ክፉ ልክፍት!... ድንቅ መድሃኒት!!
ሰውየው፡- “ቀድሞ (ለማጨት ሳስባት) በሚስቴ በምደነቅ ጊዜ … አላህ የሷ አይነት በአለም ላይ የፈጠረ አይመስለኝም ነበር፡፡
ካጨኋት በኋላ ብዙዎቹ ሴቶች የሷው አምሳያ ሆነው አገኘሁ፡፡
ካገባኋት በኋላ #ብዙዎቹ ሴቶች ከሷ የበለጡ ቆንጆዎች እንደሆኑ ተገነዘብኩ፡፡
ተጋብተን ጥቂት አመታት ካለፉ በኋላ ግን #ሁሉም ሴቶች ከሷ የሚበልጡ ቆንጆዎች እንደሆኑ ደመደምኩ” አለ፡፡
ሸይኹ በዚህን ጊዜ፡- “ይልቅ ከዚህ የከፋውን አልነግርህም?” አሉ፡፡
“ይንገሩኝ” አለ ሰውየው፡፡ የአለም ሴቶችን በሙሉ ብታገባም በየጎዳናው የሚልከሰከሱ ውሾች ከአለም ሴቶች ሁሉ በላይ ቆንጆዎች ይሆኑብሃል!!”
ሰውየው፡- በስሱ ፈገግ አለና “ለምን እንዲህ አሉ?” ሲል ጠየቀ፡፡
ሸይኹ፡- “ምክንያቱም ችግሩ ከሚስትህ አይደለም፡፡ ችግሩ የሰው ልጅ ስግብግብ ልቦና፣ ልክስክስ አይን ሲኖረውና አላህን ከማፈር ከሐያእ ሲራቆት ነው፡፡ በዚህን ጊዜ አይኑን የመቃብሩ አፈር እንጂ አይሞላውም፡፡ ልክ ነብዩ ﷺ ‘የአደምን ልጅ አይኑን አፈር እንጂ አይሞላውም…’ እንዳሉት፡፡ ሰውየ!! ችግርህ አይንህን አላህ ከከለከለው ነገር አለመስበርህ ነው፡፡ ይልቅ ሚስትህን ልክ እንደ ቀድሞዋ (ከአለም ሴቶች ሁሉ ቆንጆ) የምታደርግበትን ዘዴ እንድነግርህ ትፈልጋለህ?” አሉት፡፡
“አዎ” አለ ሰውየው፡፡
“አይንህን ስበር!!” አሉት ሸይኹ!!
ከዐረብኛ ፅሑፍ የተቀዳ ነው፡፡
#ከኢብኑ_ሙነወር