የ8ተኛ እና የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል !
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊየን ማቲዎስ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ፈተናን በተመለከተ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ መንግስት የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የህግ ማስከበርና የፀጥታ ጉዳዮችን እንዳረጋገጠ ይሰጣል ብለዋል።
ተማሪዎች ይህንን ተገንዝበው ለፈተና እየተዘጋጁ እንዲጠባበቁ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ አሳስበዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ እና ሼር ያድርጉ!
@Ethio_Students@Ethio_Students