Репост из: Bahiru Teka
ለመጨረሻ ውይይት ጥሪ ምላሽ
ቀደም ሲል ወንድማችን ኢብኑ ሙነወር ለውይይት ጥሪ በማድረጉ ምክንያት ፣ የውይይቱን ጥሪ ለመቀበል ሁለት መስፈርቶችን ማስቀመጣችን ይታወሳል ፡፡
መስፈርቶቹም ፣ በኢብኑ መስዑዶች ላይ አሁን ያላቸውን አቋም ግልፅ እንዲያደርጉና ፣ ክብርራቸውን የነኳቸውን መሻኢኾች ይቅርታ እንዲጠይቁ የሚጠይቁ ነበሩ ፡፡
የመጀመሪያውን መስፈርት በተመለከተ ፡-
ኢብኑ ሙነወር ይህን በተዘዋዋሪ መንገድ አቋማቸውን ግል አድርጓል ። ይኸውም : –
በመጀመሪያ ፁሑፉ ላይ ኢብኑ መስዑዶች የውይይቱ አካል ሆነው ሳለ እንደ መስፈርት መቅረቡ ተገቢ አለመሆኑን በመግለፅ ። በሌላ አባባል እነርሱ ሰለፍይ ናቸው ብለው እንደሚያምኑና ከኛ ጋርም ውይይቱ በዚህ ላይ እንደሚሆን በመግለፅ ።
በሁለተኛው ፁሑፉ ላይ ባህር ዳር ሄደው ከነ ሸይኽ ሐሰን ገላው ጋር ስለኢብኑ መስዑዶች ተወያይተው አሸንፎ እንደመጡ ለማሳየት ሞክሯል ። ይህም አሁንም በኢብኑ መስዑዶች ላይ ያላቸው አቋም ሰለፍዮች ናቸው የሚል መሆኑን ያጠናክራል ።
ሌላው ለዚሁ የውክልና ውይይት እኛን ኢልዛም ለማድረግ ከሰለፍ ዑለሞች እነ ኢብኑ ዐባስ ፣ ዑመር ኢብኑ ዐብዱል ዐዚዝ እንዲሁም ኢማሙ አሕመድና ከዘመናችን ዑለሞች ደግሞ ሸይኽ አልባኒ
ከኸዋሪጆች ፣ ከሙእተዚላዎች እና ኢኽዋኖች ጋር መወያየታቸውን በመጥቀስ ፣ "እናንተ ከነኢብኑ ዐባስ ከኢማሙ አሕመድና ከነአልባኒ ትበልጣላችሁ ወይ ..."? የሚል ጥያቄ አንስቷል ፡፡ ይህን ሀሳቡን የጀመረውም :–
" በያዘው አቋም መተማመን ያለው አካል እንዲህ አይነት ማሰናከያ አያቀርብም " በማለት ጭምር ነው ፡፡ እነዚህ ሁሉ ትርፍ ንግግሮች የተቃራኒ ወገንን ስሜት ለመንካት ታስበው የተሰነዘሩ ጉሸማዎች መሆናቸው ግልፅ ነው ::
እዚህ ላይ የወንድማችን ኢብኑ ሙነወር ሐሳብ እርስ በርሱ የተጋጨ ሆኖ እናገኘዋለን ። ከላይ እንዳየነው በውክልና ሊወያይላቸው የተዘጋጀላቸው የመርከዙ ሰዎች ሰለፍዮች ናቸው እንደሚል ነበር ። አሁን ደግሞ ከኸዋሪጅ ፣ ሙእተዚላና ኢኽዋን ጋር አመሳሰላቸው !!!! ። ከዚህ ጋር በተያያዘ መታወቅ ያለበት ነጥብ ማንኛውም ትክክኛ ሰለፍይ በማንኛውም የዲኑ ጉዳይ ቁርአንና ሀዲስን በሰለፎች ግንዛቤ ነው የሚከተለውና የሚተገብረው ፡፡ በዲን ላይ የሚደረግ ውይይትም ከዚህ ውጭ አይስተናገድም ፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን ነጥቦች ማየት ግድ ይላል ።
1– ኢብኑ ሙነወር የጠቀሳቸው ሰለፎች ከአፈንጋጭ ቡድኖች ጋር ያለ መስፈርት ወይም ቅድመ ሁኔታ የተወያያዩት ፣ ያፈነገጡት ቡድኖች አቂዳም ሆነ መንሀጅ ፍንትው ብሎ የታወቀ ከሆኑ አካላት ጋር ነው ፡፡ መንሀጃቸውን ፣ አቂዳቸውንም ሆነ አቋማቸውን ይፋ አድርገው እያለና ለዐቂዳቸው እየሞገቱና ወደ እሱም እየተጣሩ ፤ "መንሀጃችሁ" ወይም "አቂዳችሁ" ወይም "አቋማችሁ ምንድነው? መጀመሪያ እሱን አሳውቁን" ብሎ መጠየቅ ተገቢም አይደለም - ምናልባትም ቂልነት ቢሆን እንጂ ፡፡
ለዚህም ነው ኢብኑ ሙነወር የጠቀሳቸው ሰለፎች ይህን ጉዳይ መስፈርት ያላደረጉት ፡፡
የነኢብኑ ሙነወር የውይይት ጥሪ ግን ከሙኻሊፎቹ ጋር ቀጥታ ሳይሆን እነሱ ሙኻሊፎች አይደሉም ሰለፍዮች ናቸው ለሚሉዋቸ አካላት የውክልና ውይይት ጥሪስለሆነ ነው ። በኢብኑ መስዑዶች ላይ አሁን ያላቸውን አቋም ግልፅ እንዲያደርጉ የጠየቅናቸው ፡፡
የዚህ አይነት የውክልና ውይይት ከሰለፎች አልተገኘም ምናልባት ከዚህ በኋላ እነኢብኑ ሙነወር በቀደዱት ቦይ የሚፈስ ከተገኘ እንጂ ።
የኢብኑ መስኡድ ሰዎች ፣ በተለይም ደግሞ ከጥቂት ከአመታት ወዲህ በሀገራችን ላይ ከተከሰተው የፖለቲካ ለውጥ ጀምሮ እጅግ ግልፅ በሆነ የመንሀጅና የዐቂዳ ሙኻለፋ ላይ ላይ ወድቀው ተመለሱ ሲባሉ አሻፈረኝ ብለው ለአቋማቸው ወላእና በራእ መስርተው ይገኛሉ ፡፡ በመሆኑም ነው እኛ ከኢብ መስዑዶች ጋር ያለን ልዩነት የሚንሃጅና የዐቂዳ ነው ያልነው ። እነርሱ ማለት አሁን ከነ ኢብኑ ሙነውር ጋር የልዩነታችን ዋና ምክንያት ስለሆኑ ፣ እነኢብኑ ሙነወር በኢብኑ መስኡድ ሰዎች ላይ ያላቸውን አቋም ግልፅ ማድረግ ይኖርባቸዋል እያልን የነበረው ፡፡ አሁን አሳውቀውናል አልሐምዱ ሊላህ ።
እዚህ ጋር መታወቅ ያለበት ይህ ውይይት ከኢብኑ መስዑዶች ጋር ቢሆን ኖሮ ይህ መስፈርት የማይቀርብ እነደነበር ነው ።
2 – ሌላው ኢብኑ ሙነወር ከጠቀሳቸው የእነዚህ ሰለፎች ውይይት ፣ ሌላም ልንረዳው የሚገባ ትልቅ ነጥብ አለ ፡፡ እሱም በየዘመናቸው ከነበሩ አፈንጋጭ ቡድኖች ጋር ውይይት ያደረጉት አንዴ ብቻ ነው ፡፡ በመጀመሪያው ውይይታቸው አፈንጋጭ ቡድኑ ወደ ሀቁ ጎዳና ከተመለሰ እሰዬው ።
የተያያዘው የቢድአና የጥመት ጎዳና ልቡን ሰልቦት "አሻፈረኝ" ካለ ግን ፣ "መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ" ብለው ነው የሚተውት ፡፡ እናም ከአንድ አፈንጋጭ ቡድን ጋር ፣ በድጋሜ የተወያዩበት ሁኔታ የለም፡፡
አሏህ ሀቅን ለማየት ለወፈቀው ሰው ፣ ሀቅ ሁሌም ግልፅ ነው፡፡ የውሀ ወቀጣ አይነት ክርክር ፣ ውዝግብ ፣ ጭቅጭቅና ንትርክ አላስፈለጋቸውም ፡፡ ሀቁን እንዲያይ አሏህ ካልወፈቀው ደግሞ የፈለገ ጊዜ ያህል ውይይት ፣ ክርክር ቢካሄድ የሚገኝ ውጤት የለም - የልብ ድርቀትን ከመጨመር ውጭ ፡፡ ለዚህም ነው ሰለፎቹ የቢድዐና የጥመት መንገድን ከሚከተሉ ቡድኖች ጋር ከአንዴ በላይ ያልተወያዩት ፡፡ ይሄን ያደረጉት ግን በያዙት አቋም መተማመን አጥተውና ማሰናከያ ፈልገው አይደለም ፡፡
ለምን ይሆን ታዲያ እነ ኢብኑ ሙነወር የውክልናውን ውይይት ባህርዳር ሄደው አድርገው ከመጡ በኋላ በድጋሚ የፈለጉት ? ወይስ እነርሱ እዛ አሳክተነዋል ያሉት ድል !!!!! ለሁለተኛ ጊዜ ደግመውት ቲፎዞዎቻቸውን አስጩኸው ዋንጫውን ለኢብመስዑዶች በተመልካች ፊት ለማስረከብ ?
3 – ሌላው ልንረዳው የሚገባን ነጥብ - በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሰው እንደ ተጠበቀ ሆኖ - አብዛኛዎቹ ሰለፎች ከሙብተዲኦች ጋር ለውይይት አልተቀመጡም ፡፡ ከሙብተዲእ ጋር መወያያትን አጥብቀው ይጠሉ ነበር ፡፡ እንደውም ለውይይት መቀማመጥ ቀርቶ ለትንሽ ደቂቃም ቢሆን ከሙብተዲዖች ጋር መቀመጥን አምርረው ይሸሹ ነበር ። ይህ ነው የሰለፎች መርህ ። የቢዳዐንና የጥመት መንገድ ልክ እንደ ተላላፊ በሽታ ይፈሩት ስለነበር ፡፡
አሁን ነገሮች ተገለባበጡና "አህለ ሱና ነን" የሚሉ አካላት ራሳቸው ፣ "ለሙኻሊፎች ( መሻኢኾች ሙብተዲዕ ላሏቸው) ጠበቃ ሆነን ካልተከራከርን" የሚሉበት ዘመን መጣና ይሄውና ውይይቱ በአደባባይና በህዝብ ፊት ካልተደረገ ፣ "ሞተን እንገኛለን" አይነት ጥሪ በየጊዜው እያቀረቡ ይገኛሉ ፡፡ ውይይቱን በጃሂሉም ፣ የዲን እውቀትን ገና በመማር ላይ በሚገኘውም ፣ የመንሀጅን ምንነት በተረዳውም ፣ ባልተረዳውም ፊት "ካልሆነ አንወያይም" ማለትስ ያውም የውክልና ውይይት ከየትኞቹ ሰለፎች የተገኘ አካሄድ ይሆን ?
ለማንኛውም የዲን ውይይት ፣ የምርጫ ቅስቀሳ ካለመሆኑም በላይ ፤ የቲፎዞ ጭብጨባም ፣ አጨብጫቢም አያስፈልገውም ፡፡