Books and Opinions


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


Beautiful Books, impressive Ideas and more Presented!👍

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ወግ ብቻ:
(ከቤኩምሳ ስዩም ከበእውቀቱ ስዩም)

በጄኔሬተር የሚሰራ ጄኔሬሽን
ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
ለጥንቃቄ ሲባል በብእር ስም የተፃፈ



የሆነ የድሮ ዘፈን ትዝ አለኝ:: ዘፈኑ፦
"በጎፈሬው ማህል ፤ሚዶውን ሰክቶ"
አይሂ
"በድልድል ጫንቃው ፤ላይ አልቢኑን አንግቶ"
አይሂ
እያለ ይወርዳል::
የድሮ ጉብል ሲያነጣጥር ፣ሲተኩስ፣ሲመታ ሲገድል ስለሚውል በምን
ጊዜ እንደሚያፈቅር አይገባኝም::
የድሮ ሰዎች ያለ ትግል መኖር እንደማይችሉ ለመረዳት የሚፈልግ
የጦርነት ዘፈኖችን መስማት አይጠበቅበትም:: የሰርግ ዘፈኖችን
ማስታወስ ብቻ በቂ ነው:: አሁን ሰርግን በመሰለ የፍቅር መደረክ ላይ "
አናስገባም ሰርገኛ እደጅ ይተኛ"ብሎ ነገር ፍለጋ ምንድነው:: ይሄ እኮ"
የማክበር ሰላ-ምታ-ችንን እያቀረብን ፣ በልጃችን የሰርግ ስነስራት ላይ
ያዘጋጀነውን ዱላ እንዲቀምሱልን እንጠይቃለን" የሚል መጥርያ
እንደመላክ ነው:: (ማህበረሰቡ ለድብድብ ያለውን ፍቅር ለማወቅ
የሚፈልግ ሰው "እስክስታ ምታ፤ ቤት ምታ "የሚሉ ቃላትን መመልከት
ይችላል:: የሚገርመው፣"ሰላምታ"በሚለው ቃል ውስጥ ራሱ
"ምታ"የሚል ቃል መገኘቱ ነው)
ኮኔክሽን ያላችሁ፤ እንደምናችሁ !! እኔ ጉንፋንና ኮማንድ ፖስቱ ሰንገው
ይዘው ያናፍጡኛል:: የድሮ ጉንፋን እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም:: ድሮ
ጉንፋን ሲይዘን ፤አንድ ሁለቴ በስሱ አስነጥሰን ፤ይማርህ የሚል ምርቃት
ከያልፎሂጁ አፍሰን ፤በዳማ ከሴ የጦዘ ቡን ፤ በባለቅጠሉ ፍንጃል
ጨልጠን፤ ያፍንጫችንን ተረፈ ምርት በምሳና ቅጠል ተናፍጠን ፤
"ኖርማል "እንሆን ነበር:: ዘንድሮ ልጄ! ወይ ጉንፋን ከጊዜው ጋር
ገግሙዋል::ወይ የመከላከል አቅማችን በጀሶ እንጀራ ምክንያት
ተዳክሙዋል:: ከህመሙ በላይ ያዳከመኝ የጠያቂው ምክር ነው::
ምኡዝ ደወለልኝ፤
"ሄሎ"
"አቤት"
"የበውቀቱ ስልክ አይደለም እንዴ?"
"ነው "
"በውቄ ድምፅህ ምን በልቶ ነው ሶስት ኪሎ የጨመረ? ስልክህን ጋሽ
ሙላቱ አስታጥቄ ያነሳው መስሎኝ ነበር"
"ጉንፋን ይዞኝ ነው"
"ለምን አጥሚት ነገር አትወስድበትም?"
በለው ምክር! እሺ ያጥሚት እህል አለኝ እንበል፤ በምን አባቴ
እንዳፈላለት ፈልጎ ነው? ኤሌክትሪኩ እንደሆነ የጣርያው ፍሬቻ ከሆነ
ሰነበተ:: " መብራት መጣ!"ብለን ከጎረቤቶቻችን ጋር ተቃቅፈን ዘለን
ሳንጨርስ ፤ አያ መብራት" ወደ ጂቡቲ ስሄድ እግረመንገዴን አይቻችሁ
ልለፍ ብየ ነው"ብሎ እልም ይላል::
በነገራችን ታች፤ በንግሊዝና በኢቶጵያ ትብብር ፣ ከቺቺኒያ እስከ ንግሊዝ
ኢምባሲ የሚደርስ በፀሃይ ሀይል የሚሰራ የመንገድ መብራት ተዘርግቶ
ነበር::(በትብብሩ ወቅት እንግሊዝ የስራ ማስኪያጃ ፓውንድ ስታዋጣ ፣
ኢትዮጵያ ፀሃይ አዋጥታለች::) የሚገርመው ነገር የመንገዱ መብራት
ገና የምርቃቱ ቀን ስለተቃጠለ የምርቃቱ ፕሮግራም የተካሄደው
በጄኔሬተር ድጋፍ ነበር:: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የመብራት ምሶሶዎች ብቸኛ
ተግባር አምሺቶ የሚገባን ሰካራም ግንባር መፈንከት ሆኑዋል::
ምክሩ ይቀጥላል፤
"ለምን ባህር ዛፍ አትታጠንበትም?"
"ከታጠንኩ በሁዋላ ባሰብኝ"
" እንዴት ሊሆን ይችላል?"
"ያዲሳባ ባህር ዛፍ ፤ ከስሩ ሽንት እየተሸናበት ስለሚያድግ በጉንፋን
ሲማቅቅ የሚኖር ነው::ራሱ የሚታጠነው ነገር ቢያገኝ አይጠላም"
ሌላው ለምን ብርቱካን አትበላም አለኝ::ምክሩን ተቀብየ እዚህ እኛ
ሰፈር የሚገኝ ፍራፍሬ ቤት ሄጄ አንድ ኪሎ አስመዘንኩ::ሻጩ ሶስት
ብርቱካን መመዘኛው ሰሃን ላይ አስቀምጦ ሲያበቃ " አንድ ኪሎ
ነው"ብሎ ደረቀ::
"ነፍሴ እንዴት ሆኖ ነው ሶስት ፍሬ ብርቱካን አንድኪሎ የሚመዝነው ?
በርግጥ ይሄ ነገር ብርቱካን ነው ወይስ የከረንቦላ ድንጋይ? "
አንዱዋ እህቴ "ስፔሻል ሻይ ብጠጣበት ይለቅካል " አለችኝ ::
አልተሳሳተችም:: የሆነ ቦታ ገብቸ ስፔሻል ሻይ ጠጥቸ ሂሳብ ስጠይቅ
ስድሳ ሁለትብር ተባልሁ:: ጉንፋን እንደስርቅታ በድንጋጤ እንደሚለቅ
ያወቅሁት ያኔ ነው::
ስለድንጋጤ ሲነሳ አንድ ነገር ትዝ አለኝ:: ከሶስት ወር በፊት አንድ
ዲያስፖራ ባልንጀራየ ፣ጠርሙስና ናፍጣ
በመጠቀም ቤት ውስጥ ተቀጣጣይ ቦምብ እንዴት መስራት
እንደምችል የሚያስረዳ ነገር ኢምቦክስ አረገልኝ:: " በውቄ፤ አንድ
አድማ በታኝ መኪና ስታቃጥል ባልጄዚራ ለማየት ጉዋጉቻለሁ" አለኝ
ጉዋዴ:: ኮማንድ ፖስቱ በታወጀ ማግስት ልጁን ብሎክ አረኩት:: ቤቴ
ውስጥ የሚገኙትን ጠርሙሶች ሁሉ ጠርጌ ለቆራልዮ
ሰጠሁዋቸው::ባጠቃላይ የጠርሙስ ፎቢያ ያዘኝ::
ባለፈው እዚህ ሃያሁለት ወደሚገኘው እውቅ ሊኪየር ሃውስ ጎራ ብየ፤
" እትየ አዛለች ፤ ወይን አለ?"
"አለ"
"በጠርሙስ ነው?"
" ታድያ እንደ ማማ ወተት በላስቲክ ተጠርዞ እንዲቀርብልህ ፈለግህ"?
በዘንድሮ ዘፈን ልሰናበታችሁ፤
በማህደሩ ውስጥ ፤አይፎኑን ሰክቶ
አይሂ
ባለዋይፋይ ሆቴል ፤ግንቡን ተጠግቶ
አይሂ
ላይክ እያዘነበ ፤ለቆንጆ ልጅ ፎቶ
አይሂ
ማርጀት እየቻሉ ፤መኖር እስከመቶ
አይሂ
ማን ሸቤ ይገባል ፤መፈክር ፖስቶ
አይሂ::

@booksandopinions
@booksandopinions


ምርቃት እንደወረደ

“እጅህን ከቁርጥማት -ጉሮሮህን ከቢራ ጥማት ይሰውረው። ከይሉኝታ ቢስ ቀፋይ- ጠላ ጋብዞ ውስኪ ከሚያስከፍል ግብር አስከፋይ -ይሰውርህ!
ደስታህ ፍፃሜ አይኑረው። ሞትህን ያስቀረው። ካልሆነ አሟሟትህን ያሳምረው- እግርህን በቀይ ምንጣፍ ላይ ያውለው- ስንቅህን ያክብደው እዳህን ያቅለለው- አለባበስህን ፋሺን-ኪስህን ATM ማሺን ያርግልህ-ምቀኛህን ለዘብጥያ ይዳርግልህ.. ጠላቶችህ እንደባዘቶ ይዳመጡ-ሽንት ቤት ሲቀመጡ-ይበርታባቸው ምጡ-”

ውድ ተመራቂዎች ቢራ የሚለውን;"ውሀ"፣ ጠላና ውስኪን ደግሞ እናንተ በመረጣችሁት ለስላሳ መጠጥ ቀይራችሁ አንብቡልኝ። (የለጣፊው ማስታወሻ)

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ

@booksandopinions
@booksandopinions


ኖረሽ እይው በቃ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጨለማ ነህ ብለሽ እኔን ስትተቺ
ዘለሽ አትጠግቢ፥ስቀሽ አትሰለቺ
ወርሃ ፅጌ ነው ፤አመት ሙሉ ላንቺ

ደሞ በየቀኑ
ፋሲካ ነው ኑሮሽ
ያለም ሰቀቀኑ
ሩቅ ነው ለጆሮሽ
(የፍጥረት ሰቆቃ)
ለጋ ነው ላ'እምሮሽ
ገላሽም ነው ጮርቃ
ሌላም አልልሽም፤ ኖረሽ እይው በቃ ፤

በየጎዳናሽ ላይ ፥አደይ የሚያነጥፍ
በየዛፉ ቅርፊት፥ ስምሽን የሚጥፍ
በዝቶልሽ፥ፈልቶልሽ ፥አንቺን ሚያሽሞነሙን
ቀምሰሺው አታቂም፥ የብቻነት ሸክሙን

አዎ!
መፈቀር ፥ መታጀብ ከኔክታር ይጥማል
ግን ደግሞ ይገጥማል
በተወደሱበት አንደበት መነቀፍ
ውብ ገላ ጠብቆ፣ ርጥብ ነፋስ ማቀፍ፥

አንዳንዴም ይገጥማል
የማይሰምር ምኞት ፥የማይልቅ ጥበቃ
ሌላም አልልሽም፤ ኖረሽ እይው በቃ፤

አንቺ ደስታ ወዳጅ
በለምለም አፀድ ውስጥ፥ ቢራቢሮ አሳዳጅ
ኑሮ ምትታይሽ፤ እንደ ጣኦስ ቀልማ
እንዳትሸወጂ ባዝማሪዎች ዜማ
በሸንጋዮች ቃላት
ህይወትም እንደ ጃርት፥የሾህ ቀሚስ አላት፤

ተድላም ከሃዘን ፣ጋር ያልፋል በፈረቃ
ከሳቅ በስተጀርባ፥ ይሰለፋል ሲቃ
ሌላ ምን ልበልሽ ፥
ኖረሽ እይው በቃ

(ከ-አዳምኤል)


@booksandopinions
@booksandopinions


#ስለ ሊዮ ቶልስቶይ በስሱ
-----------------
ሊዮ ቶልስቶይ በሙሉ የመዝገብ ስሙ ሲጠራ Lev Nikolayevich Tolstoy ይባላል። የተወለደው እኤአ መስከረም 9, 1829 በራሽያ ከሚገኙት የኢንዱስትሪ ከተሞች ውስጥ አንዷ በሆነችው ቱላ ተብላ በምትጠራው ከተማ አቅራቢያ Yasnaya Polyana ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ።

ሊዮ ቶልስቶይ ለቤተሰቦቹ ከአምስት ልጆቻቸው ውስጥ አራተኛው ልጃቸው የነበረ ሲሆን የቤተሰቦቹም ሁኔታ የባላበት ቤተሰብ (aristocrat) የሚባሉ ነበሩ ። ሊዮ ቶልስቶይ እናቱ በልጅነቱ ከሞቱበት በኋላ ከአባቱና ከቀሩት ቤተሰቦቹ ጋር በመሆን ከተወለደበት አካባቢ ካዛን ከተማ ወደሚገኙት ዘመዶቹ (አክስቱ) ጋር ለማደግ ሄደ ።በካዛንም ከዘመዶቹ ጋር ሆኖ እያደገ እየኖረ ከ7 ዓመት ቆይታ በኋላ ደግሞ አባቱ በሞት ተለዩት ።

ከአባቱም ሞት በኋላም የሊዮ ቶልስቶይ ብቸኛ ዕጣ ፈንታ በድጋሚ ሌሎች ዘመዶቹ (አክስቶቹ) ጋር ማደግ ብቻ ነበር ።
በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ ያደገው ሊዮ ቶልስቶይ በልጅነቱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ፈረንሳይና ጀርመንኛ ቋንቋዎችን ጨምሮ የተማረው በቤት ውስጥ እንደነበር ይነገራል ።
ሊዮ ቶልስቶይ በእነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ ካለፈና ካደገ በኋላ በመጨረሻም በትልቁ የካዛን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በህግና የምስራቃዊ ቋንቋዎች (Law & Oriental Languages) የትምህርት ዘርፍ መማር ጀመረ ።
ቢሆንም ግን የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ተምሮ መጨረስ ከሚገባው ጊዜ ውስጥ ግማሽ ያህሉን ከተማረ በኋላ ትምርቱን አቋረጠ ።

በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ወቅትም ያስተማሩት መምህራን እሱን ሲገልፁት ሊዮ ቶልስቶይ በብዙ ነገሮች ላይ የማይቻልና ፈፅሞ ፈቃደኝነት የማይታይበት ዓይነት ሰው ነበር ብለውታል ።
ከዚህም ሁኔታ በኋላ ሊዮ ቶልስቶይ ከካዛን ወደ ትውልድ አካባቢው Yasnaya Polyana ተመለሰ ።
ከዛም በቀጣይነት በቱላ እንዲሁም በዋና ከተማዋ በሞስኮ የተወሰ ጊዜ ኖረ ።
ከዛም በኋላ በመጨረሻም ደግሞ በሴንት ፒትርስበርግ ከተማ መኖር ጀመረ ።

በሴንት ፒትርስበርግም ከሁሉም በተሻለ ሁኔታ የተረጋጋ የህይወት ዘይቤን (Leisurely life style) መምራትን ጀመረ ።
ሊዮ ቶልስቶይ በፒትርስበረግ ምቾትን አገኘ ።
ይሄም የተረጋጋ ሁኔታ በውስጡ የነበረውን የመፃፍ አቅም እንዲያወጣው መነሻ ሆነለትና ሊዮ ቶልስቶይ ፅሁፎቹን መፃፍም ጀመረ ።
የእሱ የመጀመሪያ ፅሁፍ የሆነው Child Hood የተፃፈው በዚህ ወቅት ሲሆን በቀጣይነትም
- Boy Hood
- Youth
- Sevastopol Sketches
- The Death of Ivan Llyich
- Family Happiness
የተሰኙት ምርጥ ስራዎቹ በተከታታ ያለዕረፍት ፃፈ ።

አሁን ታላቁ ሊዮ ቶልስቶይ ተፈጠረ ።ይሄ በሩሲያና በዓለም የስነ-ፅሁፍ የክፍለ ዘመናት ጉዞ ውስጥ ታላቅ ፀሀፊ እንደሆነ የሚነገርለት ሰው በሂደት በጣም ብዙ ድንቅ ፅሁፎችን ለዓለም አበረከተ ።
ሊዮ ቶልስቶይን በብዙዎች ዘንድ የምንግዜም ምርጡ ፀሀፊ እሱ ነው እንዲሉለት ያስገደዳቸውንና በብዙዎች ደግሞ የምንግዜም ምርጡ መፅሀፍ ተብሎ የሚጠራውን ባለብዙ ሺ ገፅና ብዙ ገፀ ባህሪያት የተቀመጡበትን ትልቁ መፅሀፉን War & Peace እኤአ በ1869 የፃፈ ሲሆን ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ ሌላኛው በአንባቢዎች የምንግዜም ምርጥ መፅሀፍ ነው የሚባለውን Anna Karenina የተሰኘ ረጅም ልብ-ወለድ መፅሀፉን ደግሞ እኤአ በ1877 ለንባቡ ዓለም አብቅቷል ።
እነዚህ ሁለት የሊዮ ቶልስቶይ መፅሀፎች የእሱን ታላቅ ፀሀፊነት በደንብ ያሳዩ እንደሆኑ ታላላቅ ፀሀፊዎች ሳይቀሩ እየመሰከሩ ተናግረውለታል ።

ሊዮ ቶልስቶይ የማዕበራዊ ኑሮን በተመለከተ ያለው አስተሳሰብ የሩሲያ ጭቁን ህዝብን በጣም የሚወድ ሰው የነበረ ሲሆን ይሄም ጭቁን የህብረተሰብ ክፍልም (መደብ) ለሊዮ ቶልስቶይ ፍቅር እንደነበረው ይነገራል ።
ሊዮ ቶልስቶይ እኤአ በ1862 ዕድሜው 34 ሲሆን በ16 ዓመታት በዕድሜ የሚበልጣትን የ18 ዓመቷን Sophia Behrs ን አገባት። ቶልስቶይ ከዚህ በጊዜው አወዛጋቢ ተብሎ ከተጠራው ትዳሩ በጊዜ ሂደት ውስጥ ሆኖ ከባለቤቱ Sophia 13 የሚሆኑ ልጆችን አጊንቷል ።

ነገር ግን የሊዮ ቶልስቶይ ልጆች ብዛት በአጠቃላይ 14 ነበሩ ።
ታላቁ ፀሀፊ ሊዮ ቶልስቶይ በፃፋቸው ድንቅ የስነ-ፅሁፍ ስራዎቹ መነሻነት በተደጋጋሚ ጊዜ ለትልቁ የኖቬል ሽልማት በስነ-ፅሁፍ ዘርፍ ( Noble Prize in Literature) ለአራት ተከታታይ ዓመታቶች ዕጩ ሆኖ የቀረበ ሲሆን ከዚህም ውጪ ባያሸንፍም እንኳን በዚሁ ትልቅ የሽልማት መድረክ ላይ የሠላም ኖቬል ሽልማት (Noble Prize in Peace) በሚለው ዘርፍ ላይ ለ3 ዓመታትም ታጭቶ ነበር ።
ሩሲያዊው ታላቅ የስነ-ፅሁፍ ሰው ሊዮ ቶልስቶይ ህዳር 20, 1910 ቀን ዘመን የማይሽራቸውን ታላላቅ ስራዎቹን ለዓለም አስቀምጦ በ82 ዓመቱ ይቺን ምድር በሞት ተሰናብቷታል ።

በአጠቃላይ
- የረጅም ልብ-ወለድ ፀሀፊ (Novelist)
- የአጫጭር ታሪኮች ፀሀፊ (Short Story writer)
- የቲያትር ፀሀፊና ደራሲ (Play-wright)
- የዕለት ተዕለት የስነ-ፅሁፍ ስራዎች ፀሀፊ (Literary genre)
እና የተወሰኑ የፍልስፍና ፅሁፎች ባለቤት የነበረው ታላቁ ፀሀፊ ሊዮ ቶልስቶይ በአጭሩ ሲገለፅ ይሄ ነበር ።

@booksandopinions
@booksandopinions


የአዘርግ መጽሐፍት ስብስቦች👆👆👆👆☝️☝️☝️👆👆👆☝️☝️☝️☝️☝️
Share to friends as always

@booksandopinions
@booksandopinions
















⭐️🌟⭐️ አብሪ ኮከቦች 💫💥💥

🇪🇹🇪🇹ቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ🇪🇹🇪🇹

ቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ (፲፰፻፺፯ ዓ.ም. በደብረ ኤልያስ ቀበሌ፣ ጎጃም ተወልደው ሰኔ ፴ ቀን በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም. አረፉ) ስመ ጥር ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነበሩ። እኚህ ታላቅ ደራሲ በርካታ ድርሰቶችን የጻፉ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ለሕትመት አልበቁም። የመጀመርያውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉሥሽ” የሚለውን የደረሱት ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፤ ስለአገር ፍቅርና ጀግንነት የሚያወሱ በርካታ ድራማዎችና መዝሙሮችን የደረሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል “አፋጀሽኝ”፣ “እለቄጥሩ” ወይም “ጎበዝ አየን” ይገኙበታል።


ከድል በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ከ፲፱፻፴፭ ዓ/ም እስከ ሕልፈታቸው ድረስ አገልግለዋል። የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመታባበር ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ የተመረቁትን እና የቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤን እንዲሁም የደራስያን፤- ነጋድራስአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ እና አቶ [[ተመስገን ገብሬን ምስል የተቀረጸባቸው ቴምብሮችን ገበያ ላይ አውለዋል። (ዊክፕድያ)


ዮፍታሔ ንጉሴ፣ ብሔረ ነገዱ፣ ሀገረ ሙላዱ፣ ጎጃም፤ ቅኔ የተቀኘበት፣ ድጓ የተማረበት፣ ምስጢር ያገመረበት ደብረ
ኤልያስ ነበር። ጠይም ረዥም፤ ጠጉረ ሉጫ፤መልከ መልካም የቆንጆ ጠር፤ ቀጭን ዠርጋዳ ጣተ መልካም ፤ሽቅርቅር ጥዩፍ፤ ኮከቡ ሚዛን ነፋስ ነበር። ምዕ.1 ዮፍታሔ የቀለም ትምህርቱን ከመጀመሩ አስቀድሞ ምግበ አእምሮው የሆነውን የኤልያስን አየር እየተመገበ፣ ዝንጀሮ ያልቸውን ሁሉ ዘፈኑን፣ ስለምኑን፣ቁም ነገሩን፣ ወዘበሬታውን፣ ተረቱን፣ድርሳነ ባልቴቱን፣ ቀረርቶውን፣ልቅሶውን፣እማ በራዩን፣ ሙሻሙሾውን፣አይኮሉን፣ አረቦኑን፣ ወዘተ... እየሰማ ነበር ያደገው። ይኽ ሁሉ ኋላ ለተቀኘው ቅኔና ለደረሰው መዝሙር፣ ቲያትርና ስለምን ዐይነተኛ ዳራ ሁኖታል። ምዕ.1 የቅኔ ትምህርተ ተራውና ደረጃው ከፀዋትወ ዜማ ቀጥሎ ከትርጓሜ መጻሕፍት አስቀድሞ በጉልምስና ወራት ነው። ... ቅኔ የንባብና የጸዋትወ ዜማ ደጀን የትርጓሜ መጻሕፍት ፊታውራሪ ነው።


... ቅኔን ከጸዋትዋ ዜማ በፊት ከትርጓሜ መጻሕፍት በኋላ ለመማር በፍጹም አይቻልም። ይኽውም ከዘር በፊት ቡቃያ ከባል በፊት ልጅ ይሆናል። የቅኔ ትምህርት...የትውልድ አገርን ትቶ ጋራ ዙሮ፣ ወንዝ ተሻግሮ ወጥቶ ወርዶ፣ከውሻ ተከላክሎ ፣ቁራሽ እንጀራ ለምኖ ፣ ደበሎና ማቅ ለብሶ፣ ተዋርዶ ተንከራትቶ፣ ብዙ ፈተና ተቀብሎ፣ አይመስሉ መስሎ፣ ቀይ የነበረው ጠቁሮ፣ ረዥም የነበረው አጥሮ፣ተርቦ ተጠምቶ ፣ ፀዋትወ መከራውን ሁሉ ታግሶ የሚማሩት የተባሕት ትምህርት ነው። "ምዕ.1፤ አለቃ ዕንባቆም ቃለ ወልድን ጠቅሶ" ስለደራሲው በጥቂቱ " ኮከብ እምኮከብ ይኄይስ ክብሩ" የሚል የኖረ የግእዝ አባባል አለ:: አንዱ ኮከብ በብርሀኑ፤ በግዘፉ፤ መጠቅላላ ተፈጥሮው ከሌላው ኮከብ ይበልጣል::


እኔን የሚያስገርመኝ ይኽ አይደለም:: እንዳንድ ከዋክብት አሉ--በተለየ አጠራር ተወርዋሪ የምንላቸው:: በሌሊቱ ኅዋ ውስት ከአንዱ መአዘን ሰማይ ወደ ሌላው ተወርውረው ብልጭ ብለው ይጠፋሉ:: ይህ ሁሉ የሚሆነው በቀፅበት ነው::ያንን በጨለማው ግርማ የተዋጠውን ኅዋ በብርሃን ጎርፍ ሰንትቀው አጥለቅልቀውት ይጠፋሉ:: ተመልካችም ከመገረም በሚመነጭ ዝምታ ይዋጣል:: በኢትዮዽያም የሥነ ጽሑፍ ኅዋ ውስጥ ዮፍታሔ ንጉሤ አንድ ተወርዋሪ ኮከብ ነበር።


ብሩህ ነጸብራቁ፤
ውበቱና ድምጹ አንድነት ተሰማ
ተው አንድነት ቢበርቁ፤
የመያው ቅለት ጠፍቶ፤
ምስጢሩን አካቶ፤
ተወርዋሪ ኮከብ በራሱ ነበልባል በራሱ ነዲድ ተቃጥሎ የጠፋ፤
ተወርዋሪ ኮከብ በምናየው ሰማይ ነበረ በይፋ።


አዎን፤ ነበረ። በዚያን ቅጽበት በሆነው የጽሁፍ ዘመን ዮፍታሔ፤ የኢትዮዽያን የስነጽሁፍ ኅዋ በቅኔ ፤ በግጥም ፤በመዝሙርና በተውኔት የብርሃን ጎርፍ ሰንጥቆ አጥለቅልቆት ጠፍቷል። ዛሬ የሚያሳዝነው የዚህ ተወርዋሪ ኮከብ ተጽእኖ በዘመናችን
መጥፋቱ ነው። ስለ ዮፍታሔ ንጉሴ በሕፃንነቴ እናት አባቴ ሲያወጉ፤ ሲወያዩ፤ አንዳንዴም ሲከራከሩ እሰማ ነበርበተለይ አባቴ ከዮፍታሔ ንጉሴ ተውኔቶችና መዝሙሮች በቃሉ የሚያስታውሳቸውን ስንኞች ሲያንጎራጉር እየሰማሁ የዮፍታሔ ፍቅር በሕፃን ልቦናዬና ስሜቴ ተሳለብኝ ። ያኔ ከሰማኋቸው ትዝ የሚሉኝ "አንተ ባ...ጎራዴ ግዛ" እና "ወላድ ኢትዮዽያ ለልጆቻ ብላ እጅግ ሳይትሩባት ሳይዘሯት አብቅላ" የተባሉት መዝሙሮች ናቸው። ሁለተኛው በጣም ጠሊቅ መዝሙር ነው። ጠሊቅነቱ የተገነዘብሁት ካደግሁ በኋላ ነው። ያኔ መዝሙሩ ይመስጠኝ የነበረው በቃላቱ ጣእመ ዝማሬ ነበረ። የፊተኛውን መዝሙር ግጥሙን በሙሉ ላገኘው አልቻልሁም። የኋለኛው ግን "ብርሃንና ሰላም" ይባል በነበረው ጋዜታ በሙሉ ተጽፎ ስላገኘሁት ከዚህ ቀጥሎ ጽፌዋለሁ፤

ወላድ ኢትዮዽያ ለልጆቿብላ፤
እጅግ ሳይጥሩባት ሳይዘሯት አብቅላ፤
ስንዴውን ጠብቃ እንክርዳዱን ነቅላ፤
ስትመግበን አየን በፀሐይ አብስላ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናብ መንግሥታችን።
በመልካሙ ዘርእ ላይ እንክርዳቸ ሲዘራ፤
ታሳድገውና ከእንክርዳዱ ጋራ፤
ገለባ ሲቃጠል ገበሬ ሲያመራ፤
ታቃጥለዋልች እንክርዳዱን አብራ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።
አይዞህ የኛ ጌታ ነገርህን አትርሳ፤
አለስልሰህ ዝራ የስንዴውን ማሳ፤
የተዘራችው ዘርእ ፈርሳና በስብሳ ፤
ታፈራልቸ ፍሬ ሙታ ስትነሣ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።
በጊዜው የዘራ መልካም ዘር አትርፎ፤
ከበሮቹ ጋራ ማታ ከትላ አርፎ፤
ብርነት ታትቆ በቅን ተሰልፎ፤
በቸርነት ታጥቆ በቅን ተሰልፎ፤
ደግሞ ዘሩን ዘራ መክር አሳልፎ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።

………………
ማንም በዕድሜው ብዛት አያስጠራም ስሙን
በጥቂቱም ዕድሜው ይሠራል ሐውልቱን።
ታሪክ ሲያበላሸው ረጅሙም ያጥራል፣
ታሪክ ሲያሳምረው አጭሩም ይረዘማል፤
ብዙ ዘመን ቢኖር ዕድሜውም ቢበዛ፤
በሳቅ በጨዋታ ዋዛን በፈዛዛ፣
ሲለዋውጥ ኖሮ ሃሳቡን ሳይገዛ፣
እንዲሁ ይቀራል እንዲያው እንደዋዛ።

📖ከ "ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ" መፅሀፍ የተወሰደ ፤ ደራሲ ዮሐንስ አድማሱ

🙏🙏ክብር ለታላቁ ደራሲና ገጣሚ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ✍✍

@booksandopinions
@booksandopinions
@booksandopinions


#አክሱም_ሀውልት_እና_መፅሃፈ_ሔኖክ


አክሱም ሀውልት ከ1700 አመታት በፊት እንደተሰራ የታሪክ በዛግብት ይናገራሉ። ይህ ሀውልት በአይነቱ ለየት ያለ ቅርፅን የያዘ ሲሆን በአሁን ሰአት ለአርኪዎሎጂስት አጥኚዎች ጥያቄ የፈጠረባቸው በዛ ስለጣኔ ባልነበረበት ዘመን እንዴት ይህን ግዙፍ ሀውልት ቀረፀው አቆሙት የሚል ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ብዙ መላምቶች ይቀርባሉ ከነሱም ውስጥ አንዱ አክሱም ሀውልት አባቶች ያቆሙት በዝሆን ጎትተው ነው የሚል የተሳሳተ የአጥኚዎች አስተሳሰብ ነው።
ሆኖም ይህን አስተሳሰብ ብንቀበል እንኳ አሁንም ድረስ የአክሱም ሀውልት የኢትዮጵያን ቀደምት ስልጣኔ ፍንትው አደርጎ ያሳያል።

ዘመናዊ መሳሪያና መለኪያ በሌለበት ዘመን የዘመኑ ሕንፃ ባለሙያዎች በቀላሉ ሊሰሩት የማይቹሉትን ልኬትና ቅርፅ ጠብቀው ድንቅ የሆነ የጥበብ አሻራቸውን አባቶቻችን አስቀምጠዋል።
አክሱም የጥበብ መሠረት የስልጣኔ ምንጭ የኢትዮጵያዊነት ጥበብ ድብቅ ምስጢር ነው ጣልያን ይህ ቢገባት ነው ነቅላ ወስዳ በሮም አደባባይ ያቆመችው። አክሱም ይህ ስፍራ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ፅዮን ማርያም ቤተክርስቲያን ያለችበት ቦታ ነው በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥም የመጀመሪያዋ ሙሴ ከእግዚአብሔር የተቀበላት አስርቱ ትዕዛዛት የተፃፈባት ፅላት ዘመሴ ተብላ የምትጠራው የታቦተ ፅዮንም መናገሻ ነው። ስለ ታቦተ ፅዮን በሌላ ጊዜ የምንዳስሰው ሲሆን አሁን ግን ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስና አክሱም ሀውልት ከአንድ ወጥ አለት ድንጋይ ተፈልፍሎ የቆመ ሲሆን ከላይ እንደጠቀስነው እንዴት ተፈለፈለ ማን ፈለፈለው ለምን ተፈለፈለ እንዴት ቆመ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ከአይምሮ በላይ ይሆናል ምክንያቱም ያን ጊዜ ቴክኖሉጂ የለም ብረት አቅልጠው በመዶሻና በብረት ቀጥቅጠው ካልፈለፈሉት በቀር በየትኛው ማሽን ሊፈለፈል ይችላል? ብለን ካሰብን ትልቅ ስህተት ይሆናል አባቶቻችን ይህንን ሀውልት ጎትተው አላቆሙትም ቀጥቅጠውም አልፈለፈሉትም ይልቁንም በእጃቸው የነበረውን መፅሐፈ ሄኖክን ተጠቅመው አነፁት እንጂ።

መፅሐፈ ሄኖክና አክሱም ሀውልት ምን አገናኘው ትሉኝ ይሆናል ነገር ግን መፅሐፈ ሄኖክን የጠቀስኩበት ምክንያት ወደ ማስረዳት ልሂድ።
ሄኖክ ከፍጠረት ሁሉ ያላየው ያልጎበኘው የለም እግዚአብሔር ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ለሄኖክ ያላሰየው የለም ታድያ እነዚህ ካያቸው ነገሮች መካከል የጥበብ እፅዋት ማዕድናትና የከበሩ ደንጋዮች ይካተቱበታል ከከበሩት ማዕድናት መካከል አንዱ ደንጋይን የማቅለጥ ሀይል ያለው ማዕድን እንደነበረና ይህ ማዕድንም በኢትዮጵያ ብቻ እንደሚገኝ አባቶች ይናገራሉ። ታድያ አክሱም ሀውልት ቅርፁን ሳይለቅ በዝሆን ሳይጎተት አባቶቻችን በበልሀት የቀረፁት በዚህ ድንጋይን በሚያቀልጥ ማዕድን እንደሆነም ፀሀፍት አባቶች ይናገራሉ የማእድኑም ስም #እልመቅሊጦስ ይባላል። በአለማችን ላይ እስካሁን ድረስ ብረትን እንጂ ድንጋይን የሚያቀልጥ ማእድን እስካሁን ድረስ የለም ከኢትዮጵያ ሊቃውንት በቀር።

አክሱም ሀውልትን ለምን ይጠቀሙበት ነበረ?
አክሱም አካባቢ ከፍተኛ የሆን ስልጣኔና የንግድ ስራ በስፋት የነበረበት ሲሆን ከተለያዩ አለማት ነጋዴዎች ወደዚህ ስፍራ በመምጣት የንግድ ስራቸው ያጧጡፉ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ይናገራሉ።
ታድያ እነዚህ ከተለያዩ ክፍል ዓለማት የሚመጡ ነጋዴዎች በምሽትም ሆነ በቀን ወደ አክሱም ለመምጣት አይቸገሩም ነበረ። እንዴት ያላችሁኝ እንደሆነ ነገሩ እንዲህ ነው።
አክሱም ሀውልትን አትኩረን ስንመለከተው ከላይ ክቧ ጋር የተበሳ ቀዳዳ ነገር አለ ይህ ቀዳዳ በዛን ዘመን አንድ የከበረ #በረቅ የሚባል ማዕድን ነበረ ነው። ይህ ማዕድን ቀን የፀሀይ ብርሀንን በመሰብሰብ ማታ ማታ ለአካባቢው ደማቅ የሆነ የተለያየ ቀለም ያለው ብርሀንን ያወጣ ነበረ። ። ታድያ ይህን ያሸበረቀ ቀለም ከሩቅ ሆነው የሚመለከቱ ነጋዴዎች በቀላሉ ወደ አክሱም ለመምጣት ይረዳቸዋል ለከተማዋም እንደ መብራትነት ያገለግል ነበረ። ይህ ማዕድን አባቶች አውርደው እንደደበቁት የሚናገሩ አሉ አንዳንዶቹም ግራኝ አህመድ ወስዶት ነው ይላሉ ዮዲት ጉዲት ናት የወሰደችውም የሚሉ አሉ ነገር ግን ግራኝ አህመድ ከወሰደው ወዴት አደረሰው?? ዮዲት ጉዲትስ ወዴት ሸሸገችው?? ብለን ስንጠይቅ አባቶች አውርደው ደብቀውታል ወደሚለው ያመዝንብናል።

የአክሱም ሀውልት ቅርፅ
የአክሱም ሀውልት ቅርፅ የወንድ ልጅን ብልት የሚመስል ሲሆን በዚህም አምሳል የተሰራበት ምክንያት ቀደምት ኢትዮጵያውያን በአምልኮተ እግዚአብሔር የነበሩ በአንድ አምላክ የሚያምኑ አብርሀማውያን በመሆናቸው አብርሀም አባታችን ብለው ያምኑም ስለነበረ በኦሪቱ ስርአት የአብርሀም ዘር የአንድ አምላክ አማኞች መገረዝ ግዴታቸው ነበረ ያልተገረዘ የአብርሀም ዘር አደለም ስለሚባል ልክ በሐዲስ ኪዳን ያልተጠመቀ ክርስቲያን እንደማይባል ሁሉ በኦሪቱም ያለተገረዘ እንደዛው ነው ስለሆነም የአብርሀም ዘር ነን በእግዚአብሔር እናምናለን ሲሉ ኢትዮጵያውያን የተገረዘ የወንድ ልጅ ብልት ቅርፅ አድርገው አክሱምን አቁመውታል ከሩቅ የሚመለከቱት ነጋዴዎች ስደተኞች ሁሉ ይህ ስፍራ ማረፊያቸው ነበረ። በሐውልቱም ላይ ብዙ ምስጢራዊ የሆኑ ምልክቶችና መልዕክቶች አስፍረውበታል።
በአጠቃላይ አክሱም የምስጢሮች ሁሉ ቁልፍ ናት እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይባርክ።

አሜን

Share አይረሳ


. Join 👇👇👇

@booksandopinions
@booksandopinions


#የህይወት_ዋጋው_ስንት_ነው?

ከእለታት ባንዱ ቀን አንድ ታዳጊ አባቱን
“የህይወት ዋጋው ስንት ነው?” ሲል
ጠየቀው፡፡ አባትም መልስ በመስጠት
ፈንታ ልጁን እንዲህ ሲል አዘዘው፡፡
“እንካ ይህንን የድንጋይ ቁራጭ...ወደ
ገበያ ውሰደው "
"ሰዎችም ዋጋውን ከጠየቁህ
በጣቶችህ ሁለት ቁጥርን ብቻ
አሳያቸው እንጂ ምንም አትናገር”
አለው፡፡ ልጁም ድንጋዩን ወሰደ፡፡
ወጥቶም በገበያ መሃል ቆመ፡፡ አንዲት
ሴትም መጣች፡፡
“ይህ ድንጋይ ዋጋው ስንት ነው?
ብትሸጥልኝ ወስጄ ግቢዬ ውስጥ
አስቀምጠዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም
እንደታዘዘው ምንም ሳይናገር ሁለት
ጣቶቹን አሳያት፡፡ እሷም አለች
“ሁለት ብር? እወስደዋለሁ!!”
ልጁም ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ በገበያ
ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም አለው
“አሁን ደግሞ ድንጋዩን ይዘህ ወደ
ሙዚየም ሂድ ዋጋውን ሲጠይቁህም
ሁለት ጣቶችህን አሳይ”
ልጁም ወደ ሙዚየም ወጣ፡፡ ገዢም
መጥቶ ዋጋ በጠየቀው ጊዜ ሁለት
ጣቶቹን አሳየው፡፡ ገዢውም “ሁለት
መቶ ብር? እወስደዋለሁ!” አለው፡፡
ልጁም በድንጋጤ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡
ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም ተናገረ፡፡ “አሁን ደግሞ
በመጨረሻ ድንጋዩን ይዘህ ወደ የከበሩ
ማዕድናት መሸጫ ሂድ ለባለቤቱም
አሳየው”
አለው፡፡ ልጁም ሄደ ለሱቁም ባለቤት
አሳየው፡፡ የሱቁ ባለቤት በመገረም
“ይህ እኮ አለም ላይ እጅግ ውድ ከሆኑ
የከበሩ ድንጋዮች አንዱ ነው” አለ፡፡
“ከየት አገኘኸው? ስንትስ
ትሸጠዋለህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም
ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳየ፡፡
የሱቁም ባለቤት አለ.... “ይህንን
ድንጋይ በሁለት መቶ ሺህ ብር
እወስደዋለሁ፡፡”
ልጁም በመገረም እየሮጠ ወደ ቤቱ
ተመልሶ ያጋጠመውን ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም “ልጄ አሁን የህይወትህ
ዋጋ ተገልጦልሃል” አለው፡፡
አየህ የመጣህበት ቦታ፣ ዘርህ፣
ሃይማኖትህ፣ የቤተሰቦችህ ሃብት፣
የተወለድክበት ቦታ ልዩነት
አይፈጥርም፡፡ ዋናው ራስህን
የምታስቀምጥበት ቦታ፣ ራስህን
የምታገኝበት የሰዎች ስብስብ ነው፡፡
ልዩነቱ ያለው ራስህን ለመሸከም
በምትመርጥበት መንገድ ነው፡፡
ህይወትህን ሙሉ የሁለት ብር ድንጋይ
ዋጋ ስትሰጠው ኖረህ ይሆናል፡፡
ህይወትህን ሙሉ የኖርከው ዋጋህ
ሁለት ብር ብቻ እንደሆነ በሚያስቡ
ሰዎች ተከበህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን
እያንዳንዱ ሰው ውድ የሆነ የከበረ
ድንጋይ በውስጡ ይዟል፡፡ ልዩነቱም
ያለው ውስጣችን
ያለውን የከበረ ድንጋይ አይተው ዋጋ
በሚሰጡን ሰዎች መሃል መገኘትን
ስንመርጥ ነው፡፡ ራሳችንን በገበያ
ወይም በከበሩ ማዕድናት ሱቅ
የማስቀመጥ ምርጫው አለን፡፡
በሌሎች ሰዎች ውስጥ ያለውንም
ውድ ዋጋ ለማየት ምርጫው የኛው
ነው፡፡ ሌሎች ሰዎችም የከበረ
ዋጋቸውን እንዲረዱ ማድረግ
እንችላለን፡፡ አብረህ የምትውላቸውን
ሰዎች በጥንቃቄ ምረጥ፡፡ ይህ
በህይወትህ ልዩነትን ይፈጥራልና !!



┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄
             
   ╔═══❖•🌺•❖═══╗ #ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ

           ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤
@booksandopinions
@booksandopinions
@booksandopinions


የባዕድ ሐገር ስሞች ትክክለኛ የግዕዝ ትርጓሜያቸው።

፩. ኮሌጅ ------ መካነ ትምህርት
፪. ዩኒቨርስቲ ------ መካነ አምሮ
፫. ሌክቸር ------ ትምህርተ ጉባኤ
፬. ሌክተቸረር ------ መምህረ ጉባኤ
፭. ዲን ----- ሊቀ ጉባኤ
፯. ቢሮ ------ መስሪያ ቤት
፰. ባንክ ------ ቤተ ንዋይ
፱. ሲቪል ሰርቪስ ------ ሰላማዊ አገልግሎት
፲. Custom ------ ኬላ
፲፩. ኮምፒተር ------ መቀመሪያ
፲፪. ድግሪ ------ ማዕረግ
፲፫. ሚኒስተር ------ ምሉክ
፲፬. Mass media ------ ምህዋረ ዜና
፲፭. ፎቶ ግራፍ ------ ብራናዊ ስዕል
፲፮. ራዲዮ ------ ንፈሰ ድምፅ
፲፯. ፖሊስ ------ የህግ ዘበኛ
፲፰. ኢንተርኔት ------ የህዋ አውታር
፲፱. ሎሬት ------ አምበል ፣ ተሸላሚ የቅኔ
፳. ዶክተር ------ ሊቀ ሙህር
፳፩. ኢምባሲ ------ የእንደራሲ ፅ/ቤት
፳፪. ዲፕሎማት ------ የመንግስት መልክተኞች
፳፫. ኢኮኖሚክስ ------ ስነ ብዕል
፳፬. ሀዋላ ------ ምህዋረ ንዋይ
፳፭. ሳሎን ------ እንግዳ መቀበያ
፳፮. ቱሪዝም ------ ስነ ህዋፄ
፳፯. ስካን ------ ምክታብ
፳፰. ፕሬዝዳንት ------ ሊቀ ሀገር / ሙሴ
፳፱. ቴሌኮሚኒኬሽን ------ ምህዋረ ቃል
፴. ቪዛ ------ የይለፍ ፍቃድ
፴፩. ፓስፖርት ------ የኬላ ማለፊያ
፴፪. ቴሌቪዥን ------ ምስለ መስኮት / መቅረፀ ትይንት
፴፫. Voice Recorder ----መቅረፀ ድምፅ

@booksandopinions
@booksandopinions
@booksandopinions


When we reach 500 we will start to accept request so please share our link to friends and family
@booksandopinions
@booksandopinions
@booksandopinions


All the best books👆👆👆👆


Репост из: Godfather
The_Count_of_Monte_Cristo__Pen.epub
1.3Мб
The Count of Monte Cristo


Репост из: A R
The Great Gatsby.epub
435.8Кб
#Classics #Fiction #Literature #Historical #Romance #Young_adult
Join ➠(group) @books_hub_english
Join ➠ @fiction_book
Join ➠ @nonfiction_book
Join ➠ @self_help_books_english

Показано 20 последних публикаций.

71

подписчиков
Статистика канала