በምናልባት ኑሮ
አይቦዝን አንቀልባው
አይሞላም ጉድጓዱ
ሺሆች ሞተው ቢያድሩ
ሺሆች ተወለዱ
ይመሻል ይነጋል
ያው እንደልማዱ፤
መሬት ባህር ሆኖ፥ድሀን ሰለቀጠው
ትልልቁ ቪላ፥ትንሹን ቤት ዋጠው
በመስታወት ጫካ፥በጡብ በብረት ደን
አየሁ ባደባባይ፥ሰው በሰው ሲታደን፤
ማን በገላገለኝ፥የጄን ሰዓት ሰብሮ
በምናልባት አገር፥በምናልባት ኑሮ
የመጣው ይምጣ እንጂ፥ማን ያቅዳል ደፍሮ።
በእውቀቱ ስዩም
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥
አይቦዝን አንቀልባው
አይሞላም ጉድጓዱ
ሺሆች ሞተው ቢያድሩ
ሺሆች ተወለዱ
ይመሻል ይነጋል
ያው እንደልማዱ፤
መሬት ባህር ሆኖ፥ድሀን ሰለቀጠው
ትልልቁ ቪላ፥ትንሹን ቤት ዋጠው
በመስታወት ጫካ፥በጡብ በብረት ደን
አየሁ ባደባባይ፥ሰው በሰው ሲታደን፤
ማን በገላገለኝ፥የጄን ሰዓት ሰብሮ
በምናልባት አገር፥በምናልባት ኑሮ
የመጣው ይምጣ እንጂ፥ማን ያቅዳል ደፍሮ።
በእውቀቱ ስዩም
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥