✨አደግሁ መሰለኝ....ሲከፋኝ ነጠላዬን አንጠልጥዬ ወደ ቤቱ እከንፋለሁ፨ልክ ቅጥሩን እንዳለፍኩ ከሰዉ ባዶ የሆነ ቦታ ላይ ሆኜ እንደሆንኩት ሆኜ ለእርሱ አወራለሁ፨በለቅሶዬ አጅቤም ይሁን....አልያም ወደጉልላቱ እያየሁ..አልያም በግንባሬ ተደፎቼ ብቻ የሆንኩትን ሁሉ ከመሆኑ በፊትም ለሚያዉቀኝ አምላክ አነበንብለታለሁ.....ሲቀለኝ:ስረጋጋ:ደኅና ስሆን ራሴን አየዋለሁ፨ከዛ ተመቻችቼ እቀመጣለሁ.....ዝምምም ብዬ...
ድሮ ድሮ የሆነ ነገር ስሆን የመጀመሪያ ፍለጋዬ የሚያቅፈኝ ክንድ ነበር፨በቀስታ የሚያባብሉኝ..ዝም ብለዉ የሚሰሙኝ....ፀጉሬን እየደባበሱ አይዞሽ ያልፋል የሚሉኝን የጓደኞቼን እቅፍ..
አሁን አሁን ማብራራት ደከመኝ መሰለኝ፨ሁሉም ሰዉ የየራሱ ትግል እንዳለበት ገባኝ ነገር...ዉስንነታችንስ አለ አይደል፨ትክክለኛዉ ፈዉስ ያለ ጠባሳ በሚያድነዉ ባለመድኃኒት እጅ ላይ አይደል...ብቻ ሁሌም ተሸናፊ ደካማ መስሎ ላለመታየትም ይሁን...ምፅ የሚል ድምፅን ላለመስማት....ሙሉ በሙሉ ባልተወዉም ሳድግ ቀነስኩት፨
...እንዲህ ከሆነ ከሆኑ ቀናት በኋላ...ድንገት ድንገት ልቤን አመመኝና...ወደ ቤቱ ገሰገስኩ.....ሰዉ እንቅስቃሴ የሚያቆምበት ጠራራ ተሲያት ስለነበር ቤቱ ዉስጥ ጥቂት ሰዎች ብቻ በጣም ተራርቀዉ ተቀምጠዋል፨
ወደአዉደምኅረቱ የመጠጋት ብቃት አልነበረኝምና ያልራቀም ያልቀረበም ብቻ ፊት ለፊት የርህራሄ ምስለ ስዕሉን ከማይበት ስፍራ ከአንድ ዛፍ ስር ራሴን አገኘሁት....እስኪደክመኝ...አቅሜ ሙጥጥ ብሎ የማልቀስ አቅም እስካጣ ድረስ አለቀስኩበት፨
በዝምታ...እያወራሁ...እየጠየኩት..ሁሉንም የተሰሙኝን ሁሉ ዝርግፍ አድርጌ ነገርኩት....ቀስስስ እያልኩ ስሰክን ይታወቀኛል...ከሆኑ ጊዜያት ቆይታ በኋላ ተረጋግቼ ተቀመጥኩ....ምስለስዕሉን ተመለከትኩት...አይኖቹ ሲፈትሹኝ አፈርኩት፨
ማሰብ ጀመርኩ..የሆነልኝን ..ያደረገልኝን...ከምን እንዳነሳኝ...ምን ያህል እንደወደደኝ...ትናንትናዎቼ ላይ ስፈራ:መራመድ ሲያቅተኝ የሸሸገኝን ያሻገረኝን አሰብኩትና...አሁን ያደናቀፈኝም ከእነዛ አይበልጥም ኣ አስባለኝ...እንዳለፉት እረሳዉ ይሆናል፨
ቁዘማዬን ስጨርስ ተነስቼ በጀርባ በር ወጣሁ...አስፓልቱን ተሻግሮ መካነ መቃብር አለ፨ምድር ላይ ካሉ ነገሮች ሁሉ አብልጬ የምፈራዉ አስከሬንና መቃብር ነዉ፨በተለይ ብቻዬን አይታሰብም የልጅነት ፍርሃት/childgoodtrauma/አለብኝ..ከሁለት ሳምንታት በፊት ከጓደኛዬ ጋር በዚህ መንገዴ እያለፍን ለምን ገብተን አናየዉም ብላኝ ገብተን ነበር፨
አሁን ዙሪያዉ ብዙ ሰዎች አሉ...መኪና የሚያጥቡ...እንጨት የሚያመላልሱ....ሰብሰብ ብለዉ የሚያወሩ...ብቻ በሰዎች ተሞልቷልና ቀጥ ብዬ ገባሁ፨በልዩነት አጠገቡ የምሄድለት ቤተሰብም ሆነ የማዉቀዉ ሰዉ ስለሌለ ፊት ለፊት ከሃዉልቶቹ አጠገብ ከበቀለች አንድ ዛፍ ስር ሔጄ ቆምኩኝ፨አንድ ሰዉ ለመቃብር የሚሆን ጉድጓድ እየቆፈረ ነዉ...ከሁለት ሳምንት በፊት መጥቼ ነበር ብያችሁ የለ...አምላኬ ሆይ ከዛ በኋላ በጣም ብዙ አዲስ መቃብሮች ተጨምረዋል፨
የሃዉልት ላይ ፅሁፎች በማንበብ ደቂቃዎችን አሳልፌያለሁ፨ከህፃን እስከ ወጣት..ከጎልማሳ እስከ አረጋዊ ሁሉም አይነት እድሜ አለ....እዉነቱን ለመናገር ወደ ጭንቅላቴ የመጣዉ የመጀመሪያው ጥያቄ"ምናልባት ነገ ትሞቻለሽ ብባል...እንዲህ ያስለቀሰኝ ነገር ከሚያሳስበኝ ነገሮች አንዱ ይሆናል?የሚል ነበር...
ግን ምላሼ አይደለም ነዉ....ከምር በጭራሽ ላስበዉ የማልችለዉ ነገር ነዉ...ራሴን ጅል ነዉ ያልኩት...ያዉም ድምፅ አዉጥቼ....ረጅም ደቂቃዎችን ቆይቼ...ወጣሁ.....ፈገግ ብዬ ነበር የተመለስኩት...ስሄድ ያዩኝ ጓደኞቼ ስመለስ ደኅና ነሽ ብለዉ ጠየቁኝ....አዎን....ቤቱ አይደል የሄድኩት ደኅና ነኝ አልኳቸዉ....ደኅና አደረገኝ....ያ ጊዜ ያ ሳምንት ብዙ ነገሮቼን ቀይሯቸዉ እንደነበር አልክድም....ግና አለፈ..
ህይወት አይደለ...አንድ ጊዜ ብቻ የሚሆንና የሚቀጥል ደስታ:የማያቋርጥ ልቅሶ ብሎ ነገር የለም....ህይወትስ መንገድ አይደለች...ተፈጥሮም እንዲሁ....ወቅቶች እንደሚቀያየሩት ሁሉ....አኗኗሯችንም በሚገጥሙን ሁነቶች ላይ ተመስርቶ ከፍ ዝቅ...ወዝገብ ወዝገብገብ ማለቱ አይቀርም...የሆነዉ ሆኖ መኖር መልካም ነዉ፨
በእቅፉ ያኑረን💙💙
✍𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮
https://t.me/yeesua_queen