Reslan Ibnu Neja(asslefy)


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


እቺን ኡማ ምንም ነገር አያስተካክላትም የመጀመሪያዎቹን ያስተካከላቸው ነገር ቢሆን እንጂ (እነሱ ያስተካከላቸው ቁርአን ሀዲስን 'አልላህ ባዘዘበት ና መልእክተኛው ባስተማሩበት ተረድተው ስለተገበሩ ነው) ስለዚህ እኛ እንስተካከል ዘንድ ቁርአን ሀዲስን አልላህ ባዘዘበት መልእክተኛው ባስተማሩበት (ሰለፉነ ሷሊሆች) መልካም ቀደምቶች ተረድተው በተገበሩበት ተረድተው መተግበር ነው::አልላህ ይወፍቀን

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🌹ሰለፍያ እንስቶች🌹

ሰለፊያ እንስቶች፣
የሱና አበቦች፣
የዲናችን ጌጦች፣
የኢስላም ወዳጆች፣
የሀያዕ ንግስቶች፨
🌱🌱🌱🌱🌱🌱
እነሱ ማለትኮ...
ሀያዕ የለበሱ የውበት ብርድ ልብስ፣
ከወንድ ሲያወሩ አይደሉም ቅልስልስ፣
〰🥀〰🥀〰🥀〰🥀〰🥀〰
ጌጣቸውን ሸፋኝ የማይገላልጡ፣
ጅልባባቸውን ለብሰው ከቤት ሲወጡ፣
➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿
ፊታቸውን ሸፋኝ በውቡ ኒቃብ፣
ምግባራቸው ቆንጆ አኽላቃቸው ውብ፣
አጅነቢ አይቀርባቸው በዚህም ሰበብ፨
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
አቤት ሲያምርባቸው የሱና ጌጣቸው፣
ላለበሰው ሁሉ የሚያስቀኑ ናቸው፣

ደሞ ናቸውኮ ጠለበተል ዒልም፣
የማይሰላቹ ንቁ ምንጊዜም፣
☘〰☘〰☘〰☘〰
እርስ በራሳቸው የሚመካከሩ፣
ተናናሽም ናቸው አይደሉም ኩሩ

አልላህ ይይጠብቃቸው በያሉበት
Join⬇️⬇️⬇️join
Join us ⬇️⬇️⬇️join⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1


ታላቁ ዓሊም ሱፍያን አስ-ሰውሪይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-

"የቢዳዓ ባልተቤት ጋር የተቀማመጠ ከሶስት ነገር ባንዱ ሰላም አይሆንም

1, ወይ ለሌሎች ሰዎች ፊትና ይሆናል! (ይህ በብዛት በዚህ ጊዜ የሚስተዋለው ከባድ አደጋ ነው)

2, ወይ በልቦናው ላይ የሆነ ነገር ሊከሰት (ይችላል) በርሱ ምክኒያት ይጠምና አላህ እሳት ያስገባዋል

3, አልያም (ሙብተዲዕዎች) በተናገሩት ንግግር በአላህ ይሁንብኝ ደንታ የለኝም፣ እኔ በነፍሴ እተማመናለሁ፣ ይላል። አላህን ደግሞ የዐይን እርግብታ ያክል በዲኑ ላይ (ምንም አያደርገኝም በራሴ እብቃቃለሁ በማለት) የተማመነ (አላህ) ዲኑን ይቀማዋል።"

【አል–ኢዕቲሷም 1/130】

አኚህ ታላቅ ዓሊም ከቢዳዓ ሰዎች ጋር የሚቀማመጥን ሰው በነዚህ ሶስት ከባባድ አደጋዎች አስጠንቅቀዋል!!።

ስለዚህ:-
ከቢደዓ ባለቤቶች ጋር ከመቀማመጥ እራስህን እራስሽን ቆጥብ /ቢ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️join⬇️⬇️⬇️
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1


◆◇◆◇◆◇ بسم الله الرحمان الرحيم

🔶🔹سجود التلاوة🔹🔶

📚روى مسلم(81) عن أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم: «إِذَا قَرَأَ ابْنُ آدَمَ السَّجْدَةَ فَسَجَدَ، اعْتَزَلَ الشَّيْطَانُ يَبْكِي، يَقُولُ: يَا وَيْلَهُ! أُمِرَ ابْنُ آدَمَ بِالسُّجُودِ فَسَجَدَ فَلَهُ الْجَنَّةُ، وَأُمِرْتُ بِالسُّجُودِ فَأَبَيْتُ فَلِيَ النَّارُ».

▪️هذا الحديث فيه فضل سجود التلاوة .

📌وقد أجمع العلماء على مشروعية سجود التلاوة.

◆◇◆◇◆◇

🔹🔶حكم سجود التلاوة🔶🔹

🍂مستحب، وهذا قول جمهور العلماء، والدليل على ذلك حديث زَيْدِ بْنِ ثَابِتٍ رضي الله عنه أَنَّه قَرَأَ عَلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم: ﴿وَالنَّجْمِ﴾ فَلَمْ يَسْجُدْ.

📚قال الشيخ ابن باز رَحِمَهُ الله في «مجموع الفتاوى» (11/415): دل ذلك-أي: حديث زيد رضي الله عنه-على عدم وجوب سجود التلاوة؛ لأن النبي صلى الله عليه وسلم لم ينكر على زيد تركه. اهـ. ويحتمل أنه لم يسجد لما قرأ عليه زيد بن ثابت؛ لأن زيدًا كان هو القارئ، ولم يسجد. فلذلك لم يسجد رسول الله صلى الله عليه وسلم. «الاستذكار» (8/100).

📚وعَنْ عُمَرَ بْنِ الْخَطَّابِ رضي الله عنه أَنَّه قَرَأَ يَوْمَ الْجُمُعَةِ عَلَى الْمِنْبَرِ سُورَةَ النَّحْلِ، حَتَّى إِذَا جَاءَ السَّجْدَةَ، نَزَلَ فَسَجَدَ وَسَجَدَ النَّاسُ، حَتَّى إِذَا كَانَتِ الْجُمُعَةُ الْقَابِلَةُ قَرَأَهَا، حَتَّى إِذَا جَاءَ السَّجْدَةَ قَالَ: يَا أَيُّهَا النَّاسُ، إِنَّمَا نَمُرُّ بِالسُّجُودِ فَمَنْ سَجَدَ فَقَدْ أَصَابَ، وَمَنْ لَمْ يَسْجُدْ فَلَا إِثْمَ عَلَيهِ. وَلَمْ يَسْجُدْ عُمَرُ.

▪️هذا دليل ظاهر على أن سجود التلاوة غير واجب؛ لأن عمر بن الخطاب رضي الله عنه سجد في المرة الأولى ولم يسجد في الثانية.

🔻وذهب أبو حنيفة إلى الوجوب، واحتج بقوله تعالى: ﴿ فَمَا لَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ (20) وَإِذَا قُرِئَ عَلَيْهِمُ الْقُرْآنُ لَا يَسْجُدُونَ (21)﴾. وقد أجاب عن هذا الاستدلال الإمام النووي رَحِمَهُ الله، وقال: (وَأَمَّا الْجَوَابُ عَنِ الْآيَةِ الَّتِي احْتَجَّ بِهَا أَبُو حَنِيفَةَ رضي الله عنه فَظَاهِرٌ؛ لِأَنَّ المُرَادَ ذَمُّهُمْ عَلَى تَرْكِ السُّجُودِ تَكْذِيبًا، كَمَا قَالَ اللهُ تَعَالَى بَعْدَهُ: ﴿بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا يُكَذِّبُونَ﴾).

የተለያዩ ትምህርቶችን ለመከታተል
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ⬇️⬇️⬇️join us ⬇️⬇️⬇️⬇️

https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1


🎤 የሶሐባዎች መንገድ ለምን ?
ከሰለፍያ ዳዕዋ መርህ አንዱ ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች ( በሶሐባዎችን ) ግንዛቤ ወይም ፈህም መሰረት አድርጎ መጓዝ የሚል ነው ። ወይም የእነርሱን አካሄድ መከተል ነው ።
ይህ የሆነበት ምክንያት እነርሱ አላህ ዲኑን ሊያደርሱ የመረጣቸው አእምሮሯቸውን ንፁህ ፣ አንደበታቸው ሩቱእ ፣ የአገላለፅ ብቃት ያደላቸው ፣ ቁርኣንን እንደወረደ በነብዩ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ምላስ ያዳመጡና የተረዱ ፣ የነብዩ ባልደረባ ለመሆን የተመረጡ ፣ የዲን ዘቦች ፣ ሚንሃጃቸው ግልፅና ወጥ ፣ ግንዛቤያቸው እንከን የለሽ ፣ የአላህንና የነብዩን ፍላጎት ተረድተው የተገበሩ በመሆናቸው ነው ። ይህን አስመልክቶ ዐብዱላሂ ኢብኑ መስዑድ – ረዲየላሁ ዐንሁ – እንዲህ ይላል : –
يقول ابن مسعود – رضي الله عنه –
"إن الله نظر إلى قلوب العباد فوجد قلوب محمد – صلى الله عليه وسلم – خير قلوب العباد ، فاصطفاه لنفسه فابتعثه برسالته ، ثم نظر إلى قلوب العباد فوجد فوجد قلوب أصحابه خير قلوب العباد ، فجعلهم وزراء نبيه ، يقاتلون على دينه ، فما رأى المسلون حسنا فهو عند االه حسن، وما رأوه سيئا فهو عند الله سيء "
رواه إمام أحمد بسند حسن
مسند إمام أحمد ( 1 /379 )
" አላህ የባሮቹን ልብ ተመለከተ የሙሐመድን ልብ ምርጥ ሆኖ አገኘው ለራሱ መረጠውና በመልእክቱ ላከው, ከዛም የባሮቹን ልብ ተመለከተ የሶሐባዎችን ልብ ምርጥ ሆኖ አገኘው, በዲኑ ላይ የሚጋደሉ የመልእክተኛው አማካሪ ( ሚኒስቴር ) አደረጋቸው ። እነርሱ መልካም ነው ያሉት እሱ አላህ ዘንድ መልካም ነው ። እነርሱ መጥፎ ነው ያሉት እሱ አላህ ዘንድ መጥፎ ነው ። "
ከዛም እንዲህ አለ : –
" من كان منكم مستننا فاليستن بمن قد مات ، فإن الحي لا تؤمن عليه الفتنة ، أولئك أصحاب محمد – صلى الله عليه وسلم – كانوا أفضل هذه الأمة ، وأبرها قلوبا ، وأعمقها علما ، وأقلها تكلفا ، قوم اختارهم الله لصحبة نبيه، فاعرفوا لهم فضلهم، واتبعوا في آثارهم، وتمسكوا بما استطعتم من أخلاقهم ودينهم ، فإنهم كانوا على الهدى المستقيم "
انظر المصدر السابق
" ከናንተ ውስጥ ፈለግ ማድረግ የፈለገ በሞቱት ሰዎች ፈለግ ያድርግ ። በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትምና ። እነዚያ የነብዩ ባልደረቦች ናቸው ። የዚህ ኡመት በላጮች ነበሩ ፣ ልባቸው የጠራ ፣ እውቀታቸው የጠለቀ ፣ በማያውቁት ነገር ላይ መጨነቃቸው የቀነሰ ፣
ሰዎች ናቸው አላህ ለመልእክተኛው ባልደረብነት ዲኑን ለማቆም የመረጣቸው ። ደረጃቸውን እወቁላቸው ። ፋናቸውን ተከተሏቸው ። በዲናቸውና በስነምግባራቸው የቻላችሁትን ያዙላቸው ። እነርሱ ቀጥ ባለ ጎዳና ላይ ነበሩ ። "
እነዚህ ናቸው ሞዴላችን ፋናቸውን እንድንከተል የታዘዝነው ። አላህ እነሱን ተከትለው ከእነርሱ ጋር ከሚቀሰቀሱት ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka


አሰለፍያ;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;

ጥርት ያልሽ እውነታ ነሽ።
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;

የነብያት ጥሪ የቀደምቶች ፋና፡
እኔስ እኖራለው
ባንቺው ሰለፍያ በነብዩ ሱና፡
የጠራሽ ነሽ ከቢደአት፡
እንደዚሁም ከኹራፋት፡
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ከየትኛውም ያልተደመርሽ፡
ሰለፍያ ጥርት ያልሽ እውነታ ነሽ።
የሰለፎችን መንገድ የያዝሽ፡
ተአጀብን ባንቺው በመንገድሽ፡
ከቢደአት ከኹራፋት ከሙብተዲዕ የነፃሽ፡
ሰለፍያ ጥርት ያልሽ እውነታ ነሽ።

ቻናላችን ይቀላቀሉ ⬇️⬇️⬇️ ioin
⬇️⬇️ join ⬇️⬇️⬇️

https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1


💢ኒቃብ ከለበስኩ ትዳር አላገኝም⁉️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

ኒቃብ ላለመልበስ የሚቀርቡ ተልካሻ ምክንያቶች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

🍃ኒቃብ ከለበስኩኝ ባል አላገኝም፣ ስራ አላገኝም፣ ሰዎች ይጠሉኛል፣ ሰዎች ያርቁኛልና የመሳሰሉ ምክንያቶችን በመደርደር ከኒቃብ የሚዘናጉ ብዙ እህቶች አሉ። ይህ ሊቀረፍ የሚገባ የተሳሳተና ውድቅ የሆነ አባባል ነው።

🍃ኒቃብ መልበስ አላህን ከመታዘዝ እንዲሁም የመልእክተኛውን ሱና ህያው ከማድረግ የሚቆጠርና የሴት ልጅ ንፅህናዋንና ክብሯን ከሚጠብቁ ከታላላቅ ሸሪአዊ ተግባሮች ውስጥ የሚመደብ ታላቅ ሸሪአዊ ትእዛዝ ነው። ታዳ በምን ሂሳብ ነው ኒቃብ በመልበስ የአላህንና የመልእክተኛውን ትእዛዝ መፈፀም የትዳርን በር ሊዘጋ የሚችለው? ኧረ እንዴት ብሎ ነው ሪዝቅን ሊከለክል የሚችለው?

🍃እንደውም ነገሩ አንቺ ከምታስቢው በተቃራኒ ነው፦ ኢማን ያለው፣ የተውሂድ ባለቤትና ሱና ወዳድ የሆነ ባል ኒቃብሽን፣ ጥቡቅነትሽንና ጨዋነትሽ አይቶ ነው የሚመጣው።

🌹ከዚህ ፍራቻና ብዥታ የተነሳ አንዳንድ እህቶች ኒቃብ የመልበስ ፍላጎቱ እያላቸው ራሱ ለምን አትለብሱም ሲባሉ ከትዳር በኋላ ነው የምለብሰው ይላሉ።

🍃ነገር ግን ይህ አመለካከት ከሸይጧን ጉትጎታ የመነጨ እንጂ ሌላ ምንም አይደለም። እንደሚታወቀው ሸይጧን አላህን እንዳንታዘዝ የተለያዩ ምክንያቶችን በማምጣት ያዘናጋናል አልፎም ያስፈራራናል። ብዙ ሴቶችም ይህንን የሸይጧን ማስፈራሪያ በመስማት ከኒቃብ ርቀውና ተዘናግተው ይታያሉ።

🍃እውነታው ግን ወዲህ ነው፦ ሶላት መስገድሽ፣ ቁርአን መቅራትሽ የሲሳይ በር ቢከፍትልሽ እንጂ ሪዝቅሽን ወይም አላህ ላንቺ የወሰነልሽን ነገር በፍፁም ሊያሳጣሽ አይችልም። ልክ እንደዚሁ የአላህን ውዴታ ፈልገሽ ሰዎችን ከመፈተንና ራስሽንም ከመፈተን ለመራቅ አስበሽ ኒቃብ መልበስሽ የኸይር በር ቢከፍትልሽ እንጂ በፍፁም አይዘጋብሽም።

🌹አላህ ሱብሀነሁወተአላ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ብሎ ቃል ገብቶልሻል
◾️وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا
💧አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ በነገራቶች ላይ መውጫ ቀዳዳን ያበጅለታል፡፡
◾️وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ ۚ وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ
💧እንዲሁም ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይለግሰዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡
◾️وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مِنْ أَمْرِهِ يُسْرًا
💧አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ መግራትን ያደርግለታል፡፡
◾️وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يُكَفِّرْ عَنْهُ سَيِّئَاتِهِ وَيُعْظِمْ لَهُ أَجْرًا
💧አላህንም የሚፈራ ሰው ኀጢኣቶቹን ከእርሱ ይሰርዝለታል፡፡ ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል፡፡

🌹 አብሽሪ ኒቃብን ልበሺ አትፍሪ ኒቃብና ኒቃቢስቶች አስመልክቶ የሚወራውና የሚሰማው ሁሉ ውሸት ነው። ኒቃብ ያለው ክብር፣ ልቅናና ጥፍጥና የቀመሱት እህቶች ይንገሩሽ። በዚህ በጥቁር ኒቃብ ውስጥ የጌታሽ ውዴታ፣ የክብርሽ ማማ፣ የጥቡቅነትሽ አርማ፣ የታማኝነትሽ ማሳያ፣ የታዛዥነትሽ ድካ የቀደምት የሶሀብያቶች ተምሳሌት መከተል አለበትና ዛሬውኑ ልበሺ።

ቻናላችን ይቀላቀሉ ⬇️⬇️⬇️ ioin
⬇️⬇️ join ⬇️⬇️⬇️

https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1


ኡሉል ዐዝም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

46፥35 *"ከመልእክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ"*፡፡ فَاصْبِرْ كَمَا صَبَرَ أُولُو الْعَزْمِ مِنَ الرُّسُلِ

አምላካችን አሏህ ወደ መጀመሪያው ነቢይ ወደ አደም ወሕይን አውርዷል፥ ግን አደም አሏህ አትብላ ያለውን በመርሳት ቆራጥነትን አልተገኘበትም፦
20፥115 *"ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ ረሳም፡፡ ለእርሱም ቆራጥነትን አላገኘንለትም"*፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَا إِلَىٰ آدَمَ مِن قَبْلُ فَنَسِيَ وَلَمْ نَجِدْ لَهُ عَزْمًا

"ዐዝም" عَزْم ማለት "ቆራጥነት" ማለት ነው። ዩኑሥ ከአሏህ መልእክተኞች መካከል አንዱ ነው፥ በትእግስት ቆራጥነት ስላልታየበት፦ "እንደ ዓሣው ባለቤትም አትኹን" የሚል መመሪያ አለ፦
37፥139 *"ዩኑሥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው"*፡፡ وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
68፥48 *"ለጌታህም ፍርድ ታገሥ! እንደ ዓሣው ባለቤትም አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ ጌታውን በተጣራ ጊዜ"*፡፡ فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ الْحُوتِ إِذْ نَادَىٰ وَهُوَ مَكْظُومٌ

"ኡሉል ዐዝም" أُولُو الْعَزْمِ ማለት "የቆራጥነት ባለቤት" ማለት ሲሆን ከአሏህ መልእክተኞች መካከል "የቆራጥነት ባለቤት" የተባሉት መልእክተኞች የትእግስት ምሳሌ ስለሚሆኑ፦ "ከመልእክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ" የሚል መመሪያ አለ፦
46፥35 *"ከመልእክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ"*፡፡ فَاصْبِرْ كَمَا صَبَرَ أُولُو الْعَزْمِ مِنَ الرُّسُلِ

"ረሡል" رَسُول ማለት "መልእክተኛ" ማለት ሲሆን "ሩሡል" رُّسُل ማለት ደግሞ "መልእክተኞች" ማለት ነው፥ "ሩሡል" ከሚለው ቃል በፊት "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ በራሱ "ኡሉል ዐዝም" የተባሉት ሁሉም መልእክተኞች ሳይሆኑ በከፊል መሆናቸውን ጉልኅ ማሳያ ነው። እነዚህም "ኡሉል ዐዝም" የሚባሉት መልእክተኞች ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሣ፣ ዒሣ እና ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ናቸው፥ አሏህ ከእነዚህ የቆራጥነት ባለቤት መልእክተኞች ጋር የከበደን ቃል ኪዳን አድርጓል፦
33፥7 *"ከነቢዮችም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሣም ከመርየም ልጅ ዒሳም በያዝን ጊዜ አስታወስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን"*፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا
42፥13 *"ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፣ ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን፣ ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን፣ ሙሳን እና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን ደነገግን"*፡፡ شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ

“ፈድል” فَضْل የሚለው ቃል “ፈዶለ” فَضَّلَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስጦታ” “ችሮታ” “ጸጋ”Bounty” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በደረጃ በማብለጥ የተለያየ ፈድል ሰቷቸዋል፦
2፥253 *"እነዚህን መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፥ ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አለ፡፡ ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ"*፡፡ تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۘ مِّنْهُم مَّن كَلَّمَ اللَّهُ ۖ وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَاتٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አበለጥን" ለሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል "ፈደልና" فَضَّلْنَا ሲሆን ፈድል በመስጠት ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በደረጃ ማብለጡን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ነገር ግን የተሰጣቸው ፀጋ የራሳቸው ስላልሆነ እኛ አንዱን መልእክተኛ ከሌላው መልእክተኛ ሳንለይ በሁሉም መልእክተኞች መልእክት እናምናለን፦
4፥152 *"እነዚያም በአላህ እና በመልክተኞቹ ያመኑ፣ ከእነርሱም በአንድም መካከል ያለዩ እነዚያ ምንዳዎቻቸውን በእርግጥ ይሰጣቸዋል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው"*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ وَلَمْ يُفَرِّقُوا بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ أُولَـٰئِكَ سَوْفَ يُؤْتِيهِمْ أُجُورَهُمْ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 87, ሐዲስ 54
አቡ ሠዒድ 4ንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በነቢያት መካከል አታማርጡ"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تُخَيِّرُوا بَيْنَ الأَنْبِيَاءِ ‏"‌‏.‏

አምላካችን አሏህ ከመልእክተኞች የቆራጥነት ባለቤቶች ከሆኑት ጋር መልካም ጎረቤት ያርገን! አሚን።
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1


በይቱል መቅዲሥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥71 *”እርሱን(ኢብራሂምን) እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረክናት ምድር በመውሰድ አዳን”*፡፡ وَنَجَّيْنَاهُ وَلُوطًا إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا لِلْعَالَمِينَ

ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት በመካህ አገር ውስጥ ይገኛል፥ ይህም የአሏህ ቤት “በይቱል ሐረም” بَيْت الْحَرَام ማለትም “የተቀደሰው ቤት” ወይም “የተከበረው ቤት” ይባላል፦
3፥96 “ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክ እና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ ያለው ነው”፡፡ إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَالَمِينَ
14፥37 «ጌታችን ሆይ! እኔ *"አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤትክ አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ"*፡፡ رَّبَّنَا إِنِّي أَسْكَنتُ مِن ذُرِّيَّتِي بِوَادٍ غَيْرِ ذِي زَرْعٍ عِندَ بَيْتِكَ الْمُحَرَّمِ

ይህንን ቤት መሠረት ጥሎ የመሠረተው ኢብራሂም ነው፥ ይህ ቤት ያለበትን አገር መካን የቀደሰውም እርሱ ነው፦
2፥127 *ኢብራሂምና ኢስማኢልም* «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ *"ከቤቱ መሠረቱን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 69
የነቢዩ"ﷺ" ባልተቤት ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ለእርሷ፦ *"የአንቺ ሕዝብ(ቁረይሽ) ከዕባህን ሲገነቡ በኢብራሂም በተመሠረተው እንዳልገነቧት ታውቂያለሽ? አሏት። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنهم ـ زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ لَهَا ‏"‏ أَلَمْ تَرَىْ أَنَّ قَوْمَكِ لَمَّا بَنَوُا الْكَعْبَةَ اقْتَصَرُوا عَنْ قَوَاعِدِ إِبْرَاهِيمَ ‏"‌‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 15, ሐዲስ 521
ጃቢር እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ኢብራሂም መካን ቀድሷል፥ እኔም መዲናን ቀድሻለው”። عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ حَرَّمَ مَكَّةَ وَإِنِّي حَرَّمْتُ الْمَدِينَةَ

"ቀዋዒድ" قَوَاعِد ማለት "መሠረት" ማለት ሲሆን ኢብራሂም የዚህ ቤት መሥራች መሆኑን ፍትው እና ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ በተጨማሪም “ሐረመ” حَرَّمَ የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! “ሐረመ” حَرَّمَ ማለት “ቀደሰ” ወይም “አከበረ” ማለት ሲሆን ይህም ቤት “በይቱል ሐረም” بَيْت الْحَرَام ይባላል። ከዚያም አምላካችን አሏህ ኢብራሂምን በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረክናት ምድር ወደ ሻም ወሰደው፦
21፥71 *”እርሱን(ኢብራሂምን) እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረክናት ምድር በመውሰድ አዳን”*፡፡ وَنَجَّيْنَاهُ وَلُوطًا إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا لِلْعَالَمِينَ

“መሥጂድ” مَسْجِد የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ሰገደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መስገጃ” "ማምለኪያ" ማለት ሲሆን “ሡጁድ” سُّجُود ደግሞ “ስግደት” ማለት ነው፥ የጥንት ሰዎች መሥጂድ አርገው የሚሠሩት ድንኳን ነበር። በኢብራሂም መካህ የተመሠረተው የመጀሪያው መሥጂድ “አል-መሥጂዱል ሐረም” الْمَسْجِدِ الْحَرَام ማለትም “የተከበረ ወይም የተቀደሰ መሥጂድ” ሲሆን ሁለተኛው መሥጂድ ደግሞ በሻም ምድር በኢብራሂም የተመሠረተው “አል-መሥጂዱል አቅሷ” الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى ማለትም “የሩቅ መሥጂድ” ነው። በሁለቱ መሣጂድ ምሥረታ መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት 40 ዓመት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 45
አቢ ዘር ሰምቶ እንደተረከው፦ “እኔም፦ ”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በምድር ላይ መጀመሪያ የተመሠረተው የትኛው መሥጂድ ነው? አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል ሐረም” አሉ። እኔም፦ “ከዚያስ ቀጥሎ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል አቅሷ” አሉ። እኔም፦ “በሁለቱ መካከል ምን ያህል የጊዜ ልዩነት አለ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አርባ ዓመት” አሉ”። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَىُّ مَسْجِدٍ وُضِعَ فِي الأَرْضِ أَوَّلُ قَالَ ‏”‏ الْمَسْجِدُ الْحَرَامُ ‏”‌‏.‏ قَالَ قُلْتُ ثُمَّ أَىٌّ قَالَ ‏”‏ الْمَسْجِدُ الأَقْصَى ‏”‌‏.‏ قُلْتُ كَمْ كَانَ بَيْنَهُمَا قَالَ ‏”‏ أَرْبَعُونَ سَنَةً،

“ዉዲዐ” وُضِعَ ማለት “ተመሠረተ” ማለት ነው፥ ከዚያም አምላካችን አሏህ ዙሪያውን በባረከው በሁለተኛው የሩቁ መሥጂድ ላይ ሱለይማን ሕንጻ አል-በይቱል መቅዲሥ ገነባ፦
34፥13 ”ከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል”፡፡ አልናቸውም፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ

ቻናላችን ይቀላቀሉ ⬇️⬇️⬇️ ioin
⬇️⬇️ join ⬇️⬇️⬇️
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1




يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው፡፡
[ ሱረቱ አል- ጁሙዓህ - 9 ]

فَإِذَا قُضِيَتِ الصَّلَاةُ فَانتَشِرُوا فِي الْأَرْضِ وَابْتَغُوا مِن فَضْلِ اللَّهِ وَاذْكُرُوا اللَّهَ كَثِيرًا لَّعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡
[ ሱረቱ አል- ጁሙዓህ - 10 ]

وَإِذَا رَأَوْا تِجَارَةً أَوْ لَهْوًا انفَضُّوا إِلَيْهَا وَتَرَكُوكَ قَائِمًا ۚ قُلْ مَا عِندَ اللَّهِ خَيْرٌ مِّنَ اللَّهْوِ وَمِنَ التِّجَارَةِ ۚ وَاللَّهُ خَيْرُ الرَّازِقِينَ

ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተዉህ ሲኾኑ ወደእርሷ ይበተናሉ፡፡ አላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው፡፡ «አላህም ከሰጪዎቹ ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጭ ነው» በላቸው፡፡
[ ሱረቱ አል- ጁሙዓህ - 11 ]

ተጨማሪ መረጃዎችን ከታች ያገኛሉ!!!
➷➴➘👇👇👇↙️↙️↙️


أقوال ﺃﺋﻤﺔ ﺍﻟﻌﺼﺮ ﻓﻲ ﻓﺮﻗﺔ ﺍﻹﺧﻮﺍﻥ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﺍﻟﻬﺎﻟﻜﺔ ﻭ ﺃﻧﻬﻢ ﻟﻴﺴﻮﺍ ﻣﻦ
ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﻭ ﺍﻟﺠﻤﺎﻋﺔ
ﻓـﺮﻗـﺔ ﻫـﺎﻟـﻜـﺔ ... ﻗـﺎﻟـﻬـﺎ ﺍﺑﻦ ﺑﺎﺯ
ﻭﻏـﺎﻳﺘﻬﺎ ﺍﻟﺴﻠﻄﺔ ... ﻗﺎﻟﻬﺎ ﺍﻟﺠﺎﻣﻲ
ﻭﻫﻢ ﻣـﺒـﺘـﺪﻋـﺔ ... ﻗﺎﻟﻬﺎ ﺍﺑﻦ ﻋﺜﻴﻤﻴﻦ
ﻭﻻ ﻳﻌﺮﻓﻮﻥ ﻣﻦ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﺇﻻ ﺍﻟﻬﺘﺎﻓﺎﺕ ...
ﻗﺎﻟﻬﺎ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ
----------------------------
ﻗﺎﻝ ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺍﺑﻦ ﺑﺎﺯ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ :
" ﺣﺮﻛﺔ ﺍﻹﺧﻮﺍﻥ ﻳﻨﺘﻘﺪﻫﺎ ﺧﻮﺍﺹ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﻌﻠﻢ ، ﻓﻬﻲ ﻻ ﺗﺪﻋﻮﺍ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺘﻮﺣﻴﺪ ،
ﻭﻻ ﺗﺤﺬﺭ ﻣﻦ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﻭﺍﻟﺒﺪﻉ ، ﻭﻻ ﺗﻌﺘﻨﻲ ﺑﺎﻟﺴﻨﺔ ".
ﻭﻗﺎﻝ : " ﺟﻤﺎﻋﺔ ﺍﻹﺧﻮﺍﻥ ﻭﺍﻟﺘﺒﻠﻴﻎ ﻣﻦ ﺍﻟﺜﻨﺘﻴﻦ ﻭﺍﻟﺴﺒﻌﻴﻦ ﻓﺮﻗﺔ ﺍﻟﻬﺎﻟﻜﺔ ".
----------------------------
* ﻭﻗﺎﻝ ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ :
" ﻟﻴﺲ ﺻَﻮَﺍﺑًﺎ ﺃَﻥ ﻳُﻘَﺎﻝَ ﺃﻥَّ ﺍﻹِﺧْﻮَﺍﻥ ﺍﻟﻤُﺴْﻠِﻤِﻴﻦ ﻣِﻦْ ﺃَﻫْﻞِ ﺍﻟﺴُﻨّﺔ ﻷَﻧَّﻬُﻢ
ﻳُﺤﺎﺭِﺑُﻮﻥَ
ﺍﻟﺴُﻨَّﺔ ".
ﻭﻗﺎﻝ : " ﺿﺮﺭ ﺍﻹﺧﻮﺍﻥ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﺃﻛﺒﺮ ﻣﻦ ﺍﻟﻴﻬﻮﺩ " .
-------------------------------
ﻭﻗﺎﻝ ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺣﻤّﺎﺩ ﺍﻷﻧﺼﺎﺭﻱ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ :
" ﺇﻥ ﺍﻹﺧﻮﺍﻥ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﻣﻦ ﺃﻧﺼﺎﺭ ﺍﻟﺨﻤﻴﻨﻲ ﻭﺍﻟﺮﻭﺍﻓﺾ ".
ﺍﻟﻤﺠﻤﻮﻉ : ‏( 699/2 ‏) .
-------------------------------
ﻭﻗﺎﻝ ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺻﺎﻟﺢ ﺍﻟﻠﺤﻴﺪﺍﻥ - ﺣﻔﻈﻪ ﺍﻟﻠﻪ -:
"ﺟﻤﺎﻋﺔ ﺍﻻﺧﻮﺍﻥ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﺩﻋﻮﺗﻬﻢ ﺳﻴﺎﺳﻴﺔ ﻭ ﻟﻴﺴﻮﺍ ﺩﻋﻮﺓ ﺳﻠﻔﻴﺔ
ﺻﺤﻴﺤﺔ ".
-------------------------------
ﻭﻗﺎﻝ ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺍﻟﻤﺤﺪﺙ ﺃﺣﻤﺪ ﺷﺎﻛﺮ – ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ - ﻓﻲ ﺟﻤﺎﻋﺔ
ﺍﻹﺧﻮﺍﻥ :
" ﺣﺮﻛﺔ ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺣﺴﻦ ﺍﻟﺒﻨﺎ ﻭﺇﺧﻮﺍﻧﻪ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﻗﻠﺒﻮﺍ ﺍﻟﺪﻋﻮﺓ
ﺍﻹﺳﻼﻣﻴﺔ ﺇﻟﻰ ﺩﻋﻮﺓ ﺇﺟﺮﺍﻣﻴﺔ ﻫﺪﺍﻣﺔ ، ﻳﻨﻔﻖ ﻋﻠﻴﻬﺎ ﺍﻟﺸﻴﻮﻋﻴﻮﻥ ﻭﺍﻟﻴﻬﻮﺩ
ﻛﻤﺎ ﻧﻌﻠﻢ ﺫﻟﻚ ﻋﻠﻢ ﺍﻟﻴﻘﻴﻦ " .
‏[ ﺍﻟﻤﺼﺪﺭ : ﺷﺆﻭﻥ ﺍﻟﺘﻌﻠﻴﻢ ﻭﺍﻟﻘﻀﺎﺀ، ﺹ 48 ‏]
-------------------------------
ﻭﻗﺎﻝ ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺻﺎﻟﺢ ﺁﻝ ﺍﻟﺸﻴﺦ :
" ﺟﻤﺎﻋﺔ ﺍﻹﺧﻮﺍﻥ ﻻ ﻳﺤﺘﺮﻣﻮﻥ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﻭﻻ ﻳﺤﺘﺮﻣﻮﻥ ﺃﻫﻠﻬﺎ ، ﻭﻫﻢ ﺃﺻﺤﺎﺏ
ﺗﻠﻮﻥ ﻭﺍﻟﻐﺎﻳﺔ ﻋﻨﺪﻫﻢ ﺍﻟﻮﺻﻮﻝ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺴﻠﻄﺔ ".
-------------------------------
ﻭﻗﺎﻝ ﻣﺤﺪﺙ ﺍﻟﺪﻳﺎﺭ ﺍﻟﻴﻤﻨﻴﺔ ﺍﻹﻣﺎﻡ ﻣﻘﺒﻞ ﺍﻟﻮﺍﺩﻋﻲ - ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ - :
" ﻭﻟﺴﻨﺎ ﻧﺘﻜﻠﻢ ﻓﻲ ﺍﻹﺧﻮﺍﻥ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﻷﻧّﻬﻢ ﻳﺤﻠﻘﻮﻥ ﻟﺤﺎﻫﻢ ، ﻓﻔﻲ
ﺍﻟﺸﻌﺐ ﺍﻟﻴﻤﻨﻲ ﻣﻦ ﻫﻮ ﺷﺮ ﻣﻨﻬﻢ، ﻭﻻ ﻷﻧّﻬﻢ ﻳﻠﺒﺴﻮﻥ ﺍﻟﺒﻨﻄﻠﻮﻥ، ﻓﻔﻲ
ﺍﻟﺸﻌﺐ ﺍﻟﻴﻤﻨﻲ ﻣﻦ ﻫﻮ ﺷﺮ ﻣﻨﻬﻢ، ﻟﻜﻦ ﻧﺘﻜﻠﻢ ﻓﻴﻬﻢ ﻷﻧّﻬﻢ ﻳﻠﺒّﺴﻮﻥ ﻋﻠﻰ
ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺑﺎﺳﻢ ﺍﻹﺳﻼﻡ، ﻭﻳﺤﺎﺭﺑﻮﻥ ﺩﻋﻮﺓ ﺇﺧﻮﺍﻧﻬﻢ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺴﻨﺔ، ﻭﻛﺬﻟﻚ ﺩﻋﻮﺓ
ﺃﺻﺤﺎﺏ ﺟﻤﻌﻴﺔ ﺍﻟﺤﻜﻤﺔ ﺃﺻﺒﺤﺖ ﺗﺘﻌﺎﻭﻥ ﻣﻊ ﺍﻹﺧﻮﺍﻥ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﻋﻠﻰ ﺃﺫﻳﺔ
ﺷﺒﺎﺏ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺴﻨﺔ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ ﻳﻘﻮﻝ : { ﻭﺗﻌﺎﻭﻧﻮﺍ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﺒﺮّ ﻭﺍﻟﺘّﻘﻮﻯ
ﻭﻻ ﺗﻌﺎﻭﻧﻮﺍ ﻋﻠﻰ ﺍﻹﺛﻢ ﻭﺍﻟﻌﺪﻭﺍﻥ }.
ﻭﺍﻟﺬﻱ ﻳﺴﺎﻋﺪﻫﻢ ﺑﺎﻷﻣﻮﺍﻝ، ﻳﺴﺎﻋﺪﻫﻢ ﻋﻠﻰ ﻣﺤﺎﺭﺑﺔ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺴﻨﺔ " .
ﺍﻟﻤﺼﺪﺭ : ﺗﺤﻔﺔ ﺍﻟﻤﺠﻴﺐ ﺹ 53 .
* ﻗﺎﻝ ﺍﻹﻣﺎﻡ ﺍﻟﻤﺠﺪﺩ ﻣﻘﺒﻞ ﺍﻟﻮﺍﺩﻋﻲ - ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ - :
ﻓﻴﻨﺒﻐﻲ ﺃﻥ ﻳﻌﻠﻢ ﻫﺬﺍ ﺣﺘﻰ ﻻ ﻳﻠﺒﺲ ﻋﻠﻴﻨﺎ ﺍﻟﻤﻠﺒﺴﻮﻥ، ﻭﺣﺘﻰ ﻳﻜﻮﻥ ﻛﻼﻡ
ﺍﻹﺧﻮﺍﻥ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﻋﻨﺪﻧﺎ ﻣﺜﻞ ﺍﻟﺒﻌﺮ ﻟﻴﺲ ﻟﻪ ﻗﻴﻤﺔ، ﻭﺇﻻ ﻓﻌﻨﺪﻫﻢ ﻣﺎ ﻫﻮ
ﺃﻗﺒﺢ ﻣﻦ ﻫﺬﺍ ﻓﻘﺪ ﺧﻄﺒﻮﺍ ﺧﻄﺒًﺎ ﻛﺜﻴﺮﺓً ﻳﺆﻳﺪﻭﻥ ﻓﻴﻬﺎ ﺍﻟﺨﻤﻴﻨﻲ ﺍﻟﻀﺎﻝ،
ﻭﻟﻜﻨﻬﻢ ﺍﻧْﻬﺰﺍﻣﻴﻮﻥ ﻓﻠﻤﺎ ﻋﺮﻑ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺿﻼﻝ ﺍﻟﺨﻤﻴﻨﻲ ﺗﺮﺍﺟﻌﻮﺍ، ﻓﻼ ﻳﺴﺘﺤﻴﻮﻥ
ﺃﻥ ﻳﻘﻮﻟﻮﺍ ﺍﻟﻴﻮﻡ ﻗﻮﻻً ﻭﻳﺮﺟﻌﻮﻥ ﻋﻨﻪ ﻏﺪًﺍ ﺛﻢ ﻳﺮﺟﻌﻮﺍ ﺇﻟﻴﻪ ﺑﻌﺪ ﻏﺪ .
ﻭﺃﺿﺮﺏ ﻟﻜﻢ ﻣﺜﺎﻻً ﻋﻠﻰ ﺫﻟﻚ، ﻓﻘﺪ ﻛﺎﻥ ﻋﺒﺪﺍﻟﻤﺠﻴﺪ ﺍﻟﺰﻧﺪﺍﻧﻲ ﻳﻘﻮﻝ :
ﺍﻟﺸﻴﻮﻋﻴﻮﻥ ﻛﻔﺎﺭ، ﻭﻗﺪ ﺍﺣﺘﻠﻮﺍ ﺍﻟﺒﻼﺩ، ﻓﻠﻤﺎ ﺣﺼﻠﺖ ﺍﻟﻮﺣﺪﺓ ﺇﺫﺍ ﻫﻢ ﻳﻘﻮﻟﻮﻥ :
ﺍﻷﺥ ﻓﻼﻥ، ﻭﻓﻌﻞ ﺍﻷﺥ ﻋﻠﻲ ﺳﺎﻟﻢ ﺍﻟﺒﻴﺾ ﻛﺬﺍ . ﻭﻳﻨﻜﺮﻭﻥ ﻋﻠﻲّ ﺃﻧﻨﻲ ﺃﻛﻔﺮ
ﻋﻠﻲ ﺳﺎﻟﻢ ﺍﻟﺒﻴﺾ، ﻓﺄﻗﻮﻝ : ﻫﻮ ﻋﻨﺪﻱ ﻛﺎﻓﺮ ﻣﻦ ﻗﺒﻞ ﻭﻣﻦ ﺑﻌﺪ، ﻓﻨﻘﻮﻝ :
ﺇﻧﻪ ﻟﻴﺲ ﻟﻺﺧﻮﺍﻥ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﻣﺒﺪﺃ، ﺑﻞ ﻣﺒﺪﺅﻫﻢ ﻫﻮ ﻣﺎ ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺠﻤﻬﻮﺭ .
ﺍﻟﻤﺼﺪﺭ : ﺗﺤﻔﺔ ﺍﻟﻤﺠﻴﺐ ﺹ 37 .
ﻭﻗﺎﻝ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ :
"ﻓـﻠـﺘـﻘـﺮ ﻋـﻴـﻨــﻚ ﻳـﺎ ﺃﻣـﺮﻳـﻜـﺎ ﺃﺑـﺸـﺮﻱ ﻋـﻨـﺪﻙ ﺍﻹﺧـﻮﺍﻥ
ﺍﻟـﻤـﻔـﻠـﺴـﻮﻥ ﻣـﺴـﺘـﻌـﺪُّﻭﻥ ﺇﻟﻰ ﺃﻥ ﻳﺪﻋـﻮﺍ ﺇﻟﻰ ﻣـﺎ ﺗُـﺮِﻳـﺪﻳـﻦ ﻭﺃﻥ
ﻳُـﻠْـﺒِـﺴُـﻮﺍ ﺩﻋـﻮﺗـﻚ ﻟِـﺒَـﺎﺳـﺎً ﺇﺳـﻼﻣـﻴـّﺎَ . ﻣـﺴـﺘـﻌـﺪﻭﻥ ﻟـﺬﻟﻚ ".
ﺍﻟﻤﺼﺪﺭ : ﺗﺤﻔﺔ ﺍﻟﻤﺠﻴﺐ

⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/⤵️abuabdurahmen⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️


አንተ ወንድ ሆይ ቅናታም ወንድ ሁን አቦ!
እነኝህ የዝንጀሮ እና የአሳማ ወንድሞች አውሮፓውያን የአሳማን ስጋ በልተው ቅናት ሚባል ድራሹ ጠፋባቸው የኛ ወንድ ተቢዬዎች የምን ስጋ በልተው ነው ቅናታቸው የሞተው?!

በምስትህ በልጅህ በአህትህ አትቀናም ገበያ ላይ እንደረከሳ እቃ የያት እና የለፈባት አካል ሁሉ እጅ እግሩን ይዘረጋባት?
ዝንቦች ቁስልን ካዩ እኮ አያምጣው!

ሌላው አመለካካት🔊
እህትህ ቀይ መስመር🔺
እናትህ ቀቀይ መስመር🔺
ምስትህ ቀይ መስመር🔺
ልጆችህ ቀይ መስመር 🔺
አክስትህ ቀይ መስመር🔺
የሌላ ሰው ልጅ እህት እናት አክስት መገናኛ መስመር ወየም መንገድ ትሁን ‏⛔?

ቅና ወንድነት ነወ?‏


⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/⤵️abuabdurahmen⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️


ከትላንት የቀጠለ

ጥያቄ ቁ:(2)ጠያቂ ለምንድነው ኢማሙ ማሊክ ለጠያቂው ከሱ መጠየቅ ቢዳዓ ነው ያሉት ?
መልስ ቁ:(2) በመጀመሪያ ቢዳዓ ብሎ ማለት ምን ማለት እነደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል

ቢዳዓ ማለት በቋንቋ ደረጃ ከሱ በፊት ምንም ያልተፈጠረ አዲስ ነገር ባጠቃላይ ጥሩም ይሁን መጥፎ ቢዳዓ ይባላል

እንደ ኢስጢላህ (እንደ ሸሪዓዊ) ትሩጓሜ ደግሞ በቁረአን በሐዲስ ያልተጠቀሰ ከሰሀቦች ያልተገኘ በዲን ላይ የሚጨመር ባጠቃላይ ቢዳዓ ይሰኛል ይህ ደሞ በጣም ከባድ አደጋ ነው ምክንያቱም
አልላህ በተከበረው የቁርአን አነቀፁ እንዲህ ይላል
وقوله: الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا [المائدة:3]

ዛሬ ለእናንተ ዲናችሁ ሞላሁላችሁ በእናንተ ላይም ፀጋዬንም ዋልኩኝ ከሀይማኖት በኩል ደሞ ለእናንተ እስልምና ወደድኩላችሁ አልማኢዳህ (3) እንግዲህ ከዚህ አንቀፅ እንደምንረዳው የአላህ ዲን ሙሉ እንደሆነ ነው። ዲኑ ሙሉ ከሆነ ቢዳዓ ደሞ ጭማሪ ከሆነ ሙሉ የሆነ ነገር ላይ መጨመር ደሞ የሞላውን ማፍሰስ ነው

عن عائشة -رضي الله عنها- قالت: قال رسول الله -صلى الله عليه وسلم-: "من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد "
".(رواه المسلم)
እናታችን አዒሻ አልላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና ባስተላለፈችው ሐዲሣ የአልላህ መልእክተኛ (ሰልለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ ፦በዚህ ዲናችን ዉስጥ አዲስ ነገርን የጨመረ (ቢዳዓን) የፈፀመ ከሱ ያልሆነን ነገር (ከቁርአን ከሀዲስ ) ስራው ወደራሱ ተመላሽ ነው። በሌላ ዘገባ ደሞ

 " وفي رواية " مَن عَمِلَ عملًا ليس عليه أمرُنا فهو رَدٌّ".(رواه مسلم)

ስራን የሰራ ሰው በሚሰራው ስራ ላይ የኛን ትእዛዝ የሌለበት(የአልላህና የመልእክተኛው)
ስራው ወደራሱ ተመላሽ ነው ።ማለት ተቀባይነት የለውም( መስሊም ዘግበውታል)
ቢዳዓ ደሞ ባጠቃላይ ጥመት ነው የዝንጀሮ ቆንጆ እንደሌለ ሁሉ የቢዳዓ ጥሩ የለውም
كل بدعة ضلالة
ቢዳዓ ባጠቃላይ ጥመት ነው

 قال عبد الله بن عمر بن الخطاب رضي الله
عنه " كل بدعة ضلالة وإن رآها الناس حسنة

"አብደላህ ኢብኑ ኡመር ኢብኑል ኸጧብ አልላህ መልካም ስራቸው ይውደድላቸውና እንዲህ ይላሉ ቢዳዓ ባጠቃላይ ጥመት ነው ሰዎች ጥሩ ብሎ ቢያስቡትም እንኳን

መለስ ቁ፦(2)ኢማሙ ማሊክ ከሱ መጠየቅ ቢዳዓ ነው ያሉበት ምክንያት ይህን ጥያቄ ሰሀቦች ስላልጠየቁት ነው ምናልባት ሰሀቦች ያልጠየቁት (እነሱ ያልሄዱበትን መንገድ እንሂድ ምንል ከሆነ ከዚህ ቁርአን አንቀፅና ከዚህ ሐዲስ እንጋጫለን፦

وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلْأَوَّلُونَ مِنَ ٱلْمُهَٰجِرِينَ وَٱلْأَنصَارِ وَٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُم بِإِحْسَٰنٍۢ رَّضِىَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُواْ عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّٰتٍۢ تَجْرِى تَحْتَهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ التوبة(100)
እነዚያ ቀዳሚዎች ከስደተኛ (መሀጂሮች)ና ረዳቶች (አንሷሮች)ሲሆኑ እነሱንም በበጎ የተከተልዋቸው አልላህ ከነሱ ወደደ እነሱም ከሱ ወደዱ ለነሱ ከስሮችዋ ብዙ ወንዞች የሚፈስሱባ በስዋ ውስጥ ለዘላለም ዘውታሪ ሲሆኑ አዘጋጅቶላቸዋል ይህ ደሞ ትልቅ እድል ነው አትተውባ(100)

وقوله -صلى الله عليه وسلم: «فمن يعش منكم بعدي، فسيرى اختلافا كثيرا، فعليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين المهديين من بعدي، عضوا عليها بالنواجذ»

መልእክተኛው ሰልለላሁዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ ከናንተ ውስጥ ከኔ በኋላ ብዙ የኖረ ሰው ብዙ መለያየትን ያያል ስለዚ በሱናዬ ላይ አደራ እንዲሁም የተመሩ ቅን መሪ በሆኑ ሰሀባዎቼ ሱና ላይ አደራ በመንጋጋ ጥርሣችሁ አጥብቃችሁ ያዙት

وقال عبدُ الله بن مسعود -رضي الله عنه-: " اتَّبِعوا ولا تبتدِعوا؛ فقد كُفِيتُم، وكل بدعةٍ ضلالة". أخرجه الدارمي وصححه الامة الألباني
አብዱላሂ ኢብን መስዑድ አልላህ መልካም ስራው ይውደድለትና እንዲህ ይላል ፦
ተከተሉ አዲስ ነገርን አትፍ ጠሩ በእር ግጥ ተበቅታችኋል (ቢዳዓ) አዲስ ነገር ባጠቃላይ ጥመት ነው ይላል። ኢማም አዳረሚ ዘግበውታል አልባኒ ሰሂህ ብለውታል
ስለዚህ ወንድም አለም የቁርአን አንቀፁ ሀዲሱ የሚያመላክቱት ሰሀቦች ለኛ ትልቅ ተመሣሌትና አረአያ እንደሆኑ ነው ዝለዚህ እነሱ ያሉትን ማለት እነሱ የቆሙበት መቆም ለነሱ የበቃቸው ለኛ ይበቃናል። ወንድማችን በስሱም ቢሆን ለጥያቄህ መልስ እንዳገኘህ ተስፋ አደርጋለሁ ግልፅ ካልሆነም መድረኩ ክፍት ነው በተቻለን ያክል እንሞክራለን ካልቻልነውም ችግር የለም ለእውቀት ባልተቤቶች አሣልፈን እንሰጣለን
فَسْـَٔلُوٓاْ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ النحل (43)
የማታውቁ ከሆናችሁ የእውቀት ባልተቤትን ጠይቁ አነህል (43

ሀዛ ወልላሁ አዕለም

በወንድ ረስላን ኢብኑ ነጃ

https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1


🔷 ወደ ቢዳዓ ተጣሪ
ቢዳዐን በግልፅ የሚሰራና ወደዛ የሚጣራን መቃወም መጥላት በግልፅ ከሱ ማስጠንቀቅ ራሱ እንዲመለስና ሌሎ-ች እሱን እንዳይከተሉት ያደርጋል ። ይህን አስመልክቶ ሸኹል ኢስላም የሚከተለውን ይናገራል : –
قال شيخ الإسلام – رحمه الله –
" ..... من كان مظهرا للفجور أو البدع يجب الإنكار عليه ونهيه عن ذلك ، وأقل مراتب الإنكار هجره لينتهي عن فجوره وبدعته ، ولهذا فرق جمهور الأئمة بين الداعية وغير الداعية ، فإن الداعية أظهر المنكر فاستحق الإنكار عليه ، بخلاف الساكت ، فإنه بمزلة من أسر بالذنب، فهذا لا ينكر عليه في الظاهر ، فإن الخطيئة إذا خفيت لم تضر إلا صاحبها، ولكن إذا أعلنت فلم تنكر ضرت العامة، ولهذا كان المنافقون تقبل منهم علانيتهم وتوكل سرائرهم إلى الله تعالى، بخلاف مو أظهر الكفر. "
الفتاوى ( 23/ 342 )
" ቢዳዐና ጥመትን ግልፅ ያደረገን እሱ ላይ መጥላትና ከድርጊቱ መከልከል ግድ ነው ። ትንሹ የሚጠላበት ( አትስራ የሚባልበት) ደረጃ እሱን ማኩረፍ አለማናገር ነው ። ከቢዳዐውና ከጥመቱ እንዲወጣ ። ለዚህ ነው አብዛኛዎች ዑለሞች ወደ ቢዳዓህ በሚጣራና በማይጣራ መካከል የለዩት ። ወደ ቢዳዓ የሚጣራው መጥፎን ነገር ግልፅ ስላደረገ በሱ ላይ መጥላትና መልስ መስጠት የተገባው ። ከዝምተኛው በተቃራኒ , ዝምተኛው ወንጀል ተደብቆ እንደ ሚሰራ ሰው ነው ። የዚህ አይነቱ በግልፅ ምላሽ አይሰጠውም ። ወንጀል ከተደበቀ ባለቤቱን እንጂ አይጎዳምና, ነገር ግን ግልፅ ከተደረገና ዝም ከተባለ ህዝቡን ይጎዳል ። ለዚህ ነበር ሙናፊቆች ( ኩፍራቸውን ደብቀው ኢማን ግልፅ የሚያደርጉ የነበሩት) ላያቸውን ተቀብለው ውስጣቸው ለአላህ ይተውት የነበረው ። ኩፍሩን ግልፅ ካደረገው በተቃራኒ

የተለያዩ ተምህርቶች ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
join us ⬇️⬇️⬇️ shar⬇️⬇️⬇️
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1


ጠያቂ ፦ለምንድነው ኢማሙ ማሊክ ጠያቂውን እንዲወጣ ያዘዙት መጀመሪያ ለሰላምታህ

ወአለይኩሙ ሰላም ወራህመቱላ ወበረካቱህ ወንድማችን የጠየከው ጥያቄ አሪፍ ነው ፦በመጀመሪያ ጥያቄው እነመልከት

سئل الإمام مالك بن أنس رحمه الله فقيل: يا أبا عبد الله {الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى} كيف استوى؟ فقال: الاستواء غير مجهول، والكيف غير معقول، والإيمان به واجب، والسؤال عنه بدعة # وأظنك صاحب بدعة#. ثم أمر بالرجل فأخرج. الأسماء والصفات للبيهقي2/305
ታላቁ ኢማም ማሊክ ተጠየቁ‹‹ የአባ አብዲላህ ‹‹አራህማን ከዓርሹ በላይ ከፍ አለ፡፡›› እንዴት ከፍ አለ ተብለው ተጠየቁ እሳቸዉም እንዲህ አሉ‹‹ አል-ኢስቲዋእ(ከፍ ማለቱ) የማይታወቅ ነገር አይደለም(ግልፅ ነው)፣ እንዴት የሚለው አእመሮ ሊደርስበት የማይችል ነው፣ በእርሱ ማመን ግዴታ ነው፣ ስለዚህ(እንዴት) ብሎ መጠየቅ ቢድዓ ነው
አንተ የቢዳዓ ሰው ነህ ብዬ እጠረጥርለለሁ አሉትና ፡›› ሰውየው እንዲወጣ አዘዙ እና አስወጡት፡፡አል-አስማእ ወሲፋት ሊልበይሀቂ 2/305
ኢማሙ ማሊክ በአላህ ባህሪ ዙርያ የነበራቸው አቋም እንደተመለከትነው የአላህ ባህሪዎችን እንደወረዱ ማፅደቅ ነበር

ነገር ግን ሰውየው የጠየቀው ከይፊያው (ሁኔውን) ነበር ስለ አልላህ ስምና ባህሪይ በቁርአንም ሆነ በሀዲስ ከይፊያው(ሁኔታው )አልተነገረንም ይህ ሲባል ለኛ አልተነገረንም እንጂ ከነ ጭራሹ የለውም ማት አይደለም

ወደ ወንድማችን ጥያቄ እንመለስ
#(1)፦ኢማሙ ማሊክ ለምን ጠያቂው እንዲወጣ አዘዙ #(2) ለምንድ ነው ከሱ መጠየቅ ቢዳዓ ነው ያሉት
መልስ፦1 እንዲወጣ ያዘዙበት ምክንያት ከላይ እንደተጠቀሰው የቢዳዓ ሰው ነህ ብዬ እጠረጥርሀለሁ ብለውት ነበር ከቢዳዓ ሰው ጋ አብሮ መቀማመጥ እደ ማይቻል ከቁርአን ና ከሰለፎች ንግግር የተወሰነ እጠቅስልሀለሁከቁርአን ፦ وَإِذَا رَأَيْتَ الَّذِينَ يَخُوضُونَ فِي آيَاتِنَا فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ وَإِمَّا يُنسِيَنَّكَ الشَّيْطَانُ فَلَا تَقْعُدْ بَعْدَ الذِّكْرَىٰ مَعَ الْقَوْمِ 68الظَّالِمِينَ انعم
እነዚያ በአንቀፆቻችን የሚዋኙትን (የሚገቡ)ትን ባየህ ጊዜ ከነሱ ተዋቸው (እራቃቸው)ሌላ በሆነ ወሬ እስኪገቡ ድረስ ተዋቸው ሸይጧን እነሱ ከመከልከል ቢያስረሳህ ባሰታወስክ ጊዜ ከበደለኞች ሕዝቦች አትቀማመጥ አንዓም 68
፦እንግዲህ የቁርአን አንቀፁ እንደሚያመላክተው ከበደለኛ ሕዝቦች ሲል የቢደዓ ባልተቤት ከበደለኛ ሕዝቦች ናቸው

وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِى ٱلْكِتَٰبِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُواْ مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُواْ فِى حَدِيثٍ غَيْرِهِۦٓ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ ۗ النساء 140
በመፅሐፋችሁ ወስጥ በእርግጥም በናንተ ላይ ወረደ ምን ሚል በአልላህ አንቀፆች ላይ ሲካድባት ሲላገጥበት በሰማችሁ ጊዜ ሌላ በሆነ ወሬ እስኪገቡ ድረስ ከነሱጋ አንድላይ አትቀማመጡ ያን ጊዜ እናንተ ቢጤያቸው (አምሣያቸው) ናችሁ አንኒሳእ 140 ቢጤያቸው ናችሁ ሲል ከነሱ እስካላስጠነቀቃችሁ ና አስካልራቃችሁ ድረሰ ማለት ነው ኢማም አል ቁርጡቢ ይህ የቁርአን አንቀፅ ሲፈስር እዲህ ይላል፦አልላህ ሚታመፅበት ቦታ የተቀመጠ ሁሉ እስካልተቃወመ ድረስ ከወንጀሉ ተካፋይ ይሆናል
ሰለፎቻችን ከአህሉሌ ቢዳዓ አብሮ መቀማመጥ በተመለከተ የነበረቸው ጠነካራ አቋም በትንሹ፦
وقال ابن عباس رضي الله عنهما يقول( لا تجالس اهل الأهواء فإن مجالستهم ممرضة للقلوب الإبانة (43/2)
አብደልላሂ ኢብኑ አባስ ረዲየልላሁ ዓነንሁማ አነዲህ ይላል፦ ከስሜት ባልተቤት አትቀማመጡ ከነሱ መቀማመጥ ልብን ታሣምማለች አልኢባና(43/2)

وقال مصعب ابن سعد رحمه الله: لا تجالس مفتونا،فإنه لن يخطءك منه احد اثنتين:اما ان يفتنك فتتابعه اويؤذيك قبل ان تفارقه الإبانه(45/2)
ሙስዓብ አብኑ ሰዐድ አልላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል በዲኑ ከተፈተነ ሰው ጋ አተቀማመጥ ከተቀመጥክ ከነዚህ ከሁለት አንድ ነገር ያገኝሀል 1ይፈትንህና እሱን ትከተለዋለህ ወይም ከሱ እስከ ምትለይ ድረስ አዛ ትሆናለህ (አልኢባና 45/2) እነዚህ ለናሙና ያክል ከብዙ ጥቂት ብዬ ነው ተጨማሪ ከፈለክ አያሣስብም ምክንያቱም ሀቅን ለፈለገ (1)ትክክለኛ ማስረጃ በቂው ነው። ፅሁፉ እንዳይረዝም ብዬ ነው ጥያቄ (2)
ጠብቁኝ እመለስበታለሁ ኢንሻአልላህ

ወንድም ረስላን ኢብኑ ነጃ
የተለያዩ ትምህረቶች ለማግኘት ቻናላችን join ያድርጉ ይቀላቀሉ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1


بسم ٱلله ٱلرحمن ٱلرحيم إن الحمدالله نحمده ،ونستعينه ،ونستغفره ونعوذ بالله من شرور أنفسنا ومن سيءات أعمالنا من يهده الله فلا مضل له، ومن يضلل فلا هادي له وأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له، وأشهد أن محمدا عبده ورسوله صلى' الله عليه وعلي' آله وأصحابه ومن تبعهم بإحسان، وسلم تسليما كثيرا

أما بعد السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ውድና የተከበራችሁ ወንድምና እህቶች እንዲሁም የቻናሉ ተከታታዮች ባችሁበት አልላህ ሰላሙን ያስፍንባችሁ

# የዚህ ቻናል ዋና አላማውና ግቡ
በአልላህ ፍቃድ በሱና መሻ
ኢኾች ና ኡስታዞች የተደረጉ

1:-ሙሀደራዎች
2:-የተቀሩ ኪታቦች
3:-አጫጭር ፅሁፎች ና
4:-ወቅታዊ መረጃዎች
የሚለቅበት ይሆናል::
ቻናላችን ይቀላቀሉ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ያድረጉ ⬇️⬇️⬇️join ⬇️⬇️⬇️
⬇️⬇️⬇️join ⬇️⬇️⬇️
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1
https://t.me/Reslan1

Показано 16 последних публикаций.

217

подписчиков
Статистика канала