሆነም ጠቅሰው አካል ጉዳተኛ በመሆኔ አንድም ቀን ልጆቼን ለምኜ አብልቼ አላውቅም ብለዋል፡፡

እኔን አይታቹ ስሩ በማለት የሚመክሩት አርሶአደሩ የሚሰሩት ሞዴል ስራዎች የወረዳው መንግስት በመስኖ ስራ ውጤታማ መሆናቸው በመመልከት ተጨማሪ የእርሻ መሬት እንደሰጣቸውም ጠቅሰዋል፡፤ ስለ አባይ ግድብ ሲወራ አባይ ግድብ ብዬ የቆፈርኩት የውሀ ጉድጓድ ስም ሰየምኩለት፣ የቤተሰብ የውሃ ጉድጓድ ፣ ልሞክረው የሚል ስያሜ ለቆፍርኳቸው ጉድጓዶች ስያሚ ሰጥቼ እየተጠቀምኩባቸው
ነው ብለው አንድ ትልቅ ጉድጓድ በጄኔረተር የሚሰራ ውሃም አለኝይላሉ፡፡

በተሰማሩበት የግብርና ስራ ውጤታማ ስራ በመስራታቸው
በፌደራል፣በክልል፣በዞንና በወረዳ ደረጃ በተለያዩ ጊዜያት ሽልማት እንደተበረከተላቸውም ነግረውን አሁን ለደረሱበት ደረጃ ታላቁ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ ለህዝቡ ዶማና አካፋ ገዝተን እንሰጠዋል ብለው በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ስሰማና እንዲሁም የወረዳው የግብርና ባለሙያ የነበረችው ወይዘሮ ፈለቀች ሀብቴ በወቅቱ እየሰራሁት ያለውን እንቅስቃሴ በመመልከት የ7 ብር ካሮትና ቀይስር ገዝታ
ሰጥታኝ ብርታትን ተላብሼእንደሰራ አስችላኛለች፡፡

አካል ጉዳተኛ ተሁኖ ስራ መስራት አይከብድም እራስህን ካሳመንከው ትልቁ የሚከብደው ነገር ሰው ፊት መቆም ነው ያሉት ማየትጨየተሳናቸው አርሶአደር ደሊል በአሁኑ ወቅት በርካታ ከብቶች ፣ባዝራዎች እንዳላቸው ጠቅሰው ደረጃውን የጠበቀ 130 ቆርቆሮ ቤት መስራት ችለዋል፡፡

ልመናን አእምሮን መጉዳትና ሀገርን መበደል ነው ለእኔ ወረዳው መሬት እኮ የሰጠኝ ሁለት መቶ ኪሎ ግራም የሚመዝን ጉቶ እየነቀልኩ ነው መንግስት አካፋና ዶማ ገዝቶ ሰጥቶኛል ብለው አንድም ቀን ለልመና ልጆቼን ይዤ ወጥቼ አላውቅም መንገድ ላይ ለልጆቼ ገንዘብ ሲሰጥዋቸው እንዳትቀበሉ እያልኩ እከለክል ነበር ሲቀበሉ የደበደብኳቸው ቀን አለ፡፡

መንፈሰ ጠንካራው አካልጉዳተኛው ሞዴል አርሶአደር በሚለብሰው ልብስ ጀርባው ላይ ‹‹ድህነት በልመና ሳይሆን በስራ ማሸነፍ ይቻላል›› በማለት መፈክር አነግቦ እየጠንቀሳቀሰ ነው፡፡

በመጨረሻም አካል ጉዳተኛ ሆነው ቤት ውስጥ የተቀመጡ
የህብረተሰብ ክፍሎች የይቻላልን መንፈስን በመላበስና ከልመና በመውጣት በየተኛውም መስክ ተሰማርተው በመስራት እራሳቸውን ችለው መኖር ይኖርባቸዋል በማለት መእልክት አስተላልፈዋል፡፡

መረጃዉ በድጋሚ የቀረበ ነዉ።

ኑሬ ረጋሳ




በኮባ ቅጠል እና በአጋም እሾህ ነዉ ፊደል የቆጠርኩት...

(ብርጋዴን ጄኔራል ተስፋዬ ሀ/ ማርያም )

የእኚህ ታላቅ ሰዉ የህይወት ተሞክሮ ከብዙ በጥቂቱ
ላስቃኛቹሁ ወደድኩ መልካም ንባብ፡፡

ብርጋዴን ጄኔራል ተስፋዮ ሀ/ማሪያም ተወልደዉ ያደጉት በጉራጌ ዞን በቸሀ ወረዳ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ ሲሰ መንደር ዉስጥ ነዉ፡፡

የጦር ሜዳ ዉሎ የተሰኘዉን መጽሀፍ አሳትመዉ ለንባብ ያበቁናለሀገሪቱ ትልቅ አሻራ ያኖሩ ጀግና ናቸዉ፡፡

ከአርሶአደር ቤተሰብ ነዉ የተወለድኩት ትምህርትም የጀመርኩት በወረቀትና በእርሳስ ሳይሆን የኮባ ቅጠል ቆርጬ በእሳት ለብ አድርጌ እንደ ወረቀት በመጠቀም የአጋም እሾህ ጫፍን በእሳት አቃጥዬ እንደ እርሳስ በመጠቀም ነዉ ሀሁ ፊደል የቆጠርኩት፡፡

ከዚህ ተነስቼ ነዉ ደረጃ በደረጃ በእምድብር ከተማ ዛሬ የለም ከቤተክርስቲያኑ በስተ ሰሜን አቅጣጫ አንድ ህንጻ ነበር በጣሊያን ጊዜ የተሰራ ሲሆን በዚህ ህንጻ ስር ነበር መጀመሪያ የተማርነዉ አንደኛ፣ ሁለተኛ ሶስተኛ ክፍል የሚባል ክፍል አልነበረም በአስተማሪዎች ብቻ ነበር የሚለየዉ እና እንደዚህ ሆነን ነዉ ፊደልን የቆጠርነዉ፡፡

ብርጋዴን ጄኔራል ተስፋዬ ሀ/ማሪያም በ19 46 አመተ ምህረት በእምድብር ከተማ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ6ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የተማሩ ሲሆን በ1948 አመተ ምህረት የ8ኛ ክፍል ፈተና መፈተናቸዉ ነግረዉኛል፡፡

ከሰኞ እስከ አርብ በእምድብር ከተማ ትምህርት እየተከታተሉ ቅዳሜና እሁድን ቤተሰብ ጋ በማሳለፍ ሰኞ ከለሊቱ 11 ሰአት ተነስተዉ ለሳምንት ቀለብ የሚሆናቸዉ ተሸክመዉ 20 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ትምህርታቸዉን ተከታትለዋል፡፡

ተፈትነዉ እንደጨረሱም በዛን ጊዜ በኢትዮጵያ 5 አዳሪ ትምህርት ቤቶች ማለትም ተፈሪ መኮንን ፣ዊንጌት ፣ምንሊክ ፣ቀዳማዊ ሀ/ስላሴ እና የአንቦ እርሻ ልማት ትምህርት ቤቶች ነበሩ ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማሪያምም አንቦ እርሻ ትምህርት ቤት ገብተዉ ተከታትለዋል፡፡

በእኔ ዘመን የጨለማ ዘመን ነዉ ማለት እችላለዉ ስለትምህርት የምናዉቀዉ ነገር የለም እኔ ተምሬ ምን እንደምሆንና ለምን እንደምማር አላዉቅም በዛን ጊዜ ብቻ በእኛ በተማሪዎች መካከል መንፈሳዊ ቅናት ነበር የአካባቢ ልጅ አንድ ነገር ሲሰራ እኔስ ለምን አልሰራም በሚል መንፈሳዊ ቅናት መሰረት በማድረግ ነዉ የምንማረዉ፡፡

ተምረህ ዶክተር ፣መሀንዲስ ፣ጠበቃ ፣ኢኮኖሚስት ትሆናለህ ብሎ የሚያስረዳህ ሰዉ የለም እንደዉም በዛን ወቅት ስሙም አይታወቅም እኛም ሰምተንም አናዉቅም እንድንማር ብቻ ያደረጉን የቤተሰብ ግፊትና መንፈሳዊ ቅናት ነዉ፡፡

እኔ የሙያና የዜግነት ግዴታዬን በሚገባ ተወጥቻለሁ ብዬ ነዉ የምናገረዉ ይህንን ሳላደረግ ቀረሁኝ የምለዉም ነገር የለም አቅሜ በፈቀደ መልኩ የሙያና የዜግነት ግዴታዬን ተወጥቻለሁ ነዉ የምለዉ፡፡

በሙያዬ ብዙ ቦታዎች ስልጠና ወስጃለሁ የአየር ወለድ ስልጠና ትምህርት እዚሁ ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉ የተማርኩት ፣ እስራኤል ሀገር የኮማንዶ ትምህርት ፣ አሜሪካ ሀገር ስፔሻል ፎርስ ፣ሶሻል ላይ ሞስኮ ሄጄ ተምሪያለሁ እንዲሁም ህንድም ሀገር ሄጄ ሙያዬን በስልጠና ያዳበርኩት፡፡

የስራ ሀላፊነቴ ትንሽ ጠንከር የሚል ሲሆን የኮማንዶ አባል መሆን የህይወት መሰዋትነት በግልም በቡድንም ነዉ ግዳጅ የምትወጣዉ ይህ ደግሞ የህይወት ዋጋ ያስከፍላል ።

ለምሳሌ በኢትዮጵያና በሱማሊያ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት እንዲሁም ከሱዳንም ጋር በነበረዉ ግጭት በዲፕሎማሲ ለመፍታት ብዙ ተሞከረ 1969 አመተ ምህረት ላይ ነገር ግን ችግሩን ለመፍታት ብዙ ጥረት ተደርጎ መፍታት አልተቻለም፡፡

መፍትሄ ሊሆን የሚችለዉ ቲት ፎር ታት መሆን አለበት የሚል አቋም ይዘን ወደ መፍትሄዉ ገባን እነሱ ደግሞ ከጅግጅጋ ለጋፍር እስከ ጎዴ ድረስ እንደዉም አልፈዉ መጥተዉ እስከ ሜኢሶ ድረስ ያለዉ በፈንጅ አጥረዉት ነበር፡፡

ይህ መሰናከል ለሰራዊቱ እና ለህዝቡ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ለማቅረብ በጣም ችግር ተፈጠረ አማራጩ አንድ ነገር ብቻ ነዉ ይህዉም የእነሱ ግዛት ክልል ዉስጥ ዘልቆ በመግባት እና ፈንጅ የመቅበር ስራ ግዳጁ ለእኔ ተሰጠኝ እኔ የምመራዉ ቡድን ድንበር አቋርጠን ሶስት ቀን ሌሊትም በመጓዝ ገብተን ከስር ወደዚህ ፈንጅ እየቀበርን መጣን በቀበርነዉ ፈንጅ ብዙ ሰዎች ተጎዱ ብዙ ንብረትም ወደመ ያኔ ወደሰላም መጡ ይህ ትልቅ ዉጤት ነዉ፡፡

ሌላዉ ትልቁ ችግር የነበረዉ ከኤርትራ ጋር በነበረዉ ግጭት ሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የፖለቲካዊ ድጋፍ ታደርግ ነበር ይህንንም በዲፕሎማሲ መንገድ ድርድር ተጀመረ ብዙ ተሞክሯል ግን አልተቻለም ነገር ግን ደቡብ ሱዳን መገንጠል እንደምትፈልግ በማወቅ እና እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ፍንጭ በመረዳት ከዛ ስደተኛ ሆነዉ የመጡትን የመጀመሪያዉ መሪ ዶ/ር ጆን ጋራን የሚባል ነበር ዛሬ ላይ ያለዉን የደቡብ ሱዳን መንግስት በሁለት እግሩ እንዲቆም የደረኩት እኔ ነኝ ማለት እችላለዉ፡፡

የኢትዩጵያ አየር መንገድ በጠለፋ በጣም ከፍተኛ ችግር ገጥሞ ስለነበረ አንዳንድ ቦታዎች ላይ በረራ ያቆሙበት ሂደት ነበር ለሰራተኘ እንኳን ደሞዝ መክፈል ያልተቻለበት ሁኔታ ነበር እና የበረራ ደህንነት እንዲቋቋም መንግስት ሲወስን የዛን ደህንነት አባላትና አሰልጣኞች አብሮ እንዲጓዙ ያቋቋምኩት እኔ ነኝ፡፡

ለራስ ህይወት መሰረቱ ስነ- ስርአት ነዉ የሚሉት ብርጋዴን ጄኔራል ተስፋዬ ሀ/ማሪያም በኢትዮጵያ ምድር ዉስጥ ጥይት በሚፈነዳበት ቦታ ሁሉ እኔ ያልተሳተፍኩበት በጣም ጥቂት ሲሆን አብዛኛዉ በተሳተፍኩባቸዉ ቦታዎች በድል ወይም በስኬት ነዉ የተጠናቀቁት፡፡

በግልም በቡድንም የምሰራዉ ነገር አለ የመራሁትም ሰራዊት ዉጤታማ ነዉ ብለዉ የአየር ወለድ ጦር አዛዥ ነበርኩ የአየር ወለድ ጦር ግዳጅ በጣም ከባድ ነዉ እና ናቅፋ ላይ የተደረገዉ ዝላይ በአለም ላይ ተደርጎ ያልታወቀ እስካሁን ድረስ ያልተደረገና ወደ ፊት ሊደረግ ይችል ይሆናል ፡፡

አንድ ጦር 6 ወር በጠላት ተከቦ ሰርቫይቭ ያደረገ በአለምም የለም የኛ ሰራዊት ግን 6 ወር ድረስ ሲታገል ቆይቶ ሰብሮ በህይወት የወጣ ታሪካዊ የአየር ወለድ ሰራዊት ነዉ፡፡እንደዚህ አይነት ነገሮች ናቸዉ ልዩ የሚያደርገኝ፡፡

ማንም ሰዉ ብቁ አሰልጣኝ ካገኝ አየር ወለድ መሆን ይችላል እኔ መጀመሪያ ላይ የአየር ወለድ ስልጠና እስራኤሎች ናቸዉ ያሰለጠኑኝ በዛን ጊዜ ደግሞ በአየር ወለድ ጥሩ ስልጠና በመስጠት ይታወቃሉ የእኛ ሰራዊትም የሰለጠነዉ ከእስራኤሎች ነዉ፡፡
እኔ ተመርቄ የወጣሁት ማሰልጠኛ ማዕከል ሀረር ጦር ሚሊተሪ ተቋም ነዉ፡፡

በአለም ላይ አራት ታዋቂ ማሰልጠኛ ተቋም አሉ እነዚህም የእንግሊዙ ሳንድረስት ፣የአሜሪካዉ ዌስት ፖስት ፣የፈረንሳይ ሳንሰን እና የህንዱ ናሽናል አካዳሚ አሉ ሀረር ማሰልጠኛ ተቋምም በወቅቱ ከነዚህ የሚወዳደር ነበር በዚህ ተቋም 3 አመት ህንዶች ናቸዉ ያሰለጠኑን ፡፡

(ወድ አንባብያን የኚእህ ታላቅ ሰዉ የህይወት ተሞክሮን ከብዙ በጥቂቱ ነዉ የጻፍኩት....መልካም ንባብ )

◈ ።።።።◆◈ኑሬ ረጋሳ◆◈።።።። ◆




◆ኢንስትራክተር ባሀሩ ተካ ነገ ይሞሸራል◈

መልካም ጋብቻ ለኢንስትራክተር ባሀሩና ለወ/ሪት ሰሚሀ ሺፋ

በኢትዮጵያ ፕሪሜሪሊግ በዋና ዳኝነት ለ5 አመት አገልግሏል።

ተወልዶ ያደገዉ ወልቂጤ ከተማ ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ እግር ኳስ በመጫወት በፕሮጀክት ታቅፎ በመጫወት አሳልፏል።

ለወልቂጤ ከተማ ፣ለዞን ለክልል፣ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተማሪ እያለ የዩኒቨርሲቲ ዉድድሮች ጅማ ዩኒቨርሲቲ በመወከል ተጫዉቷል።

እግር ኳስ ለእኔ ህይወቴ ነዉ የሚለዉ ኢንስትራክተር ባሀሩ በ19 99 አመተ ምህረት የሁለተኛ ደረጃ የዳኝነት ኮርስ በመዉሰድ በወልቂጤ ከተማ የዉስጥ ለዉስጥ ዉድድሮች በመዳኛት ስራ ጀምሯል።

አማተር ባለሙያ እያለሁኝ የወረዳና የዞን ዉድድሮችን እና በኦሮሚያ ክልልየኦሮሚያ ሊግ ዉድድሮች ለ3 አመት የዳኝነት ሙያዉ በመስራት ጠሩ ጊዜያቶች አሳልፊያለሁ።

ከልጅነቴ ጀምሬ ለእግር ኳስ ልዩ ፍቅር ነበረኝ ያለዉ ወጣቱ ኢንስትራክተር የመጀመሪያዉ የዳኝነት ኮርስ በወልቂጤ ከተማ ላይ እንደወሰደና የፌዴራል የዳኝነት ኮርስ ለመዉሰድ በጣም ከፍተኛ መሰዋትነት ከፍያለሁኝ ብሏል።

የፌዴራል የዳኝነት ኮርስ ለማግኘት ከፍተኛ ጉጉት ስለነበረኝ ሁለት አመት ኦሮሚያ ላይ በቂ ክፍያ ሳይከፈለኝ በእረፍት ጊዜዬ የዳኘነት ስራ በመስራት ለ15 ቀናት በግል ወጪ በማዉጣት የፌዴራል የዳኝነት ኮርስ አግኝቷል።

አሁን ላለሁበት በኢትዮጵያ ፕሪሜሪሊግ የዳኝነት ሙያ አቅም የሆኑኝ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ ጥሩ አቅም ያላቸዉ ኢንስትራክተሮች እና የሙያ አጋሮቹ በተለያዩ አጋጣሚዎች ጥያቄዎች በመጠየቅ እና ዳኝቼ በምወጣበት ጨዋታ አስተያየት በመቀበል ትልቅ ትምህርት ተምሬባቸዋለሁኝ ይላል።

በ2008 አመተ ምህረት ወደ ፕሪሜሪሊግ የዳኝነት ሙያ ያደዉ ኢንስትራክተሩ በኢትዮጵያ ፕሪሜሪሊግ በዋና ዳኝነት ለ5 አመት አገልግሏል።

ለእኔ ሞዴል ተጫዎች ከዉጭ ሪዮ ፈርዲናንድ ፣ ከሀገር ዉስጥ በቅርቡ በሞት ያጣነዉ የወልቂጤ ከነማዉ መዝገቡ ወልዴ ነበር ይላል።

ከዚህ በፊት የስፖርታዊ ጨዋነት ችግሮች በሄድኩበት ቦታ ሁሉ ያሳፍረኝ ነበር ፣ አሁን ላይ የተሻለ ነገር አለ ማለት እደፍራለሁ ይላል።

ካለፍት ጊዜያት ይልቅ በእግር ኳሱ ላይ የተሻለ ነገር ይታየኛል ነገር ግን ፕሪሜሪ ሊጉ የራሱ የሆነ አርማ የለዉም ቢኖረዉ እና የፕሪሜሪሊግ ጨዋታዎች በተለያዩ ቻናሎች የቀጥታ ስርጭት ቢኖራቸዉ የተሻለ ዉጤት ኢትዮጵያ ዉስጥ ይመጣል።

የሁሉም ክለቦች ደጋፊዎች ፣ማህበራት ፌዴሬሽኑ፣የክለቦች አመራሮች ፣የሚዲያ ባለሙያተኞች እና ሰፊዉ የእግር ኳስ ወዳድና ተመልካቾች አንዲሁም ደጋፊዎች እያደረጉት ያለዉየን ፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት እጅግ ጥሩ ነዉ ብሏል።

የወልቂጤ ከነማ ደጋፊዎች መስፈርቱ ፍቅር ነዉ በሚል መሪ ቃል ኳሱ በፍቅር ተጀምሮ በፍቅር እንዲጠናቀቅ እየሰሩት ባለዉ ስራ በሄድኩበት ቦታ ሁሉ እኮራለሁኝ ከልብ አመስግኗል።

የወልቂጤ ከነማ እግር ኳስ ክለብ እንደ አዳጊ ክለብ ያለበት አቋም ጥሩ ነዉ መሻሻል ያለባቸዉ ችግሮች ማለትም ተቃራኒ ክለቦች ላይ ግብ የማስቆጠር ችግራቸዉን የሚቀርፍ ተጫዎቾች ከወዲሁ ካላስፈረመ አስጊ ነዉ እንደሆነ የተናገሩት ኢንስትራክተር ባሀሩ በቀላሉ ከስጋት መዉጣት የሚችልበት አቅም አይቼበታለሁኝ ይላል።

ወጣቱ የፌዴራል ዋና ዳኛ ኢንስትራክተር ባህሩ የያስከዉን የዳኝነት ሙያ የበለጠ ዉጤታማ ስራ በመስራትና ባለህ የዳኝነት ሙያ ሌላዉ የማብቃት ስራ መስራት እና የተለያዩ ቀሪዉ እድሜህ የተሳካና ስኬታ ጊዜ ይሁንልህ ።

ለኢንስትራክተር ባሀሩ ተካ እና ለወይዘሪት ሰሚሀ ሺፋ መልካም ጋብቻ ይሆንላቹሁ።

ነገ ያገባልና መልካም ጋብቻ ተመኘኙልህ።

Показано 16 последних публикаций.

240

подписчиков
Статистика канала