የሀቅ ብቻ ጠበቃ እንሁን
ውድ የአላህ ባሮች ሆይ አላህ ውደታችንንም ሆነ ጥላቻችንን ሊላህ ያድርግልን። ምንጊዜም ቢሆን ሀቁ ምንድነው የሚለውን እናስቀድም ሀቅን ላለመቀበል የአላዋቂዎች ምክያቶችን አናምጣ።
በዚህ ጉዳይ ብዙዎቻችን ተፈትነናል፣ አንዳንድ ጊዜ ለነፈስያችን ስንል እንወዳለን፣እገሌ ይመቸኛል ፣እገሌ አይመቸኝም ደረቅ ነው አይጥምም፣ ብዙም እውቅት የለውም፣ እገሌ እኮ ትልቅ ሸክ ነው ብዙ ኪታብ ቀርቷል፣ ወዘተ ።
አንድ የሱና ወንድምህ ስለ ቢድዓህና ስለቢድዓ ሰዎች ሲነግርህ ካላመንከው ያለውን ነገር እውነታ አጣራ ካለበለዚያ ሃቅን በተልካሻ ምክንያት አታስተባብል ፣ሀቅ ሙስሊም የጠፋው እቃ ናት የትም ቢያገኛት ይይዛታል።ዛሬ ዛሬ ግን ሀቅ የራሱ ሸክ ወይም ኡስታዝ ካልነገረው እንደባጢል እየታየ ፣ሀቅ በእልክ እየተቀየረ መጥቷል፣ መቼም የሀገራችን ኡስታዝነት ባስተማረ ሳይሆን በቀራ ስለሆነ ስንት አመት ሙሉ በተውሂድ ዳእዋ ላይ የቆዮ ሰዎች ጃሂሎች ሲባሉ ሰለፊዮችን የሚተቹ ደግሞ ዶክተሮች ፣ኡስታዞች መባል ከጀመረ ሰነባብቷል። ነገር ግን ወደድንም ጠላን የጀነት ሰዎች ብሉ ጠጡ የሚባሉት አውቀው በሰሩት ምክንያት እንጅ ባወቁት ወይም በቀሩት ብቻ እንዳልሆነ ሁላችንም ልንገነዘብ ይገባል፣ ብዙ አውቀን ስራ ላይ ደካማ ከምንሆን ትንሽ አውቀን ብንሰራ ይሻላል ። አላህ የሚናገሩትን ከሚተገብሩ፣ ወደተውሂድ ከሚጣሩ ያድርገን።