Sayat love 😊💖😍😘


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


>>>>>>የሳያት ፎቶዎች
>>>>>>ስለ ሳያት
>>>>>>አስተማሪ &አዝናኝ ታሪኮች
>>>>>>ቀልዶች ⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇
sayat love 😊💖😍😘
ሀሳብ እና አስተያዬቶች @sayatloveu

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Soul of inspiration


Репост из: Soul of inspiration


Репост из: Soul of inspiration


#ላንዲት_የገጠር_ሴት

ስትፈጭ የኖረች ሴት
መጁ በመጠኗ ፣ ወፍጮውም በልኳ
ጓያ ትፈጫለች
ጓያ ሽሮ ሲኾን ያበቃል ታሪኳ።

አስባው አታውቅም
ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደ መጣች
ከ'ለታት አንድ ቀን ከ ናቷ ሆድ ወጣች
ከ'ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች
ከ'ለታት ሌላ ቀን ለባሏ ተሰጠች
ተዚያን ቀን ጀምራ
ተዚያን ቀን ጀምሮ
ድንግል ድንጋይ ወቅራ
ትፈጫለች ሽሮ።
አታውቅም፣
ማን እንደሚባሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ
አታውቅም፣
ሹማምንት፣ በ'ሷ ስም፣ምን እንደሚሰሩ
አነሣኹት እንጂ እኔም ለነገሩ
በፖለቲካ ጥበብ ራስን ማራቀቅ
ምን ይጠቅማትና፣ጓያዋን ለማድቀቅ።
ከቶ ማንም የለ፣አበባ የሚሰጣት
ከቶ ማንም የለ፣ከተማ የሚያወጣት
ከቶ ማንም የለ፣በዳንኪራ መላ፣ወጠቧን የሚያቅፋት
ልፋቷም፣ዕረፍቷም፣
ወደዚህ መጅ መሳብ
ወደዚያ መጅ መግፋት።
እንደ ዓባይ ፏፏቴ ሺሕ ዓመትቢንጣለል
ቢጎርፍም ዱቄቱ
እንደ ሲኦል ወለል
ጫፍ የለውም ቋቱ ።

ከዘመናት ባ'ንዱ
መስታወት ፊት ቆማ፣በተወለወለው
ፊቷን ለማየት
ከፀጉሯ ላይ ያለው
ዱቄት ይኹን ሽበት ሲያቅታት መለየት
ያኔ ይገባታል የተሰጣት እጣ
ከማድቀቅ ቀጥሎ መድቀቅ እንደ መጣ።

የመጅ አገፋፏ አምሳለ ሲሲፈስ
ከቋት ስስት እንጂ ሲሳይ አይታፈስ
ትቢያ ሚተነብይ ዱቄት በዙርያዋ
ከባርኔጣ አይሰፋም የኑሮ ጣርያዋ
"ስትፈጭ የኖረች ሴት " ይህ ነው መጠሪያዋ።


#ሲሲፈስ- በግሪክ ተረት ውስጥ የሚገኝ ተኮናኝ ሲኾን ኩነኔው ያለግብ ድንደፈጋይ መግፋት ነው።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
@sayatmekdi


#አካሔድ

ፍጥነት የምንለው ነው የማዝገም ጥላ
ወደፊት የሄደ ቀርቷል ወደኋላ።
ብልሆች በመንገድ ማዝገም ነው የሚመርጡት
የደረሱ ናቸው መድረሻ የሚያጡት።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
@sayatmekdi


"ቆንጆ ነኝ" ባይ ማነሽ?

በውበትሽ ማርከሽ
ንጉስን ከዙፋን ፥ ማውረድ ሳትችዪ
ማነሽ "ቆንጆ" ሲሉሽ ፥ አቤት የምትዪ?

ድሮ ድሮ እኮ
የሴት ልጅ ውበቷ ፥ ዙፋንን ያስረሳል
ያንዲት ሴት ቁንጅና ፥ ካንድ ጦር ይብሳል።

ድሮኮ ድሮኮ
መንግስት ህዝብ ላይ ፥ በስልጣን ሲለግም
ከዙፋን ለማውረድ
አንዲት ቆንጆ እንጂ ፥ ትግል አያስፈልግም።

ድሮኮ ድሮኮ
ፈጣሪ የሾመው ፥ ጥበብን አድሎት
ዙፋኑን እንዳይለቅ
"ቆንጆ አታሳየኝ" ነው ፥ ያንድ ጠቢብ ፀሎት።

ንጉስን ለማውረድ ፥ህዝብ ሲያጣ አቅም
እኛው ከኛው ጦር ጋር ፥"ልቀቅ አንለቅም"
እየተባባልን ፥እርስ በርስ ብናልቅም
ቆንጆ ስንል አቤት ፥ ያለንን አናውቅም።

ንጉስን ከዙፋን
በውበትሽ ማርከሸ ፥ ማውረድ የማትችዬ
አንዳችም ደም ሳይፈስ ፥ ህዝብ የምታስጥዬ
ማነሸሸ "ቆንጆ" ሲሉሽ ፣ "አቤት"የምትዪ

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
@sayatmekdi


ት/ቤት መፅሀፍ ሲሰጥህ ያንተ ንብረት ነው ተንከባከበው ይሉሀል ሲጠፋብህ ግን

የመንግስት ንብረት ነው ልፈል ይሉሀል


😆😂🤣
Join👉 @sayatmekdi
Share  & Invite ur Frinds


በዚች አለም ላይ የፈለከውን ያህል ገንዘብ እና ሀብት ቢበዛ ደስታን ሊገዛ አይችልምና...

#እባካችሁ_ወደኔ_አካውንት_አዘዋውሩት😜
@sayatmekdi


👉 በጋዜጣ የተጠቀለለ ማንኛውንም አይነት መብል አይመገቡ ለምን ብትሉ ጋዜጣ ላይ ያሉትን ፅሁፎች ለማስፈር ቀለም ይጠቀማሉ ይህ ቀለም ቀጥታ ለካንሰር ያጋልጠናል @sayatmekdi




@ifamlucky
👆🙏❤️


​​​​​​​​┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺ተመኘው ልኖረው🌺̶̥✽̶┉┉┄┄
          
በእናቴ ሆድ ሳለው ነበር ሀገሬን ያየኋት
ተወልጄ ሳይሆን ከማህፀን ሳልወጣ
የሀገሬን ፍቅር በሰው ተመስሎ
ከእንናቴ ሆድ ወጣው
ማርያም ማርያም ብለው
ፍቅር ተጀመረ በእናት እቅፍ ውስጥ
የማይሻር ፍቅር የማያልቅ ሰቀቀን
ተወልጄ እስካድግ የእናት መሳሳት
ስወጣ ስገባ የጉረቤት ስራ
እኔን መሳም ነበር አጥፍቶ ጥላቻ
ተምሬ ነበር እውቀትን ተግብሬ
ቁጥር ቆጥሬለው ግእዙን ደምሬ
ቃላት ገጥሜለው ቅኔው ጨምሬለው
ስለ ሀገር ፍቅር ቃላት ፈልጌለው
ስለ እናት ፍቅር ቃላት አጥቻለው
የማይቆጠር ዘመን የማያልቅ ትንሳኤ
ስለ ሀገር ፍቅር
ስለ እናት ህይወት
ተዘርዝሮ አያልቅ ድንግልው ሀገርሽ





┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

       @sayatmekdi
┈┈••◉❖◉●••┈ @kezimkezamofficial
┄┄┉┉✽̶»̶̥✿🌺✿»̶̥✽̶┉┉┄


​​​​ 😢አልቻልኩም😢
​​​​​​​​​​✽┉┉̶»̶̥🌷✿🌷»̶̥✽̶┉┉
ቃል አቅም የለው ምክን ነው ፊደሉ፣
ሰፍረው ከብራናው ሞልተው የጎደሉ፣
ሳቄ የእምባ ነው ደስታዬ የለቅሶ፣
ፈውሴ የህመም የማይድን ተዳብሶ፣
በቃ እንዲዚ ነኝ ናፍቆት ያቃተኝ ለት፣
ልቤ ማይመለስ በግዝት በስለት፣
አይኔ እየተራበሽ አለ እየኖረ፣
ሌላውን እንዳያይ በፍቅር የታወረ፣
ካንቺ ሌላ ደስታ ሊሰጡኝ ቢጥሩ፣
ለኔ ሀዘን ሆነብኝ እልፍ ቢያማትሩ፣
የለመደሽ ልቤ በናፍቆትሽ ናውዞ ይኸው ይዋልላል፣
ሚመልስሽ ባይኖር እየደጋገመ አንቺን ይጠይቃል፣
ግን አይከብድም ውዴ፣
ሳቄ ደስታ ቢስ ነው፣
እንቅልፌ ረፍት የለው፣
አካሌ የደከመ ናፍቆት ያመነነው፣
ደና ነህ ለሚሉኝ እላለሁኝ ደህና፣
ቁስሌ እየባሰ ናፍቆት እየፀና፣
አንቺ ግን እንዴት ነሽ የልቤ ትርታ፣
የመጀመሪያዬ የፍቅሬ ሀሌታ፣
እኔ አልቻልኩበትም ያነጫንጨኛል፣
በሆነው ባልሆነው ቶሎ ይከፋኛል፣
ያ ያለፍነው ጊዜ ብርታት ባይሆነልኝ፣
እኔ አልችልም ነበር ናፍቆት በገደለኝ፣
ቀኑ ነግቶ እስኪመሽ አንቺው ነሽ ሃሳቤ፣
ውዴ አልቻልኩበትም ነይልኝ ረሃቤ፣
ጨዋታና ሳቅሽን እያሰላሰልኩኝ፣
ካጠገቤ ሳጣሽ በንባ ፅፌ ላኩኝ፣
ቀኑ ይከብደኛል አያልቅም ሰዓቱ፣
ያላንቺ አያምርም ቢመሽም መንጋቱ፣
ደግሜ አይሻለሁ አልተጠራጠርኩም፣
ግን መቼ ነው ውዴ ኸረ እኔ አልቻልኩም፡፡
​​​​​​​​​​✽┉┉̶»̶̥🌷✿🌷»̶̥✽̶┉┉
ከዚህም ከዚያም ከዚህም ከዚያም
@sayatmekdi


#አስተማሪ ፡- ሰይፉ ፀጉር ቤት ሄዶ አያውቅም ፡፡ በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ ሰይፉ ምንድን ነው ??
ተማሪ ፡- መላጣ
😂😁😂😄😆😃😃

JOIN:- @sayatmekdi


What Will You Get

In a mathematics class...
TEACHER: If you have 12 chocolates and you give 5 to Mahlet, 3 to Helen and 2 to Yordi , then what will you get?
HUSTLER: 3 new girlfriends!
🤣🤣🤣😂😂😂


😂እስቲ ፈገግ በሉልኝ😂

አንድ ሰው በሚስቱ ክፋት ተማረረና ለአንድ ሸህ ብሦቱን ተናገረ፡፡ እነ ሸህ “ምላሷን አልቻልኩም፣ አቆሰለችኝ፡፡” አላቸው፡፡
ሸሁም “እስቲ አትናገራት፤ መጥፎ ይሁን ጥሩ በምትሠራው ነገር ሁሉ ዝም ብለህ አወድሳት፡፡” አሉት።
ሰውዬው የሸሁን ምክር ተቀበለ፡፡ ወደ ተግባር ለመለወጥም ተዘጋጀ፡፡

አንድ ቀን ሚስቱ እራት አመጣችለት፡፡ አስቀምጣለትም ዘወር አለች፤ እንዳትርቅበት እየተጣደፈ ገና አንድ እንደጎረሰለት
“ዉይ ዉዴ የዛሬው ምግብሽ ስጣፍጥ እኮ!” አላት፡፡

እሷም “አልቀረብህም፤ እንደው እኮ ትገርማለህ! ስንት ዓመት ሙሉ መርዝ የበላህ የኖርክ መሰለህ፤? እኔ የሠራሁትን ምግብ አንድም ቀን ሳታሞግስና ሳታደንቅ ዛሬ ጎረቤታችን ያመጣችዉን ምግብ የምታደንቀው?፡፡

ለካስ የቀረበለት ምግብ ከጎረቤት የመጣ በሀዲያ መልክ የመጣ መሆኑን አላወቀም ነበር ሚስኪን ባል፡፡
ወይ ኪሳራ
@sayatmekdi


የመብራይት ሀይል ሰራተስኛ ከስራ ተባረሀል
ተብሎ ምን አጠፋው ሲል


እኮ ምንም ስላላጠፋክ እኮ ነው
@sayatmekdi


መሬት ላይ ተደፍቼ እያየኝ ወድቀሽ ነው ይለኛል 😳







አይ ጉንዳኖች ተጣልተው እየገላገልኳቸው ነው 😒😂😂
@sayatmekdi


~ጥሩ ዜና~
ሰውየው እግሩን ታሞ ሀኪም ጋር ይሄድና በዶክተር ይታያል።

ሀኪሙም የምርመራው ውጤት ይዞ እየገባ "አንድ መልካምና አንድ መጥፎ ዜና ይዤ መትቻለው ከየቱ ልጀምር "ይላል?...

ሰውየው ከመጥፎው!

ሀኪም ሁለቱም እግርህ መቆረጥ አለበት

ሰውየው እና ጥሩው ዜና ታድያ ምድነው

ሀኪም እዛኛው ክፍል ውስጥ ጫማህን የሚገዛ ሰው ተገኝቶዋል😂😂😂😂
@sayatmekdi


🤔ለፈገግታ😁

👱አንዱ ሰውዬው ወንዝ ዳር ቁጭ ብሎ ያለቅሳል😭😭😭

👀ይህንን የተመለከተ አንድ🙎‍♂ ሰው ወደ እርሱ ይመጣና "ለምንድነው የምታለቅሰው?" ይለዋል

👱ሰውዬውም " አንድ ማንኪያ ሙሉ ስኳር እዚህ ወንዝ ውስጥ ጨምሬ የወንዙን ውሃ ብቀምሰው ምንም አይጣፍጥም"😢ሲለው

🙎‍♂፡ ሌላኛው ሰውዬ ሳቁን ይለቀዋል😂፡፡

👱ሰውዬው----"ምን ሆነህ ነው የምትስቀው?"😡

 " " " " " " " "
🙎‍♂አንተ ጅል! መጀመሪያ አታማስለውም ነበር! 😃
😂😂😂😂
@sayatmekdi


ትምህርት ለመጀመር ሙሉ ዝግጅቴን ጨርሻለው... አሁን የቀረኝ ስንተኛ ክፍል እንደነበርኩና
.
.
.
የት ት/ቤት እማር እንደነበር ማስታወስ ነው 😂😂😂
@sayatmekdi


እንዴት አደራችሁ
መልካም እለተ ሐሙስ
ቀኑ የሰላም 🕊
የፍቅር 👩‍❤️‍👩💑👨‍❤️‍👨
የጤና 😊
የደስታ 😁😆
እንዲሆን ተመኘው

Показано 20 последних публикаций.

209

подписчиков
Статистика канала