😢አልቻልኩም😢
✽┉┉̶»̶̥🌷✿🌷»̶̥✽̶┉┉
ቃል አቅም የለው ምክን ነው ፊደሉ፣
ሰፍረው ከብራናው ሞልተው የጎደሉ፣
ሳቄ የእምባ ነው ደስታዬ የለቅሶ፣
ፈውሴ የህመም የማይድን ተዳብሶ፣
በቃ እንዲዚ ነኝ ናፍቆት ያቃተኝ ለት፣
ልቤ ማይመለስ በግዝት በስለት፣
አይኔ እየተራበሽ አለ እየኖረ፣
ሌላውን እንዳያይ በፍቅር የታወረ፣
ካንቺ ሌላ ደስታ ሊሰጡኝ ቢጥሩ፣
ለኔ ሀዘን ሆነብኝ እልፍ ቢያማትሩ፣
የለመደሽ ልቤ በናፍቆትሽ ናውዞ ይኸው ይዋልላል፣
ሚመልስሽ ባይኖር እየደጋገመ አንቺን ይጠይቃል፣
ግን አይከብድም ውዴ፣
ሳቄ ደስታ ቢስ ነው፣
እንቅልፌ ረፍት የለው፣
አካሌ የደከመ ናፍቆት ያመነነው፣
ደና ነህ ለሚሉኝ እላለሁኝ ደህና፣
ቁስሌ እየባሰ ናፍቆት እየፀና፣
አንቺ ግን እንዴት ነሽ የልቤ ትርታ፣
የመጀመሪያዬ የፍቅሬ ሀሌታ፣
እኔ አልቻልኩበትም ያነጫንጨኛል፣
በሆነው ባልሆነው ቶሎ ይከፋኛል፣
ያ ያለፍነው ጊዜ ብርታት ባይሆነልኝ፣
እኔ አልችልም ነበር ናፍቆት በገደለኝ፣
ቀኑ ነግቶ እስኪመሽ አንቺው ነሽ ሃሳቤ፣
ውዴ አልቻልኩበትም ነይልኝ ረሃቤ፣
ጨዋታና ሳቅሽን እያሰላሰልኩኝ፣
ካጠገቤ ሳጣሽ በንባ ፅፌ ላኩኝ፣
ቀኑ ይከብደኛል አያልቅም ሰዓቱ፣
ያላንቺ አያምርም ቢመሽም መንጋቱ፣
ደግሜ አይሻለሁ አልተጠራጠርኩም፣
ግን መቼ ነው ውዴ ኸረ እኔ አልቻልኩም፡፡
✽┉┉̶»̶̥🌷✿🌷»̶̥✽̶┉┉
ከዚህም ከዚያም ከዚህም ከዚያም
@sayatmekdi
✽┉┉̶»̶̥🌷✿🌷»̶̥✽̶┉┉
ቃል አቅም የለው ምክን ነው ፊደሉ፣
ሰፍረው ከብራናው ሞልተው የጎደሉ፣
ሳቄ የእምባ ነው ደስታዬ የለቅሶ፣
ፈውሴ የህመም የማይድን ተዳብሶ፣
በቃ እንዲዚ ነኝ ናፍቆት ያቃተኝ ለት፣
ልቤ ማይመለስ በግዝት በስለት፣
አይኔ እየተራበሽ አለ እየኖረ፣
ሌላውን እንዳያይ በፍቅር የታወረ፣
ካንቺ ሌላ ደስታ ሊሰጡኝ ቢጥሩ፣
ለኔ ሀዘን ሆነብኝ እልፍ ቢያማትሩ፣
የለመደሽ ልቤ በናፍቆትሽ ናውዞ ይኸው ይዋልላል፣
ሚመልስሽ ባይኖር እየደጋገመ አንቺን ይጠይቃል፣
ግን አይከብድም ውዴ፣
ሳቄ ደስታ ቢስ ነው፣
እንቅልፌ ረፍት የለው፣
አካሌ የደከመ ናፍቆት ያመነነው፣
ደና ነህ ለሚሉኝ እላለሁኝ ደህና፣
ቁስሌ እየባሰ ናፍቆት እየፀና፣
አንቺ ግን እንዴት ነሽ የልቤ ትርታ፣
የመጀመሪያዬ የፍቅሬ ሀሌታ፣
እኔ አልቻልኩበትም ያነጫንጨኛል፣
በሆነው ባልሆነው ቶሎ ይከፋኛል፣
ያ ያለፍነው ጊዜ ብርታት ባይሆነልኝ፣
እኔ አልችልም ነበር ናፍቆት በገደለኝ፣
ቀኑ ነግቶ እስኪመሽ አንቺው ነሽ ሃሳቤ፣
ውዴ አልቻልኩበትም ነይልኝ ረሃቤ፣
ጨዋታና ሳቅሽን እያሰላሰልኩኝ፣
ካጠገቤ ሳጣሽ በንባ ፅፌ ላኩኝ፣
ቀኑ ይከብደኛል አያልቅም ሰዓቱ፣
ያላንቺ አያምርም ቢመሽም መንጋቱ፣
ደግሜ አይሻለሁ አልተጠራጠርኩም፣
ግን መቼ ነው ውዴ ኸረ እኔ አልቻልኩም፡፡
✽┉┉̶»̶̥🌷✿🌷»̶̥✽̶┉┉
ከዚህም ከዚያም ከዚህም ከዚያም
@sayatmekdi