Репост из: وقل رب زدنى علما
‘ወህሃቢዩ’ ዘሩቅ
~~~
በሱፍያው ዓለም በሰፊው ከሚታዩ ጥፋቶች ውስጥ አንዱ በመቃብር ላይ የሚፈፀመው ድንበር ማለፍ ነው። በአሁኑ ጊዜ ይህንን ጥፋት የሚያወግዝን ሰው ልክ አዲስ ሃይማኖት እንዳመጣ ሰው “ወህሃቢ” ብለው ያወግዙታል። ያላስተዋሉት ወይም ሊያስተውሉ የማይፈልጉት ግን እነሱ እራሳቸው ከሚያወድሷቸው ቀደም ያሉ ዓሊሞች ውስጥ ይህንን ተግባር ያወገዙ መኖራቸው ነው።
ለዛሬ መጥቀስ የፈለግኩት አቡል ዐባስ አሕመድ ዘሩቅን ነው። ከማሊኪያ መዝሀብ ታዋቂ ምሁራን ውስጥ አንዱ ናቸው። እንደለመዱት “የሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ተከታይ ነው፣ ወህሃቢ ነው” በማለት እንዳይከሷቸው ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ከመወለዳቸው 216 ዓመታት ቀደም ብለው በ899 ሂ. የሞቱ ናቸው። ምን ነበር ያሉት? ይሄውና:-
«من البدع اتخاذ المساجد على مَقبرة الصالحين، ووقد القناديل عليه دائمًا، أو في زمانٍ بعينه، والتمسُّح بالقبر عند الزيارة، وهو من فعل النصارى، وحمل تراب القبر تبركًا به، وكل ذلك ممنوعٌ بل يَحرُم» اهـ.
“የደጋጎችን መቃብር የአምልኮ ቦታ አድርጎ መያዝ፣ በቋሚነት ወይም በሆነ በተገደበ ጊዜ በነሱ ላይ ሻማዎችን ማብራት እና በጉብኝት ጊዜ ቀብር ጋር መተሻሸት ከቢድዐዎች ውስጥ ናቸው። ይሄ የክርስቲያኖች ተግባር ነው። የቀብርን አፈር ለበረካ ብሎ መውሰድም እንዲሁ። ይሄ ሁሉ ክልክል እንዲያውም ሐራም ነው።”
[ሸርሑ ሪሳለቲል ቀይረዋኒ፣ ዘሩቅ: 1/434]
IbnuMunewor
https://t.me/wequl_Rebi_zidni_elmen