مدرسة نور الهدى


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций












ዒባዳ ላይ ፅና ወደ ኋላ አትሽሽ
በፆም አሳምረህ ሲወጣ አታበላሽ
ረመዳን ሲወጣ ከጌታው የሚሸሽ
ምንኛ ሞኝ ነው የሰራውን አፍራሽ

የረመዳን ዓቢድ በፆም ብቻ ሰጋጅ
መስጂድ አጨናንቆ ሲወጣ ተወጋጅ
ረመዳን ሲወጣ ወደ ወንጀል ነጓጅ
መሆኑን አውጇል የእስረኛው ወዳጅ

እባክህ ወንድሜ ጌታን ሁሌ አምልክ
በሰላትህ ዘውትር ትሆናለህ ብሩክ
ከሸይጣን ወጥመድ ራቅ ለሱ አትንበርከክ
ዓላማህ ላይ ፅና እውነት ወንድ ከሆንክ

እህቴዋም ፅኚ በጌታሽ መንገድ ላይ
በሰላት በሂጃብ አትሁኝ ወላዋይ
ወንድን ምታሳስት አትሁኝ አማላይ
ራስሽንም ጠብቂ ከፋጂር አታላይ

እንዴት ያምር ነበር ረመዳን ነሻጣው
ፆሙ ተራዊሁ ድባቡ ሞቅታው
ቲላወቱል ቁርአን ብዛቱ የኺትማው
ተሰናብቶን ሄደ ሁሉም ተወጋጅ ነው

ቀድሞም ተነግሮናል ቶሎ እንደሚሄድ
አያመል መዕዱዳት ፈጥኖ ሚገባደድ
ለነገ ቤታችን በቂ ስንቅ ሳንሰንቅ ባግባቡም ሳንነግድ
ገባ ሲባል ወጣ እየተቻኮለ እያየን ሲነጉድ

ግን ተሰፋ አልጨለመም በረመዳን መውጣት
ሀጅም ተከትሏል ፆም በሄደ ማግስት
ሰላት ሁሌም አለ በቀንም በሌሊት
ሱና ፆምም አለ ዚክርም ማታ ጠዋት

በዒባዳ ፅና አታቁም ስራህን
ረሱልን ተከተል አታምፅ ወዳጅህን
በሱና ፆም በርታ አታቁም ሰላትክን
ፅናት እንዲሰጥህ ተማፀን ጌታህን


አል ሁዳ ኢስላማዊ የርቀት ትምህርት ከቀድሞው በተለየ መልኩ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍል ተማሪዎችን እየመዘገበ ይገኛል። ከአረብ ሀገራትና አሜሪካ ወጣ ብሎ ቻይና ጀርመን አዝረቢጃን እና ለሎችም የአፍሪካ የአውሮፓና ኤዥያ ሀገራት ተማሪዎች በመመዝገብ ላይ ናቸው።

እርሶም የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አል ሁዳ በሩን ከፍቶሎታል።


ያሉበት ሀገር የትምህርቱ ተሳታፊ ከመሆን አያግዶትም።

ይመዝገቡና ባሉበት ሆነው ዲኖን ይማሩ!!!


አልሁዳ ኢስላማዊ የርቀት ትምህርት 0911347676
0921987272




የ ከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ልዩ የዳዕዋና የዚያራ ጉዞ አጭር ሪፖርት

የጉዞ መነሻ ፣ አዲስ አበባ ረመዳን 25 ለሊት

የተጓዦች ቁጥር ፣ ከ አዲስ አበባ 16 እና ከ ስልጤ አካባቢ 4 ተጨማሪ በድምሩ 20

የጉዞ ርቀት ፦ 330 ኪሜ በላይ

ይዘን የሄድነው የዳዕዋ ግብአቶች ፦ *5 የተለያየ ርእስ ያላቸው ፓምፍሌቶች የእያንዳንዳቸው ብዛት 500 በድምሩ 2,500
50 መፃህፍት*

ይዘን የሄድነው ሌሎች ቁሳቁስ ፦
*100 ኩንታል የበቆሎ ዱቄትና 5 ካርቶን ቴምር*
የመጓጓዣ ብዛት ፦ *2 መኪና*
አጠቃላይ ወጪ ፦ *105,198*

በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ላይ የታደሙ ሰዎች ቁጥር ፦ ከ *700* *በላይ*

*የዳዕዋው ሁኔታ ፦*
በቅድሚያ *ሰልሰቢል ዙመካን* መሀሲነል ኢስላም በሚል ርዕስ ል 1 ሰአት ከ 8 ደቂቃ ያህል የቆየ ዳዕዋ ያደረገ ሲሆን በመቀጠል *አወል ሸርሞሎ* ለ 50 ደቂቃ ሙሀደራ አድርጓል። በመሀሉም ለሁለት ጊዜ ያህል የጥያቄና መልስ ፕሮግራም ተካሂዷል።

*የእርዳታው ሁኔታ ፦*
የእርዳታ ፈላጊውና የእርዳታው መጠን ባለመመጣጠኑ የተነሳ ብዙ ወከባ ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም በአላህ እርዳታ እና ቀጥሎም በወንድሞች ርብርብ ሁኔታው ከቁጥጥር ሳይወጣ ለመጠናቀቅ በቅቷል፤ ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው።

ቴምሩን አንዱ ካርቶን ለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰጠ ሲሆን አራቱን ካርቶን ለመስጂዱ ኢማም እና ሙአዚን መስጀከድ ውስጥ ለማስፈጠር እና ለመሳኪኖች እንዲሰጡ ተረክበዋል።

የጉዞ መመለሻ መነሻ ፦ *ረመዳን 25 ከ መግሪብ* በፊት ሲሆን *ረመዳን 26 ለሊት* ሁለቱም መኪኖች ያለ ምንም ችግር አዲስአበባ ገብተዋል፤ ምስጋና *ለአላህ* የተገባ ነው።




ክቡር እንግዳችን ታላቁ ረመዳን
ከነፍክብንሳ ከንቅልፍም ሳንባንን
በደምብ ሳንጠግብ ተራዊህ ለይሉን
ሚስኪን ሳናስፈጥር ሳናኸትም ቁርአን

የቁርአን ወር ነበር የሚኸተምበት
ከገፍላ ተላቀን የምንዘክርበት
በዱዓ በሰላት ምንጠነክርበት
ሄደ ግን በቶሎ ሳንጠቀምበት

ያ ረብ! መቼም ቸርነትህ ሁሌም ተከጃይ ነው
ምህረትና አፍውህ ሁሌም ተስፋችን ነው
ከስራችን ይበልጥ እዝነትህ ወሳኝ ነው
ይቅር በለን ረህማን ራህመትህ ቅርብ ነው

ለይለተል ቀድርንም ወፍቀን ያ ረህማን
አልፉርቃን ከዙል ዐርሽ የወረደበትን
ከአንድ ሺ ወራት በላጭ የሆነውን
መልአኮች ከሩህ ጋር የሚወርዱበትን

ወፍቀን ያ ረህማን ለለይል ሰላቱ
ልንፀልይህ ከልብ ልንሰግድ በሌሊቱ
ለምህረትህ ልንቀርብ ልንባል ዐፈውቱ
ልንለማመጥህ ልትለን ፈዐልቱ

ያ ረብ! አፅናን በአምልኮህ አድርገን ሙስተቂም
ረመዳን ሲወጣም በዒባዳህ ምንቆም
ከለይም ከፆሙም መልካምን ማናቀም
የቂን እስኪመጣን ቀጥ አርገን ያ ረሂም

ሰልሰቢል ዙመካን የቅርብ ወንድማችሁ
በርግጥ ገጣሚ ነኝ ብየ አልዋሻችሁ
ብዬ ነው እንግዲህ ያቅሜን ላስታውሳችሁ
ሱጁድ ላይ በሌሊት አውሱኝ በዱዓችሁ






አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
ዛሬና የፊታችን ተከታታይ ሌሊቶች ወርቃማ ጊዜያት ናቸውና በንቃት እንጠቀምባቸው። ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የረመዳን የመጨረሻዎችን ሌሊቶች ሽርጣቸውን አጥብቀው ለሊቶችን በዒባዳ ህያው ያደርጉ ነበር። ቤተሰቦቻቸውንም ይህ እድል እንዳያመልጣቸው ሲሉ ይቀሰቅሱ ነበር። በነዚህ ሌሊቶች ውስጥ አንድ ሺ ወራት ዒባዳ ከማድረግ በሷ ሌሊት ዒባዳ ማድረግ በላጭ የሆነ ለይለተል ቀድር አለች። የእሷን መልካም የተነፈገ በርግጥ ከታላቅ ነገር ተነፈገ። ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም «ለይለተል ቀድርን ሰላት ቆሞ ያሳለፈ ያለፈው ኃጢኣቱ ይማርለታል» ብለዋን እና የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች ይህን አጭር ጊዜ በዒባዳ በማሳለፍ እድለኞች ሁኑ። በነዚህ ሌሊቶች ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የመከሩንን ዱዓ አብዙ፦
اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني






የአልሁዳ ኢስላማዊ የርቀት ትምህርት አዲሱ ዙር ትምህርት የሚጀምረው ረመዳን እንደወጣ ሸዋል 2 ላይ ሲሆን ከወዲሁ መማር የምትፈልጉ ሙሉ ስማችሁን አስመዝግባችሁ የመጀመሪያ ሴሚስተሩን ክፍያ መፈፀም ይጠበቅባችኋል።
ትምህርቱ 14 ወራት ማለትም አንድ አመት ከሁለት ወራት የሚወስድ ሲሆን እያንዳንዱ ሶስት ወራት የሆኑ አራት ሴሚስተሮች አሉት።
ተማሪው በየሴሚስተሩ የሚያነባቸው መፅሀፎችን ያገኛል በዋትስ አፕ ጉሩፕ የሚለቀቁ ማብራሪያዎችን ያደምጣል። እንዲሁም የሚለቀቁ መልመጃዎችንና ዎርክ ሺቶችን ይሰራል። በመጨረሻም የሴሚስተሩን ዋና ፈተና ይወስድና ውጤት ይሰጠዋል። በተመሳሳይ መልኩ የተቀሩትን ሴሚስተሮች ተምሮ ሲያጠናቅቅ ዲፕሎም ያገኛል።
በመጀመሪያ ሴሚስተር የሚሰጡ ትምህርቶች፦
1 ዓቂዳህ
2 ፊቅህ
3 ተጅዊድ
4 ዓረብኛ
5 አል አኽላቅ ወል አዳብ
የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርቶች፦
1 ዓቂዳ 2
2 ፊቅህ 2
3 ሀዲስ
4 ዐሉሙል ቁርአን
5 ሲራ
የሶስተኛ ሴሚስተር ትምህርቶች፦
1 ዓቂዳህ 3
2 ፊቅህ 3
3 ኡሱሉል ፊቅህ
4 ተፍሲር
5 ሙስጠለሁል ሀዲስ
የአራተኛ ሴሚስተር ትምህርቶች፦
1 ኒካህና ፍች
2 ኢስላማዊ የውርስ ህግጋት
3 ኢስላማዊ የግብይት ህግጋት
4 ኡሱሉ ዳዕዋ
5 ሱና እና ቢድዓ
ይመዝገቡ! ወዳጆችዎም እንዲመዘገቡ ያድርጉ!
ባሉበት ሆነው ዲኖን ይወቁ!!!
0911347676
0921987272
በቀጥታ ደውል በዋትስ አፕ ወይም በቴሌግራም ያግኙን።


አልሁዳ ኢስላማዊ የርቀት ትምህርት ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ በዋትስ አፕ ትምህርቱን መከታተል ለሚፈልግ አማራጭ ፈጥሯል። ተመዝግበው ባሉበት ሆነው ይከታተሉ። ለፈተናም ሆነ ለማንኛውም ጉዳይ ቢሮ መመላለስ አይጠበቅቦትም።
0911347676/0921987272 ዋትስ አፕ ላይ ያግኙን!! ያስተውሉ፦ ኢትዮጵያ ላሉ ተማሪዎች ኢንተርኔት መጠቀም ግድ አይደለም። አቅራቢያዎ ካለው የአልሁዳ ጣቢያ መፅሀፎችና ሲዲ በማግኘት የመማሩ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ ይህን ያልፈለገ ወይም ያልተመቸው ደግሞ ያለበት ቦታ መፅሀፍ ተልኮለት ማብራሪያውንና ፈተናውን በዋትስ አፕ የመውሰድ አማራጭ ተፈጥሮለታል።
ማሳሰቢያ፦ የሀገር ውስጥ የሴሚስተር ክፍያ ባለበት ሆኖ መፅሀፉን ወዳሉበት ለመላክ የሚያስከፍለውን ተጨማሪ ክፍያ መሸፈን ይጠበቅቦታል።

0911347676
0921987272
0921878704
ይደውሉ ወይም በዋትስ አፕ ይፃፉልን። አህለን ቢኩም




ከኢትዮጵያ ውጭ ላላችሁ ሶስተኛ ዙር የዋትስ አፕ ጉሩፕ ሸዋል 1 ስለሚከፈት የመማር ፍላጎት ያለው ከወዲሁ እንዲመዘገብ ጥሪ እናቀርባለን።
አልሁዳ ኢስላማዊ የርቀት ትምህርት ያሉበት ይደርሳል

Показано 20 последних публикаций.

3 537

подписчиков
Статистика канала