📲 قَنَاةُ أَبِي رَسْلَانْ حَنِيْفِ الْأَمْبَوِيِّ


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


✍ አላማችን ሱናን ለማሰራጨት እና የቢድዓን ምሽግ ለማፍረስ ነው።
✅ መፈክራችንም ከታች የምታነቡት የወንድም አቡ ሳራ ግጥም ነው
ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤
ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤
ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤
እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር።

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: የ ሸይኽ ሙሐመድ ሀያት ቻናል
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎
ትንሽ ስለግሩፑ አላማና ቦታ ገለፃ
ወድ  የተከበራችሁ በአለም ላይ የምትገኙ ሙስሊሞች በሙሉ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን
እንደሚታወቀው መድናችን ሀሮ ከተማ በመባል የምትታወቅ ወብ ከተማ ናት ይቺ ውብ ከተማ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ዉስጥ የምትገኝ ስትሆን
ምንም እንኳ አየርዋ ሞቃታማ ብትሆንም ከተማዋ ግን በቅርብ ጊዜ ተነስታ ከታላላቅ ከተሞች ጎን ለመሰለፍ ደፋ ቀና እያለች ያለች ውብ ከተማ ናት‼️ 9 ቀበሌዎችን በመያዝ  በንኡስ ወረዳነት ሁና የቆየች ሲሆን ታላላቅ ስራወችን በመስራት ና የአካባቢዋን የሚገኙ 9 ቀበሌዎችን በመያዝ   ወረዳ ለመሆን ከወረዳ እስከ ዞን ጨርሳ ለክልሉ አቅርባ   ውሳኔን ብቻ የምትጠብቅ ዉብ ከተማ ናት ‼️
ታዳ ይች ውብ ከተማ  የጅቡቲ መስመር መተላለፊያ ወደብም ነች ለአማራና ለትግራይ ክልል ትልልቅ ከተሞች የሚመጡ መንገድ  መሄጃ ዋና ድልይ ስትሆን ለእድገታ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርግላታል  !!
ይህን ያክል እንደመንደርደርያና እንደ ማስታወቂያ ካልኩ
ሀገሪቱን ለየት የሚያረጋት በፎቅም፣ በሀብትም ፣ በሌላ የዱንያ ቁሳቁሶች ሳይሆን ሀገሪቱ የሙስሊምና ሙስሊም መወለጃና መነሀርያ መሆኖ ነው‼️
በዝች የመሰለች  ከተማ ላይ መስጅድ አለ ብሎ ለማውራት የሚከብድ ነው ። በከተማይቱ ያለው ብቸኛ መስጊድ ለሀገሪቱ ድባብ የሚሆን ና ማስታወቂያ መሆን የሚችል መሀል ከተማ ላይ ያለ በከተማይቱ ላይ ያለፈ ሁሉ መስጅዱን ሳየየው ማለፍ ከማይችልበት ቦታ ላይ ያለ እና ለሱኑዮች//ለሰለፍዮች በከተማይቱ ያላቸው ብቸኛ ና የአይናቸው ማረፊያ የሆነ መስጅድ ነው።  ከዚህ መስጅድ ጸሀይና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው ነው የሚሰግ ዱት እናም መሀል ከተማ በመሆኑ በዚች ዉብ ከተማ የሚያፍ የሚሰግድበት ቦታ ነው።
ስለሆነም ሀሮ ከተማ የሚታወቀው ሙስሊም እና ሙስሊም ብቻ በመሆኑ ነው ቢሆንም በአካባቢው ትልቅ የሺርክ ና የቢድአ መፈልፈያ ቦታ የለበት ከመሆኑ አንጻር ትልቅ ስራ መሰራት ያለበት አካባቢ ነው‼️
ከዚህ መስጅድ ላይ ሀቅ ባለመጥፋቱ በጌታችን እርዳታ በአንዳንድ ወንድሞችና ሸይኾች የዚህ መስጅድ ሀላፊወች  ጭምር ትክክለኛውን የኢስላም አስተምሮት በስሱም ቢሆን ተውሂድ ላይ ባለመደራደራቸው የማይበገሩም ወጣቶች በውስጥ በመኖራቸው ሀቅን የሚያንቀሳቅሱ ጀግኖች ያሉበት መስጅድ ነው ‼️‼️‼️
ስለሆነም አሁን ላይ  እነዝሁ ጀግኖች በዝች ግሩም በሆነች ከተማ ታላቅና ሰፊ የሆነ መስጅድ ግንባታ አስበው  በግንባታ ላይ ናቸው በመሆኑም  አለም ላይ ያላችሁ ሙስሊሞች ሆይ
አርዱን እያሉ ከአላህ በመቀጠል ወደናንተ ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ‼️
የሁላችንም ትብብር መተጋገዝ መረዳዳት አንድነት የስፈልገናል በማለት የጌታ አላሁ ﷻ ቃል መሰረት በማረግ
قوله -تعالى-: (وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاء بَعْضٍ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ الصَّلاَةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَيُطِيعُونَ اللّهَ وَرَسُولَهُ أُوْلَئِكَ سَيَرْحَمُهُمُ اللّهُ إِنَّ اللّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ).
በዝህ የቁራአን አንቀፅ መሰረት ጥሪ አስተላልፈናል።
በነብዩም ﷺንግግር መሰረት
وعن ابن عمر رضي الله عنه، أنَّ النَّبيَّ صلى الله عليه وسلم قال: ((المسلم أخو المسلم، لا يظلمه، ولا يسلمه، ومَن كان في حاجة أخيه، كان الله في حاجته، ومَن فرَّج عن مسلم كربةً، فرج الله عنه كربةً مِن كربات يوم القيامة، ومَن ستر مسلمًا، ستره الله يوم القيامة  ))
በዝህ የመልእክተኛው ንግግር መሰረት  ጥሪ አቅርበናል
ታላቁ የሱናሊቅ የሆነው ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያም እንድል በለው መሠረት
قال ابن تيمية رحمه الله: "حياة بني آدم وعيشهم في الدنيا، لا يتم إلا بمعاونة بعضهم لبعض في الأقوال أخبارها   وفي الأعمال أيضًا"[2].
ጥሪያችንን እናስተላልፍ አለን።
وعن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: ((مَن نفَّس عن مؤمن كُرْبَةً مِن كُرَبِ الدُّنْيا نفَّس الله عنه كُرْبَةً مِن كُرَبِ يوم القيامة، ومَن يسَّر على معسر، يسَّر الله عليه في الدُّنْيا والآخرة، ومَن ستر مسلمًا ستره الله في الدُّنْيا والآخرة. والله في عون العبد ما كان العبد في عون أخيه...  )
ታላቁ የዘመናችን አሊም የሆኑት ኢማሙ ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸው እና ባሉት መሰረት ጥሪ አስተላልፈናል
قال ابن باز رحمه الله: "التعاون على البر والتقوى هو تعاون على تحقيق ما أمر الله به ورسوله قولًا وعملًا وعقيدة، وعلى ترك ما حرَّم الله ورسوله قولًا وعملًا وعقيدة
እንድንረባረብ እንድትተጋገዝ ድናችን መሰረት ባረገልን ቁራአን  ጥሪ አቅርበናል ‼️
ومن القواعد العظيمة الجليلة التي قررها الإسلام قوله تعالى:
﴿ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَى وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ﴾ [المائدة: 2]،
ففي الآية قاعدة عامة في تعامل المسلم مع الناس،
ስለ መስጅድ ግንባታ እንድህ ተብለናል
قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلم.
[ من بنَى مسجدًا بنَى اللهُ له بيتًا في الجنَّةِ.]
የአሏህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسم) እንዲህ ብለዋል:-
[ መስጂድ የገነባ ሰው አላህ ለሱ ጀነት ውስጥ ቤት ይገነባለታል።]
ቲርሚዚ ዘግበውታል።
          ወደ ግሩፓችን ለመቀላቀል ለመርዳት
        👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+kbJDxdsM7xhhNzU0


Репост из: ሙሀመድ አል―ወልቂጢይ
↪️ የሱና ወንድምና እህቶች የሱና ቤተሰቦች ሆይ አለህ ባላቹበት ይጠብቃቹ። አላህ የሞቱትን ይዘንላቸው። ያሉትን ይጠብቃቸው። የታመሙትን ይፈውሳቸው። የተጨነቁትን ያሳርፋቸው። የተራቡትን ይመግባቸው። የተቸገሩትን ነፃ ይድርጋቸው። የተሸበሩትን ሰላም ያድርጋቸው። የወጡትን በሰላም ይመልሳቸው። የታረዙትን ያልብሳቸው። የተሳሰቱትን ይምራቸው።
((አሚን!! አሚን!! አሚን!!))


Репост из: 📝Abu Nuh ሚስባህ ሙሐመድ
📢🔊 የጁመዕ ቀን ዒባዳዎች በላጭነት
➠➻➠➻➠➻➠➻➠➧➠➻➠➻➠➻➠➧
🔹የጁመዕ ቀን ሱቢህ የፈጅር ሶላት

📣 عن ابن عمر رضي الله عنهما قال : قال الرسول صلى الله عليه وسلم
  أفضل الصلوات عند الله صلاة الصبح يوم الجمعة في جماعة ،
📚 رواه البيهقي في شعب الإيمان وصححه الألباني في صحيح الجامع (1119)

ከዐብደላህ ኢብኑ ዑመር ረዲየአላሁ ዐንሁማ ረሱል ﷺ አላህ ዘንድ ከሶላቶች ሁሉ በላጩ ሶላት የጁመዕ ቀን በጀመዕ የሚሰገደው የፈጅር ሶላት ነው

📚ኢማሙ በይሀቂይ ሹዐቡል ኢማን ለይ ዘግበውታል
📚 ኢማሙል አልባኒይ ሷሂሁል ጃሚዕ ለይ ሷሂህ ብለውታል 1119

🔹የጁመዕ ቀን በረሱል ﷺ ላይ ሶለዋት

 عن أوس بن أوس، قال: قال النبي صلى الله عليه وسلم: «إن من أفضل أيامكم يوم الجمعة، فأكثروا علي من الصلاة فيه، فإن صلاتكم معروضة علي»، قال: فقالوا: يا رسول الله: وكيف تعرض صلاتنا عليك، وقد أرمت؟ - قال: يقولون: بليت - قال: «إن الله تبارك وتعالى حرم على الأرض أجساد الأنبياء صلى الله عليهم ،

📚رواه أبو داود 1531

አውስ ቢን አውስ ረዲየአላሁ ዐንሁ
ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ ይላል ፥
በላጩ ቀናችሁ የጁመዕ ቀን ነው በዚህ ጁመዕ ቀን በኔ ላይ ሶለዋት ማውረድን አብዙ ሶለዋታችሁ እኔ ጋ በተመደቡ መለኢካዎች አማከኝነት ይቀርብልኛል ።
በዚህ ሰዐት ሶሃባዎቹ ረሱልን ﷺ እንዲህ አሉዋቸው ያረሱለላህ እንዴት ሶለዋታችን ይቀርብልሃል በርግጥም አፈር በልቶህ በስብሰሃል ረሱልም ﷺ እንዲህ ብለው መለሱላቸው የተቀደሰው አላህ በምድር ላይ የነቢያቶችን ሰውነት ሀራም አድርጎባታል ።

📢ኢብኑ ዑመር ረዲየአላሁ ዐንሁማ ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ ይላል አላህ ዘንድ በላጩ ሶላት የጁመዕ ቀን በመስጂድ ከሙስሊሞች ጋር በጀማዕ የሚሰገደው የሱቢህ ሶላት ነው ።

🔹የጁመዕ ቀን ገላውን ታጥቦ ምስቱንም ያስታጠበ

✅عَنْ أَوْسِ بْنِ أَوْسٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( مَنْ اغْتَسَلَ يَوْمَ الْجُمُعَةِ وَغَسَّلَ وَبَكَّرَ وَابْتَكَرَ وَدَنَا وَاسْتَمَعَ وَأَنْصَتَ كَانَ لَهُ بِكُلِّ خُطْوَةٍ يَخْطُوهَا أَجْرُ سَنَةٍ صِيَامُهَا وَقِيَامُهَا

📚رواه الترمذي (496)

☑️አውስ ቢን አውስ በዘገበው ሀዲስ ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ

🔹የጁመዕ ቀን ሰውነቱን ታጥቦ ሚስቱንም   ትጥበትን ዋጅብ  አስደርጎባት ( ግንኙነት አድርጎ ) ያስታጠባት መስጂድ በግዜ የገባ ለመጀመሪያው ኹጥባ የደረሰ ከእማሙ ጠጋ ብሎ ዝም በማለት ኹጥባውን የደመጣ
በእያንዳንዱ እርምጃው ቀኑ የሚፆም ሌሊቱ የሚሰገድ የአንድ አመት አጅር አለው

እማሙ ቲርሚዚይ / 496 /

https://t.me/MisbahMohammed


🎤 ታላቅ የዳዕዋ እና የንያ ፕሮግራም ጥሪ↩️

✅ በአይነቱ ለየት ያለ ሃገር አቀፍ የዳዕዋ እና የንያ ዝግጅት ተደግሷል

⚙ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ቦታ በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ በሃሮ ከተማ  በሰለፍዮች መስጂደ አል ፋሩቅ ብቅ ዘለቅ ማለተዎን እንዳይ ዘነጉት

✅ ታላቅ የዳዋና የገቢ ማሰባሰቢያ  ሂደትም ዝግጅትም ስለሚካተትበት በታባለው ቦታ ትላልቅ የእውቀት ባልተቤቶች ይገኙበታል ችላ በማለት እንዳዘነጉት እዳይነድሙ ሁላችሁም ታድማችኋል

➖በሃሮና አካባቢዋ ለመትገኙ ሙስሊም ማሃበረሰብ በሙሉ ሁላችሁም በተባለው ወርና ቀን  እንግዳን  ለመቀበልና ለማስተናገድ ታጥቃችሁና ተሰንቃችሁ ተዘጋጁ

🌎 በውጭ ለምትኖሩ እህቶችና ወንድሞች የዚሁ የተባረከ የዳዕዋና የንያ ጥሪ ተካፋይና ተቋዳሽ ሁነው  የአጅሩ ተካፋይ ለመሆን ያመች ዘንዳ እነሆ

➖የኦላይን ስርጭት (online) ተዘጋጂቷል።

የፕሮግራሙ አዘጋጆች፦
 
   ✅ የሀሮ ሰለፍያ ጀመዓወች

🪑 የእለቱ ተጋባዠ እንግዶቻችነን ፦↩️

📝 በቅርብ ቀን የምናሳውቅ ይሆናል የሱና ብርቅየ መሻይኮቻችንና ኡስታዞቻችን ለዚህ የተባረከ የዳዕዋና የንያ ፕሮግራም ጥሪን በማክበር ይገኛሉ ከትንሽ ቀን ቦኋላ እሹክ የምንላችሁ ይሆናል  እነማን እደሚገኙ በጉጉት ጠብቁን

🗓 ፕሮግራሙ የ
ሚካሄድበት ወርና ቀን ታህሳስ /27/2017/መሆኑን እንዳይዘነጉት

፦በተባለው ወር አስታውሰው ለመምጣት ይደገሱ በጧት 2:00 ሰአት ቡሀላ ይጀመራል ቀድማችሁ
በመገኘት የፕሮግራሙ ተካፋይ ይሁኑ
!!!

♻️ ፕሮግራሙን ለመከታተል ሊንኩን
በመጫን ይቀላቀሉ።

✍በቻናል እና በግሩፓች ሼር በማድረግ
ሀላፍትናችንን እንወጣ


➷➷➷➷➷➷➷➷➷

https://t.me/hussenhas
🌐 ሸር በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣ

🗓 ታህሳስ ቀን/27/2017/ታላቅ የዳዋ ጥሪ በሃሮ ከተማ ለመካሄድ ታስቧል አሏህ አክበር

https://t.me/+P0hA_4jHbeEzYjlk ሼር
ሼር


Репост из: ሙሀመድ አል―ወልቂጢይ
🌹🌹ታላቅ ብስራት ለወልቂጤና አካባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ🌹🌹

🟢 ውድና ገሳጭ የዳዕዋና የሙሀደራ ፕሮግራም እሁድ ቀን 22/03/2017 በወልቂጤ ከተማ ብቸኛ የሰለፊያ መድረሳ በሆነው በዳሩል ሁዳ መድረሳ ውብና ማራኪ በሆነ መልኩ አዘጋጅቶ ይጠብቃቹሀል።

✅ ከእርስዎ የሚጠበቀው ከዘመድ አዝማድዎ ጋር በመሆን በዚህ ፕሮግራም ላይ መታደም ብቻ ነው።

🔷 እንኳን መቅረት ማርፈድ እራሱ ያስቆጫል።

⏰ ሰዓት:2:30 ጀምሮ።

🌏 አድራሻ: ሀይስኩል ጀርባ ከተወከል ብረታ ብረት ዝቅ ብሎ ወደ ግራ በሚያስገባው ቅያስ ላይ።


https://t.me/shikmubarek


Репост из: Bahiru Teka
🚫   ምቀኝነትን ተጠንቀቅ

   ምቀኝነት የልብ በሽታ ሲሆን አላህ ለባረያው የሰጠውን ፀጋ እንዲወገድ መመኘትና ለዚህም አስባብ ማድረስ ነው ። የዚህ አይነቱ ምቀኝነት በክፋት የመጨረሻው ደረጃ የደረሰው አይነት ሲሆን መጨረሻ ላይ የሚጎዳው ባለቤቱን ነው ። ምክንያቱም የአላህን ውሳኔ ለመቀየር መታገል ስለሆነ አይሳካምና ። አላህ ከባሮቹ ለሻው በሚሻው ነገር ይለየዋል ወይም ስኬታማ ያደርገዋል ። ይህ ማለት በሰዎች እይታ ነው ምክንያቱም የመጨረሻው ስኬት ከጀሀነም ተጠብቆ የጀነት መሆን ስለሆነ ። ይኼኛውን ስኬት ደግሞ ከአላህ ውጪ የሚያውቀው የለም ። ነገር ግን በምቀኝነት በሽታ የተለከፈ ሰው ይህን ፀጋ በሚያይ ጊዜ ውስጡ በምቀኝነት እሳት ይነዳል ። ከዚህ በላይ ምን አይነት ጉዳት ይኖራል ።
      ምቀኝነተ በሁሉም ላይ ሊኖራ የሚችል አስቀያሚ ባህርይ ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ታግለው ይደብቁታል ። ግልፅ አያደርጉትም ለዚህም አላህን በመፍራት ይታገዛሉ ። የተበላሸ መንፈስ ያላቸው ወራዶች ግን ከላይ ለመግለፅ በተሞከረው መልኩ የአላህን ውሳኔ ወይም መሺአ ለመቀየር ይታገላሉ ። እንቅልፍ ያጣሉ ፣  ይብከነከናሉ ፣ ጨጓራቸውን ይልጣሉ በዚህም የዱንያ ላይ ቅጣት ያገኛሉ ።
    የእነዚህ ሰዎች ምሳሌ እንደ አይጥ ነው ። አይጥ ጥሩ ነገርን  ከስር እየቦረቦረች ለማጥፋት ትዳክራለች ። ይሁን እንጂ ሀሳቧ ሳይሳካ የወጥመድ እራት ትሆናለች ። የምትያዘውም አንገትዋ ወይን አፏ ነው ።
    ምቀኝነት መጀመሪያ የጀመረው ኢብሊስ ነው ። በአባታችን ኣደም ላይ በመመቅኘት ። አላህ አባታችን ኣደምን ከጭቃ ከፈጠረው በኋላ ለመላኢካዎች ስገዱለት አላቸው ። መላኢካዎችም የጌታቸውን ትእዛዝ ተቀብለው ሰገዱ ። ከእነርሱ ጋር የነበረው ኢብሊስ ግን አልሰግድም አለ ። እንዳይሰግድ የከለከለውም ምቀኝት መሆኑን እንዲህ ብሎ መሰከረ : –

« وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ قَالَ أَأَسْجُدُ لِمَنْ خَلَقْتَ طِينًا »

                         الإسراء  ( 61 )

" ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ወዲያውም ሰገዱ ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ፡፡ «ከጭቃ ለፈጠርከው ሰው እሰግዳለሁን» አለ ፡፡ "

« قَالَ أَرَأَيْتَكَ هَٰذَا الَّذِي كَرَّمْتَ عَلَيَّ لَئِنْ أَخَّرْتَنِ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَأَحْتَنِكَنَّ ذُرِّيَّتَهُ إِلَّا قَلِيلًا »

                 الإسراء   ( 62 )

«ንገረኝ ይህ ያ በእኔ ላይ ያበለጥከው ነውን
እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ብታቆየኝ ዘሮቹን ጥቂቶች ሲቀሩ ወደ ስህተት በእርግጥ እስባቸዋለሁ» አለ ፡፡"
        ኢብሊስ ሊሰግድ የከለከለው ሁለት ነገር ነበር ። ኩራትና ምቀኝነት ። ኩራቱን ከጭቃ ለፈጠርከው ልስገድ ወይ በማለት ገለፀው ። ምቀኝነቱን ደግሞ ይህ ነውን ከኔ ያስበለጥከው በማለት ገለፀው ። በዚህም ከአላህ እዝነት የተባረረና እስከቂያማ የሚረገም ሆነ ።
     ምቀኝነት አላህ ለባሪያው የሰጠውን ፀጋ እንዲፃረር ያደረገው ሰው በመፃረሩ ልክ ከአላህ እዝነት የመራቅና የመረገም ድርሻ አለው ።

       አላህ በዱንያ ላይ በምቀኝነት እሳት ከመንደድ ይጠብቀን ።

አንገብጋቢ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ

  https://t.me/bahruteka


Репост из: Bahiru Teka
🔷  የምቀኝነት እሳት አይጠፋም

قال أبو حاتم – رحمه الله:-
"الحسد من أخلاق اللئام، وتركه من أفعال الكرام. ولكلِّ حريق مُطفِئ، ونار الحسد لا تُطفَأ."
روضة العقلاء : (١٣٤)

👉  አቡ ሓቲም የተባለ ዓሊም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል፦

"ምቀኝነት የወራዶች ባህርይ ነው። ምቀኝነትን መተው ደግሞ የተከበሩ ሰዎች ተግባር ነው። ለሚነድ ነገር ሁሉ ማጥፊያ አለው። የምቀኝነት እሳት ግን አይጠፋም ‼።"

https://t.me/bahruteka


አዲስ ወሳኝ ሙሓደራ

🌷ዛሬ ከመግሪብ እስከ እሻዕ በሳንኩራ በአለም ገበያ ካተማ የተሰጣው ዉብ ሙሓደራ


🕌 በፈትህ መስጅድ

↪️ ርእስ፦ "የዘካ"አሳሳቢነት

🎙 አቅራቢ፦ ሸይኽ ዐብዱል ሀሚድ ያሲን አል-ለተሚይ ሀፊዘሁላሁ ተዓላ

ቀን 17/3/17


ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት ወደ ቻናላችን #ጆይን ይበሉ 👇👇👇
https://t.me/Ibnushaffi
https://t.me/Ibnushaffi
https://t.me/Ibnushaffi


Репост из: የሰለፍዮች App develop
ኡሱሉ ሰላሳህ በሸይኽ ሙሀመድ ሀያት.apk
31.9Мб
📱 አድስ አፕሊኬሽን ተለቀቀ
      〰〰〰〰〰〰〰
↪️ የኪታቡ ስያሜ ⬇️

📚الأصول الثلاثة
📚 ኡሱሉ ሰላሳህ

🎙በሸይኽ ሙሀመድ ሀያት

ለሌሎች ሼር በማድረግ ላልደረሳቸው እናዳርስ

ሊንኩንም ሼር ማረግን አትርሱ
      👇👇👇👇👇
https://t.me/safya_app

📨 መሰል  ቂራአት እና ሙሀደራወች ለማሰራት የሚከተልውን አድራሻ ይጠቀሙ
      👇👇👇👇👇
  @selfy_app_developer


Репост из: 🎀ምክር ለባላ ትደሮች🎀🥀
ሴት ልጅ ከልቧ ስትወድህ ንፁህ ፍቅርን ትሰጥሀለች።  ስታገኚህ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ትሆናለች። ምንም እንዳልገባት ሞኝ ትሆንልሀለች። ለደቂቃ ልታጣህ አትፈልግም።ስትናፍቃት ትጨቃጨቅሀለች። ከአንተ ጋር  መሆን ያስደስታታል። ብዙ ነገር ቢከፋት ትንሹ ነገር ያስደስታታል።  ከልቧ ታዝንልሀለች በስስት አይኗ ታይሀለች። ደስታህ ያስደስታታል። ሲከፋህ ትከፋለች። ፍቅሯ ከተረዳሀት በምድር ላይ ሁለተኛ እናት ትሆንልሀለች።

https://t.me/alfrkatu_anajeya


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
የተውሒዷን ሀገር ሳዑዲን በተለያየ መንገድ የማጠልሸት ሴራ
—————ክፍል 2
አይ ሳዑዲ!
ጠላቶቿ መዘርዘር የሚችሉት ጥቂት ኃጢያቶቿን ቁጭ ብለው ይለቃቅማሉ፣ እኛ ደግሞ ሌተ ከቀን መልካም ስራ በመስራት ደፋ ቀና እያለች መልካም ስራዋን አብዝታ ቆጥረን ልንዘልቀው አልቻልንም!!

ስለ እነዚያ በኢስላም ስም ስለሚነግዱ ነጋዲዎች ንገሩኝ እስኪ? ቁጭ ብለው የሙስሊሙን ደካማ ጎን ጠብቀው ከማስተጋባት በስሜት እንዲጋልብ ከማድረግ የዘልለለ ለእስልምና ምን ውለታ ነው የዋሉት??
ንጉሶቿ ከየትኛውም ፖለቲካ እችላለሁ ከሚሉ የአለማችን ፖለቲከኞችና የሀገር መሪዎች የላቀ የፖለቲካ ብቃት ያላቸው ንጉሶች ናቸው!። ይህን የፖለቲካ ብስለትና ብቃትም እንደ ሀገራቸውና እንደመላው የአለም ሙስሊም ሀገራት ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማነፃፀር የላቀ ጥቅም በሚያስገኝ መልኩና ጉዳትን በሚከላከል መልኩ በአግባቡ ይጠቀሙበታል!። የማንም በዲኑ ስም የሚነግድ የፖለቲካ ነጋዴ ጩሀት ያለ አቅጣጫ እንዲሄዱ አያደርጋቸውም!።

አንዳንድ ሰዎች ለሳዑዲና ለንጉሶቿ ያለቸው ጥላቻ፣ አንዳንዴ የሚከሰቱ ኃጢያቶቿ እነሱ እንዲኖሩባቸው ከሚመኙዋቸው ከባባድ ወንጀሎች ህጋዊ ሆነው ከተስፋፉባቸው፣ ሺርክና ሰዶማዊናት  በግልፅ በመንግስት ደረጃ ፈቃድ አግኝተው ከተንሰራፉባቸው ሀገራት አንፃር እሩብ ያህል እንኳን ሀገሪቷ ላይ ኃጢያት ተንሰራፍቶ አይደለም!!

የሚደንቀው ሁል ጊዜ አል-ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን ሳዑዲን ለማጠልሸት የሚጥሩበትን መንገድ እንደየ ቦታው መለያየታቸው (መቀያየራቸው) ነው።

- ሸሪዓን ለሚወደውና ለሚደግፈው ለሙስሊሙ የህብረተሰብ ክፍል ልክ ለዲኑ እንደተቆረቆረ "ሳዑዲ ሸሪዓን ጥሳ እንዲህ አደረገች፣ እንዲህ አደረገች፣ በቃ እኮ አሁንማ ተበላሸች፣ አለቀላት፣  በአውሮፓዎች ቀኝ አገዛዝ ወደቀች…ወዘተ" እያሉ ያታልሉታል።

- አውሮፓዎች ጋር ሲሄዱ ደግሞ "ሳዑዲ አንባገነን ናት፣ ዲሞክራሲን አታከብርም፣ ሴቶችን አፍናለች፣ በነፃነት መናገር የለም…" የመሳሰሉትን እያሉ ሳዑዲ ላይ ያነሳሱዋቸዋል። ሁልጊዜም ትግላቸው ሳዑዲን እንደ ቱኒዚያ፣ሶሪያ፣ግብፅና ሊቢያ… ለማውደም ነው። እኔን ይበልጥ የሚገርመኝ ደግሞ እዚሁ ቁጭ ብሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሳዑዲን እንዲጠላ የሚያራግቡ የነ ሰልማነል አውዳ ቡችሎች ናቸው!።

በውስጧ ያሉት ኢኽዋኖች ለሳዑዲ ባላቸው ጥላቻ ከውጮች አይሻሉም፣ ውጪ ያሉት ከውስጦች አይሻሉም፣ ሆኖም ግን አላህ በረህመቱ ከሺዓም፣ ከአይሁድም፣ ከኢኽዋንም፣ ተንኮልና ሴራ ጠብቋታል!። ኢንሻአላህ ወደፊትም ይጠብቃታል!!።

አመራሮች ላይ ችግሮች የሉም ፍፁም ናቸው ማለቴ እንዳልሆነ ይሰመርበት!፣ ነገር ግን እንደ ኢስላም ሙስሊሙ ህብረተሰብ መሪውን ሲሳሳት በዓሊሞቹ መምከር ማስመከር ነው እንጂ፣ እየተቹ ከተቻለ ለጠላት አሳልፎ መስጠት፣ ይህ ካልተሳካም የእርስበርስ ጦርነት ቀስቅሶ የሙስሊሙን ደም ማፋሰስና ሸሪዓዊ ነገሮች እንዲወድሙ ማድረግ የዘመናዊ ኸዋሪጆች የኢኽዋኖች ልዩ መገለጫ እንጂ ፈፅሞ ሸሪዓው ያስቀመጠው የሙስሊሞች ስርኣት አይደለም!።

እኔ ሙስሊሙን ህብረተሰብ አደራ የምለው ነገር ቢኖር፣ የተውሒዷን ሀገር ሳዑዲንና ዓሊሞቿን አላህ እንዲጠብቅ፣ መሪዎቿን ሲሳሳቱ አላህ እንዲያስተካክላቸው ከልብ ዱዓ እንዲያደርግ ነው።
✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
አዎ! ሳዑዲ ውስጥም የተለያዩ ወንጀሎች ይሰሩ ይሆናል።
—————ክፍል 1
አንዳንድ ሰዎች ሳዑዲ ውስጥ አንዳንድ ወንጀሎች ሲፈፀሙ ሲያዩ ሳዑዲን ከሌሎች ሀገራት በተለየ መልኩ ሊጠሏት፣ ሊያብጠለጥሏት ይነሳሉ። ሳዑዲ ሀገር ማለት መላኢካ ነው ሚኖርባት ያለው ማን ነው?፣ የሳዑዲ ንጉሳን መላኢካ ናቸው አይሳሳቱም ያለውስ ማን ነው?፣ አላህ ፈጣሪያቸውን ብቻ እንደሚያመልኩና እንደማያምፁ የተናገረላቸው እኮ መላኢካዎች ናቸው።

ሳዑዲ ውስጥ የተለያዩ ወንጀሎች የንጉሳን ቤተሰብም ይሁኑ ህዝቦቿ ይፈፀሙ ይሆናል፣ ይህ ደግሞ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በነበሩበት ዘመንም አልፎ አልፎ ይፈፀም የነበረ ነው። ለዚህም ማሳያ አንዲት ሴት ዚና ሰርታ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጥታ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከወንጀሌ አፅዳኝ" ብላ እጅ እግሯን ለሸሪዓው መስጠቷ ተጨባጭ አስረጂ ነው። ይህ እንደ ምሳሌ ነው እንጂ ሌሎች ተመሳሳይ ክስተቶችም ተፈፅመዋል፣ በኸሊፋዎች ጊዜም ሰርቆ እጁን የተቆረጠ አልጠፋም።
ከዚያን ዘመን ጋር ካሉ ደጋግ ትውልዶችና አሁን ካለው ትውልድ ጋር ካሉ ታላላቅ ልዩነቶች አንዱ ልዩነታችንም ይህ ነው፣ በዚያን ዘመን እንደዋዛ ወንጀልን (ኃጢያት) የሚዳፈር አልነበረም፣ ተሳስተው እንኳን ወንጀል ላይ ቢወድቁ ትክክለኛ የሆነን ተውበት ሳያደርጉ ጌታቸውን መገናኘት ስለማይፈልጉ ህይወታቸውን አሳልፈው እስከ መስጠት የሚያደርሳቸው ቅጣት ቢሆን እንኳን ከልባቸው አምነው ይቀበሉታል። ለዚያም ነው ይህች ድንቅ ሴት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "ተውበቷ ለአለም ህዝብ ቢከፋፈል በበቃ ነበር" ያሉላት ሴት ማንም ሳያያት የሰራችውን ኃጢያት (ሀድ) እንዲቆምባት ተቀጥቅጣ እንደትገደል ወስና ወደ መልእክተኛው "ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጥታ "አፅዳኝ" ያለችዎት። አሁን ላይ እንዲህ ለሸሪዓው ታዛዥ የሆነን ትውልድ ማግኘት ርቋል።

ሳዑዲም በዚህን ጊዜ በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጊዜ ሶሃቦች ይዳኙበት በነበረው ዘላለም እንድንዳኝበት በታዘዝንበት የሸሪዓ ህግ ህዝቦቿን ወደውም ይሁን ተገደው የምትዳኝበት ብቸኛ ሀገር ናት። በሳዑዲም የሚሰሩ ኃጢያቶች አሁን ከምናያቸው ከሌሎች የአለማችን ሀገሮች ኃጢያቶች ጋር ያለው ልዩነትም ይሄው ነው። ሌሎች ሀገራት ላይ አንዳንድ ሰዎች ለሙስሊሙ ተቆርቋሪ አድርገው የሚስሏት ቱርክን ጨምሮ ኃጢያት በመንግስትና በሀገሪቱ ህጋዊ ተደርገው ይፈፀማሉ። ሳዑዲ ውስጥ ግን ፍቃድ ሊያገኝ ይቅርና ኃጢያት የፈፀመ ሰው በሸሪዓችን የሚገባውን ቅጣት ተግባራዊ ያደርጉበታል። ይህ ማለት አልፎ አልፎም ቢሆን የሀገሪቱን ህግ በሚፃረር መልኩ በአንዳንድ ባል ስልጣኖች አማካኝነት አይከሰትም ማለት አይደለም።

ይህቺ ናት ሳዑዲ…
ያገባ ሆኖ ዚና የሰራ ሸሪዓው በሚያዘው መልኩ በአደባባይ ተቀጥቅጦ የሚገደልባት ሀገር ማን ናት?! ሳዑዲ ናት።
ሰው የገደለ በሸሪዓው መሰረት የሚገደልባት ሀገር ማን ናት?! ሳዑዲ ናት።
የሰረቀ በሸሪዓው መሰረት እጁ የሚቆረጥባት ሀገር ማን ናት?! ሳዑዲ ናት።
የደዕዋ ሚኒስቴር አቋቁማ ከራሱዋ አልፋ ለሌሎች ለአለማችን ሀገራት ደዒዎችን በመላክ ደዕዋ በማድረግ ተውሒድና ሱናን የምታሰራጭ ሀገር ማን ናት?! ሳዑዲ ናት።
የተለያዩ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎችን አቋቁማ የዲን እውቀት ፍለጋ ከአለም ወደሷ ለሚጎርፉ ተማሪዎች ሙሉ ወጪያቸውን ችላ በነፃ ምታስተምር ሀገር ማን ናት?! ሳዑዲ ናት።
ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንቶች የሚፈልቁባትና ከእኛ ሀገር ለሄዱት ሳይቀር አመቻችታ አስቀምጣ እየተንከባከበች እንዲያስተምሩ ምታደርግ ሀገር ማን ናት?! ሳዑዲ ናት።

የሳዑዲ ንጉሳን ሁጃጆችን "የአላህ እንግዶች" ብለው ገንዘባቸውን አፍሰው፣ ጊዜያቸውን ሰውተው ተንከባክበው ተቀብለው ሺርክን የሚያንኮታክቱ፣ ተውሒድን የሚያነግሱ ድንቅ ኪታቦችን ስጦታ ሰጥተው በሰላም ወደመጡበት ሀገራቸው ይሸኛሉ።

አንዳንድ ሰዎች ለተከታዮቻቸው የሚያቀርቡት የማጭበርበሪያ ውሸት አለ፣ እሱም "ሳዑዲን ንጉሶቿን እንጂ ሀገሪቷንና ህዝቦቿን አንጠላም" የሚሉት ውሸት ነው። ውሸታሞች ናቸው!። ንጉሶቿ ቀና ባይሆኑ ሀገሪቷ ላይ የሸሪዓ ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን ባልፈቀዱ ነበር!፣ ንጉሶቿ ቀናነት ባይኖራቸው ኖሮ ሀገሪቷ ላይ ያሉ ኢስላማዊ ተቋማትን አዳክመው በበታተኑ ነበር፣ ንጉሶቿ የተውሂድና የሱና ጠላት ቢሆኑ ኖሮ ከሀገራቸው አልፈው አለም ላይ ለሚደረጉ ኢስላማዊ እንቅስቃሴዎች ገንዘባቸውን ባላፈሰሱ ተውሒድና ሱንና እንዲሰራጭ ትኩረት ሰጥተው ባልሰሩ ነበር።

ሌላኛው የቀጣፊዎች የቅጥፈት ክስ "ሳዑዲ ዑለማን ታስራለች" የሚል ወዳጆቻቸውንና ተጨባጩን የማያውቁ ሰዎችን የሚያጭበረብሩበት ቅጥፈት ነው። እስኪ ልጠይቅ፣ ሀገራችን ውስጥ ዓሊም ነኝ ብሎ የጠመጠመና ህዝቡን ከጠላቶቹ ጋር ሆኖ የሚያሰቃይ፣ አለያም ለጠላቶቹ አሳልፎ ሊሰጥ የሚችልበትን አይነት አካሄድ የሚሄድ ሁሉ ዓሊም ነውን?!፣ መልሳችሁ አይደለም! ከሆነ፣ አዎን! ሳዑዲም በዲን አስታከው ፖለቲካ ቀላቅለው ህዝቡን የሚያጭበረብሩ የሚያምታቱና ህዝብን ወደ ጥፋት የሚመሩ  የሸሪዓዋን ሀገር ለሌላ አደጋ ሊያጋልጣት የሚችል አይነት አካሄድ የሚሄዱ "ዓሊም ነኝ፣ ዳዒ ነኝ" ባዮችን ከጥፋታቸው እንዲመለሱ ታስራለች የተለያዩ ተመጣጣኝ እርምጃዎችን ትወስዳለች። የሚገባቸውን አይነት እርምጃ ባትወስድባቸውማ አሁን ያለችዋን ሰላም የሆነችዋን ሳዑዲን ማየት ይናፍቀን ነበር!። እንደ ቱኒስ፣ ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ የመን ሆና እናገኛት ነበር። እነዚህ ሀገራት በእንዲህ ያሉ የዲን ነጋዴዎችና አጭበርባሪዎች ለራሳቸው ተንደላቀው ተቀምጠው ምስኪኑን ህዝብ በማነሳሳት ለዚህ ሁሉ እልቂት መዳረጋቸው ሲገባው ሳዑዲ የምትወስድባቸው እርምጃ እውነታው ቁልጭ ብሎ ይታየዋል።

ሳዑዲ ምንም እንኳ የውስጥና የውጭ (የእልምናን ጭንብል ያጠለቁና ሙስሊም ያልሆኑ) ጠላቶቿ ቢበዙም በሀቅ ሰዎች ልብ ውስጥ ናት። አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ሳዑዲን ማብጠልጠል የሚፈልጉ ሰዎች በስሜትና በጭፍን ጥላቻ ታውረዋል። ሌላ መልካም ጎንዋን አይመለከቱም፣ ተራራ የሚያህል መልካም ስራዋን ጠጠር በሚያህል ስህተት ሊንዱት ይፈልጋሉ።

በእርግጥ! ጮሌና አዕምሮው ፈጣን የሆነ ሰው፣ የአለምንና የሳዑዲን ተጨባጭ ሁኔታ የሚያውቅ ሰው፣ ሳዑዲን የሚያጠለሹ ሰዎች ከጀርባቸው ምን ድብቅ አጀንዳ አዝለው እንደሆነ ጥቆማ ሳይፈልግም ይገበዋል። ቀጣፊዎች ሳዑዲ ላይ ያሻቸውን ሲቀጥፉባትና ጠጠር የምታክልን ስህተት እንደ ተራራ የሚያጋንኑትን ተግባራቸውን፣ አንዳንድ ሰዎች እውነት መስሏቸው የሚያምኑዋቸው ስለ አለምና ሳዑዲ ተጨባጭ ሁኔታዎችን በጭራሽ የማያውቁ አልያም ለነዚህ ቀጣፊ ሰዎች ጭፍን ተከታይ የሆኑ ናቸው።

ሳዑዲ!
ሱናን በማሰራጨት ቁ. 1
የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ በመከተል ቁ. 1
የሸሪዓ ህግን ተፈፃሚ በማድረግ ቁ. 1
እስልምናን በማሰራጨት ቁ. 1
ፍልጤንን ጨምሮ አለም ላይ ላሉ ችግርተኛና ተጨቋኝ ሙስሊሞች ፈጥና በመድረስና በመንከባከብ ቁ. 1
ትክክለኛውን ሸሪዓዊ እውቀት በማሰራጨት ቁ. 1
ለሱንና ሊቃውንቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት ቁ. 1
ለፍልስጤን ጉዳይ (ኢኽዋን በሚያጭበረብርበት መንገድ ሳይሆን) በትክክለኛው መንገድ ትኩረት በመስጠት ቁ. 1
ራፊዳዎችና ሺዓዎችን በማንበርከክ  ቁ. 1
የቢድዐ ሰዎችን እና ተክፊሮችን (ኢኽዋኖችን) በማንበርከክ ቁ. 1 ወዘተ…
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]


ፎቶው ላይ ጨረር ምናምን ያልተጠቀምኩት በደንቡ እንዲያስታውቅ ብዬ ነው ።


ይህን ታውቁ ነበር?


የኢስላም ጠላቶች በዚህን ያክል ነው ሙስሊሞችንና የሙስሊም ሃገርን ለማጠልሸት የሚሯሯጡት ተመልከት ፎቶውን እዴት አድርገው እዳቀናበሩት !!

ስንቶቻችን ነን ይህን ፎቶ ስናይ በማዘን ከንፈራችንን ስንመጥ የነበርነው ? እውነታው ግን ይህ ነው።
https://t.me/abuAmtullahHanif


Репост из: ጀግና ሴቶች
🟢ዘመናዊ ኸዋሪጆቾ

የሆነ የሙስሊም ሀገር ወይም መሪ ጥፋት ሲታይበት ወይም ተፈላፍሎ ጥፋት በማውጣት ማቀነባበር ፣ መንጫጨትና ዜና መስራቱ ረብሻ የሚያስነሳ የኸዋሪጆችና የኢስላም ጠላቶች አካሄድ ነው:: ህዝብ የማሳመፅ ልዩ ሴራም ነው:: ይህ ደግሞ በሙስሊሞች ላይ ከጭፈራ ፣ ከአስካሪ መጠጥ ፣ ከዝሙት ወዘተ የከፋ መዘዝ እና ውድቀት ያመጣል::

ኢስላማዊ መፍትሄ
በእንዲህ አይነት ሀገርም ሆነ መሪ ላይ ጥፋት ሲታይ ሙስሊም መሪዎችን በግል መምከርና ማስመከር ነው::ዱዓም ማድረግ :: አጥፊዎችንም በሸሪኣው ህግ መቅጣት::

እወቅ: ነቢያቶችም ሆኑ ምርጥ ተከታዮቻቸው በሚመሩት ማህበረሰብ ውስጥ ወንጀሎች ይሰሩ ነበር::

👌ችግሩ ሸሪኣዊ ከሆነ መፍትሄውም ሸሪኣዊ ይሁን:: ጫጫታና ግርግር በራሱ የከፋ ችግር ነው::

https://t.me/Abuhemewiya


Репост из: ድነል ኢስላም//መነሀጅ አልሰለፊያ//كوني منهج السلفية
🔷 ወንድማዊ ምክር

የሰውን ሐሳብ የኔ ነው ብላችሁ ስሙንና ሊኩን አጥፍታችሁ በቻናላችሁ ላይ የምትለቁ ይህ ተግባር በየትኛውም መመዘኛ ስህተት ነው ። ወንድሜ ሆይ እራስህን ለመሆን ሞክር , ምክንያቱም በሌላ የተሸፈነ ማንነት ሽፋኑ ተነስቶ መታየቱ አይቀርምና ። አንድ ሙስሊም ነኝ ከሚል ሰው እንዲህ አይነት ተግባር አይጠበቅም እንኳን ወደ ሱና ከፍ ብያለሁ ከሚል ይቅርና ።
አላህ ሰዎች እንኳን ባልሰሩት ስራ መመስገን ሊፈልጉ ይቅርና በራሳቸውም ስራ ሊመፃደቁ እንደማይገባ ካልሆነ ግን ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እንዲህ በማለት ይነግረናል : –
" لَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ يَفْرَحُونَ بِمَا أَتَوا وَّيُحِبُّونَ أَن يُحْمَدُوا بِمَا لَمْ يَفْعَلُوا فَلَا تَحْسَبَنَّهُم بِمَفَازَةٍ مِّنَ الْعَذَابِ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيم ٌ"
آل عمران ( 188 )
" እነዚያን በሠሩት ነገር የሚደሰቱትንና ባልሠሩትም መመስገንን የሚወዱትን አታስብ ፤ ከቅጣት በመዳን ላይ ናቸው ብለህ አታሰባቸው ፡፡ ለእነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው " ፡፡
ይህ አንቀፅ የዚህ አይነቱ ተግባር የሙስሊሞች አለመሆኑን ነው የሚያሳየን ። በዲን ጉዳይ አንድን ንግግር ስንወስድ ንግግሩን ወደ ባለቤቱ ማስጠጋት አማና ዒልሚያ በመባል ይታወቃል ። የእውቀት አደራ ነው ። ይህ ከሌለ አደራ እንደመብላት ይቆጠራል ።

https://t.me/bahruteka


Репост из: Muhammed Mekonn
የእናቱን ጡት ያጣ ህፃን
➶➶➶ እና  ↙️↙️↙️
ስልጣን ያላገኘው ኢኽዋን

❴ሁለቱም ሲያገኙ ዝም ይላሉ❵
【ሲያጡ ደግሞ ይጮሃሉ】


📝 قال شيخنا الشيخ محمد حياة الولوي حفظه الله تعالى፡
📝 ሸይኻችን ሸይኽ ሙሐመድ ሀያት አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ፦

🏝 «أهم الأمور عند الإخوان العلو على الكراسي فإذا فقدوها صاحوا  وإذا وجدوها راحوا  مثلهم مثل الرضيع إذا فقد ثدي أمه صاح وإذا وجده راح» اه‍ ¹

🏝 «ኢኽዋኖች ዘንድ ከአሳሳቢ ነገሮች ወንበር ላይ ከፍ ማለት ❴ስልጣን መያዝ ነው።❵ ወንበሯን ያጡ ጊዜ ይጮሃሉ
ያገኟት ጊዜ ደግሞ ይረካሉ። ምሳሌያቸው እንደሚጠባ ህፃን ነው። የእናቱን ጡት ያጣ ጊዜ ይጮሃልያገኘው ጊዜ ያርፋል (ዝም ይላል)»
    📚 ₁الدرة البهية صـ ٣٠

🏖 ምንኛ ያማረ እና ተጨባጩን ያማከለ ምሳሌ ነው። ኢኽዋኖች ማለት ትላልቅ ህፃናት ናቸው። በሀገራችን ያሉት ኢኽዋኖች ስልጣን በተነፈጉበት ጊዜ በማለቃቀስ ስንቱን ህዝብ መስዋዕትነት አስከፈሉ ስልጣኗን ሲያገኙ ግን ፀጥ አሉ። ልክ እንደህፃኑ ጡቱን ሲያጣ አልቅሶ አባቱን እህቶቹን ወንድሞቹን ሌሎችም በቤት ያሉትን በለቅሶው ይሰበስብና ጡቱን ሲያገኝ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ይላል ለሱ ብለው የተሰበሰቡትን ማመስገን አንኳን አይችልም። ኢኽዋኖችም ልክ እንደዚሁ ናቸው።

💡 እውነትም የሽማግሌ ህፃናት ናቸው።


📝 አቡ ዒምራን


🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy


Репост из: Um Redwan bint Mohamed_Aselfyit
{ وَإِن تَتَوَلَّوْا يَسْتَبْدِلْ قَوْمًا غَيْرَكُمْ ثُمَّ لَا يَكُونُوا أَمْثَالَكُم} ከዚህ የቁርዓን አያ ምን እንረዳለን?
Опрос
  •   ለዲኑ ብለን ዲኑን መርዳት እና መጠበቅ እንዳለብን
  •   ለራሳችን ብለን በድኑ ላይ ቀጥ ማለት እንዳለብን
  •   ከአዳድስ ፈጠራዎች መራቅ እንዳለብን
  •   መልስ የለም
61 голосов


የአህባሽና ካፊሮች እምነት
➶➶➶➶➶➶

🔎 በድምፅ ማስረጃ የታጀበ

🎙 በወንድም አቡ ዒምራን

📚 ከሸይኽ ሁሴን ኪታብ «ሸርህ ኡሱሉ ሰላሳህ» ደርስ ላይ ✂️ የተቆረጠ

👉 አህባሽ የተባለው የቆሸሸ እምነት ባለቤት በዚህ መልኩ ጭምልቅልቅ ያለ እምነት ይዘው ሌሎችን ከእስልምና ማስወጣታቸው ገርሞ ገርሞ ይገርማል!

አላህን በሆነች ሴት ልጅ አባት እያመሳሳሉ ግን ውሃብያ አላህን ከፍጡር ያመሳስላሉ ብሎ መጮህ ሳይከሱኝ ቅድሜ ልክሰስ እንደማለት ነው።

አቡበከር ሱለይማን የተባለው አህባሽ እምነቱን ከካፊሮች የተማረ እስከሚመስል የካፊሮችን ጥሪ ይናገራል።

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

Показано 20 последних публикаций.