سورة الزخرف
بسم الله الرحمن الرحيم
ክፍል አንድ
ምእራፏ እስላማውይ ዳአዋ በመካ የገጠሙትን እንቅፍቶች ችግሮች ሙግቶች ክርክሮች ትዳስሳለች ቁርአን እነኝህን ችግሮች በምን አኳኋን ይፈታና የሰዎችን ልቦና ያክም እንደነበር የ ጃሂልያን አመለካከት ከሰዎች አምሮ በመፍቅ በምትኩ ኢስላማውይን አመለካከት የሚያሰርጽበትን ስልት በትቂቱም ቢሆን ታሳየናለች ።የዚህ ክፍል አናቀፅ በዚህ እረገድ የራሳቸውን ድርርሻ ይወጣሉ።
ዐረቦች በቅድመ ኢስላም ከእንስሳት ጋር የተያያዙ በርካታ የተሳሳቱ እምነቶች ነበሯቸው።ከነኝህ እንስሳወች አላህ የራሱ ድርሻ አማልክቶቻቸውም የራሳቸው ዲርሻ እንዳላቸው ያምናሉ።ከእንስሳት ለምግብነት ለግልቢያም የማይጠቀሙባቸውም ነበሩ ።በዚህ ክፍል ለነኝህ አጓጉል እምነቶቻቸው ተገቢ ምላሺ ተሰቷቸዋል እንስሳት የአላህ ፍጡራን ከአላህ ታአምራትም የሚፈርጁ ናቸው።አላህ ለሰው ልጆች መገልገያነት የፈጠራቸው መሆናቸው የሰው ልጂም ለዚህ ውለታው ምላሺ አምላኩን ማመስገን እንጂእንስሳቱን ለጣኦታት አምልኮ ማዋል እንደሌለበት ከእንስሳት ጋር በተያያዘ አላህ ያልደነገገውን ህግ መከተላቸው አግባብነት እንደሌለው ተብራራላቸው።
መላእክት የአላህ ሴት ልጆች ናቸው የሚል እምነትም ነበራቸው ።ይህ እምነታቸውም አጉል እንደሆነ በሚገባቸው ቋንቋ ና አመክንዮ (ሎጂክ)ተገለፀላቸው።
ይህን ሁሉ የወረሱት ከአባቶቻቸው እንደሆነ በኩራት ይናገሩ ነበር ።እምነት መርምረውትና አጢነውት የሚገቡበት እንጂ እንደቁስ ከአባት የማይወረስ በጭፍኑ ሊከተሉት የማይገባ እንደሆነ የአባቶቻቸውን ስህተት መድገማቸው ወደጥፋት የሚያመራ አካሄድ መሆኑ የታሪክ አማኝ ተጠቅሶ ተናግሯል ።
አላህ ምን አለ
إنا جعلنه قرءانا عربيالعلكم تعقلون
እኛ (ጥበብን ማወቅና)መረዳት ትችሉ ዘንዳ ቁርአንን በዐረበኛ አደረግነው። ይላል አላሁ ሱብሀነሁ ወታእል
وإنه فى أم آلكتب لدينالعلى حكيم
እርሱ በእርግጥም ከኛ ዘንዲ ከመፀሀፎች እናት ውስጥ የሰፈረ ደረጃውም ከፍተኛና በጥበብ የተሞላም ነው።
የዚህ አንቀፅ ማብራሪያው
የመፀሀፍ እናት በሚል የተጠቀሰው "ለሕወል መሕፉዝ"(የተጠበቀ ሰሌዳ በመባል የሚታወቀው ሲሆን የመለኮታውይ መለአክት ምንጭ መሆኑን ቁርአን ውስጥ ጠቅሷል ።
وكم أرسلنامن نبى فى آلأولين
በቀደምት ህዝቦች ውስጥ በርካታ ነብያቶች ልከናል
የዚህ አንቀፅ ማብራሪያ
የቀደምት መሠሎቻቸውንም ታሪክ ትምህርት ይሆናቸው ዘንዲ ይዘክርላቸዋል።
መልክተኞችን ላከላቸው ግን መልክቱን በቀና ልቦና አላስተናገዱም ።በነብያት አፌዙ በቁም ነገር ቀለዱ ።በመሆኑም አላህ አጠፋቸው ።
https://t.me/gfffffffbbb