Tena.et


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ለተጨማሪ ክትትል እና አዳዲስ መረጃዎች ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ::
https://tena.et
ሁኔታዎች: https://tena.et/update
Bot: @TenaETbot

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


በኢትዮጵያ ተጨማሪ 145 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የሟቾቹ ዝርዝር መረጃ

~ 1ኛ ሟች ከአዲስ አበባ ወንድ 64 ዓመት በህክምና ላይ የነበረ

~ 2ኛ ሟች ከአዲስ አበባ ወንድ 65 ዓመት በህክምና ላይ የነበረ

~ 3ኛ ሟች ከአዲስ አበባ ወንድ 65 ዓመት በህክምና ላይ የነበረ

~ 4ተኛ ከአዲስ አበባ ሴት 90 ዓመት በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረች

~5ተኛ ከአዲስ አበባ ሴት 40 ዓመት ከአስከሬን ላይ የተወሰደ ናሙና
@tenaet
@tenaetbot


ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,775 የላብራቶሪ ምርመራ 185 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4848 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 47 ወንድ እና 138 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ3 ወር - 80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 184 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የውጭ ዜጋ ነው።

160 ሰዎች ከአዲስ አበባ (105 ሰዎች ተመላሾች እና በማቆያ የነበሩ) ፣ 7 ሰዎች ከደቡብ ክልል ፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል እና 1 ሰው ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 30 (11 ከጤና ተቋም እና 19 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።

@tenaET | tena.et/update


ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,238 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ አንድ (131) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4,663 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 94 ወንድ እና 37 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ2-80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 130 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የውጭ ዜጋ ነው።

98 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 16 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ፣ 4 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 3 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ፣ 3 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 2 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል ፣1 ሰው ከአማራ ክልል እና 1 ሰው ከትግራይ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 26 (10 ከጤና ተቋም እና 16 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ አምስት (75) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አራት (84) ሰዎች (79 ሰዎች ከ አዲስ አበባ፣ 2ሰዎች ከ ኦሮሚያ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ እና 1 ሰው ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1297 ነው።

@tenaET | tena.et/update


ኢትዮጲያ ተጨማሪ 63 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ሪፖርት ተደረገ

የሟቾቹ ዝርዝር መረጃ

~የ 75 ዓመት ወንድ ከኦሮሚያ ክልል ከአስከሬን ምርመራ

~ የ 34 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ በህክምና ላይ የነበረች

የታማሚዎች ዝርዝር ሁ ኔታ

~ በ24 ሰዓት ውስጥ 63 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ4,457 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 63 ኢትዮጲያዉያን በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

~ 42ቱ ወንዶች ሲሆኑ 21ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።እድሜያቸዉ ከ14 እስከ 76 ዓመት የሆኑ ናቸዉ።

~ የመኖሪያ ስፍራቸዉ 31 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ፣ 1 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣9 ሰው ከሶማሊ ክልል ፣ 3ሰዎች ከአማራ ክልል ፣ 4 ሰዎች ከድሬዳዋ ፣ 3 ሰው ከጋምቤላ ክልል፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል ፣ 2ከደቡብ/ብ/ብ/ህ ክልል ፣ 1 ሰው ከሀረሪ ክልል ናቸው



ተጨማሪ መረጃ ፦

~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 216,328 ደርሷል።

~ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ #91ሰዎች (67 ከአዲስ አበባ ፣ 16 ከሶማሊ ክልል ፣ 2 ከኦሮሚያ ፣ 4 ከአማራ ፣ 2 ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል) አገግመዋል፡፡

~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 1,213 ደርሰዋል።

~ በጽኑ ህሙማን መከታተያ ዉስጥ የሚገኝ 32 ታማሚዎች አሉ ፡፡(+2 ቀንሷል)

~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 3,243 ናቸው።

~ የ 74 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ እስከ አሁን ድረስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4,532 ደርሷል።
@tenaet
tena.et/update


ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4848 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ (399) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4469 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 195 ወንድ እና 204 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ4 እስከ 85 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 398 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የውጭ ዜጋ ነው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 135 ሰዎች ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ፣ 132 ሰዎች ከደዋሌና ጋሊሌ ለይቶ ማቆያ፣ 86 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 18 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 14 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ 9 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 1 ሰው ከደቡብ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ እና 1 ሰው ከሱማሌ ክልል ናቸው።

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ዘጠና አምስት (95) ሰዎች (82 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል ፣ 1 ከትግራይ ክልል፣ 1 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1122 ነው።

@TenaET


የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በዛሬው እለት ከቀብር ስነስርዓትና አስክሬን ምርመራ፣ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ እና የቤት ውስጥ ራስን ለይቶ ማቆየትን በተመለከተ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህ መሰረት በተለያዩ ምክንያቶች ለሞት የሚዳረጉ ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በማህበረሰቡ የቀብር ሥነ-ሥርዓት መፈጸም ተፈቅዷል። ይህም ከዚህ ቀደም የአስክሬን የላብራቶሪ ውጤት ከመምጣቱ በፊት የቀብር ሥነ-ሥርዓት መፈጸም አይቻልም የሚለውን መመሪያ መሻሻሉን ዶክተር ሊያ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ በቀብር ሥፍራ ላይ ከዚህ ቀደም የተቀመጠው 50 ሰዎች ብቻ ተገኝተው ሥርዓቱን ማከሄድ አለባቸው የሚለው መመሪያው አልተሻሻለም።

ግለሰቦች በኮሮናቫይረስ ቢያዙ የሚያገለግሏቸው የቤተሰብ አባላትና የራሳቸው ፍላጎት ከግምት በማስገባት ተፈጻሚ የሚሆን መሆኑንም ጠቅሰዋል። የግለሰቦችን የአኗኗር ሁኔታ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት አግባብ ከሆነ በቤታቸው እንዲቆዩ እንደሚደረጉም ተገልጿል።

ከውጭ የሚገቡ ሰዎች በተለይም ወደ አገር ከገቡ በኋላ ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ ከመጡበት አገር ተመርምረው ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ መረጃ ይዘው ከመጡ ናሙና ተወስዶ በቤታቸወ 14 ቀናት እንዲቆዩ ይደረጋልም ተብሏል።

በሌላ በኩል ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ሪፖርት ይዘው ለማይመጡ መንገደኞች ናሙናቸው ተወስዶ ለሰባት ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ይደረጋል ብለዋል። ይህም ከዚህ ቀደም ለ14 ቀናት የነበረውን አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ወደ ለ7 ቀናት ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።
@tenaet


በኢትዮጵያ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ1000 አለፈ!

በትላንትናው ዕለት ዘጠና ሶስት (93) ሰዎች (88 ከአዲስ አበባ ፣ 2 ከአማራ፣ 2 ከሱማሌ ክልል 1 ከኦሮሚያ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው (ኮቪድ-19) ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,027 ደርሷል።
@tenaet
https://tena.et/update


በኢትዮጲያ ተጨማሪ የሰባት ሰዎች ሞት በኮሮና ቫይረስ ተመዘገበ።የሟቾች ብዛት 72 ደርሰል

የሟቾች ዝርዝር መረጃ

~ 1ኛ የሶማሊ ክልል ነዋሪ ወንድ 70 ዓመት በህክምና ላይ የነበረ

~ 2ኛ የአዲስ አበባ ነዋሪ ወንድ 68 ዓመት በህክምና ላይ የነበረ

~ 3ኛ የአዲስ አበባ ነዋሪ ወንድ 45 ዓመት በህክምና ላይ የነበረ

~ 4ኛ የድሬደዋ ነዋሪ ሴት 78 ዓመት በህክምና ላይ የነበረች

~ 5ኛ የሀረሪ ክልል ነዋሪ ወንድ 4 ወር በህክምና ላይ የነበረ

~ 6ኛ የአዲስ አበባ ነዋሪ ወንድ 85 ዓመት በህክምና ላይ የነበረች

~ 7ኛ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሴት 40 ዓመት ከአስክሬን ምርመራ
@tenaet
https://tena.et/update


በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4,000 አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,809 የላብራቶሪ ምርመራ 116 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4,070 ደርሷል።
@tenaet
https://tena.et/update


በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 65 ደርሷል!

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 44 (19 ከጤና ተቋም እና 25 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።

ከዚህ ባለፈ ሁለት (2) በህክምና ማዕከል ውስጥ ህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው የለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ አምስት (65) ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ60 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።
@tenaet
https://tena.et/update


በኢትዮጵያ ተጨማሪ 195 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,853 የላብራቶሪ ምርመራ 195 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,954 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 90 ወንድ እና 105 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 95 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉ። ኢትዮጵያውያን ናቸው።


ቫይረሱ የተገኘባቸው 144 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 12 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 12 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 7 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ ፣ 7 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል እና 2 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች (73 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 934 ደርሷል።
@tenaet
https://tena.et/update


በኢትዮጵያ ያገገሙ ሰዎች 849 ደረሱ!

በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ አስራ አንድ (111) ሰዎች (109 ከአዲስ አበባ ፣ 2 ከድሬዳዋ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው (ኮቪድ-19) ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ስምንት መቶ አርባ ዘጠኝ (849) ደርሷል።

@TenaET / https://tena.et


በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,274 የላብራቶሪ ምርመራ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,759 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 79 ወንድ እና 50 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 85 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 11 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 10 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 7 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 6 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደት እና 1 ሰው ከአፋር ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 18 (11 ከጤና ተቋም እና 7 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።

ከዚህ ባለፈ ሁለት (2) በህክምና ማዕከል ውስት ህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው የለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ ሶስት (63) ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ60 ዓመት ወንድ የድሬዳዋ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ30 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

@TenaET


#Dexamethasone

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በዴክሳሜታሶን መድሃኒት ዙሪያ የወጣውን ጆርናል የክሊኒካል አማካሪ ቡድናቸው እየገመገመው እንደሆነ ዛሬ ምሽት አሳውቀዋል።

የጤና ሚኒስትሯ በነገው ዕለት አንድ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።

በመድሀኒቱ ዙርያ የቀረበው ማስረጃ ላይ ከስምምነት ላይ ከተደረሰ 'ዴክሳሜታሶን' በኢትዮጵያ በስፋት ስለሚገኝ ችግር አይሆንም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@TenaET


#Dexamethasone

“ዴክሳሜታሰን” የተባለው መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት ለመታገድ እንደሚረዳ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁ።

ሳይንቲስቶቹ በህክምና ላይ ያሉና በቬንትሌተር የሚተነፍሱት ታማሚዎችን የመሞት እድል በሶስት እጥፍ እንደሚቀንስ የገለጹ ሲሆን በኦክስጅን ውስጥ ያሉትን የመሞት ዕድላቸውን በአምስት እጥፍ እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡

አሁን የተገኘው ይህ መድሃኒት የኮሮና ቫይረስን (ኮቪድ-19) ለማከም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተደረጉ ትልልቅ ሙከራዎች አንዱ መሆኑንም ነው የቢቢሲ ዘገባ የሚያመለክተው፡፡

ተመራማሪዎቹ የኮሮና ቫይረስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ይህ መድሃኒት ጥቅም ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ የአምስት ሺ ሰዎችን ሕይወት ማትረፍ ይቻል እንደነበርም አስታውቀዋል፡፡

ይህ መድሃኒት (ዴክሳሜታሶን) ዋጋው በጣም አነስተኛ እና ለድሃ ሀገራትም ጭምር በቀላሉ ሊገዙት የሚችሉት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ ፣ አል ዓይን

@TenaET / https://tena.et


በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 118 ሰዎች አገገሙ!

በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ አስራ ስምንት (118) ሰዎች (115 ከአዲስ አበባ ፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው (ኮቪድ-19) ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት (738) ደርሷል።

@TenaET | https://tena.et/update


ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,102 የላብራቶሪ ምርመራ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,630 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 60 ወንድ እና 49 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 78 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 81 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 9 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 3 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል እና 2 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 20 (5 ከጤና ተቋም እና 15 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን የ45 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሴት ከማህበረሰቡ በተወሰደ ናሙና የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው የለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ አንድ (61) ደርሷል።

@TenaET | https://tena.et/update


በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2,577 ደርሷል!

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ሰኔ 8/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 2,577 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 98 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 3 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣ 5 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የተቀሩት 90 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ዘጠና ስምንት (98) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 37 ሰዎች
• ቦሌ - 4 ሰዎች
• ጉለሌ - 4 ሰዎች
• ልደታ - 13 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 8 ሰዎች
• ቂርቆስ - 16 ሰዎች
• አራዳ - 7 ሰዎች
• የካ - 2 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 4 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 2 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 1 ሰው

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 2,577 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 590 ሰዎች
• ቦሌ - 411 ሰዎች
• ጉለሌ - 286 ሰዎች
• ልደታ - 265 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 243 ሰዎች
• ቂርቆስ - 155 ሰዎች
• አራዳ - 149 ሰዎች
• የካ - 144 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 133 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 79 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 122 ሰዎች

@TenaET


#TIGRAY

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 316 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 31 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ከሰላሳ አንዱ (31) መካከል 21 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 8 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆኑ 2 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

#OROMIA

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 241 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

- 2 ሰዎች ከቡራዩ (የ 38 እና 30 ዓመት ወንዶች) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ ከማህበረሰቡ የተገኙ።

- 1 ሰው ከአዳማ (የ38 ዓመት ወንድ) የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

#AFAR

በአፋር ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 49 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 66 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። በክልሉ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 33 ደርሰዋል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተደር ከተካሄደው 96 የላብራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጧል። በቫይረሱ የተያዙት ሁለቱም ወንዶች ሲሆኑ ግለሰቦቹ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው። በድሬዳዋ አጠቀላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 15 ደርሰዋል፤ 8 ሰዎች አገግመዋል።

@TenaET


በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,636 የላብራቶሪ ምርመራ 176 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,521 ደርሷል።

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 60 ደረሰ!

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 28 (17 ከጤና ተቋም እና 11 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን አንድ (1) ናሙና የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በተጨማሪ 2 በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው የለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ (60) ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ60 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ19 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

3. የ32 ዓመት ወንድ የአማራ ክልል ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት።

@TenaET

Показано 20 последних публикаций.

7 300

подписчиков
Статистика канала