"የጥቁር ሰው ቁጣ"
የሙሶሎኒ ግፍ እንጥሻ፡
ካሳው ቢርቅ እንደዋሻ..:
.....እንደ ጥሻ፡
ይማርህ ባይ የሚለው ቢያጣ
ገላጋይ ሰው ወጌሻ፡
እያደር ግፉ ሲፋፋ...
ጠቡ ጥበቱ ሲሰፋ..
እንደ ተናካሽ ውሻ ካለቅጥ ሲወበራ፡
ውሻም በደጁ ነበረ ቢኮራ ።
ሀገር ማፍረስ ..
ድንበር መቁረስ..
ቅኖና መጣስ..
ዶግማ መቀንጠስ..
ማህተብ መበጠስ..
ይህ በሽታው ታጥቶለት ፈውስ፡
አድዋ ጣለው በፈረስ ።
በአየር በፈረስ ሲቀናጣ፡
መድሀኒት ሆነው የሀበሻው ክንድ
የጥቁር ሰው ቁጣ ።
ያገሬ አርበኛ ጠላት ሲመጣ መተኮስ፡
የደላው እንደሆ ማረስ፡
የመነነ እንደሁ መቀደስ፡
በለስ ከቀናው መንገስ፡
የሀረጉ ነው የዘሩ ብቃይ፡
የዘመዶቹ የአብራኩ ክፋይ ።
የአዛውንቱ ምርቃት፡
የወዛዝርቱ እህል ስንቃት፡
የአርበኛው ሁሉ ደምፍላት፡
የጣይቱ ትኩሳት፡
የሚኒሊክ ሱባዔ፡
የመናኞቹ ጉባዔ፡
የሊቃውንቱ ወረብ፡
የፈረስ በቅሎው ወገብ፡
ቁጣመርከቡ ዘረገፋቸው
አድዋ ከደሙ ወደብ ፡
ጣልያን ሀያሉን የጥቁር ሰው
ቁጣ አስገዛው አደብ ።
#ገጣሚ ፋሲካው
ጌታቸው(አርከለዲስ)
የካቲት 23/1888 ዓ.ም
#አድዋ
@eliyasshitahun
@eliyasshitahun
የሙሶሎኒ ግፍ እንጥሻ፡
ካሳው ቢርቅ እንደዋሻ..:
.....እንደ ጥሻ፡
ይማርህ ባይ የሚለው ቢያጣ
ገላጋይ ሰው ወጌሻ፡
እያደር ግፉ ሲፋፋ...
ጠቡ ጥበቱ ሲሰፋ..
እንደ ተናካሽ ውሻ ካለቅጥ ሲወበራ፡
ውሻም በደጁ ነበረ ቢኮራ ።
ሀገር ማፍረስ ..
ድንበር መቁረስ..
ቅኖና መጣስ..
ዶግማ መቀንጠስ..
ማህተብ መበጠስ..
ይህ በሽታው ታጥቶለት ፈውስ፡
አድዋ ጣለው በፈረስ ።
በአየር በፈረስ ሲቀናጣ፡
መድሀኒት ሆነው የሀበሻው ክንድ
የጥቁር ሰው ቁጣ ።
ያገሬ አርበኛ ጠላት ሲመጣ መተኮስ፡
የደላው እንደሆ ማረስ፡
የመነነ እንደሁ መቀደስ፡
በለስ ከቀናው መንገስ፡
የሀረጉ ነው የዘሩ ብቃይ፡
የዘመዶቹ የአብራኩ ክፋይ ።
የአዛውንቱ ምርቃት፡
የወዛዝርቱ እህል ስንቃት፡
የአርበኛው ሁሉ ደምፍላት፡
የጣይቱ ትኩሳት፡
የሚኒሊክ ሱባዔ፡
የመናኞቹ ጉባዔ፡
የሊቃውንቱ ወረብ፡
የፈረስ በቅሎው ወገብ፡
ቁጣመርከቡ ዘረገፋቸው
አድዋ ከደሙ ወደብ ፡
ጣልያን ሀያሉን የጥቁር ሰው
ቁጣ አስገዛው አደብ ።
#ገጣሚ ፋሲካው
ጌታቸው(አርከለዲስ)
የካቲት 23/1888 ዓ.ም
#አድዋ
@eliyasshitahun
@eliyasshitahun