የቡታጅራ ሰለፍዮች ዉዝግብና ከጀርባው ያሉ ሴራዎች


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ዳዕዋ ሰለፊያ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


■ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ለቡታጅራና አካባቢዎቿ ሰለፊዮች በሙሉ
እነሆ የፊታችን እሁድ ማለትም
●በቀን 11,10,2015
ታላቅና በአይነቱ ለየት ያለ የዳዕዋ ፕሮግራም መዘጋጀቱ ስናበስሮ በታላቅ ደስታ ነው ::

▪︎ተጋባዥ እንግዶች
-ውዱና የሙመይዓ የእግር እሳት የሆነው ወንድማችን
● ኡስታዝ በህሩ ተካ●ከአዲስ አበባ
-ኡስታዝ ኑሩአዲስ ከቡታጅራ
-ዶ/ር ሸምሱ ሳቢር ከቡታጅራ እና ሌሎቹም እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ኢንሻአሏህ::

■ቦታ ቡታጅራ ኹለፋውራሺዲን መስጅድ ወደ ሴራሚክ መሄጃ

ሰዓት 2:30 ከች ይበሉ

●ማሳሰቢያ
የዶበና ባቲ ተይዞ የነበረው ፕሮግራም በፕሮግራም መጋጨት ም/ት ወደ ሌላ ቀን ተዛውሯል ይቅርታ እንጠይቃለን

https://t.me/ene0925


Репост из: የሙሐመድ ልጅ
📌 የዳዕዋ ድግስ በሂጅራ መስጂድ

አሰላሙዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ

ውድና የተከበራችሁ የሱና ተከታይ እህት ወንድሞች እነሆ የፊታችን እሁድ ሰኔ 11-10-2015 ዓ/ል በስልጢ ወረዳ ዶበና ባቲ ቀበሌ ገ/ማህበር ውስጥ በምትገኘዋ በሂጅራ መስጂድ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በአይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ የዳዕዋ ድግስ ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተብስሯል። ይህን ፕሮግራም ለየት ያደረገው የተጋበዘው እንግዳ ኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን መሆኑ ነው። ስለሆነም ላልሰሙ ሙስሊም ወገኖች በማሳወቅ ከወዲሁ ተዘጋጅታችሁበት በጊዜው ቦታውን ትታደሙ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

🕌 ቦታው፦
- በቡታጅራ እና በኢንሴኖ መሀል ሌጃኖ አካባቢ ሲሆን
- "ኣደም ገዱ ሻይ ቤት ወራጅ ኣለ" ይበሉ
- በትልቁ መንገድ ወደ ፀሀይ መግቢያ
- (ወደ ውስጥ) ገባ ብሎ
#ሂጅራ/አዲሱ_መስጂድ

📞 ለበለጠ መረጃ፦
0926946490 ሐሰን
0916478873 በሕረዲን
0916690047 ዐብዱልሓኪም


📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይቀላቀሉን

👇👇👇

🌐 https://t.me/ensenoanasmesjid


Репост из: የቡታጅራ ከተማ ሙመይኦች ጉድ
ለወንድም ሙሐመድ ኸይሩ


"ሐቅን እንዳንቀበል የሚያደርጉ እንቅፋቶች"

ከእንቅፋቶቹ መካከል :-

$ አለማወቅ

$ ወገንተኝነት

$ መጥፎ ጓደኛ

$$የራስህ የገቢ ምንጭ ይኑርህ !!!

በተግባር ቢሆን የተሻለ ነበር ነገር ግን ከአንተ በላይ ወገንተኝነት የሚያጠቃው አካል የለም ለአብነትም ለኤሊያስ ለእነ ኢብኑ ሙነወር : ሳዳት : ስዒድ ሙሳ እና የመሣሠሉት ትወግናለህ።

ለሁሉም ነገር አዋቂ ነኝ እየልክ ያለ አቅምህ በጎግል ፈትዋ እየሰጠህ ያለሀው አንተው ነህ።

ለማንኛውም ሀቅን ለመከተል ከስሜትህ እና ከግትርነትህ ውጣ።

أخذ الكتاب والسنة بفهم سلف هذه الأمة

የቴሌግራም ቻናል  
https://t.me/YeButajiramumeyiaGud


Репост из: በመስቃን እና በቡታጅራ ሰለፊዮች የተጠለቀ ማነቆ
በቡታጅራ ጀምዓ ለይ የተቀጠፈ ቅጥፈት
                       
                       ክፍል (4)


በክፍል ሦሥት እንደተገለፀዉ ሁሴን ሱለይማን አል ወለንዪ ከአቋሙ ከወረደባቸዉ ነጥቦች ሁለተኛዉ (2) ነጥብ በክፍል ኣንድና ሁለት ስማቸዉ የተዘረዘሩ ሰዎች ከፊሎቹን በኢኽዋንነት ከፊሎቹ በሙመዪኣነት ሲያስጠነቅቅባቸዉ የነበሩ ሰዎች ናቸው።

በተናገረው መሠረት እዉነታም ነበር ምልክቶቹ በከፊሎቻቸዉ ጎልቶ ይታይባቸዋል።

ታዲያ ለምንድነዉ ከነሱጋር ወርደህ ሰለፊዮችን የምትዎጋዉ እነሱ ከፍ ብለዉ ነዉ ወይስ አንተ ዝቅ ብለህ ነው ሲባል----
እዲህ አለ :-

£~የተብሊግ : የኢኽዋን እንዲሁም የተምዪእ ፊክር፦ (ይህን ቃል ስለ ተጠቀመዉ ነዉ) ካለባቸዉ ሰዎችጋር አብረን ብንሰራ ምን ችግር አለዉ ብሎ ብዥታዎችን ለቃቀሙ

~ምን ችግር አለዉ ላለዉ መልስ፦ከኣቋም መዉረድ

                 ወደ ንግግሩ ስመለስ

(1). አብረን ብንሰራ ላለው ከዚህ በፊት እሱ እራሱ ይመልሰዋል ~~የኢኽዋን ቃኢዳ መሆኑን ያዉም በተሰማማንበት አንድ ሆነን እንተባበር በተለያየንበት (ኡዝር) እንስጥ የሚል ነዉ።

👆 ይህ የኢኽዋኖች ድብን ያለች ቃኢዳ ነች።

(2). እኚህ ስማቸዉ የተዘረዘሩት አካላቶች የኢኽዋን የተብሊግ የተምዪዕ ፊክራ ያለባቸዉ መሆኑን ያርጋግጣል ( ይህ ስላችሁ ሙመዪዓ ያለዉ ለማጭበርበር እንጂ እሱም ምን እደሆነ አያዉቀዉም  ለዚህም ነዉ ሙመዪዓ በጀምዓ የሉም ኣለ ( ልክ በኢብኑ መስዑድ መርከዝ ዉስጥ በመሪነት ያለዉ ዶ/ር አብዱ ኸይሬ እንዳለዉ አምሳያ)  ገና ከድር ከሚሴን እየጠየቀ ነዉ ሰለ ሙመዪዓ ለካ በማያዉቀዉ ነገር ገብቶ ነዉ አለ የለም እያለ ፈትዋ ሚሰጠው) ወይጉድ ትንሽ እዉቀት ራስምታት ነዉ።

ስለዚህ ሁሴን ተቀላቅሎበታል
የኢኽዋን ቃኢዳ እየተጠቀመ ኢኽዋን መተቸት እንደ ሙሀመድ ፈረጅ 🚚 አንዳንድ ሙሪዶቹ እንደሚሉት እኛ ከነዚህ ሰዋች የተጨመር ነዉ አላማችን ለማሳካት ነዉ ይላሉ

  አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት መፅሃፍ አጠበች

፦ይህ ሌላኛዉ የኢኽዋኖች ቃኢዳ ነው
الغاية تبرر الوسيلة
አላማ ለማሳካት ማግበስበስ
ስለዚህ ኣላማቸዉ ምንድንነዉ ማይክ መያዝ  ጠይቀዉ መጥተዉ ፈታዋ መሥጠት  ሌላዉ ክፍል ሁለት መለስ ብላችሁ አጥኑ

ይህም በስህተት ነዉ እንዳንል በድጋሚ ለነ ዶ/ር ሸምሱ እንዲህ አለ የመርከዙ ሰዎች እናንተ ሙብተዲዕ እያላችሁ እኛ ሰለፊይ እያልን አብረን መቀጠል አንችልም ወይ ይላል

قائدةإخوانية وهي
نتعاون فيما اتفقنا عليه ويعذر بعضنا بعضا فيما اختلفنا فيه
  أليس منكم رجل رشيد

ኧረ አንድም ተዉ ባይ የለም  ወዴት እያቀና ነዉ?

አላህን ፈርተን ከእልህ ከወገንተኝነት ያለ-እዉቀት ከመንዳትም ይሁን ከመነዳት እንዉጣ   መቃብር ብቻችን ነዉ የምንገባዉ

ከአቋሙ የወረደበት ሶስተኛዉ ነጥብ ቀጣይ ያአሏህ ፍቃድ ከሆነ

ይጠብቁን!!!!!!!!

اللهم احفظ مدنتنا من التميع كماحفظتها من الإخوان جماعة واهد اخواننا وثبتنا على منهج السلف آمين آمين

የቴሌግራም ቻናል  
https://t.me/+crM7apacJa5mMDNk


Репост из: ሀሠን ስርዋና
السلام عليكم ورحمةالله وبركاته
አስደሳች ዜና
👉 ለኢንሴኖ እና በዙሪያዋ ለምትገኙ እውቀት ፈላጊዎች በሙሉ ታላቅ የምስራች ይዘንላቹህ ብቅ ብለናል ነገ ሰኞ (28/9/2015)በጥዋቱ ክፍለግዜም በማምሻውም ክፍለግዜ ቂርዓት የምንጀምር መሆኑን እናበስራቹዋለን የዶክተር ሸምሱ ኢዕላሙ ዱዓት ከአሱር በኃላ ይጀምራል
👌 وقال محمد بن سيرين -العلم دين فالنظر أمن تأخذون دينكم
👆ዲናዊ እውቀትን መፈለግ እራሱ ዲን ነው ከማን እንደምታነሱት ተመልከቱ =ከማንም ከሙብተዲዕ ሰው እውቀትን አትውሰድ ማለት ነው ፅድት ካለ ሰለፍይ ዕውቀትን ውሰዱ ማለትነው
አላህ ይወፍቀንን አሚንንንንን
👉 ቦታው በገነሜ መስመር በኮብሉ ላይ(መድረሰቱ ነስር) አዲሱ መድረሳችንን ጎራ ይበሉ !!https://t.me/+ZYQZSILqsokzZTBk


Репост из: " ዓብዱረህማን ዑመር"
ሙስሊሙ ሆይ ሰልፍ እያልክ መውጣትን ይመስል፣ ሸሪዓ የከለከለህን ከመስራት ተቆጠብ! ስሜታቸውን የሚከተሉ ሰባኪዎችን ተከትለህ ሸሪዓ ያልፈቀደውን ነገር አታድርግ ትዋረዳለህ። እያንዳንዱ ነገር ስትሰራ የቁርአን የሀዲስ መረጃውን ጠይቀህ መሆን አለበት።
ሴቶች ደግሞ ከወንድ ጋር መዝለል ምንዲን ነው? ሸሪዓ የከለከለሽን ተዳፍረሽ ብትደፈሪ ራስሽንም ሸሪዓንም አስደፍረሻል።

✏️
ወደ ዋናው ጉዳየ ስገባ፣ እንደ ሳልባጅ ነጋዴ አስፓልት ዳር፣ ገበያ ላይ፣ የረከሰ እምነት ግድ ካልተሸከማችሁ የሚሉ ጼንጤዎች! ያ፣ አላዋጣቸው፣ አልበቃቸው ብሎ አሁን በግዲያ ገብተዋል።

ይሄንም እቅዳቸውን ቀደም ሲል፣  ራሳቸውን አስተማሪ ነን ብለው፣ በህዝብ ትከሻ ላይ በተቀመጡ ዱርየ ፓስተሮች፣ በርካታ ህዝብ በተሰበሰበበት አዳራሽ፣ በሙዚቃ ክላሲካል በጭፈራ ታጅበው፣ "ከአሁን በኋላ እያባበሉ መስበክ ቀርቷል። በሀይልና በስልጣን ነው።" ሲሉ ተደምጠዋል ።

በጼንጤ አስተሳሰብ የሚመራው የሀገራችን ታጣቂ ዛሬ አኗር መስጅድ ለጁሙዓ ሶላት ለመስገድ በሄደው ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ አሰቃቂ ትእይንት ፈፅሟል።

የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
https://t.me/Abdurhman_oumer
-


Репост из: ابدلكريم حسن
👉  ሰለፍይነት በድምፅ ብልጫ አይደለም ።

   የሰለፍያ ዐቂዳና ሚንሀጅ በዋነኝነት በወላእና በራእ ( ሙወሒዶችን በመወዳጀት ፣ በመተባበር ፣ በማክበር ከጎናቸው በመሆን, የቢዳዓ ባልተቤቶችን በመጥላት ፣ በመራቅ ፣ በማሳነስ ፣ በማዋረድ ፣ ከእነረሱ በማስጠንቀቅና ለባጢላቸው ምላሽ በመስጠት)  ላይ የተመሰረተ ነው ። ይህ ነው የሰለፍይነት መለኪያ ። አንድ ሰው ሰለፍይ መሆኑና አለመሆኑ የሚታወቀው ለሙብተዲዖች ባለው ጥላቻና ከእነርሱ በመራቁ ነው ። እገሌ ሙብተዲዕ ነው የሚባለው ይህን አስል ጥሶ ወይም ከሙብተዲዕ ጋር ተወዳጅቶ አብሮ ሲቀማመጥ ፣ አብሮ ሲበላ ፣ የዲን ስራ አብሮ ሲሰራ ፣ እሱን ሲያወድስ ፣ በነርሱ ላይ ረድ ሲደረግ የሚከፋውና የሚበሳጭ ከሆነና እነዚህ አካላት ሙብተዲዕ መሆናቸው በመረጃ ተነግሮት አልመለስም ሲል ነው ። የዚህ አይነቱ ሰው ወደደም ጠላም ሙብተዲዕ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰለፍይ ነው ብለው ቢጮሁም ። ሌት ከቀን ቢፅፉም ። ለሙብተዲዕ ዲፋዕ የሚያደርግ ፣ ሙብተዲዕን የሚያወድስ ፣ ወደ ሙብተዲዕ ሰዎችን የሚጣራ ሰለፍይ የሚሆነው በሙብተዲዕ አእምሮ ውስጥ እንጂ በሰለፍያ ሚዛን አይደለም ። እንዲህ አይነቱን ሰው ሰለፍይ ነው ለማሰኘት ድምፅ ማሰባሰብና ተከታይ ማብዛት ከዛው ጎራ እንዲመደብ የሚያደርግ እንጂ ሌላ ውጤት አያመጣም ።
    ሰለፍይነት ማንም ሰው የወደደውን የሚያስገባበት የጠላውን የሚያስወጣበት ጎጆ ቤት አይደለም ። የራሱ ሚዛን ያለው መመለሻው ወደ ቁርኣንና ሐዲስ ሆኖ በሰለፎች ግንዛቤ ተግባራዊ የሚደረግ መርህ ቢሆን እንጂ ።
በሀገራችን የዳዕዋ ታሪክ ይህን መሰረት ሲያስተምሩ የነበሩ አካላት በተለያየ ጊዜ በተለያየ ምክንያት ያስተማሩትን የሰለፍያ መርህ ጥሰው ወደ ቢዳዓ አንጃዎች እየገቡ ወጣቱን ለማደናገር ሰለፍዮች ናቸው የሚል ድምፅ ሲያሰባስቡ ይታያል ።
🔹 ከእነዚህ አካላት አንዱ የሆኑት የኢብኑ መስዑድ ሰዎች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች በሰለፍያ መርህ ላይ በነበሩበት ጊዜ በኢኽዋኖችና ሱፍዮች መካከል የተደረገውን ስምምነት የሰለፍያን መርህ የናደ የቀደምቶችን መሰዋእትነት ዋጋ ያሳጣ ስምምነት ነው ትክክለኛን እስልምና አይወክልም ብለው ረድ አድርገው ህዝበ ሙስሊሙን ከኢኽዋን መሪ የሆኑት ከዶክተር ጀይላንና ሙሐመድ ሓሚዲንና ከመሳሰሉት አስጠንቅቀው ሰለፍዮች አለመሆናቸውን በአደባባይ አውጀው ነበር ። ይህ የኢብኑ መስዑዶች አቋም እንቅልፍ የነሳቸው የኢኽዋን መሪዎች በዋና ዋና የኢብኑ መስዑድ ሰዎች ላይ ስራ መስራት ጀመሩ ። ያለመሰልቸት በሚገርም ትእግስት እቅዳቸውን ለማሳካት የሰሩት ኢኽዋኖች ያለሙት እውን ሆኖ የመርከዙን ሀላፊዎች በመረባቸው ጠልፈው በተራቸው የመርከዙ ሰዎች በአደባባይ ከሱፍዮችና ከኢኽዋኖች ጋር አንድ ነን አሉ ። አንድነታቸውንም አብረው በመብላትና በመጠጣት ለህዝበ ሙስሊሙ አሳዩ ። በመቀጠልም በሂደት መርከዙ ወደ ጎራቸው  እንዲደባለቅ አደረጉ ከዚያም ከመጅሊሱ የስልጣን ፍርፋሪ ለቅምሻ ያክል ጣል አድርገውላቸው ከስራቸው ሆነው ጭራቸውን እንዲያስለመልሙ አደረጉዋቸው ። ‼
 🔹 ሁለተኛው አካል የዚህን የመርከዙ ሰዎች ሚንሀጅ ቀይሮ ከኢኽዋን ጋር መስራት በዋነኝነት ሲዋጉና ሲያስጠነቅቁ የነበሩት እነኢብኑ ሙነወር ናቸው ። የነኢብኑ ሙነወር የረድ ብትር መቋም የከበዳቸው የመርከዙ ሰዎች ከአለቆቻቸው ከነዶክተር ጀይላን በተሰጣቸው የቤት ስራ መሰረት ቀን ከለሊት በእነርሱ ላይ መስራት ጀመሩ በማይታመንና ግራ በሚያጋባ መልኩ እንዲህ አይነት ከሙታን መንፈስ አምላኪዎች አንድ ከምንሆን ቀባሪ አጥተን ጀናዛችን አሞራ ይብላው ብለው የመርከዙ ሰዎችን የአንድነት ጥሪ ሲያወግዙና ኢኽዋን በዘፈነ ቁጥር ካላጨበጨብኩኝ ማለት ምንድነው ደመረኩሙላህ ሲሉ የነበሩት እነኢብኑ ሙነወር አቋም ቀይረው የመርከዙ ሰዎች ሰለፍዮች ናቸው ብለው ድምፅ መስጠት ጀመሩ ። በዚህ አላቆሙም ድንበር ታልፎባቸዋል በእነርሱ ላይ ብይን የሰጡ ዑለሞች ብይናቸው ተቀባይነት የለውም ችኩል ናቸው የሚሉትን አያውቁም ሽበታቸው የእንጨት ሽበት ነው ውሸታሞች ዘግይተው የመጡ ሀዳድዮች ናቸውና የመሳሰሉ ዘለፋና ብይን መስጠት ጀመሩ ።‼ እነዚህ አካላት ሰለፍይነት በድምፅ ብልጫና በተከታይ ብዛት የሚለካ ይመስል የወጣቱን አእምሮ ከመመዘኛው አውጥተው የተለያየ ቀመርና አመክንዮ በመደርደር ሰለፍዮች ናቸው ብሎ ከባድ መሀላ እንዲምል ማድረጉን ተያይዘውታል ። ይሁን እንጂ ሁሉም ሊያውቀው የሚገባው አሁንም ሰለፍይነት በድምፅ ብልጫ አለመሆኑን ነው ።
አላህ ሐቅን አውቀን የምንከተለውና ባጢልን አውቀን የምንርቀው ያድረገን ።

https://t.me/bahruteka


■ታላቅ የምስራች ኢንሴኖና አካባቢዎቿ ለምትገኙ ሰለፍዮች

ዛሬ ጁምዓ ምለትም በቀን 18/09/2015
ከአስር በዃላ ዒዕላሙ ዱዓት በዶ/ር ሸምሱ ሳቢር ደርስ ስለሚጀመር ኢንሴኖ ኢማሙ ሻፊዒይ መስጅድ ጎራ ይበሉ::

ማሳሰቢያ
በዚህ ፊትና በበዛበትና ዳዕወተ ሰለፊያን እንደነበረ ለማስቀጠል እውቀትን መታጠቅ አስፈላጊ ነውና ጊዜዎን መስዋዓት አርገው እንዲገኙ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን::


🟢ከኢብኑ ሙነወር ሸሮች 1⃣

🟢 እንደ ኢብኑ ሙነወር ከሆነ  "የኸዋሪጆች ሀዲስ ውዳሴ ወይም ሙዋዘና አለበት። ስለዚህ ረድም ቢሆን ውዳሴ ቢኖርበት …"

👉ሰው በጥፋቱ ይወደሳልን⁉️

👉ከዚህ የከፋ ገደል ውስጥ ሳትገቡ በፊት ከእልህና ከተመዩዕ ውጡ ❗️

https://t.me/Menhaj_Alwadih
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Abumahiraselefiy
https://t.me/Abumahiraselefiy


Репост из: " ዓብዱረህማን ዑመር"
አሁን ይሄን ፁሁፍ ብትመለከት የዛሬ አምስት አመት ገደማ  ኢብኑ ሙነወር በሰዓቱ ተጣልቷቸው የነበሩ አካላቶችን እነ ኢልያስንና እነ ዶክተር ጀይላንን ለማስፈራራትና ህዝቡን ከነሱ ጉያ አውጥቶ ወደ ትክክለኛ ዓሊሞች ለመመለስ ሲኳትን በነበረበት ወቅት ስለ ታላቁ የሀገራችን ዓሊም ስለ ዱክቱር ሸይኽ ሁሴን አስልጤ የፃፈው ነበር። ዛሬ ላይ ግን ከአቋማቸው ሲንሸራተቱና መንገድ ሲስቱ ሸይኹ (ሸይኽ ሁሴን) ልክ እንደ ልማዱ በነ ኢልያስ ላይ ሲያደርገው የነበረውን የብዕሩን ነበልባል ሲያቀምሳቸው በግልፅም በስውር የሚያደርጉትን ማጠልሸት አትጠይቅ!

#እኛ_አሁንም_እንላቸዋል!
አዎ! ሸይኻችን አሁን ላይ ለረጅም አመታት በሸመቱት እውቀት ሀገር እየጠቀሙ ነው።

ለዱዓው አሚን ብለናል! እናንተንም አላህ ወደ ነበራችሁበት ብርሃናማ መንሀጅ ይመልሳችሁ!

የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
https://t.me/Abdurhman_oumer/4857
-


ሰበር መረጃ
ዛሬ እሁድ ከዝሁር በዃላ ዅለፋው ራሺዲን መስጂድ ኡስታዝ ሻኪር በድንገት ስለተጋበዘ ላልሰማ በማሰማት የፕሮግራሙ ተሳታፊ ይሁኑ


✅ ሙመይዓዎች ይህንን ሁሉ ዲንጋይ የሚፈነቅሉት ለምን የመርከዙ ሰዎች ተነኩ ብለው ነው። እሚያቀራውንእና የሰውየውን ተግባር ተመልከቱ!

አሁንም እነዚህ ሰዎች እዛ እዚህ እያሉ እሚያጭበረብሩት ከመርከዙ ሰዎች ለመከላከል ነው!

⚠️የዚህ አይነት አላዋቂዎች እና የሱ ተከታዮች ናቸው እንግዲህ ሰለፍያን ከፊት ሁነን ካልመራናት የሚሉት❓

" አሁን ይሄንን ሰውዬ ጤነኛ ነው ብል ጤነኛ ሰው ያምነኛልን?"

https://t.me/abunehla


Репост из: በመስቃን እና በቡታጅራ ሰለፊዮች የተጠለቀ ማነቆ
በቡታጅራ ጀምዓ ለይ የተቀጠፈ ቅጥፈት
                         ክፍል (3)

''ሆድ ከጠገበ /ጥርስ ከበላ አይን ያፍራል'' ይባላል።

ለማንኛዉም ጉዳዩ እንዲህ ነዉ በክፍል ሁለት እንደተገለፀው የሆነዉ ከሆነ በዃላ እንዲህ አለ (ላክልላችሁ ካላይ በክፍ 2 የተገለፀዉ እዉነታ ማጤን እና መቀበል ትተው የሙሪድነት አባዜ የተጠናወታቸዉ አካላቶች ለምን ተፃፈበት እያሉ አድማስ መዳሰሳቸዉ ነዉ የሚገርመዉ መሆን የነበረበት ምስጥሩን ለምን ይፋ ሆነበት ሳይሆን እንኳን ይፋ ሆነልን ተብሎ የችግሩን ባለቤት ማን እደሆነ ማወቅ ነበር ትዝ አለኝ ሱፊይ ብለን የምንወርፋቸዉ ሙሪዶች ሼኼ ጀሃነም ከገባ እኔም ልግባ ይላሉ (ዉርስ)።

በጣም የሚገርመዉ የሰዉዬዉ ችግር ገና ሳይነካ መንቀዥቀዣቸዉ ነዉ።
እንኳን ለመፃፍ የዘገነኑኝ ሚስጥርች አሉ በዚሁ ከቀጠለ ግልፅ ማዉጣታችን አይቀርም።

ወንድማዊ ምክር አይኔ ግንባር ከላለ በስተቀር የማይክዳቸዉ እዉነታዋች ናቸዉ።

በተከታዮቹ ያለዉ ግዴታ በእዉነት ወዳጆቹ ከሆኑ እሱን መምከር እንጂ ፀሃፊዉ ለማወቅ ቤት ለቤ እና ሱቅ ለሱቅ መዞር አልነበረም።

አንዳንዶቹ ለምን ስሙ ተጠራ ሌሎች ደግሞ ለምን አገሩ ተጠቀሰ ለመሆኑ አገር አልባ ልታረጉት ነዉ? ለማንኛዉ ፀሃፊዉ ከእናንተ በላይ ጓደኛና ሚስጥር ተካፋዩ ነበርኩ አሏህን ፈርተን በድፍን በጭፍን ከመነዳት ከትላንትናዉ አቋም የዛሬዉ መቀየሩን ማማዛዘን ነው።

እሱ ግን አልተቀየርኩም ይላል ዉፍረትና ዉሸት ለባለቤቱ አይታወቀዉም።
ለማንኛዉ የተዘረዘሩት ከአቋሙ ዝቅ ያለበት ሰበቦቹ ሲሆኑ በመንሃጁ የወረደባቸዉ ጉደዮቸ አንድ ብዬ ልጀምርላችሁ)

1. ሙመይዓ የሚባል በጀሞዓ ደረጃ የለም ባህሪ ነገር ነዉ በማለት በተጠየቀዉ ጥያቄ በቅዠት መልኩ መለሰ ተመልከቱ በአለም አቀፍ በታላላቅ ኡለማዎች ሊቆች የጥሜት አንጃ መሆናቸዉን  በኪታቦቻቸዉ በድምጽ በማስረጃ ያረጋገጡት በዚህ መልኩ አስተባበለ ዶሮ ሲያታሉላት በመጫኛ አሏት ይህንን በተመለከተ ምናልባት አሁን ካለበት አቋም እስካልተመለሰ ድረስ በሌላ ጊዜ ከነድምፁ እመለሳለሁ። ኢንሻ አሏህ

ወደ ርዕሱ ልመለስ  በዚህ መልኩ ባስተባበለ ጊዜ ትላንትና ምንም ከማንም እንደላስጠነቀቀ አዲስ ካባ ለበሶ በዛን  ጊዜ ቀዉጢ ፈላ ጥያቄ በጥያቄም ሆነ ይሄኔ በተለመደዉ መልኩ በዉስጥ መስመር ስራዉን ቀጠለ አሊሞችን በመተቸት ብሎም መርጂዕ አሊሞች ኢትዮጵያ ዉስጥ የሉም እያለ ራሱን መቆለል ብሎም የሱ አቋም ያልተከተሉ በሙመይዓ ጠንካራ አቋም ያላቸዉ  እንደ ተለመደዉ ስያሜ በመስጠተ ለከፊሉ ከፍ ብሎዋል ኧረ እንኳን ሚዘገንን ስያሜ አልቀረዉም ''ዉሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው'' ይባላል።

ከማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይ ኖራቸዉም ዉሸት መለጠፍ በየመስጂዱ የሚያስቀሩ ኡስታዞች ደረሶች ከሚያባርሩ ሰዋች ጋር ኋላ ኋላ በመሄድ ብሎም ኡስማን መስጂድ በአካል በመገኘት የማባረር ስራ ሰርቶ እያለ ደረሶች በተኑብኝ እያለ ዉሸት መለጣጠፍ የሚገርመዉ እሱና መሰሎቹ የሚሰሩት ደባን ቅጥፈት ወደ ሌላ ማላከካቸዉ ነዉ።

ትላንትና ከምታስጠነቅቅባቸዉ ሰዎች ጋር ለምን አብረህ ትዘምታለህ ሲባል ምንአለ መሰሎቹስ ደግሞ ደረሶች ከቂርዓት ከመስጂድ የማባረር ዘመቻ አጃቢ የማብዛት እና የይምረጡኝ ዘመቻ አምሳያ ቅስቀሳ ከእነማን ሰፈር   ይጠብቁን።

ኢንሻ አሏህ¡¡

اللهم احفظ مدنتنا من التميع كماحفظتها من الإخوان جماعة واهد اخواننا وثبتنا على منهج السلف آمين آمين


Репост из: " ዓብዱረህማን ዑመር"
ያ ሰለፍይ! በውሸትና በተረት ተረታቸው ቢዚ አትሁን! ይልቅ ስራህን ስራ! አቋሙን ለቆ የተንሸራተተ አካል ውድቀቱን ለመሸፈን የማይገባበት ሽርንቁላ የለም! ቢያመቻቸው ኖሮ ሀጃዊራህ ናቸው ሊሉን ነበር ጅማሯቸው! ዘግይተው መምጣታቸው እንጅ ሀጃዊራህ ናቸው ብለው የነበሩ ሰዎች፣ ታዲያ ሌላ ውንጀላና ውሸትማ ለነርሱ ምናቸው ነው!?
|
https://t.me/Abdurhman_oumer


Репост из: Muhammed Mekonn
ስለ ሀራው ፕሮግራም መረጃ ከፈለጋችሁ...
➺➺➺➺➺➺➺


የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የሱንና ወዳጆች በቅርቡ በሚካሄደው ታላቅ እና አጓጊ ፕሮግራም ዙሪያ አንዳንድ ጥያቄዎችን እያነሳችሁ ነው። በተለይ ሀራ የት አካባቢ ነው!? የሚለው የብዙዎቻችሁ ጥያቄ ነው።

አድራሻቸውን በተመለከተ፦
ሀራ ከተማ ማለት በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ከወልዲያ ከተማ በ23 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጡ እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጅት ላይ ነች።

ከደቡብ የወሎ ክፍሎች የምትመጡ ከደሴ መሳፈር ትችላላችሁ።
ከደቡቡ የሀገራችን ክፍል ከአዲስ አበባ እና ሰሜን ሸዋ አካባቢ እንዲሁም በከሚሴ በኮምቦልቻ በደሴ ዙሪያ የምትገኙ በሙሉ ከደሴ ወልዲያ በመጓዝ ከወልዲያ ደግሞ በ30 ትራንስፖርት ወደ ሀራ መግባት ትችላላችሁ!


በተጨማሪም ማንኛውንም መረጃ ከፈለጋችሁ በሚከተሉት ስልኮች ወንድሞቻችሁን ማነጋገር ትችላላችሁ!

1ኛ አቡ መሥኡድ ሙሀመድ ሠይድ
📲📲📲 0922936435
2ኛ አቡ አማር ጉማታ ሠይድ
📲📲📲 0921522566
3ኛ አወል ሙ አዚን
📲📲📲 0914148290
4ኛ አቡ ኡሠይሚን ሁሴን ሊበን
📲📲📲 0913887868
5ኛ አቡ ሂላል  ኑራድሥ ሙሀመድ
📲📲📲 0973292577


■የሙሪዶች ጋጋታ■

አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድና የተከበራቹ ሰለፊይ እህትና ወንድሞች እንዴት ናቹህ?አላህ ሰላማቹ ያብዛልን እያልን በሰሞኑ በአንድ ወንድማችን በተለቀቀ ፅሁፍ ላይ ትንሽ ነገር ልበል ብዬ ነው::

●በመሠረቱ ስለ ፅሁፉ ምንነትና ማንነት አይደለም ማውራት ምፈልገው::
እኔ ጥቆማ መስጠት ምፈልገው በጣም በሙሪድነት ለጦዛቹ ወንድሞች ነው::

♤▪︎እኔ ምለው ሙሪድነት ብሎ ማለት ምን ማለት ነው?
ኧረ ወገን እንንቃ እንጂ!!!
☆ሸሪዓው እኮ ሚያዘን ሀቅን እወቅ የሀቅ ባልተቤቶችን ታውቃለህ ነው::
እናንተ ግን መንሀጅን ከግለሰብ ጋር አቆራኝታችሁ ሲያለቅስ ታለቅሳለህ ሲስቅ ትስቃለህ::
♡እዚ እዚ ቦታ ተሳስቶዋል ስትባሉ አንተ ከሱ ተሽለሀል ወይ?አንተ ማነህ?የሚል ጥያቄ ታመጣላቹ::ም/ቱም ያለምንም ማጣራት እሱ እና መሰሎቹ እውነት ያሉት እውነት ውሸት ያሉት ደግሞ ውሸት ማለቱና ስለ አንድ ነጥብ ማስረጃ ቢጤ ብለው ያቀረቡት ነገር ካለ ሲናገሩ ካስነጠሳቸው እያስነጠሳቹ copy-paste አርጋቹ ታቀርባላቹ ሀቅን የኻለፈ ይሁን አይሁን አይጣራም¡¡¡ እንዴት እነሱ ናቸዋዋዋ::

■ታዲያ በአባቶቻችን ለምን እንፈርዳለን ?ምንም እንኳ ደረጃው ቢለያይም እነሱም እኮ እገሌ ወልይ ጀሀነም ከገባ እኔም ልግባ ይሉናል::መረጃ መጣ አልመጣ"::
ይህም ማለት መንገዳቸው መንገዴነው ማለታቸው ነውና ልንጠነቀቅ ይገባል::ሀሳቤ ግልፅ ነው!!!!::

እኛም ደግሞ መርጦ ማልቀስ የለምና መረጃ አልከተልም ላለ ሁሉ ሰይፋችን የሰላ ነው::

●በመጨረሻም■
እሺ በቃ ፈርደን ወተቅዲረን በወንድማችን ተቀጠፈበት ብንልና ሀቅ ላይ ነው ብላቹ ምታምኑ ከሆነ ረሱል( ሰዐወ) ሳሂር እብድ ተብለዋል እኮ::
ወይስ የሱ ክብር ከረሱልም[ ሰዐወ] ክብር በላይ ነው???

●ከዚ በላይ ሙሪድነት አለ???አላሁልሙስተዓን::


🟢 ሀቅን ሸፋፍኖ ማለፍና መደበቅ?


🟢የፈትዋ ቁጥር 1⃣7⃣4⃣




መልስ
🔊አሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አለተሚይ


በዚህ የፈታዋ ብቻ ቻናል⤵️
https://t.me/FATTAWAS


የፈትዋ ጥያቄ ለመጠየቅ⤵️
https://forms.gle/1iDs6V7JPMHREx4GA




Репост из: በመስቃን እና በቡታጅራ ሰለፊዮች የተጠለቀ ማነቆ
በቡታጅራ ጀምዓ ላይ የተቀጠፈ ቅጥፈት
ክፍል(1)
ጉዳዩ እንዲህ ነው ከስር መሠረቱ ለማየት ጊዜ ቢፈልግም ገረፍ ለማድረግ/አጠር ለማድረግ ልሞክርላችሁ እንደሚታወቀዉ ኣንዳንድ ኣባቶች እንደሚናገሩ ቡታጅራ ከተማ ዉስጥ በኣህሉ አስሱና ወል ጀምኣ ቡዙ ጥቃቶች ደርሶባቸዋል ኣንዳንዴ መስገጃ ቦታ በማጣት ኣንዳንዴ መቅሪያ ቦታ በማሳጣት ሲንግላቱ ቆይተዋል ለዚህም በቂም ሥክር ሼ/ሚፊታ በመባል የሚታወቁ ኣሊም ናቸዉ እርሳቸዉ መቼም ታሪክ አይረሳም አንድ አባት እንደነገሩኝ እርሳቸዉ  መድረሣ በመባል በሚታወቀዉ መሥጅድ ኹጥባ ለማድረግ በቆሙበት ጊዜ ነበር ከሚንበሩን ታንቀዉ የተወረዱት ለምን? የሚለዉ የብዙ ሠዋች ጥያቄነዉ ይሁን እንጂ እዉነታዉ እንዲህ ነበር በጊዜዉ ካሉ ሠዎች በእዉቀት በልጠዉ ስለሚገኙና ሽርክና ቢድኣን ስለሚቃወሙ ነበር ም/ ያቱም ሰዋች ካወቁ ከቀሩ የሰዉ ተከታይ አይሆኑም እና በዚህ ሁኔታ አሏህ ቃል በገባዉ መሠረት ምንም እንኳን የተደበደቡት ቢደበደቡም የተባረሩት ቢባረሩም የበላይነት  ለገሳቸዉ በዚሁ ሁኔታ እያለን  መቼም በጥሩ ነገር መጥፎ አይጠፋም እና ኣንድ ልጅ ትምህርት በመማር ምክንያት በመድረሳ መሥጂድ በኩል ብቅ ኣለ የሡና ሠዎችንም መሠሎ ማሥቀራትም ጀመረ ከዛም እያለ ቀጠለ የተዉሠኑ ተማሪዎችንም ያዘ (በነገራችን ላይ ልጁ እዉቀት ኖሮት ሳይሆን ሪከርዶች እያዳመጠ ነበር የሚያስቀራዉ) ከዛም በዉስጥ መስመር በኣህሉ አስሱና ሰዋች ላይ መናገር ጀመረ ላንዱ ተብሊግ ነው ለሌላኛዉ ደሞ ኢኽዋን ነው እያለ ጀምዓዉን ይሸራሽር ጀመረ ወደዚህም ደረሰ ወደ ቆዳናሌጦ መስጅድ እንደሚታወቅ በግዜው ታዋቂ ኹጥባ የሚኾጥብ ጀምዓ ሰብስቦ የያዘ ወጣት ነበር እሱም ማንንም ሰያውቅ ኢኽዋን ነዉ በማለት ከመስጂድ እነዲባረር ኣስደረገ ( ኣንድ ጥቃት) ለመሆኑ ማን ነበር ይህ ሰዉ በነገራችን ላይ ሰዉዬዉ በግዜዉ እነ ኣቡበክር ያሲን ኑሩ ይወድ ነበር እያለ ቀጠለ እና ሌላ ኢማም የሚየስቀራ ኡስታዝ ከኣዲስ ኣበባ ተመጣ የተወሰነቀንም አፎይታ ይገኛል ቢባልም መቼም ለመጥፎ የተቃኘ ምን ያምረዋል እሱም በዉስጥ መስመር ስም በመሥጠት እንዲባረር ኣስደረገ
(ሁለተኛ ጥቃተ) ያአላህ!! እንዲህ እንዲህ እያለም ቀጠለ በቀጣይም ሌላ ኡስታዝ ከባህር ዳር ተመጣ እንደተለመደዉ ኣዋቂዋች ካሉ ኣጃቢ አይኖርም እና በማይታወቅ ምክንያት እንዲወጣ አስደረገ (ሶስተኛጥቃት)ዎ!ሙሲባዉ ሲደጋገም የተባለዉም ሰዉ በዉስጥ መስመር  እንድገና ስራዉን ቀጠለ እንዲሁም ኣለ ኡስታዝ ሳኒ ተጠንቀቁቁት ኢኽዋን ነዉ ሼ/ነስሬም እንደዚሁ ከፍብሎም ሼ/ሙሀመድ መኪን በሱማ የተሰራዉ ሌላ ነዉ እንዳይቀራ ድረሥ እርምጃ ሌሎችም ከአዲስ ኣበባ ይህ ከአራት ኣመትበፊት የሠራዉ ግፍ ነዉ  ወረድ ብሎም እነ ያዕቁብ እነ ተዉፊቅ ለነሱማ ጭራሹም እንዲህ ኣላቸዉ እነሱ እስካሉ ደዕዋ ሰለፊያ ቡታጅራ ዉሰጥ በእግሩ አይቆምም በማለት በጀምኣዉ እንዲ ጠሉና ተሰሚነት እንዳይኖራቸዉ ኣደረገ እነዚህ ስማቸዉ የጠቀስኩት ለኣብነት ያክል ነዉ ይህም ልጅ እየነጣጠለ እየከፋፈለ ከፋፍሎ መግዛት ጀመረ በቃ ይህ ሌላኛዉ ጥቃት ነዉ (አሏህ ሆይ እርዳታህን) ጉዳዩ በዚህም አላበቃ ኡስታዝ ሳኒ ለማባረር ከኣንዳንድ መስጂዶችም እንደያስቀራም ማደም ጀመረ እናም የፈረቃ ኢማም ሆኖ ቁጭ!ምን ይህ ብቻ ገና ጉዱ አልተጀመረም ለመሆኑ ማን ይሁን እንዲህ እያካፈለ እየከፋፈለ እየበጠበጠ እንዳዉ ጠንካራ ናቸዉ የሚባሉ የሹራ መሪ የነበሩ ጀማዓን ስብስበዉ በመያዝ የሚታወቁ ወጣቶች  በሚሰራዉደባና ጩቆና መነጣጠል በኣቅም ማነስ ምክንያት
የተነሳ ከመሥጅ ወጡ ለመሆኑ ይህሁሉ ብጥበጣና ሽብርት የጀምዓዉ ኣንድነት የሚያቅረዉ እያጋጨ መኖር የሚፈልግ አካል ማን ይሁን? በዚህስ ብቻ ቆመ እንዴ?
እነማንንስ ገፋ?
ክፍል ሁለተ ይጠባበቁ------


Репост из: ابو البيان البتاجري
🟢የሚዲያ ተጠቃሚዎች ሆይ:

በተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎች (ሚዲያዎች) ላይ የምትንቀሳቀሱና ዲናዊ ትምህርቶችን የምታሰራጩ ሁሉ የሚከተሉትን ነጥቦች ተጠንቀቁ⤵️

1⃣ ያለ እውቀት መዳፈር

አላህ በጥብቅ የከለከለው ጉዳይ ነው:
قال الله سبحانه
《وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا》  الإسراء:(36)
"እውቀት በሌለህ በሆነ ነገር አትከተል ።መስሚያ ፣ መመልከቻም ፣ ልብም በእነዚህ ሁሉ (ተግባር) ባለቤታቸው እኮ ተጠያቂ ነው።"

ከዚህ ውስጥ ያላዳመጡትን ድምፅ ፣ ያላነበቡትን ፅሁፍ፣ ያልተረዱቱና ያለመኑበትን መልእክት ማስተላለፍ ይገባል። ጉዳዩ የስግብግቦች የጅምላ ንግድ ሳይሆን ትልቁን የነቢያትን ውረስ የማስተላለፍ ሀላፊነት ነው።

2⃣ ተከታዮችን አለማገናዘብ

መልእክቱ በቀጥታ የሚደርሳቸውን ተከታታዮች ከግምት ያለስገባ ስርጭት አደጋው ብዙ ነው። ከመምራቱ ይልቅ ማጥመሙ ሊያዘነብል ይችላልና። ከጥቅሙም ጉዳቱ። በተቻለ መጠን በአስተላለፊው ደረጃ ሳሆን ተከታታዮችን ያገናዘበ ጉዳይ ነው መተላለፍ ያለበት።
ዲኑ የምር ጉዳይ ነውና ዛዛታና የሀሰት ወሬ ይፃረረዋል። ከሚከተተሉን ውስጥ ብዙ የተከበሩ ሰዎች እንዳሉም እናተውል።
አላህ እንዳዘዘው:
﴿…وَقُولُوا لِلنَّاسِ حُسْنًا…﴾[البقرة: ٨٣]

3⃣ ቀደም ቀደም ማለት

አዲስ አጀንዳ ከማሰራጨት በፊት በጉዳዩ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸው ሰዎች ሊናገሩ ወይም ሊፅፉ እየቻሉ የደፋሮች ቀዳም ቀደም ማለት በርካታ መዘዞች አንዳሉት በመረጃም በታሪክም የታወቀ ነው።
በተለይም ኡማውን የሚመለከቱ አዳዲስ ክስተቶችን አስመልክቶ ሰለፊይ ዑለማዎች የሚሉቱን በትዕግስት መጠበቅና መጠየቅ በራሱ አዋቂነትና ሰለፊይነት ነው። ተቃራኒውም በተቃራኒ።
አላሁ ተዓላ እንዳለው:
《…وَإِذَا جَاۤءَهُمۡ أَمۡرࣱ مِّنَ ٱلۡأَمۡنِ أَوِ ٱلۡخَوۡفِ أَذَاعُوا۟ بِهِۦۖ وَلَوۡ رَدُّوهُ إِلَى ٱلرَّسُولِ وَإِلَىٰۤ أُو۟لِی ٱلۡأَمۡرِ مِنۡهُمۡ لَعَلِمَهُ ٱلَّذِینَ یَسۡتَنۢبِطُونَهُۥ مِنۡهُمۡۗ…》[النساء :٨٣]

4⃣ አመፅን ማሰራጨት

ለምሳሌ: ሱረህ (ፎቶና ቪዲዮ) ፣ የዘፈን ድምፅ፣ የአጥማሚዎችን ጣቢያ (ቻናል) ፣ ከአመፅ ሚዲያዎች (ለምሳሌ ቲክቶክ) የመጡ ነገሮች ፣ ውሸት እና የመሳሰሉትን ማስተላለፍ አለማው ጥሩ ቢመስልም በራሱ አመፅና ፈሳድን መባባስ (ማስተዋወቅ) ነው።
👌መርዝና ማር ከተቀላቀሉ መርዙ ገዳይ ነው ተብሎ አይፈራምን?!
አላህ ፀያፍ ነገሮች እንዲሰራጩ የሚፈልጉትን አሳማሚ ቅጣት እንደሚቀጣ አስጠንቅቋል።
﴿إِنَّ ٱلَّذِینَ یُحِبُّونَ أَن تَشِیعَ ٱلۡفَـٰحِشَةُ فِی ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِیمࣱ فِی ٱلدُّنۡیَا وَٱلۡـَٔاخِرَةِۚ وَٱللَّهُ یَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ﴾ [النور: ١٩]

5⃣ ስህተትን አለመቀበል

ያሰራጩት ጉዳይ ጥፋት ሆኖ  ሲነገራቸው ከማስተካከልና ወደ ሀቁ ከመመለስ ይልቅ የሚብስባቸው ቀልበደረቆችና ኩራተኞች ናቸው።
ሚዲያ ላይ ከወጡ መካሪ ብቻ ሳይሆን ምክር ተቀባይ ለመሆንም መዘጋጀት ያስፈልጋል። ሀቅን አይቶ የማይረታ ድርቀቱ የከፋ ሰለመሆኑ አላህ ነግሮናል።

﴿ثُمَّ قَسَتۡ قُلُوبُكُم مِّنۢ بَعۡدِ ذَ ٰ⁠لِكَ فَهِیَ كَٱلۡحِجَارَةِ أَوۡ أَشَدُّ قَسۡوَةࣰۚ وَإِنَّ مِنَ ٱلۡحِجَارَةِ لَمَا یَتَفَجَّرُ مِنۡهُ ٱلۡأَنۡهَـٰرُۚ وَإِنَّ مِنۡهَا لَمَا یَشَّقَّقُ فَیَخۡرُجُ مِنۡهُ ٱلۡمَاۤءُۚ وَإِنَّ مِنۡهَا لَمَا یَهۡبِطُ مِنۡ خَشۡیَةِ ٱللَّهِۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَـٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ﴾ [البقرة :٧٤]
🤲አላህ ይጠብቀን

6⃣7⃣8⃣9⃣🔟

✍አቡ ሀመዊየህ (ሸምሱ ጉልታ)
http://t.me/Abuhemewiya

Показано 20 последних публикаций.

286

подписчиков
Статистика канала