🙅♀🙅♀🙅♀
ወንድነትስ ሲባል
ሱሪዉን አጥልቆ
ቀበቶዉን ታጥቆ
ልቡን አጀግኖ እሚወጣ ነበር
ወንድም እሚባለዉ በዚ ወኔዉ ነበር
ምነዋ ዛሬ ግን ሀሞቱ ቀጠነ
ወንድነቱ ጠፍቶ ጅጋኔው መነነ
ማንነቱን ረስቶ ለስሜቱ ኖረ
አባትነት አንሶ ወንድነት ከበረ
ለዚ ለፌ ሀሳቡ
የልጁን የእህቱን መቅኔ በቁሟ ቀበረ
የመኖሩዋን ጣዕም
በአባትነት ሳይሆን ለራሱ ሠወረ
በወንድነት ወልዶ በስሜት ሲቀብራት
ታዲያ እንዲህ
አይነቱ ወንድ ነው ወይ ሚባል ወይ አባት
ቅጣቱስ ምን ይሁን ምን እንበይንለት
አይበቃው አይሆን ለሱ ሞት ቅጣት
ወይም አሳብደን ይዙር ይዋት?
አይ ወይ ይሁን ለእግዜር እንተውለት?
ፍርድም ያነሠ ለት
ወንድም አባትም ቀበቶውን የፈታ ለት::
@Be_nayas
@flawsome_poetry
ወንድነትስ ሲባል
ሱሪዉን አጥልቆ
ቀበቶዉን ታጥቆ
ልቡን አጀግኖ እሚወጣ ነበር
ወንድም እሚባለዉ በዚ ወኔዉ ነበር
ምነዋ ዛሬ ግን ሀሞቱ ቀጠነ
ወንድነቱ ጠፍቶ ጅጋኔው መነነ
ማንነቱን ረስቶ ለስሜቱ ኖረ
አባትነት አንሶ ወንድነት ከበረ
ለዚ ለፌ ሀሳቡ
የልጁን የእህቱን መቅኔ በቁሟ ቀበረ
የመኖሩዋን ጣዕም
በአባትነት ሳይሆን ለራሱ ሠወረ
በወንድነት ወልዶ በስሜት ሲቀብራት
ታዲያ እንዲህ
አይነቱ ወንድ ነው ወይ ሚባል ወይ አባት
ቅጣቱስ ምን ይሁን ምን እንበይንለት
አይበቃው አይሆን ለሱ ሞት ቅጣት
ወይም አሳብደን ይዙር ይዋት?
አይ ወይ ይሁን ለእግዜር እንተውለት?
ፍርድም ያነሠ ለት
ወንድም አባትም ቀበቶውን የፈታ ለት::
@Be_nayas
@flawsome_poetry