የይቅርታ እናት ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ !
✍️-የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የተጋድሎ ታሪክ እንደ ባሕር አሸዋ፣እንደ ሰማይ ክዋከበት ተቆጥሮ ተሰፍሮ ከማያልቀው ነገረ ቅዱሳን መካከል አንዱ ነው።
-ነገረ ቅዱሳንን መረዳት፣ማስረዳት ፣ማወቅና ማሳወቅም የወንጌልን አዝመራ መሰብሰብ ነው።
- ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዚህ ዓለም ከከበሩ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ደጋግ ባልና ሚስት የተገኘችና የተመረጠች እናት ናት።
✍️የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የአባቷ ስም ደራሳኒ፣የእናቷም ስም እሌኒ ይባላሉ። በሸዋ ክፍለ ሀገር በቡልጋ አውራጃ ጌየ በተባለች አካባቢ እንደ ተወለደች ታሪኳ ያስረዳል።(#ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘወርኃ መስከረም -ቊጥር-፪ )
ደረሳኒ እና ዕሌኒ ልጃቸውን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን በሃይማኖታዊና ሥነ-ምግባራዊ ሥርዓት አሳደጓት(ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘመስከረም -ቊጥር፬ ) መጽሐፈ ገድሏ" ልጅቱ ክርስቶስ ሰምራ ባደገችና ዐቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ የንጉሥ ባለሟል የሆነ••••የኢየሱስ ሞዓ ልጅ ለሠምራ ጊዮርጊስ በሕግ አጋቧት"ይላል።( ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘመስከረም -ቊጥር፮ )እግዚአብሔር በረድኤት ከሚገለጥባቸው የቅድስና መንገዶች አንዱ ቅዱስ ጋብቻ ነው።
✍️- ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለሠምረ ጊዮርጊስ ፲፩ ልጆች ወለደችለት ከነዚህም መካከል ፱ ወንዶች፣ ፪ቱሴቶች ነበሩ።(ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘመስከረም -ቊጥር- ፲፬) ልጆቿንም ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች በክብርና በሥርዓት አሳደገቻቸው።
✍️- ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትዳሯ ሰላማዊነት፣የባሏ አክብሮትና ፍቅር፣የልጆቿ መብዛት ፣የሀብትና ንብረቷ መድለብ እየሠመረ ቢሄድም የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልብ ግን የሚያስበው ግን ምናኔ ነበር።ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ፣ከዚያም በኋላ ልብሰ ምንኲስናዋን፣ ማለትም ቆቧን፣ ቀሚሷን፣ አጽፏን፣መታጠቂያዋን፣ አዘጋጀች።
✍️ ያልተለመደ ነገር ሲደረግ የተመለከቱት ቤተሰቦቿ ለምን እንደ ምታዘጋጀው ፣ለጠየቋት ጥያቄ " #ሃይማኖት ያስተማሩኝ አባቴ ልብስ አልቆባቸዋል፣ሲሉ ሰምቼ ለእርሳቸውም ነው የማዘጋጀው ፣"አለቻቸው።
ከዚህ ላይ ሃይማኖታዊ ጥበብ ያልተከሰተላቸው አስመሳዮች ለምን የሌላ ነው አለች" ሊሉ ይችላሉ።ይህ ሥርዓት ግን ለ፪ ነገር ይጠቅማል።
፩•የምናኔ ጉዞ ገና ሳይጀመር በውዳሴ ከንቱ ላለመጠለፍ፣
፪•ይህን ርምጃዋን ዲያብሎስ በተለያዩ ሰዎች አድሮ ሊያደናቅፈው ስለሚችል ከዓላማዋ ሊገታት ስለሚችል መልካም ጥበብ ነው።በሌላ በኩል ልማደ መጻሕፍትም ነው።
-✍️ ከዕለታት አንድ ቀን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አገልጋዮችን " ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሂድ" ብላ ይዛቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደች ።የምናኔው መጀመሪያ ነበር።
✍️- ከዚያም ቤተ ክርስቲያን ጥቂት እንደምትቆይ ለቤተሰቦቿ አንዲት ፣ሠራተኛና አንድ ሕፃን ብቻ አስቀርታ
ሌሎችን አሰናብታ ምናኔው ተጀመረ፣የወላድ መናኝ የሚያልፈውን በማያልፈው ዓለም ለመለወጥ ልጇን አዝላ እግሬ አውጭኝ ብላ ገሠገሠች።እግሮቿ በደም ታጠቡ፣የራስ ፀጒሯ ተላጭቶ ወደቀ።የገዳማውያን አለባበሷን ለብሳ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገባች።ማቴ 10÷37 በተግባር ላይ ሲተረጎም ተመለከትን።
✍️የተጋድሎ ሕይወቷ እየቀጠለ ኼዶ ከመከራዋ ብዛት ከገድሏ ጽናት ሰውነቷ ተበሳስቶ የዓሣ መመላለሻ እስኪሆን ድረስ ከባሕሩ ገብታ ወደ ግራና ቀኝ ሳትል ፲፪ ዓመት ሙሉ በጣና ባሕር ውስጥ ቆማ ትጸልይ ዘንድ ኃይለ እግዚአብሔር ተሰጣት።፲፪ ዓመት ሙሉ በባሕር ውስጥ መቆየት የሚቻለው ማነው? የሚል ጎደሎ እምነት ያለው ወገን ካለ: ባሕረ ኤርትራ እንደ ግድግዳ ቆሞላቸው እስራኤላውያን ማሻገር ይችላሉ ወይ?" ለሚያምን ሁሉ ይቻላል"(ማር 9÷22)
✍️መሴ በሲና ተራራ 40መዓልትና 40 ሌሊት ያለምግብ መቆየት ይችላል ወይ?ሠለስቱ ደቂቅ እሳት ውስጥ ገብተው ሳይቃጠሉ መውጣት ይችላሉ ወይ? ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን መጠየቁ የተሻለ ይሆናል።
✍️" ከአቤል ጀምሮ እስከ ዛሬ የሞቱት ከዛሬም በኋላ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚሞቱትን አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው "አለችው ( ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘግንቦት -ቊጥር፲፯ )
√ የአማላጅነት ጸጋዋ:
የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ሕይወት የቅድስና ሕይወት በመሆኑ ለአማላጅነት የተመቸ ነው።
✍️ጌታ ምን አደርግልሽ ዘንድ ትሻለሽ? አላት ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ " አቤቱ ፈጣሪየ ሆይ ! ፈቃድህስ ቢሆን የአዳም ልጆችን ከሥቃይ ከኵነኔ ይድኑ ዘንድ ዲያብሎስን ይቅር ትለው ወይም ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ:የኃጥእን መመለሱን እንጂ የጥፋቱን አትወድምና አለችው ፣ የምለምንህ ወይም ማረው የምልህ ዲያብሎስን ወድጄው አይደለም ነገር ግን እሱ ከተማረ በአዳም ልጆች ላይ ሥቃይና ኵነኔ ሊኖር አይችልም ብየ በመገመት ነው እንጂ " ( ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘግንቦት -ቊጥር36 -38 )ይህን ልመና ጌታችን የሚያስደንቅ ልመና ብሎታል።ይህ መልካም ሐሳብ የሚመነጨው የእምነት ፍቅር ካላቸው ሰዎች ልብ ውስጥ ብቻ ነው።
- የዲያብሎስን ተንኮል የሚያውቅ መድኃኔዓለም የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን የአማላጅነት ነጻነት አልገደበውም።
√ የተሰጣት ቃል ኪዳን
✍"ሥጋሽን እንደ እናቴ እንደ ድንግል ማርያም ሥጋ እቀድሰዋለሁ" ማለት የእመቤታችን ሥጋ በኅሊና አምላክ የተቀደሰ ሲሆን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ሥጋ ደግሞ በገድል ፣በትሩፋት ተቀጥቅጦ ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ያመልክታል።ነሐሴ 24 የዕረፍት መታሰቢያዋ ይከበራል።
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ወርቃማዋ ፎገራ(The Golden lans scape of Fogera) በደሴተ ጓንጉት ደብረ ምሕረት ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ክብረ በዓል ዓመታዊ በዓሏ በየዓመቱ ግንቦት ፲፪ ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡ከወረታ ከተማ በስተ ምዕራብ በኩል 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጣና ዳር ዋገጠራ ቀበሌ ትገኛለች ፡
- የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በረከቷ ፣ረድኤቷ ፣አማላጅነቷ አይለየን!
#ምንጭ
- ሐመር መጽሔት ግንቦት /ሰኔ 1997ዓ/ም
- ነገረ ቅዱሳን -፪ ( ገጽ-68)
- ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ(በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት- 1992ዓ/ም )
- ልሳነ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ ሚያዝያ 7ቀን 1993 ቁ 53
መ/ር ተመስገን ዘገዬ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገነተ ኢዩሱስ ገነተ ማርያም ቤተ ክርሰቲያን ሰባኬ ወንጌል !