ዛሬ ከትንሽ ጊዜ በኋል የተባባሩት መንግስታት ጸጥታ ምክርቤት በህዳሴው ግድብ ውዝግብ ላይ ይወያያል። የሚገርመው ነገር ጉዳዩን በ 'የአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ' በሚል አጀንዳ ስር ነው የሚያየው። የህዳሴው ጉዳይ የውሃ ክፍፍሎች ንትርክ እንጂ ወደ ጦርነት የሚያደርስ እንዳልሆነ ሁሉም ያውቃል። ግብጽ እና አሜሪካ በዚህ አጀንዳ ስር እንዲካተት ያደረጉት ጠንከር ያል ሪሶሉሽን በማሳለፍ በተባለው ሁለት ሳምታት ውስጥ ስምምነት ላይ ካልተደረስ በኢትዮጲያ ላይ ማእቀብ ለምጣል እንዲያመች ነው። የሚገርመው የወቅቱ የጸጣው ምክርቤት ፕረዚደንት ፈረንሳይ ይህን መፍቀዷ እና የኛ ዲፕሎማቶች አጥብቀው አለመቃወማቸው ነው።
በነገራችን ላይ በዲፕሎማሲው መስክ ሽንፈት እየገጠመን መሆኑን ማመን አለብን። ለዚህ ደግሞ አንዱ ምክንያት በዚህ ጉዳይ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳር ተመልካች መደፈጉ ነው። የውሃ ሚኒስቴር በቴክኒካል ድርድሩ ላይ ቀዳሚውን ሚና እንዲጫወት ማድረጉ ተገቢ ቢሆንም፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርን መግፋቱ የዲፕሎማሲው ስራ እንዲንቀረፈፍ እና እንድንሸነፍ አድርጓል። ይህን ጉዳይ በግንባር ቀደምነት መምራት የነበርተበት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው። አሁንም ባስቸኳይ ካልተስተካከል የባሰ ሽንፈት ይገጥመናል። ይታሰብበት!