Photography & Arts


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ጥበብ ብቻ።

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


#mariyamawit
@photographyarts




Italy


#አላገባሽም

አገባሻለሁ ብዬ ቃሌን ስትጠብቂ
አመታት አልፈዋል ቀኑን ስትናፍቂ
ዛሬ ግን ውድዬ እንዲህ ነው እውነቱ
የኔና'ቺ ነገር ቀርቷል መጋባቱ
ለምን ማለት ጥሩ ለምን በይኝማ
እውነቱን እወቂው ልብሽም ቢደማ
:
ታማኝሽ ነኝ ብዬ ላመታት የኖርኩት
ካንቺ ወድያ ላሳር ብዬ የፎከርኩት
እውነት እንዳይመስልሽ ሁሉም ውሸት ከንቱ
ልንገርሽ በደሌን ቁጠሪብኝ እቱ
:
(በደል 1)
:
ካስታወሽ...
ውዲቷ ጓደኛሽ የወለደች ሰሞን
ብዬ ስጠይቅሽ አባቱ ማን ይሆን
እንኳን እኔ ቀርቶ እሷስ መቼ አውቃ
ግራ ተጋብታለች ባየሀት ተጨንቃ
ያልሽኝ
በይ ዛሬ እወቂው አባቱኮ 'ኔነኝ
ከገዛ ጓደኛሽ አንድ ልጅ አፍርቼ
ስቀልድ የኖርኩት አንቺን እረስቼ
:
(በደል 2)
:
ሲሻኝም ለሳምንት በል ሲለኝም ለወር
ፊልድ ነኝ እያልኩሽ የምርቀው ካገር
እቱ ስራ አይደለም ስትሰለቺኝ ነው
የለሁኝም ብዬ ድምፄን የማጠፍው
እናማ ባንቺ ላይ ይሄን ግፍ አድርጌ
ድፍረት አይሆንም ወይ ባገባሽ ሰርጌ
እናልሽ
በጣም ብዙ አለ ገና ያልነገርኩሽ
ግና የነገርኩሽ ይሄ ሁላ ጉዴ
#አፕሪል_ዘ_ፉል ነው ምር አይደለም ውዴ

* አቤል አስመላሽ

@photographyarts
-------------------------------
@photographyarts


Belay Bekele Weya
"እእፓ"(እኛው እንታረቅ ፓርቲ)
(በላይ በቀለ ወያ) # ሼር ይደረግ!
.
.
ከኛ ካልቀደሙ ፣ ምንከተላቸው
ለኛ ካላሰቡ ፣ ምሁር ምንላቸው
ከኛ የተሻለ
ማየትን ካልቻሉ ፣ እኛን የሚመሩን
ለእርቅ ያጨናቸው ፣ በፀብ ካቃቃሩን
አንድ አርጉን ያልናቸው
በብሔር ፣ በክልል ፣ ከፋፍለው ካጠሩን
ህልውናችንን
አምነን ምንሰጣቸው ፣ ለኛ ካለሰቡ
እኛን እንደማስፋት ፣ ቀድመው ከጠበቡ
ትውልድን ከትውልድ ፣ ካላቀራረቡ
አንድ ሀገር አፍርሰው ፣ መንደር ሳይገነቡ
በእኛ ላብ ሳይወዙ ፣ በኛ ደም ሳይሰቡ
እኛው እንታረቅ !
።።።
አክቲቪስቶቻችን ፣ አክቲቮች ካልሆኑ
የጎበጠን ትውልድ ፣ ጎብጠው ካላቀኑ
ለሀገር ካልቆሙ ፣
ሚከተላቸውን ፣ ወድቀው ካላፀኑ
እኛ አለንላቹ ፣ እሚሉን ከሌሉ
እንድንጠፋፋ ፣ ነገር ከፈተሉ
ቂም የቋጠረውን ፣ ማስታረቅ ካልቻሉ
ያለፈን ጠባሳ ፣ ነቅሰው ካልኳሉ
ለተቋሰልን እኛ ፣ ከኛ ካልተሻሉ
ቁስልን እንደማከም ፣ ቁስልን ከነካኩ
ሰላም እንደመስጠት ፣ በፀብ ከተመኩ
በኛ ላብ ሳይወዙ ፣ በኛ ደም ሳይረኩ
እኛው እንታረቅ።
።።።።
ነፃ አውጪ ነን ባዩ ፣ ጭቆናን ካመነ
ነፃነት ከነሳን ፣ በውሀ ቀጠነ
በታመሙ ህዝቦች
ለታመች ሀገር ፣ መድሐኒት ካልሆነ
ፈውስ መሆን ሲችል ፣ መርዝ ከቀመመ
ለመረዙት ትውልድ ፣ መርዝ ሆኖ ከቆመ
ስላም ለናፈቀው ፣ ሽብር ከሸለመ
ከኛ የተሻለው ፣ ለእኛ ካልጠቀመ
ለእኛ የታገለው ፣ ለእኛ ካልተገዛ
በሀገር ፍቅር ፈንታ
በሀገር ላይ ጥላቻ ፣ አትሞ ካባዛ
በእኛ ደም ሳይረካ ፣ በኛ ላብ ሳይወዛ
እኛው እንታረቅ።
።።።
የፖርቲዎች ብዛት ፣ ሀገር ካላፀና
ለሚነታረክ ህዝብ ፣ ካልሰጠ ፅሞና
ከኛ የተሻሉ ፣ ለእኛ ተደራጅተው
ከእኛ ቁጥር በላይ ፣ ፓርቲዎች መስርተው
ካላስተቃቀፉን ፣ በሀሳብ ተጣልተው
እኛን ሚወክሉ
ከእኛ ካልተሻሉ
ሸክም ሳይሆኑብን ፣ ሸክም የሚያቃልሉ
በእኛ ደም ሳይፈኩ ፣ በእኛ ደም ሳይጎሉ
እኛ የኢትዮጵያ ህዝቦች ፣ ያለ አንዳች ውከላ
"እእፓ" ሚል ፓርቲ ፣ መስርተን በመላ
እኛው እንታረቅ! ፣ እኛው ስንጣላ።

@photographyarts
--------------------------------
@photographyarts


እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ(ልዑል ሀይሌ)
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
መንገድ ጥረጊልኝ
ይህቺን ብቻ አርጊልኝ!
.
ስምሽን እያነሱ
እንዳያስታውሱኝ
በሞተው ትዝታ
እንዳይቀሰቅሱኝ
ያንቺ አለመሆኔን
ዛሬ እንዳሳያቸው
ጨረቃን ፀሐይን
ምድር አውርጂያቸው
ውቅያኖስ ባህሩን
ሰማይ ስቀያቸው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
የረገጥነው አስፋልት
የሄድንበት መንገድ
ያ ያለፈው ፍቅር
ያ ያለፈው መውደድ
ፍፁም ውሸት ብዬ
እንድሸመጥጠው
ተፈጥሮን አዛቢ
መውደዴን እንድተው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ገደሉን ሙዪና
ተራራውን ናጂው
ደመናን አውርደሽ
አፈሩን ውሰጂው
የረገጥሽው መሬት
አምሮ እንድታይበት
በአበባው ፋንታ
ሳማ ትከይበት
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ያ ሁላ ቃል ኪዳን
ተበትኖ እንዲቀር
አይጥ ሀይቅ ትዋኝ
ዓሳ ሰማይ ይብረር
በህይወት ባሉት ምትክ
ሙታኖች ይነሱ
ነገስታት ይውረዱ
ባርያዎች ይንገሱ
.
ይሄን ካረግሽልኝ
መውደዴን ይቅርና
መኖር አቆማለሁ
በመኖር ብረሳሽ
ባለመኖርም ውስጥ
አስታውስሻለሁ

👏👏👏

@photographyarts
--------------------------------
@photographyarts


መርዝ ጠጣህ አሉኝ

በመርዝ የማይምቱ ፍጥረታት በሙላ
በውስኪና በጠጅ ባረቄ በጠላ
በካቲካላ መርዝ ሆዳቸው እየሞላ
መርዝ ጠጣህ አሉኝ
ጥዋት በማለዳ ከቤት እኩል ወጠን
እኩል ሌትር መጠን
እነሱ አስር ጣሳ ጠላቸውን ግተው
እነዛም በጠርሙስ አረቄ ተወግተው
እኔ ሁለት ጠርሙስ ፀበሉን ጠጥቼ
መርዝ ጠጣህ አሉኝ
በአፋቸው ገደሉኝ
በአልኰሉ ስካር በዞረ ናላቸው
በኮልታፋ አፋቸው
ትሞታለህ አሉኝ
ከቤት እኩል ወጠን
እኩል ሌትር መጠን
እኔ ከፀበሉ እነሱ ከጠላው በጠዋት ጠጥተን
መርዝ ጠጣህ አሉኝ መፅደቅን አልሜው
መቼስ እብዶች መሀል ጤነኛ ሰው ቢገኝ እብድ ነው ስያሜው



✍✍Dani yop

@photographyarts
---------------------------------
@photographyarts


ግጥምና ፍቅር
(ደሱ ፍቅርኤል)
የኔ ፍቅር............
ግጥም ልፅፍልሽ አሰብኩ አሰብኩና አሰብኩ አሰብኩና
ቃላት አጠሩብኝ እንደአፍሪካ ፀጉር እንደ ቦትስዋና
የኔ ፍቅር.........
እንደ ኢህአፓ ጓድ አሁንም አሁንም ሰዓቴን አያለሁ
ስንኝ ሲነጥፍብኝ
ጭረት የበዛበት ቆሌ የመሰለ ስዕል እስላለሁ
(የሚገርምሽ ነገር)
ስላንቺ ማሰቤን ለጊዜው አቁሜ
እንደ ባህር ከዘራ ሃሳቤን ቆልምሜ
ስለከዱኝ ሴቶች ብዕሬን ባነሣ
የቅኔ ስካሬ ዓይኑን እያሻሼ ከ'ንቅልፉ ተነሣ
ላንቺ ለምወድሽ ፈልጌ አስፈልጌ ከቆጡ ከባጡ
(ያጣኋቸው ቃላት)
ለነገር ሲሏቸው እየተራኮቱ በምናቤ መጡ
ያፈቀረን ትቶ ለካደ ማሽቃበጥ ስሙ ምን ይባላል?
(ሳምንሽ ጉድ ሰራሽኝ
ስወድሽ ጎዳሽኝ)
ምናምን እያሉ እንደ ሴት ገጣሚ ማላዘን ያስጠላል
(ኤጭ)
የኔ ፍቅር..........
ፍቅርሽ ተዓምር ነው እንደ ባታ ጸበል ድውይ ይፈውሳል
የከንፈርሽ ቃና እንኳንስ ከዱካክ ከሙታን ያስነሳል
ታስታውሽ እንደሆን የሆነ ጊዜ ላይ
ማታውን ስመሽኝ ጧቱን ጀግና ሆንኩኝ
ኢንፎርቲዬን ትቼ
ዝናሬን ፈትቼ
ከንፈርሽን ታጥቄ ጦር ሜዳ ዘመትኩኝ
ታስታውሽ እንደሆን
ጥይት እንዳይመታኝ በፍቅርሽ ተከለልኩ
በጡቶችሽ መሃል ተደብቄ ተረፍኩ
አንችኮ መውደዴ አንቺኮ ናፍቆቴ
የጥይት ማምከኛ ያ'ስማት ክታቤ ነሽ ኩንፈል መድኃኒቴ
ግና ይኸው አሁን
ግጥም ልፅፍልሽ አሰብኩ አሰብኩና አሰብኩ አሰብኩና
ቃላት አጠሩብኝ እንደአፍሪካ ፀጉር እንደ ቦትስዋና

@photographyarts
--------------------------------
@photographyarts


እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ድርሰቴ
እንደ ሰውነቴ
ልክ እንደ አቦጊዳ ልክ እንደ ቃላቴ
ሀሳብ እንደ ሞላው እንደ ልብ ምቴ

እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ሀረጌ
ልክ እንደ ስንኜ ልክ እንደ ማረጌ
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ልብወለድ
አስቦ አሰላስሎ ግጥም እንደመውለድ

እኔ እወድሻለው ቤት እንደመምታት
ሀያ መፅሀፎች ፃፍኩ እንደማለት
ደራሲ ነህ ተብሎ እንደመጠራት
እኔ እወድሻለው ለእናት እንደመግጠም
ዶ፡ር አብይ አንገት ልክ እንደመጠምጠም

እኔ እወድሻለው ልክ እንደ በውቀቱ
እንደ ታገል ግጥም እንደወረቀቱ
ልክ አንደራዕዬ ልክ እንደሎሬቱ
እያልኩኝ እያልኩኝ ምሳሌ ደርድሬ
ሀሳበ መውደዴን በፅሁፍ አስፍሬ
ላስጨነቀኝ መውደድ ላላወቅሽው ፍቅሬ
የፃፍኩት ደብዳቤ ከዚሁ አስፍሬ

ደግሜ ባነበው ደግሜ ባነበው ሆነብኝ አሰልቺ
ፍቅሬን ለማስረዳት አልቻልኩም አይበጅ
የመድረስ አምሮቴን ተናገርኩት እንጂ

✍✍Dani yop

@photographyarts
--------------------------------
@photographyarts


" ዛሬም ወድሻለው "

ዘምናትን ኖሬ እንደ ሌለው ሆኜ
ብቻዬን ሥወድሽ በፍቅርሽ ባክኜ
መክሳቴን አይቼ ልተውሽ ወስኜ
መክሳቴ ጀብድ ይሁን ለፍቅር ታምኜ

በነጋ በጠባ በሀሳቤ አንቺ ነሽ
ለኑሮዬ ድርሰት ታሪኬ የምልሽ
ከልቤ ላይ ፅፌሽ ሳነብሽ ሳነብሽ
እንደ ልዩ ድርሰት ስገረም በስምሽ

የደመቀው ምስልሽ ከቀለም የፈካው
ቀለም በምን አቅሙ ካንቺ የሚልካካው
ከውብ ገፅታሽ ላይ ፍቅር
ተጨምሮ
ቢያደማኝ ቢያቆስለኝ ገላዬን አጥቁሮ

ጉልበት እስኪከዳኝ ቢርቀኝ ውበቴ
ዛሬም ወድሻለው ዛሬም ነሽ ህይወቴ
ባጥንቴ እስክቀር እስከለተ ሞቴ


ገጣሚ ኢብራሂም ለጃ

@photographyarts
-------------------------------
@photogrphyarts


እኔ ላንቺ ማለት
ከሬሳዎች መሀል~ ወድቆ የተገኘ፣
በጣም የረከሰ ~ሞቱን የተመኘ፣
ሁሉም የጠየፈው~ ህሊናውን ሽጦ፣
ባዶውን የቀረ ~መንፈሱ ተሟጦ፣
ተተጠሪ የሌለው ~ትብያ የወደቀ፣
ወኔው እንደከዳው ~ጉልበቱ የደቀቀ፣
ሳይወለድ ሞቶ ~ሳይጀምር ያለቀ፣
በጣም ተራ ሰው ነኝ፡
ምንም የማልረባ፣
ላንቺ የማልመጥን ~ከቁብ የማልገባ፣
...በኔ መጠየቅሽ ~አካልሽ ተሳቆ፣
ዕርኩስ እንደነካው~ ውስጥሽ ተሸማቆ፣
እኔን ላለማየት ~ህይወትሽ ቢርቅም፣
....ጠልቼሽ አላውቅም።
*** ✍️እሱባለው ኢ

@photographyarts
_______________
@photographyarts


ለሷ ብቻ
*
እንቅልፌን ውሰደው ~ሞቴን አቅርብልኝ
ሰላሜን ቀንሰህ ~ ሰላሟን ስጥልኝ
*
*
ለኔ ያሰብከዉን ~ለሷ ብቻ አድርገው
እንቅፋቷን ሁሉ ~በገደል አስርገው
*
እያልኩ ዘወትር ~ ከደጅህ መቆሜ
በሷ ታስሬ ነው~ አይደለም ታምሜ
* **
(✍️እሱባለው)

@photographyarts
--------------------------------
@photographyarts


Artist- Alex

@photographyarts
-------------------------------
@photographyarts


Nice photography

@photographyarts
-------------------------------
@photographyarts


//አንዳንዴ //

ሲከፋኝ:~
ድንገት አስቀይሟት ወይም እሷ አጥፍታ
የሞቀውን ፍቅር የሳቁን ቤት ትታ
አሳየኝ አንድዬ ከባሏ ተፋታ

እያልኩኝ ልፀልይ ድንገት አስብና
ሀዘን ያጠላበት መልክሽን አይና
ተወው በቃ አምላኬ ምልጃዬን መልሰው
የኔን ልብ ትተህ የሷን እንባ አብሰው
እያለኩ ፀሎቴን ቀለብሰዋለው

ምክንያቱም ያኔ
አብረን በሰፋነው በለበስነው ሸማ
አፍሽ ከአፌ ላይ ጨዋታ እየቀማ
ያሳለፍነው ጊዜ ቀጭኑ ትውስታ
ካንቺ ባይነጥለኝ ሆኖብኝ ትዝታ
ያለጊዜ ወድጄ በጊዜ ባጣሽም
ክፉ አርገሻል ብዬ
አንቺን አልወቅስሽም

ይሄ ሁሉ ሀተታ ይሄ ሁሉ ወሬ
አንድ እውነት ልነግርሽ አስቤ ነው ዛሬ
የእስካሁኑ ይብቃ የያበጠው ይፈንዳ
አንቺንም አላሳቅ እኔም አልጎዳ

በሰፊው አደባባይ ብዙ ህዝብ ካለው
እንዲህ ይነበባል ምስጢሬን ብሰቅለው
ለሺህ የስሜቴ ጎርፍ ገላጭ ቃሉ አንድ ነው
"ባልነግርሽ ነው እንጂ ዛሬም ወድሻለው"

ምንያህል ጥላሁን
አዶኒስ

@photographyarts
-------------------------------
@photographyarts


ሰው መጣ.....ሰው ሄደ


ያይኔ የልቤ ጉጥ የዘላለም ፍቅሬ
ሰው ያየናል እዚህ ፈርቻለሁ ዛሬ
እንዲህ ተሸጉጬ በአንተ ክንድ ላይ
አባዬ ያየኝ እንደሁ አይኖርም ገላጋይ

ብዬ እያካፈልኩት ጭንቀቴን ከሆዴ
ጥላ ባየሁ ቁጥር ከእቅፉ እወጣለሁ
አወይ ልጅነቴ

ሰው መጣ ሰው ሄደ
ምንም ሳናወራ በመጨነቅ ብቻ
አንዴ እጁን ሲሰቅል አንዴ እጁን ሲያወርድ
ሰአቴ ደረሰ የመሰናበቻ
ሳልጠግበው ሳይጠግበኝ ናፍቆቴ ሳይወጣ
ሌላ የቀን ቀጠሮ ላንድ አይነት ቆይታ፡፡

ያኔ በልጅነት ባፍላነት እድሜያችን
ሰው መጣ ሰው ሄደ ነበር ስጋታችን

አመታት አለፉ ጊዜውም ነጎደ
በሰው መጣ ጭንቀት ሀሳብ ተወገደ
በትዳር ትስስር ነፃነት ታወጀ

ነገር ግን

የሰው መጣ ጭንቀት ቆይቶ ቆይቶ...
ጊዜውን ጠብቆ በር ላይ አድብቶ
እንደገና መጣ በራችን አንኳክቶ

ዐይኖችህ ከዐይኖቼ እንዳልተራራቡ
እንዳልተቃቀፍን ጠብቀን ሲዞሩ
መተቃቀፍ ጀመርን ሰው ሲኖር ከበሩ፡፡


ንፁህ ግርማ

@photographyarts
-------------------------------
@photographyarts


///የማይቻል አንድ ነገር///

እዉነት - ቤት ስትሰራ
ዉሸት - ላግዝ ካለች፣
ምስማር ካቀበለች፣
ቤቱም አልተሰራ
እዉነትም አልኖረች።

#ጌትነት_እንየው

@photographyarts
-------------------------------
@photographyarts


ሮፍናን
።ዛሬ እንጂ ነገ የት ይሄዳል።

ጊዜ እንደጅረት ይዞ ይነጉዳል
ሳናውቀው ነገር ታሪክ ይሆናል
ማነው ያልተባለ "እንዲህ ነበረ"
ዘላለም የኖረ..
ዛሬን አትጣት ነገን ብለህ
ሁሉም አሁን ነው የአንተ ጊዜህ
እንደተፃፈው ለራሱ ያውቃል
'ዛሬ እንጂ ነገ የት ይሄዳል'

ጀግና ቢባል በዚህች አለም
የጊዜ እንጂ የሰው የለም
ትላንትን የቀረበት ተው
ነገንም ለሰማይ ስጠው

መደሰት,ማፍቀር,መኖር ዛሬን ነው
ላከበረው ሰው ሁሌም ልደቱ ነው
ሁሉን በጊዜው ውብ አርጎታልና
የዛሬ ፀሀይ ነገ አትሞቅምና..

ጊዜ እንደጅረት ይዞ ይነጉዳል
ሳናውቀው ነገር ታሪክ ይሆናል
ማነው ያልተባለ "እንዲህ ነበረ"
ዘላለም የኖረ.
ዛሬን አትጣት ነገን ብለህ
ሁሉም አሁን ነው የአንተ ጊዜህ
ታምን እንደሆን ለራሱ ያውቃል
'ዛሬ እንጂ ነገ የት ይሄዳል'

እውር ነው አሞራው
ማነው ያበላው ማነው ያበላው
አሄሄሄሄሄ
እውነት እውነት አሄሄሄሄሄ
እውር ነው አሞራው
ማነው ያበላው ማነው ያበላው


@photographyarts
-------------------------------
@photographyarts




"I Hate U I Love U"
(feat. Olivia O'Brien)

Feeling used
But I'm still missing you
And I can't see the end of this
Just wanna feel your kiss
Against my lips

And now all this time
Is passing by
But I still can't seem to tell you why
It hurts me every time I see you
Realize how much I need you

I hate you, I love you
I hate that I love you
Don't want to but I can't put nobody else above you
I hate you, I love you
I hate that I want you
You want her, you need her
And I'll never be her

I miss you when I can't sleep
Or right after coffee
Or right when I can't eat
I miss you in my front seat
Still got sand in my sweaters
From nights we don't remember

Do you miss me like I miss you?
Fucked around and got attached to you
Friends can break your heart too
And I'm always tired but never of you

If I pulled a you on you, you wouldn't like that shit
I put this reel out, but you wouldn't bite that shit
I type a text but then I never mind that shit
I got these feelings but you never mind that shit

Oh, oh
Keep it on the low
You're still in love with me but your friends don't know
If you wanted me you would just say so
And if I were you, I would never let me go

I don't mean no harm
I just miss you on my arm
Wedding bells were just alarms
Caution tape around my heart

You ever wonder what we could have been?
You said you wouldn't and you fucking did
Lie to me, lie with me, get your fucking fix
Now all my drinks and all my feelings are all fucking mixed

Always missing people that I shouldn't be missing
Sometimes you gotta burn some bridges just to create some distance
I know that I control my thoughts and I should stop reminiscing
But I learned from my dad that it's good to have feelings

When love and trust are gone
I guess this is moving on
Everyone I do right does me wrong
So every lonely night I sing this song

I hate you, I love you
I hate that I love you
Don't want to but I can't put nobody else above you

I hate you, I love you
I hate that I want you
You want her, you need her
And I'll never be her

All alone I watch you watch her
Like she's the only girl you've ever seen
You don't care you never did
You don't give a damn about me

Yeah, all alone I watch you watch her
She is the only thing you ever see
How is it you never notice
That you are slowly killing me?

I hate you, I love you
I hate that I love you
Don't want to but I can't put nobody else above you
I hate you, I love you
I hate that I want you
You want her, you need her
And I'll never be her


@photographyarts
------------------------------
@photographyarts

Показано 20 последних публикаций.

430

подписчиков
Статистика канала