💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡
ህያብ…🎁👫
( ክፍል ሶስት 3⃣ )
"ማድረግ ብችል ብዙ ባደርጋቸው እምላቸው ነገሮች አሉ… ግን አልችልም ለዛ ነው አብዝቼ እምጠጣው… ስጠጣ ባላደርጋቸውም ለአፍታ ግን እረሳቸዎለው… የአፍታ ሰላም ደሞ ለእኔ ትልቅ ቦታ አለው… ለዛም ጭምር እኮ ነው ሲኖረኝ ብቻ ሳይሆን ሳይኖረኝም ቢሆን ተበድሬ እምጠጣው…" ይላል ሁሌም እሚቀመጥበት ወንበር ላይ እንደተቀመጠ።
" ሰላም ነው አንድነት…? ምን ልታዘዝህ…?" አለች መሰረት…
አንድነትም… "ሰላም የለችም እንዴ…?" ሲል ጠየቃት…
"አዎ ማዘርን ትንሽ አሞት እቤት ቀርታለች… ምነው በሰላም ነው የፈለካት…?"
…" አዎ በሰላም ነው አይ ዛሬ እንዴት ሰላም አላለቺኝም ብዬ ነው… ደብል ጅን አምጪልኝ…" … መሠረት የመጀመሪያ ልጅ ነች … ለቀልድ ቦታ የላትም …ቤት ክርስትያንም አብዝታ አትጠፋም… ያዘዘውን ይዞለት መጣች…
" ምግብ ግን በልተሀል…? …ስትል ጠየቀቺው… ቀና ብሎ ተመለከታት ፊትዎ እንደሌላው ጊዜ አልተፈታም…
" አዎ በልቻለው …ስለጠየቅሺኝ ግን አመሰግናለው…" … ብሎ አቀርቅሮ መጠጣት ጀመረ…
በጭንቅላቱ ውስጥም ብዙ ነገር ይመላለሳል… ብቻውንም ያወራል…የሚያወራውም ቀስ ብሎ አደለም… ከጐኑ ያለው ሰው በሙሉ እስኪሰማው ድረስ ከራሱ ጋር ያወራል…… " በአንቺ ህይወት ውስጥ በሆነው እና እየሆነ ባለው ነገር ምንም ቅር የሚለኝ ነገር አይኖርም… የአንቺ ደስታ በቂ ነው… ለምን እንዲ አደረግሽ ብዬ እምወቅስሽ ነገር አይኖርም… እያለ ከራሱ ጋር ያወራል…
ሰላም ዛሬ የለችም… እቤቱ ሁሉ አዲስ የሆነ ያህል ተሰማው… አዲስ እና እማያውቀው መሸታ ቤት የሆነ ያክል ተሰማው… ከራሱም ጋር እያወራ የጠጣበትን ሒሳብ ጠረጴዛው ጋር አስቀምጦ…… " እንዴት ግን ዛሬ አልመጣችም ?…ደህና እድር የሚለኝ ሌላ እንደሚለኝ እንደሌለ እያወቀች ግን እንዴት? …ቢሆንም ሰው እሚያስበው ብዙ ነገር አለው… እኛ ሰዎች ስንባል ሁሌም እንዳሰብነው አድርገን ብቻ ነው ነገሮችን እምንረዳው…ሊሆን እኮ ይችላል… ግን ደሞ ላይሆንም ይችላል…" …… እያለ ገርበብ ብሎ የነበረውን በር ከፍቶ አባቱ ወዳወረሱት እና ብቻውን ወደ ሚኖራባት ቤቱ አመራ…
ይቀጥላል…
🌵 @yegna_photo 🌵
🎋 @itsmefilimon 🎋
✍ በፊሊሞን የማሪያም ልጅ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯