አይነ በሲሩ አፋቃሪ
ክፍል-2
ደራሲና ተራኪ- አብዲ አኽላስ
ሱለይማን አስፍልቱን ለመሻገር እየሞከረ ሳለ ሲኖትራኩ በፍጥነት ወደ እሱ ቀረበ:: በዚህ ጊዜ ነበር መርየም የደወለችለት ::ስልኩ እንደጠራ ባለበት ደርቆ ቀረ:: በፍጥነት ስልኩን አንስቶ በፈግታ ተሞልቶ በጉጉት ተንገብግቦ "ሄሎ" አላት:: በዚህ ጊዜ ማየት የተሳነው እንደሆነ የተረዳው የሲኖትራኩ ሹፌር በከፍተኛ ጥብና ስልት በውሀ የረጠበውን አስፍልት ሊንሸራተት ሳይሰጋ የአስፍልቱን ጥግ አስታኮ በፍጥነት አለፈው:: ኡማ ልባቸው አረፍ አለላቸው፣ፈገግ ለማለት ሞከሩ ሱለይማን ያለውን ታሪክ አያስተውለውም ክላክሱም በሀይል ከተማውን አደብልቆት ያለፈውን የሲኖትራክ ድምፅ እንኳን ለሱ ምንም አይደለም:: የመርየምን ድምፅ ሰምቷልእና መርየም ለሁለት ቀናት ያክል ድንገት በበላችው የተመረዘ ምግብ አማካኝነት ሆስፒታል እንደነበረች ነገረችው::
በእርግጥ ለሱለይማን እንኳን ከፍተኛ ህመሟን ቀርቶ ጉንፋኗን መንገር እንኳን ከባድ እንደሆነ ታውቃለች:: ግና ሁለት ቀን የጠፍችበትን ምክኒያት ቀለል ያለ ቢሆን ክፉኛ እንደሚጎዳ ተረድታለች:: ለዚህም እውነቱን መናገር መረጠች:: ሱለይማን በድንጋጤ ልቡ ራደ:: አሁን ስላለችበት ሁኔታ ደጋግሞ ደጋግሞ ጠየቃት ደህንነቷን ጠንከር ባለ መሀላ አረጋገጠችለት:: ያኔ ልቡ ተንፈስ አለ:: በእርጋታ ቁጭ ለማለት ሞከረ:: አላወቀውም አስፋልት ላይ ነበር:: ኡማ በፈገግታ ተሞልተው እንዴት ያለ ፍቅር ነው ሲሉ ተገርመው በአጃኢብ ስሜት ወደ አስፍልቱ ሄደው ሱለይማንን እጁን ይዘው ወደ ዳር አመጡና ከአጠገባቸው የረጠበ ድንጋይ ላይ ካርቶን አስደግፈው አስቀመጡት:: ይህን ጊዜ ማን ምን ያድርግለት፣ማን ወዴት ይውሰደው ፣ለምን ይዘውት መጡ፣ምን ተፈጥሮ ነው፣ ሱለይማን አያገባውም::
እሱ በሀሳብ ካናዳ ነጉዷል:: ከእሷ ጋር ሌላ ታሪክ ውስጥ ነው::ኡማ ይህንን ስለሚያውቁ አይደለም ሊወቅሱት ሰላም ሊሉት እንኳን ጊዜ ሊሻሙት አልፈለጉም:: ስራቸውን ቀጠሉ እሱም ስራውን ቀጠለ:: ከዚህ መንደር በ 2 ኪ· ሜ ርቀት የሚገኘው አንድ ፀጥ ያለ ሰፈር ወደ እዛ እንግባ አንድ መልካም፣እጅግ የተወደሰ ሰው ወዳለበት ወደነ አህመድ ሰፈር:: ሰፈሩ በሙሉ የእነ አህመድ ሰፈር ተብሎ ይጠራል:: አህመድ በሰፈሩ ላይ ታዋቂና እጅግ ተወዳጅ ሰው ነው:: በሀብት ማማ ላይ ጣሪያ የነካ ከመሆኑም በላይ እጅግ ቢዝነስ አዋቂና ተቋራጭ ስራዎችንና ጨረታዎችን በስልትና በጥበብ አሸናፊ ነው:: አይደለም የሰፈሩ ሰው የሩቆቹ እንኳን ወዳጅ ይቅርና ባላንጣ ጠላቶቹ ተፎካካሪዎች እንኳን ይመሰክሩለታል:: ጉምቱ የንግድ ሰው ነው:: እጅግ የተሳካለት እና ከአባቱ የወረሰውን የንግድ ጥበብና ከፍተኛ ገንዘብ አማክሎ የሀብት ማማ ላይ የተሰቀለ ታላቅ ሰው አህመድ መልከ መልካም እጅግ የተዋበ ቁመናና ተክለ ሰውነት የተላበሰ ወጣት ነው:: ለጋ ወጣት የመንደሩ ሰው ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለአህመድ ዱዐ ሳያደርግ አያልፍም:: እሱን ያልመረቀው አዛውንት ለሱ ዱዐ ያላደረገ ሹማምንት የለም::
ሁላቸውም የመስጂድ ኢማሞች ሳይቀሩ ያደርጉለታል::ይኸውም አህመድ የተሳካለት በጥበቡ እና በንግድ አዋቂነት ስልቱ ሳይሆን በሰጪ እና በለጋሽነት መሆኑ ን እራሱ ይመሰክራል:: ሁል ጊዜ ጁመዐ ጁመዐ የምግብ ሶደቃ የልብስና የቁሳቁስ እደላ ያደርጋል:: አህመድ ለነገዬ ብሎ ሳይሰጋ፣ ድህነትን ሳይፈራ፣ ማጣት ሳያስበረግገው መስጠትን ይሰጣል:: እጅግ አብዝቶ ፣ አትረፍርፎ ይሰጣል:: ከእቤቱ የገባ ሳይሞላለት አይወጣም:: የመንደሩ ሰው በህመም፣ በችግርም፣ በድግስም፣ በደስታውም ጊዜ አህመድን ይፈልጋል:: ለጎደላቸው ይሞላል:: ከዚህም አልፎ የተጣላን አስታራቂ ፣ የተጠራበት ሁሉ ኺያጅ ነው። አህመድ ከፍታ ላይ ሆኖ እንኳ ማንንም አይንቅም ለሁሉም ክብር ይሰጣል። እጅግ የተንጣለለ ውብ ቤቱ ውስጥ ድሆች ሲንጎራደዱበት ማየት የተለመደ ነው። በሩ በአደገኛ አጥር አይታጠርም፤ ለሁሉም ክፍት ነው ሁልጊዜም። ታዲያ አህመድ እነዚህ ሁሉ የተሟላ ውብ ስብዕናና ማንነቱ ጎን ግን አንዲት ደካማ ጎን አለችው።ይኸውም እስካሁን ድረስ ወደ ትዳር ታጭቶ አላገባም፣ አልወለደም ብቻውን እቤት ውስጥ ይኖራል፤ ከአገልጋይ(ኻዲሞች) ጋር በተደጋጋሚ እጅግ ብዙ ጊዜ ለሚስትነት የቀረቡ ሴቶች በህይወቱ ውስጥ መጥተው የነበሩ ቢሆንም እሱ ግን ዞር ብሎ ሊመለከት አልቻለም።
ለዚህ ብቸኛ ምክኒያቱ ደሞ ከቅርብ ጊዜ በፊት በሞት የተለዩት አባቱ ናቸው። አህመድ አባቱን ይወዳል፤ አሳምሮ ይወዳል።እናትም አባትም ሆነው ያሳደጉት ከትቢያ አቧራ ላይ ተነስተው እዚህ ማማ ላይ ያደረሱት አባቱ እጅግ ይወድ ነበር።እሳቸውን በሞት ካጣ ጊዜ ጀምሮ ውስጡ ሰላም ማግኘት አቅቶታል።አህመድ ለአባቱ የሚገባውን ማድረግ ችሏል፤ በሚገባ ኻድሟቸዋል፤ ጡሯቸዋልም ጭምር ግና የአባትን ሀቅ መክፈል ፍፁም አይቻልምና ለብዙዎች ብርቅ የሆነውን የ90 አመት የዕድሜ ባለፀጋነትን እንዲጎናፀፉና የመጨረሻ የእርጅና ደረጃ ላይ ቢደርሱም እንኳን አባት ናቸውና አልጠገባቸውም። ከዚህ ሁሉ እጅግ በዲን የተሞሉትና በአደብ ያነፁት እኚህ ውድ አባት አላህ ወደ ራሱ ሊወስዳቸው ህመምን አቅልሎ፤ ያለምንም የህመም ስሜት በድንገት ነውና አህመድ ሳያስበው ሳይሰናበቱት ቁጭት ቢጤ ከልቡ ተሰንቅሯል።በዚህም ምክኒያት ለማግባት ዕድል አላገኘም፤ ለራሱም ጊዜ አልሰጠም።ዛሬ ግን ቀኑ የደረሰ ይመስላል። የግቢው በር ተንኳኳ ጋሽ አክመል ናቸው፤ ጋሽ አክመል የዚህ ሰፈር ሰው አይደሉም፤ ጋሽ አክመል እጅግ የጠና እድሜ ላይ የሚገኙ፤ ከወገባቸው ጎበጥ ያሉ ፤ በእርጅና ጉስቁል ያሉ፤ አረንጓዴ ግን የድሮ እንደሆነ የሚያስታውቅ ሙሉ ሱፍና ከተጨራመተ ጫማ ጋር ተጫምተውት አማይማ ከላያቸው ላይ ጣል አርገው ከበሩ ተሰይመዋል።
ጥበቃው በፍጥነት ሄዶ ከፈተላቸው።አሉት"እንዴት ዋልክ ልጄ ይህ ቤት የአህመድ ቤት ነው"ሲሉ ጠየቁት፤ጥበቃውም"አዎን" አላቸው።ወደ ውስጥ እንዲገቡም ጋበዛቸው።አህመድ ጋር እንዲ ነው ማንም ከውጪ ሆኖ አይስተናገድም ውስጥ ድረስ እንዲዘልቅ ይፈቀድለታል። ወደ ውስጥ አስገባቸው። ጋሽ አክመል ብዙም ጆሮአቸው አይሰማም።ከርቀት ያለን ድምፅ መስማትና መለየት ይሳናቸዋል። እጅግ ከአጠገባቸው ካልሆነ በስተቀር ድምፅ የተነገራቸው አይለዩም። ጥበቃውም ወደ ክፍላቸው ይዟቸው ገባ።ከሳሎን ደረሱ ጋሽ አክመል የጥበቃው ፊት ላይ ያለችን ትንሽ ቁስል ተመልክተው ትኩረታቸውን እዛ አደረጉ። አይናቸውን አጨምጭመው ከተመለከቱት በኃላ እንዲ ሲሉ ጠየቁት"ፊትህ ላይ የወጣብህ ነገር ምንድነው ልጄ"? አሉት።አንድም የባህል ሀኪም ስለሆኑ ቁስል ባዩ ቁጥር አያልፉም። ጥበቃውም " አይ ሽፍታ ነው" አላቸው ቀለል አድርጎ። ጋሽ አክመል ግን የመስማት ችግር አለባቸውና "ሽፍታ ነው ያልከኝ የምን ሽፍታ ደግሞ የሚያቆስል ሽፍታ ከየት መጣ ከተማም ሽፍታ አለ እንዴ" አሉት።ዘበኛውም ደንገጥ ብሎ ወደ አጠገባቸው ቀርቦ"አይደለም ቁስል ነው ቁስል"አላቸው።