ሀሳብ... እና... ትካዜ..!
❝ክፍል ➈❞
አምስተኛው ነጥብ፦ ይህ ሀሳብ.. እና.. ትካዜ ከአሏህ ﷻ የመጣ ፈተና መሆኑን ማወቅ።
ሀሳብ.. እና.. ትካዜ አሏህ ﷻ የሰዉየዉን ደረጃ ከፍ ለማድረግ ምክንያት አድርጎታል። ሀሰኑል_በስሪ እንደተናገሩት "አንድ ሰው የቂያማ እለት በመልካም ሥራው መዝገቡ ላይ ከሚያገኛቸው መልካም ነገሮች እጅግ ታላቁ በዱንያ ያጋጠመው ሀሳብና ትካዜ ነው።
አሏህ ﷻ የብዙ አማኞችን ደረጃ ከፍ የሚያደርገው፣ የቂያማ ቀንም ደረጃውን የሚያልቀው በዱንያ እያሉ በሚያጋጥማቸው ሀሳብ.. እና.. ትካዜ ነው። ለዚህም ነው የአሏህ መልእክተኛ ባልደረቦች፣ በል እንድያዉም የአሏህ ﷻ ነብያት በአደጋ የሚደሰቱት። ከአቡ ሰኢድ አል_ኹድሪይ እንደተዘገበው " በነብዩ ﷺ ላይ ገባሁ እና እጀን እሳቸው ላይ አስቀመጥኩ፣ ከተሸፈኑበት ልብስ በላይ ያለው የሰዉነታቸዉ ትኩሳት ተሰማኝ ከዛም ለነብዩ ﷺ የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! በእርግጥም ትታገሳለህ (በህመም)? አልኳቸው፣ እሳቸውም «ከእናንተ ሁሉ ሰዎች የሚያተኩሱትን ያክል እያተኮስኩ ነው። » አሉ
ከዛም አቡ ሰኢድ "እናንተ በስጦታ ከምትደሰቱት እነሱ (ነብዩ ﷺ ባልደረቦቻቸው) በአደጋ ይደሰቱ ነበር ብሎ ተናገረ። " የዚች የአቡ ሰኢድ ንግግር (መልእክት) ነብያት በአደጋ ጊዜ ሰዎች በስጦታ ጊዜ ከሚደሰቱት በላይ ይደሰታሉ ማለት ነው። የአሏህ መልእክተኛ ባልደረቦች፣ ደጋግ የአሏህ ﷻ ባሮች በስጦታ ከሚደሰቱት የበለጠ በአደጋ ላይ ይደሰታሉ ምክንያቱም የሰው ልጅ የቂያማ ቀን ሰላት፣ፆምና ሰደቃ፣ በማብዛት የሚያገኘውን ደረጃ አሏህ ﷻ በእሱ ላይ ባደረሰበት አደጋ ያገኛል። ከነዚህ አደጋዎች ደግሞ ሀሳብ...እና..ትካዜ ይካተታሉ ።
ስለዚህ፦ እነዚህ ከላይ ያሳለፍናቸው፣ አምስቱ ነጥቦች አንድ ሰው ይህንን ችግር ቀላል የሚያደርግባቸው መፍትሄዎች ናቸው። ከሌሎቹ በበለጠ እሱን እንድቀለዉ ያደርጋሉ። ነገር ግን አንድ ሰው ማወቅ ያለበት ይህ አደጋ'ና ሀሳብ ሙሉ በሙሉ አይወገድም። ሰዎች ሁሉ የተለያዩ ናቸው እንጂ ማንኛውም ሰው ላይ መከሰቱ አይቀሬ ነው። አንዳንድ ሰው ታላላቅ ነገራቶችን አሳንሶ ይመለከታል። እናም ታላቅ ጉዳዮች በሚመጡበት ጊዜ ትንሽ ነው የሚያሳስበው። ሌላው ሰው ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ ነው። ትንሽ ነገር ሲያሳስበው በነፍሱ ላይ ከተራራ በላይ ይከብድበታል። ለዚህም የመጀመሪያው ምክንያት በአሏህ ﷻ አለማመኑ ሲሆን፣ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ነገራቶችን በተገቢው ቦታቸው አለማስቀመጡ ነው። ለዚህም አንዳንድ ሰዎች የተጨነቁ እና የጠበባቸዉ ሆነው ይገኛሉ።
t.me/Binit_Seid_Al_kelaliya

ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል!
t.me/Binit_Seid_Al_kelaliya
t.me/Binit_Seid_Al_kelaliya