አይነ በሲሩ አፍቃሪ
ክፍል – 1
ደራሲና ተራኪ – አብዲ ኢኽላስ
ሱለይማን አይኖቹ ማየት የተሳናቸዉ የቀን ጨለማ የሆነበት ሰላሳዎቹን በማለፍ ላይ ያለ ለጉልምስና የተጠጋ ወጣት ነው። ሱለይማን ምንም እንዃ አይኖቹ ማየት ቢሳናቸው እንኳ ልቡ ግን በብርሃን የተሞላ ነው ።አብሶ ለመርየም ያለው ፍቅር በቃላት የሚገለፅ አይደለም ።ከሁሉ በላይ የሚዐጅበው መርየምን አንድም ጊዜ አሳይቱአት አያዉቅም እሷም አይታዉ አታውቅም ። ካናዳ ውስጥ ከሚገኝ አንድ ትልቅ ካምፓኒ ውስጥ ምትሰራው መርየም እጅግ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ በአስገራሚ ግጥምጥሞሽ ተዋውቃው እጅግ ሀያል በሆነ የፋቅር አክናፍ ውስጥ እየቀዘፉ ይገኛሉ ።
ሌላ ህይወት ሌላ አለም ፈጥረዉ በራሳቸው ምህዳር በራሳቸው ምህዋር ዉስጥ ሱለይማን ከመላው ቤተሰቡ ጋር በማያውቀው ሁኔታ ተቆራርጦአል እንዴት አንደሆነ እንኳን አያውቅም በቃ እሱ የሚያውቀው ነገር ቢኖር አንድ ሰሞን እጅግ ዉብ የነበረ ህይወት እንደነበረው ነው ።እጅግ የተዋበ ደስተኛ ቤተሰብ አንደነበረው ድንገት እንዴት እራሱን እዚህ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ትቢያ ከተሞላ ፉራሽ ውሰጥ ከወየበ ቲሸርትና ከአሮጌ ሱሪ እጅግ ከተጨራመተ ጫማና ደቃቃ ህይወት ውስጥ እንዳገኘው በፍፁም ማወቅ አልቻለም ። አይኖቹንም ቢሆን እንዴት እና ለምን እንዳጣቸው ማስታወስ ተስኖታል ያይ እንደነበር ግን ያዉቃል ።ይህን ማሰብ ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል። አሁን ግን በነዚህ ችግሮች ውስጥ ተተብትቦ ላይ ታቹን መባከን እንዲያቆም ከላይ ልዩ ስጦታ ተሰጥቶታል። መርየም በፍቅሯ አክናፍ በሀይል የነደደላት ቀንሌቱን ያለርሷ አልነጋልህ ያለው እጅግ ልዩ እና ውብ ፍቅር ውብ ፋጥረት።
መርየም እና ሱለይማን እጅግ የሚያስቀና የፍቅር አለም ውስጥ ናቸው ።በየቀኑ በየሰዓቱ በየደቂቃው ይደዋወላሉ የርሷን ድምፅ ለሰዓታት ሳይሰማ መቆየት አይችልም እሷም ብትሆን ስራ ስትገባ ስትቀመጥም ሆነ ስትነሳ ስትወጣ ትደውልለታለች በየደቂቃው ስልኩን ክፉት አድርጎ የሚጠብቀው የርሷን ስልክ ነው ከርሷ ዉጪ ምድር ላይ ሰው የሌለው እስኪመስለው ድረስ በርሷ አለም ዉስጥ ክፉኛ ተነድፎ ሌላ ነጎድጓድ ዉስጥ ነግዷል ስልኳ ሲጠራ ልክ ከአመታት በኋላ ገና እንደደወለችለት እንጂ ከትንሽ ሰአታት በፊት ያናገራት አይመስልም ልክ እንደ ህፃን ልጅ አመታትን ወደታች ቁልቁል ተጉዞ ይቦርቃል ይደሰታል የጥርሱ ፍልቅልቅታም ያኔ ፋንትው ብሎ ይታያል
አጃኢብ ያሰኛሉ ያስቀናሉም ጭምር መርየም እና ሱለይማን በጥቂት ጊዚያት እጅግ ውብ የሆነ ፍቅር
አሁን ትልቁ ችግር መርየም በቅርብ ለመምጣት ማቀዱአ ነው። ሱለይማን ደግሞ ከዛሬ ነገ እነግራታለሁ እያለ የአይኑን ማየት አለመቻል አልነገራትም። ብዙ ቀናት ዳር ዳር ቢልም እንኳን ልትረዳለት አልቻለችም ብዙ በተቀየጡና በተቀነባበሩ ቃላት ቢያወራት እንዃን ሀቁ ሊገባት አልቻለም እንዴት አድርጋ ማየት አይችልም ብላ ትመን እሷ እስትንፋሷ በሙሉ ሱለይማን ሆኑአል እሱም የሌት ቀን ህልሙ እሷ ሆናለች። ይፈቃቀራሉ የሚለው ቃል ለነሱ መጠቀም እንደ ስድብ ይቆጠራል ምክንያቱም ከዛም አልፈው ሩቅ ከተጓዙ ሰነባብተዋል እና ከመፈቃቀር አልፈዉ በስትንፋስ ደረጃ የአንዳቸው የመኖር ምከንያት እስኪመስሉ ድረስ ይፈላለጋሉ ከአቅም በላይ ሱለይማን ከገባበት እና ድንገት እንዴት እንደተፈጠረ ፍፁም ከማያውቀው ብቸኝነት ፍንትው አድርጋ ያወጣችውና ያለፈ ታሪኩን መርሳት ዳግም ያስረሳችው መርየም ነች ለርሷም ቢሆን አገር ቤት ያለውን ቆርጣ የጣለችውን ህይወቷን በብዙ ምክንያቶች ተተብትባ ከብዙ ችግሮች በኋላ አልፋ አልመለስበትም ያለችውን ሀገሯን ዳግም እንድትቃኝ አሰኛት ይኸውም የሱለይማን ፍቅር ነው።
ታዲያ በቅርብ ጊዜ ወደ እሱ ለመምጣት ማቀዷን ከነገረችው ጊዜ ጀምሮ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ይሰማዋል። አንዴ ደስ ይለዋል አንዴ ደግማ እንዳያጣት ይሰጋል። እጅግ የሚአጅበው ደግሞ ሱለይማን እስኪያያት ድረስ ነው የናፈቀው። ሱለይማን እኮ ማየት አይችልም ።ግና መጥታ በአይኑ እንደሚያያት ነው እየተሰማው ያለው አይቷት ፍቅሩን እንደሚጠግብ ናፍቆቱን እንደሚወጣ እየተሰማው ነው ። ግን እንዴት? እይታ በተነሱ አይኖቹ ሺ ጊዜ ቢመኛት እንኳን አይኑ ጨልሟል ሊያያት አይቻለውም። በልቡ ላይ የሳልትን ናት ብሎ ያሰባትን እሷን ያግኝ እንጂ መርየምም ብትሆን ሀገሬ ገብቼ የተውኩትን አለም ዳግም እኖረዋለሁ፣ የተበታተነብኝን እሰበስባለሁ ፣ ወደ ፍቅር ህይወቴ እመለሳለሁ ብላ ያሰበችው ምን አልባት አይኖቹ የሚያዩ እንጂ ማየት የተሳነውን ሱለይማንን አይደለም። እንዴት ትሁን ቅርብ አቅዳለች። ሱለይማን ከመርየም ስልክ ውጪ ሌላ ስልክጠራ ከተባለ የአንድ ሰው ብቻ ነው የኡማ ሀለውያ ። ኡማ ሀለውያ ሱለይማን ኸትሮ ሲጠራቸው ኡማ ብሎ ነው።በሀረሪ የሀደሬ ባህል ቋንቋ ኡማ እናቴ እንደማለት ነው።ታዲያ ትውልድ እና እድገታቸው የህይወት ረጅሙ ጉዟቸው ሀረር የሆኑት በነፃነትና በድፍረት የተሞሉት ኡማ በዚህ ሰአት አጠገቡ ያሉ ከጌታው ቀጥለው ብቸኛ አፅናኝ ናቸው። ኡማን ይወዳቸዋል።
ችግር ሲያጋጥመው፣ አንዳች ነገር ሲከፋው ፣ ውስጡ ድብርትና ባዶነት ሲሰማው ኡማ ጋር ሄዶ ይቀመጣል።
ይዘንብ የነበረው ዝናብ ጋብ በማለቱ አካባቢው ነግሶበት የነበረው ዝምታ በጩኸት ተሞልቷል። የመኪናና የሰው ጫጫታ አይሎ ይሰማል።ከተማው እንደወትሮው ሞቅ ደመቅ ማለት ጀመረ።ቀዝቀዝ ብላ የወጣችው ፀሀይ በሂደት ራሷን አሙቃ ለምድር ሙቀቷን መለገስ ጀምራለች ። ዝም እና ጭሽ ብሎ የነበረው የሰው እርምጃና ሩጫም በሰው ግርግር ተሞልቷል። ባልቴቶቹ ጥግጥጋቸውን ይዘው በዝናብና በበረዶ
በብርድ ለታሸው ሰው ትኩስ ነገር ማቅረብ ጀምረዋል። ችፕስ፣ የተቀቀለ ድንች እና ድንች ስኳር። ነጩን ድንች በሚጥሚጣ በቆሎን ጨምሮ ለሰው መቅረብ ጀምረዋል። ከሴቶቹ መሀከል ደግሞ አንዷ ኡማ ናቸው። ኡማ በቆሎ ይዘው ከቦታቸው ተሰይመዋል። ትኩስ በቆሎ ለበረደው ጥርስ ላለው ጥብስ ሊያቀርቡ የበቆሎ ጥብስ ።
ኡማ በገበያ አለም ውስጥ ሆነው በመሸጥ ላይ ሳሉ ድንገት አይናቸው ውስጥ አንዳች ነገር ገባ ብሌናቸው ላይ ሳይሆን እይታቸው ላይ ሱለይማን።
ሱለይማን በፍጥነት እየተራመደ ወደ እሳቸው ሲንደረደር ተመለከቱት። ደንግጠው 100ኪሎ የሚመዝነውን ከባድ ሰውነታቸውን ለማንሳት ከእጃቸውጋ መዳፋቸውን መሬት አሰደግፈው መታገሉን ተያያዙት ።
ኡማ ደንግጠዋል ምክንያቱም ሱለይማን ማየት ሳይችል እንኳ እየመጣ ያለው በፍጥነት ነው። ሱለይማን እንዲህ የሚመጣው ሁል ጊዜም በአንዳች ምክንያት ነው።ይኸውም መርየም ካልደወለችለት ። በየደቂቃው መደወል ያስለመደችው መርየም ዛሬ ከደወለች ሁለተኛ ቀኗን አስቆጥራለች። በነዚህ ሁለት ቀናት ለደቂቃም ቢሆንም እንኳን ሱለይማን እህል አልቀመሰም ፣ እንቅልፍ በአይኑ አላዞረም ፈገግ እንኳን አላለም። እዛች ደሳሳ ጎጆ ውስጥለብቻው ተቀምጦ የሷን መደወል በንቃት ሲከታተል ነበር።ትላንት እሁድ ስለነበር ኡማ አልመጡም ነበርና። የሚያወያየው ሰው አጥቶ ብቻውን በሀዘን ተቆራዶ ናፍቆቱን አሳለፈ። ዛሬ ግን እሳቸው ስለመጡለት የውስጡን ሊያወጋቸው እየተንደረደረ ወደሳቸው እየመጣ ነው ።