Репост из: Bahiru Teka
🔷 ወንድማዊ ምክር
የሰውን ሐሳብ የኔ ነው ብላችሁ ርእስ ቀይራችሁ ስሙን አጥፍታችሁ የራሳችሁን ስም ፅፋችሁ በቻናላችሁ ላይ የምትለቁ ይህ ተግባር በየትኛውም መመዘኛ ስህተት ነው ። ወንድሜ ሆይ እራስህን ለመሆን ሞክር , ምክንያቱም በሌላ የተሸፈነ ማንነት ሽፋኑ ተነስቶ መታየቱ አይቀርምና ። አንድ ሙስሊም ነኝ ከሚል ሰው እንዲህ አይነት ተግባር አይጠበቅም እንኳን ወደ ሱና ከፍ ብያለሁ ከሚል ይቅርና ። አላህ ሰዎች እንኳን ባልሰሩት ስራ መመስገን ሊፈልጉ ይቅርና በራሳቸውም ስራ ሊመፃደቁ እንደማይገባ ካልሆነ ግን ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እንዲህ በማለት ይነግረናል : –
" لَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ يَفْرَحُونَ بِمَا أَتَوا وَّيُحِبُّونَ أَن يُحْمَدُوا بِمَا لَمْ يَفْعَلُوا فَلَا تَحْسَبَنَّهُم بِمَفَازَةٍ مِّنَ الْعَذَابِ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيم ٌ"
آل عمران ( 188 )
" እነዚያን በሠሩት ነገር የሚደሰቱትንና ባልሠሩትም መመስገንን የሚወዱትን አታስብ ፤ ከቅጣት በመዳን ላይ ናቸው ብለህ አታሰባቸው ፡፡ ለእነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው ፡፡"
ይህ አንቀፅ የዚህ አይነቱ ተግባር የሙስሊሞች አለመሆኑን ነው የሚያሳየን ። በዲን ጉዳይ አንድን ንግግር ስንወስድ ንግግሩን ወደ ባለቤቱ ማስጠጋት አማና ዒልሚያ በመባል ይታወቃል ። የእውቀት አደራ ነው ። ይህ ከሌለ አደራ እንደመብላት ይቆጠራል ።
ትላንት ( ወደ አላህ ሽሹ ) በሚል ርእስ የፃፍኩትን ፁሁፍ አንዱ ተነስቶ ( ወደ አለህ እንሽሽ ) በሚል ርእስ ቀይሮ ስሙን አጥፍቶ በራሱ ስም በቻናል ላይ የለቀቀው መሆኑን ሲያሳዩኝ በጣም ነው ያዘንኩት ። ምን አይነት ትወልድ እያፈራን እንደሆነ ያውም በዲን ጉዳይ !!!!!
መልእክቱ ራሱ ከእንደዚህ አይነት ተግባር እንራቅ የሚል ነው ። ከወንጀል ርቀን ተውበት አድርገን ወደ አላህ መጠጋት እንዳለብን ነው የሚመክረው ።
ታዲያ ያልሆኑትን ነኝ እያሉ ወደ አላህ መሸሽ አለ እንዴ ?
የሰውን ሐሳብ የኔ ነው እያሉ ወደ አላህ መሸሽ አለ?
ያልሰጡትን ሰጥቻለሁ እያሉ ወደ አላህ መሸሽ አለን ?
ሰው የፃፈውን ሽፋኑን ቀዶ ጥሎ በራስ ስም ሌላ ሽፋን አበጅቶ ለአንባቢ እያቀረቡ ወደ አላህ መሸሽ አለ እንዴ ?
ይህ ተግባር እኔንም ሆነ ሌሎች ሀሳባቸው የሚሰረቅባቸውን ወንድሞች አይጎዳም የሚጎዳው ባለቤቱን ነው ። ሌሎችም ለካ እንዲህ ማድረግም ይቻላል እንዴ ብለው የዚህ አይነት የሐሳብ ሌብነት ውስጥ እንዳይገቡ ነው ለማስታወስ የተፈለገው ። እንጂ ተግባሩ የግለሰቡን ማንነት ከማሳየቱ ሌላ ፋይዳ የለውም እና ከእንደዚህ አይነት ተግባር እንጠንቀቅ ።
https://t.me/bahruteka