አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካአተሁ ዉድ የሙስሊሞች ጉዳይ የዉይይት መድረክ አባላት እዲሁም የተከበራችሁ ኡስታዞቻችን።
የዚህ ግሩፕ
👇👇👇👇
አላማ
--------------------
ልዩነትቶችን በዉቀት በታጀበ እና በሙስሊሞች አደብ የሚፈጠሩትን የአቂዳ ልዩነቶች በዉይይት ልዩነቶቸን
ማጥበብ ።
እዲሁም ደግሞ በወድሞቻችን ላይ የሚፈጠሩትን ዲናዊ ማንኛዉም ጥያቄወች በሸሪአዊ መንገድ ምላሽ መስጠት ነዉ ። የሚፈጠሩ የተቀነባበሩ የዉሸት ወሬወችን (ፖስቶችን) በመረጃ እና በማስረጃ ዉድቅ ማደረጊያ እና መማርያ ጉሩፕ ነዉ ።
እራአይ
-----------------
ሀቅን ማንገስ ባጢልን ማንኮታኮት ጭቅጭቆችን ማስወገድ ዉይይትን ማድረግ እዲሁም የተለያዩ ዲናዊ አስተምህሮቶችን በኡስታዞች አማካኝነት ማስተማር ነዉ ።
የግሩፑ ዋና ዋና ተግባራቶች
----------------------------------------------
1 ኛ 👉 የዉይይት መድረክ መፍጥር
2 ኛ 👉 የፈተዋ (ጥያቄና መልስ)
3 ኛ 👉 በኡስታዞቻችን ዲናዊ ትምህርቶችን መማር ነዉ ።
የጉሩፑ የመወያያ ህግና ደንቦች
-------------------------------------------------
👇👇
በዉይይት ወቅት
----------------------------
ከታች የሚዘረዘሩትን ህግናደንቦች መተግበር እዲሁም ማሟላት የሚችል ተወያይ ካለ ለዉይይት የተመደቡ ኡስታዞች አሉን
1 ኛ 👉
@Reyhibi (ኡስታዝ መቅሱድ ሙራድ)
2 ኛ 👉
@Habibabdery ( ኡስታዝ ሀቢብ ኑሩ)
3 ኛ 👉
@Genamintayena ( ኡስታዝ አንዋር)
4 ኛ 👉
@Aseduallah (ኡስታዝ ሀይደር ሙሀመድ)
ሌሎች ስማቸዉ ያልተጠቀሱ ኡስታዞቻችን አሉ ለዉይይት በህግና ደንቡ መስረት መወያየት ይቻላል ።
ህግ
---------------
1 ኛ 👉 ፀባይ
2 ኛ 👉የሚወያይ ሰዉ ካለ ወይ ደግሞ ልትወያዩት የምትፈልጉ ሰዉ ካለ ስም መጠቀስ እርእስ አቅርቦ ፍቃደኝነት መጠየቅ
3 ኛ 👉 ፍቃደኛ ተወያይ ሲገኝ ለዉይይት የሚመቸዉን ቀን ተወያይቶ ቀነ ቀጠሮ ማስያዝ
🙏4 ኛ 👉 ዉይይቱ ቀን ሲደርስ ማንነትን በማስተዋወቅ
5 ኛ 👉 በቂ የዲን እወቀት ይዞ መገኘት
6 ኛ 👉 ለመረጃነት የሚቀርቡትን ኪታቦች ሆኑ ማንኛዉንም መረጃ ዝግጁ አድርጎ መቅረብ
7 ኛ 👉 ከተወያዩች መካከል ጋባዡ የመግብያ ንግግር 15 ደቂቃ ያልለጠ የድምፅ መክፈቻ ማድረግ
8 ኛ 👉 የአቋም መግለጫ ንግግር ከሁለቱም ወገን 25 ደቂቃ ያል በለጠ ንግግር ማድረግ
9 ኛ 👉 ለሚጡት ምላሾች መረጃዉን እሰከ ማስረጃዉ በግልፅ ቋንቋ ማቅረብ
10ኛ 👉 የተጠየ ጥያቄ በሚገባ ተመልሶ ሳያልቅ ወደሌላ ጥያቄ መግባት የማይቻል ሲሆን ነገርግን ጥያቄ አዘል ምላሽ መስጠት የተፈቀደ ነዉ
11 ኛ 👉 ጥያቄየ አልተመልለኝም ብሎ ቅሬታ የማቅረብ መብት የተጠበቀ ሆኖ ነገርግን ግልፅ ያልሆነዉን ቦታ መናገር እና ማብራራት ግድ የሆነ ተግባር ነዉ
12 ኛ 👉 ከርእስ መዉጣት ፈፅሞ የተከለከከለ ነዉ
13 ኛ 👉 መረጃወቸን አጠናቅሮ ማቅረብ በድምፅ የሚቀርቡትን በድምፅ በፎቶ የሚቀርቡትን በፎቶ በፁሁፍ የሚቀርቡትን በፁሁፍ የማቅረብ ግዴታ አለበት
14 ኛ 👉 የዘለፋ ቃላቶችን መጠቀም የተከለከለ ሲሆን ለምሳሌ አህባሽ : ዉሀብያ : የመሳሰሉትን
15 ኛ 👉 ዉይይቱ የሚዝም ከሆነ ክፍል የሚበጅለት ይሆናል
16 ኛ 👉 የኔትወርክ ችግር ሊገጥም ስለሚችል ትግስት አስፈላጊ ነዉ
17 ኛ 👉 በማያዉቁት ነገር ላይ ምላሽ መስጠት የተከለከለ ነዉ
18 ኛ👉 ርእስ ለማስቀየር ጥረት ማድሰግ የተከለከለ ነዉ
19 ኛ👉 ዉይይቱ ወደማገባደጃዉ ሲደርስ እና ሲቋጭ
ከሁለቱም ወገን የተማሩትን ነገር እና የተደረሰበትን ድምዳሜ መግለጫ መስጠት ግዴታ ነዉ
ማሳሰብያ
--------------------
ይህ ህግ እና ደንብ የሚሻሻልበት አጋጣሚ የሚኖር ይሆናል ይህ ህግና ደንብ የጋራ እደመሆኑ መጠን ህጉን መተላለፍ የማይቻል ነዉ የተላለፈ ሰዉ ወዲያዉኑ ይቅርታ ለታዳሚያን መጠየቅ ይኖርበታል ።
የፈትዋ ወይም የጥያቄ እና መልስ ህጎች
---------------------------------------------------------
👇👇👇👇👇
የጠያቂዉ መብቶች
1ኛ 👉 ማንኛዉንም ዲናዊ ጥያቄ የመጠየቅ ሙሉ መብት አለዉ
2ኛ 👉 ምላሽ ይሰጠኝ የማለት ሙሉ መብት አለዉ
3ኛ 👉 ጥያቄወቹን በቮይስም ሆነ በፁሁፍ የማቅብ መብት አለዉ ።
የጠያቂዉ ግዴታ
-----------------------------
1 ኛ 👉ፀባይ
2 ኛ 👉 ትግስት
3 ኛ 👉 ጥያቄዉን ለተጠያቄዉ በሚገባዉ ቋንቋ የማቅረብ ግዴታ አለበት
4 ኛ 👉 ምላሽ እስኪሰጠዉ የመጠበቅ ግዴታ አለበት
5 ኛ 👉 በአድ ቀን ዉስጥ ከ 5 ጥያቄ የበለጠ መጠየቅ የተከለከለ ነዉ
6 ኛ 👉 ተራዉን ጠብቆ የመጠየቅ ግዴታ አለበት
የመላሹ መብት
1 ኛ👉 የተጠየቀዉ ጥያቄ ካልገባዉ እዲብራራለት የመጠየቅ መብት
2 ኛ 👉 በፁሁፍም ሆነ በድምፅ ምላሽ የመስጠት መብት
3 ኛ 👉 ጥያቄ አዘል ምላሽ የመስጠት መብት
4 ኛ 👉 ጥያቄዉን ወደ ለላ ኡሰስታዝ የማስተላለፍ መብት አለዉ
የመላሹ ግዴታ
-----------------------------
1 ኛ👉 ምላሹን በሚገባ ማብራራት እና መረጃ በማስረጃ ጠናቅሮ ማቅረብ
2 ኛ👉 የሚሰጠዉ ምላሽ ጠያቂዉን በሚገባዉ ቋንቋ መሆን አለበት
3 ኛ 👉 መረጃ የመሰጠት ግዴታ አለበት
4 ኛ 👉 እደተመለሰለት የመጠየቅ ግዴታ አለበት
የታዳሚያን መብት
------------------------------
1 ኛ 👉ጥያቄ የመጠየቅ መብት
2 ኛ 👉 አስተያየት የመስጠት መብት
3 ኛ 👉 የመወያየት መብት
4 ኛ 👉 የመፍትሄ ሀሳብ የማቅረብ መብት
5 ኛ 👉 ጠቃሚ ቻናሎችን የማስተዋወቅ መብት
------------------