ምን እንስራ?
ስራ መጀመር/መቀየር የሚፈልጉ ሰዎች የሚያነሷት ጥያቄ ናት። መልሷ እንደ ካፒታል መጠን፣ አከባቢ፣ የግለሰቡ ልምድ፣ እንደ ጊዜውና በሌሎች ምክንያቶች ቢወሰንም እኔ ከተመለከትኩበት አውድ ልጠቁማችሁ።
ምን ልስራ? ብላችሁ ስትጠይቁ አስከትላችሁ ማወቅ ያለባችሁ ከበድ ያለ ጥያቄ አለ። ሰው ምንድነው የሚፈልገው?
እኛ የመሰለንን፣ ወይም በህሊናችን የሳልነውን አሊያ ሌሎች ሰዎች በሌላ አከባቢ ሲሰሩት ያየነውን ለመስራት መጣደፍ ጉዳቱ/ኪሳራው ያመዝናል። ትንሽ ቆም ብለን ሰው/ተጠቃሚ/ ምንድነው የሚፈልገው? ብለን መጠየቅና በደንብ መገንዘብ፣ መለየት እንዲሁም ከተቻለ በቁጥርና በሙከራ የዳበረ መጠነኛ ጥናት ማድረግ ወሳኝ ነው።
እንደ ጥቅል ግን አብዛኛው ዝቅተኛና መሀከለኛ ገቢ ያለው ሰው አስማሚ ፍላጎቶች አሉት። የተወሰነውን ልጠቁማችሁ . . . .
1ኛ. ዕለታዊ ፍጆታ፦ ኑሮ እየተወደደ ነው። ውድነቱ በሁሉም መስክ ህዝቡን ሰቅዞ ይዞታል። ገበያ በሰአታት ልዩነት ይቀያየራል። በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ዋጋ እየናረ፣ በተቃራኒው በተለይ የተቀጣሪው ክፍያ እያደገ አይደለም። ስለዚህ ሰዎች ወጪያቸውን ለመቀነስ ይሞክራሉ። በተቻለ መጠን ለመኖር ወደሚገደዱበት ፍጆታ ይወሰናሉ። ስለዚህ በዚህ ጊዜ ስራ መስራት ያሰበ ሰው እለታዊ ፍጆታ ሽያጮች ላይ ቢያተኩር መልካም ይመስለኛል። ሸቀጥ፣ ምግብ ቤት፣ እህል ንግድ፣ ወጭ ቀናሽ አልባሳት የመሳሰሉትን ሊያካት ይችላል።
2ኛ. ርካሽ፦ ሰዎች እንደ ገቢያቸው ግዢያቸው ይወሰናል። ጥራትና ዋጋ ትይዩ ናቸው። በምንከፍለው ዋጋ ልክ ተመሳሳይ ምርት እንኳ ቢሆን የዋጋ ልዩነት አለው። ኑሮው ሲበረታ ሰዎች ጥራትን ከማማረጥ ይልቅ ዋጋ ላይ የበለጠ ትከረት ያደርጋሉ። ረከስ የሚል ነገር ይፈልጋሉ። ጥራቱ ዝቅተኛ የሆነ በርካሽ ዋጋ ለማቅረብ ከማሰብ ጥራቱ ሻል ያለ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ መንገዶችን ማሰብ የተሻለ ነው።
እንደ ነጋዴ ደግሞ ከገበያ ዋጋ ማርከስ የሚቻለው የግድ ጥራትን በመቀነስ ብቻ አይደለም። ምርታማነትን/አቅርቦትን በማሳደግ ወጪን መቀነስ ይቻላል፣ ጊዜያቶችን ጠብቆ በጅምላ በመግዛት ንረትን መቀነስ ይቻላል፣ የግዢ ሰንሰለቱን በማሳጠር(ደላላ፣ ወኪል አከፋፋይ. . . ) በመቀነስ ዋጋን ማሻሻል ይቻላል። በሌሎችም ምክንያቶች ወጪዎቻችንን በመቀነስ ከተፎካሪዎቻችን የተሻለ ዋጋ አድርገን ደንበኛ መሳብ እንችላለን።
3ኛ. ቅርብ፦ ከነዳጅ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የትራንስፓርት ዋጋ እየናረ ነው። አንዳንዴ ከእቃው ዋጋ በላይ ክፍያ የሚጠይቁ ትራንስፓርት ሰጪዎች አሉ። የሆነው ሆኖ የምንከፍተው ቢዝነስ በተቻለ መጠን ለሰዎች ተደራሽ የሚሆንበትን መንገድ ጎን ለጎን ማሰብ ይፈልጋል።
ለምሳሌ፦ ኹድራ(በድሬ ቋንቋ ነው😁፣ ሽንኩርት ቲማቲም፣ ድንች የመሳሰሉት የሚነግድ ነጋዴ አንድ ሰፈር ላይ የሚገዙ ሰዎችን አስተባብሮ በአንድ ትራንስፓርት(የትራንስፓርት ወጪው በራሱ የተሸፈነ) ቢያደርስላቸው ከሌላው ተፎካካሪ ነጋዴ እሱን ይመርጡታል! ለምን? ወጪ፣ ድካምና ሀሳብ ስለሚቀንስላቸው
ለምሳሌ በቅርቡ የጀመረውን "ሠረገላ" ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆነናል። እያልኩ ያለሁት Delivery Service ለብቻው ከፍ ባለ ክፍያ ስጡ ማለቴ ሳይሆን፣ የማድረሻ መንገዶችን ከተቻለ በነፃ ካልሆነም በዝቅተኛ ወጭ አድርሱ ነው። ሩቅ አድርጋችሁ አታስቡት . . . ይቻላል!
4ኛ. ጅምላ፦ ሸማች የብሩ ዋጋ ቀን በቀን ዋጋ እያጣበት ስለሚሄድና፣ የዋጋ ንረቱን ለመቋቋም ጅምላ ግዢ እየተበራከተ ይሄዳል። ስለዚህ በተቻለ መጠን ሰዎች በጅምላ ሲገዙ የዋጋ ቅናሽ ወይም ሌላ ልዩ ጥቅም ይፈልጋሉ። ስለዚህ በጅምላ ለሚገዙ ሰዎች የዋጋ ቅናሽ ወይም ፓኬጅ አሊያ ስጦታ ማዘጋጀትና ሰዎችን ማርካት ወሳኝ ነው።
5ኛ. ዱቤ፦ ዱቤ የለም የሚለው አባባል መስሪያ ጊዜው እየቆመ መሄዱ አይቀሬ ነው። ሰዎች ኑሮን ለማሸነፍ ተወደው ሳይሆን ተገደው ወደ ዱቤ ስርአት መግባታቸው አይቀርም። ለምን? ወጪያቸው ከገቢያቸው እየተመጣጠነ ካልሄደ የተከሰተውን የበጀት ጉድለት በምን ይሞሉታል። በዱቤ ነው! (መቼም በጉቦና ሙስና አትሉኝም!
ስለዚህ የደንበኞቻችንን የደንበኝነትና የታማኝነት ደረጃ በመለየት በጊዜያቶች የተገደበ የዱቤ አገልግሎት መስጠት ከሌላው ተመራጭ ያደርገናል። እንኳን እኛ ባንኮችም ይህ ጉድለት በጊዜ የተረዱት ይመስላል። ዳሽን ባንክ "ዱቤ አለ" የሚል አሰራር ጀምሯል፣ ቴሌብርም እንዲሁ አገልግሎት ስትፈፅሙ የጎደለባችሁን ይሞላል። ቡሀላ ከናንተው ቢወራረድም😁
እነዚህ አምስት ነገሮች የኑሮው ጫና የፈጠራቸው ናቸው። በመንግስት አያያዝ ደግሞ ኑሮው እየባሰ እንጂ እየቀለለ መሄዱን እንጃ፣ ስለዚህ ሀሰቦቹን ብናስተውላቸውነ ከራሳችን ጋር አርቀን ብናስኬዳቸው እላለሁ!
(ሀሳብ መስጠት ይቻላል!👍
https://t.me/EzedinSultan14