Репост из: SameN
My Pencil & My chronicle
ከተለያዩ የአ.አ ሰፈሮች/አካባቢዎች የመጣን ለዘመናዊ ሆቴል ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ከሆነው ጣይቱ ሆቴል ፊት ለፊት ተሰባስበናል። ኧረ እንደውም እዛው ያደረ አይጠፋ...
የጉዞው አዘጋጆች ከላይ ታች የማስተባበር ስራውን ተያይዘውታል። የማርፈድ ልምድ ያለብን አንዳንድ የአ.አ ነዋሪዎችንም ከነብርድ ልብሳችን ጭምር አስተባብረው ከመኪናው ከተቱን።
ከመኪናው ውስጥም እንደምንም የተጫጫነንን ስሜት አላቀን ጉሮሯችንን በእስክሪብቶ ጎርጉረን 'እንዴት አደራችሁ' እያልን ከባላጋራችን ሰላምታ መለዋወጥ ጀመርን። እንዲህ ባለው ስሜት አ.አ ለቀን ለመውጣት ከሹፌሩ ጋር ሞተሩንም ወሬውንም አሙቀን ተንቀሳቀስን። በመንገዳችንም አውቶቡሷ አንዳንድ የአ.አ አካባቢ ነዋሪዎችን እየለቀመች ነጎደች። አ.አ ለቀን አየወጣን ነው ወሬውን ቡና ሳናፈላ ሞቅ አርገነዋል። ይህን የተገነዘበው የፊት አጋፋሪው አቶ ዲጄ ሆዬ የበለጠ ዘና ለማድረግ ቅን ልቦና ተያይዞ መሰለኝ ሙዚቃውን ሊያንቆረቁሩት ተነሱ። ሙዚቃውንም ለቀቁት የመጀመሪያ ምርጫቸውም 'ሱሴ' የሚል ርዕሰ ዜማ ያለው ነበር። እኔን ጨምሮ ተጓዦች ያዛጉ ጀመር ትተነው የመጣነውን ቀሰቀሱብን ይመስላል። የዲጄው ነገር ይቆየንና ተጓዡ ግን ምን አስቦ ነው ሱሴ ሲባል የሚያዛጋው ቆይ ይሄም ይቆየን።
ጉዞውም ቀጥሏል አሌልቱን ቀጥሎ ሸኖን አለፍንና ጥንታዊቷ ደ.ብርሃን ደረስን መሰለኝ። አውቶቡሳችንም ለቁርስ ይሁን ለረፍት ይሁን የደ.ብርሃን እርጎ ለመሸመት ይሁን ቆማለች።
ከደ.ብርሃን አልፈን የደብረሲናን መንገድ ተያያዝነው... ተያያዝነው ስል በአውቶቡስ ነው ታድያ ቅዝቃዜውም አየጨመረ መጣ። አንደርስ የለ ቦታው ደረስን መሰለኝ... ቆይ ይሄ ምኒሊክ የሚሉት ጉድ ምን አይነት መስኮት ሰርቶ ነው እዚህ ድረስ የጠራን እያልኩ ከራሴ ማውራት ጀመርኩ.... ኧረ ጉድ ይሄን የሚያህል ከፍታ ላይ ይሄን የሚያህል ክፍተት ነው ግን መስኮት ያሉት ለማለት ፈለግኩ። ትንሽ ቆይቼ ሳስበው ሳየው ሳልመው ግን እውነትም መስኮት: አሻግረው ሲመለከቱት የአዋሽ ተፋሰስ: የአፋር በርሃማ አካባቢዎች: የይፋት ቆላማ መንደሮችን በትኩሩት ላያቸው መስኮትነቱን ማረጋገጫ ሰጥቶ ያልፋል።
ተራሮችንም መውጣት መውረዱን ቀጠልን በየመሃሉ እልፍ የሚሉ ሽኮኮ መሳይ ፍጥረቶችን እንዲሁም በሰሜን ተራሮችብቻ የሚገኘው ጭላዳ ዝንጀሮን የመመልከት እድሉን አግኝተናል። ኧረ እንዲሁም ዘመን አመጣሹን ድሮን የምትመስል ወፍ ዝርያም አይተናል: መብረር የለ ሰማይ ላይ መቆም ብቻ... ጉዞው እየተፋፋመ ሲመጣ እኔም መፃፌን አቆምኩ... ቀሪውን ሳርፍ እነግራችኋለው እስከዛው ግን በዚህች አጭር ግጥም ልሰናበታችሁ...
ምኒሊክ ተጉዞ የምትጠይቀኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ
ይቆየን....
ሳሚDire