ከደቂቃዎች በፊት የገጠመኝ ..
ሆዴን አሞኝ መድሃኒት ልገዛ ፋርማሲ ሄጄ..
ፋርማሲስቱ -"የጀርመኑ 800 ብር ነዉ የህንዱ 120 ብር ነዉ...የቱን ላድርግልሽ?"
Me -"ይሄን ያህል ልዩነት ካላቸዉ አንዱ ያድናል አንዱ አያድንም ማለት ነዉ እኮ ?"
ፋርማሲስቱ -"ሁለቱም ያድናሉ እህቴ !"
Me -"የወርቅ ሰዓት እና የወርቅ-ቅብ ሰዓት እንደመገዛት እኮ ነዉ!"
ፋርማሲስቱ- "ልዩነቱ ምን መሰለሽ..." ብሎ ጀመረ "የጀርመኑ ልክ ስትውጪዉ ባክቴሪያዉ ጋር ሄዶ ምንም ሳያናገረዉ ..ፊትለፊት ደረቱን እንደነፋ ሄዶ በአንድ ቦክስ አፍር-ድሜ ያበላዉ እና ቀጥቅጦ ይገድለዋል ...አንችም በአንድ ቀን ይሻልሻል ማለት ነዉ! .... የህንዱ ግን፣ አቅምም ኮንፊደንስም ሰለሌለዉ..ገና ባክቴሪያዉን በሩቅ ሲያየዉ.."ሰላም ነዉ ባቡጂ" ..ይለዋል.... "don kill me i came in peace! ..me you friends" ይለዋል.....እና የshahrukh khanን kuch kuch hota hai......ዘፈን ለአንድ ሳምንት ከዘፈነለት በኋላ ባክቴሪያዉ ወዳጄ
ነዉ ብሎ ሲያምን ቀስ እያለ እየቀጠቀጠ ይገድለዋል... የዛኔ አንቺ ከታመምሽ 14 ቀን ሆኖሻል ማለት ነዉ!" አለ
capitalism ሃብታምም ደሃም ስላላደረገኝ (poor for german rich for India ነኝ )...መድሃኒቱን ትቼ...ፌጦ ፣ ሎሚ እና ማር ገዝቼ ወደቤት ለመሄድ ወሰንኩ...ደግሞ ለድሃ ሆድ!🥹
@poethaymi